Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live

የማለዳ ወግ …”ነቢይ በሀገሩ አይከበርም! ”ከያኒው በበጎ ስራው ተሸለመ!

$
0
0

Josy Gebre
* እንኳን ደስ ያለህ ጆሲ ገብሬ
Jossy In Z House በሚለው ስሙ የሚታወቀው ጆሲ ገብሬ በምድረ አሜሪካ , ባልቲሞር Baltimore ውስጥ Deedee Africa Entertainment Award የተባለው ክብር ለሚገባው ክብር የሚሰጥ ድርጅት ባካሔደው ሥነ ሥርዓት ለሰብዕና ዙሪያ ለሰራው በጎ ስራ የክብር ሽልማት ማግኘቱን ሰምተናል ! እንኳን ደስ አለህ ከያኒ ጆሲ :)
ጆሲ ለበርካታ አመታት EBS በተባለው የቴሌቪዥን ፕሮግራም እስካቋረጠበት ቀን ድረስ በሚያቀርባቸው ማራኪ ዝግጅቶቹ በይበልጥ ይታወቃል ። ወጣቱ ከያኒ ጆሲ በዚህ ፕሮግራሙ የተዘነጉ ፣ የተረሱ ፣ የተገፉ ወገኖችን በመደገፍ ፣ ለመደገፍ በማነቃቃት ያደረገውን አርአያነት ያለው ስራ እንማርበት ዘንድ ልዩ በዝግጅቱ አስመስክሯል ብየ አምናለሁ ! ጆሲ በአይነቱ ልዩ በነበረው የመድረክ ዝግጅቱ የጥበብ ሰዎችን በመጋበዝ ባደረጋቸው ውይይቶች ጠቃሚ መረጃንም ያበረከተ ቅን ወጣት የጥበብ ሰው ነው ። በመድረክ አቀራረቡ ፣ በሚያቀርባቸው ቀልብን የሚስቡ የተመጠኑ ጥያቄዎች ፣ ዝግጅቶች በተጨማሪ የመድረክ ፕሮግራም መምራት አሉን ከሚባሉት ጋዜጠኞች የተሻለ ክህሎቱን ያስመሰከረ አርቲስት ነው ባይ ነኝ !
ብዙ የጥበብ ሰዎች ገንዘብ ለማጋበስ ወጥነው በሚለቋቸው ስራዎቻቸው እየተመጻደቁ ” ሀብቴ የህዝብ ፍቅር ነው ፣ ህዝቤን እወዳለሁ! ” የሚሉትን ህዝብ ድምጽ መሆኑ ቢገዳቸው ከሰብዕና ሸሽተው የከረሙት ቁጥር የትየለሌ ነው ፣ ከእኒህ ከያንያን መካከል ጆሲ ባወጣቸው የተለያዩ የጥበብና የመድረክ ስራዎቹ ጆሲ አስተማሪና አርአያነት ያለው በጎ የስራ ዘርፍ ተሰልፎ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ስራዎችን ከሰሩ ጥቂት ከያንያን መካከል አንዱ ነው ባይ ነኝ ።
ወጣቱ ከያኒ ጆሲ ገብሬ ” በሚያቀርበው ዝግጅት በጎ ስራውን ለራሱ ክብር መቆለያ ተጠቅሞበታል !” የሚል ወቀሳና ዘመቻ ሲሰነዘርበት አዝኛለሁ። ወቀሳ ዘለፋው በተሰነዘረበት ማግስት ለበጎ ስራ አርአያነት ያለው ወጣት በ EBS ከሚያቀርበው ዝግጅት መገለሉ አስከፍቶኛል ። ያስከፋኝና በገደምዳሜ የሰማነውን የ EBS ቴሌቪዥንን እርምጃ የማልደግፈው ጣቢያው ጆሲ ከተወነጀለበት የግል ዝና ግንባታ ባለፈ በችጋር የተገረፉ ፣ በድህነት ማጥ የወደቁ ፣ የተሰበሩ ልቦችን መጽናኛ መሆን ከግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ ነው ! ይህ የግል ምልከታየ ነው!
ቅዱስ መጽሐፉ ” ነቢይ በሃገሩ አይከበርም ” እንዲል አለመታደል ሆኖ ወገኖቻችን የሚሰሩትን ትልቁን መልካምና በጎ ምግባር እየዘነጋን በተራ ኩነቶች ላይ ተፈናጠን ክብር ለሚገባውቸው ለእኛ ሰዎች እኛ ክብር አንሰጥም ። ዛሬ በዚህ እኛነታችን የተከፋች ነፍሴና ውስጡ የደማ ልቤ ትፍስህት አግኝታለች ። ለወገናችን በጎ ምግባር የእኛ ያልሆኑት ክብር ሲሰጡ መመልከት የሚፈጥረው ደስታ ነፍሴ ታውዳለች !
ወደድንም ጠላንም ወጣቱ ከያኒ ጆሲ ገብሬ ሌላው ቀርቶ አሁን አሁን አልፎ አልፎም ቢሆን ጉምቱ ታዋቂ ከያንያን ወደ በጎው ሰብአዊነት ጎዳና ይመጡ ፣ ይቀላቀሉ ዘንድ አርአያ እንደሆነ ይሰማኛል ! እናም ለጆሲ ሰብአዊነትን መሰረት ያደረገ ድንቅ ስራው አድናቂ ነኝ !
ለወጣቱ ከያኒ ለጆሲ ገብሬ ክብር እሰጣለሁ!
ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 12 ቀን 2008 ዓም


Viewing all 261 articles
Browse latest View live