Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ሊሞሸር ነው * የሠርጉን ወጪ ሺህ አላሙዲ ችለዋል

$
0
0

Seifu Fantahun

(ዘ-ሐበሻ)ጋዜጠኛና ኮሜዲያን ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ጷግሜ 1 ቀን 2007 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ሊሞሸር ነው፡፡ የሰይፉ ሚዜዎች ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ አርቲስት ሚኪ(ባለታክሲው ፊልም ላይ የሚሰራው)፤ ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑት ሼህ መሐመድ አል አሙዲ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለፈው ሳምንት ሠይፉ ከአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ጋር ወደ ዱባይ አምርቶ ለሰርጉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሸማምቶ ተመልሷል፡፡ በሼህ መሐመድ አል አሙዲ የተሰጣቸውን የ165 ሺ ድርሃም በመያዝ ወደዱባይ ያቀኑት ሰይፉና ሰራዊት የሚዜዎችን ልብስና ጫማ ጨምሮ በርካታ ሻንጣ ቁሳቁሶች ገዝተው እንደተመለሱ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

Trending Articles