ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ጋር ለሁለተኛ ግዜ አይኑን በአይኑ ማየቱን በትዊተር ገጹ ባሰፈረው የደስታ መግለጫ አስታወቀ::
ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም የአንድ ወንድ ልጅ አባት የነበረ ሲሆን ዛሬ ከባለቤቱ አምለሰት ሴት ልጅ ተበርክቶለታል::
“በእግዚአብሔር ፍቃድ ሁለተኛ ልጃችን ይህችን ምድር ተቀላቀለች: : ክብርና ምዝጋና ለመድኃኔዓለም ይሁን!” ያለው ቴዲ አፍሮ ከቤተሰቡ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ በሚቀጥለው ወር በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ያቀርባል::