Image may be NSFW.
Clik here to view.
‘ሳላይሽ’ የተሰኘ ተወዳጅ አልበሙን ለሕዝብ ካቀረበ በኋላ ከፍተኛ ተቀባይነትን በማግኘቱ በየሃገራቱ እየተዘዋወረ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን በማቅረብ ላይ ያለው ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ በካናዳ ዊኒፔግ ግዛት ከትናንት በስቲያ ሴፕቴበር 6 አምርቶ ነበር:: ኮንሰርቱን ለመሥራት ወደዚያው ያመራው ይኸው ተወዳጅ ድምፃዊ በአንድ ወጣት በተወረወረ ጠርሙስ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
በጠርሙስ ፍንከታ የደረሰበት አካሉ መሰፋቱን የገለጹልን ምንጮቻችንን ጠርሙሱን የወረወረበትን ሰው ለመያዝ ፖሊስ እየጣረ መሆኑም ተሰምቷል::
ብዙአየሁ በዌኒፒግ ኮንሰርት ሊያቀርብ ሲሄድ የም ዕራብ ካናዳ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ይካሄድ እንደነበር ታውቋል::
ዘ-ሐበሻ ወደ ብዙአየሁ ደምሴ ደውላ ጉዳዩን ከ እርሱ አፍ ለመስማት ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም ከርሱ እንደሰማን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን::
ኢትዮጵያውያን በውጭ ሃገር ኮንሰርት ለማየት ሄደው በኮንሰርት ላይ መደባደብን እንደ ትልቅ ጀብዱ ማየታቸው የሚያሳዝን ጉዳይ ሲሆን; ይህን ዓይነቱን ድብድብ የሚፈጥሩት ደግሞ የራሳቸው ወገን ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ እንጂ በውጭ ሃገር ኮንሰርቶች ላይ አለመሆኑ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ነው::