በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት በኩል ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥቶ የነበረውና በተለያዩ ስቴቶች የኮሜዲ ሥራዎችን ቢያቀርብም ብዙም ተቀባይነት ሳያገኝ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው ኮሜዲያን ፍልፍሉ ተመልሶ ወደ አሜሪካ ለመምጣት ፈቃድ ቢጠይቅም በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል መከለክሉ ታወቀ::
ኮሜዲያኑ ወደ ሃገር ቤት እመለስበታለሁ ብሎ ለኢምባሲው ከተናገረበት ቀን በጣም አሳልፎ ወደ ሃገር ቤት በመመለሱ የተነሳ አሁን በድጋሚ ወደ አሜሪካ የመግቢያ ፈቃድ ሲጠይቅ ተከልክሏል:: ፍልፍሉ በስሜን አሜሪካ በተዘዋወረባቸው ከተሞች በኮሜዲ ዝግጅቶቹ ላይ የተጠበቀው ያህል ሰው ያልተገኘ ሲሆን በርካታ ፕሮሞተሮችም ለኪሳራ መዳረጋቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልጹ ይሰማል::
ፍልፍሉ ለመድረክ ስራዎች ሳይሆን ለተቀረጹ ስራዎች ብቻ የሚሆን ኮሜዲያን ነው የሚሉት ለሙያው ቀረብ ያሉ ሰዎች ያልፈጠረበትን ስታንዳፕ ኮሜዲ አቀርባለሁ ብሎ ለትዝብት መውደቁን ይናገራሉ::
ኮሜዲያን ፍልፍሉ የባለስልጣን ልጅ አግብቼ ቤተሰቦቿ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገሉኝ ይፈልጋሉ እያለ በሰሜን አሜሪካ ቆይታው ሲናገር የቆየ ሲሆን ሃገር ቤት እንደገባም በዱሪዬዎች መደብደቡ አይዘነጋም::
ኮሜዲያን ፍልፍሉ ወይም በረከት በቀለ የአሜሪካ መግቢያ ፈቃድ ከተከለከለ በኋላ በየሚዲያው በመቅረብና በሄደበት ቦታ ሁሉ አሜሪካንን በማጥላላት ላይ እንደሚገኝም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::