በምናለ ብርሃኑ
በዚህ ዘመን በወደዱት ድርጅት ወይም ተቋም የተሰራን ምርት ገበያ ላይ ፈልጎ መጠቀም ልማድ እየሆነ መጥቷል፤ የተጠቃሚዎችና የኩባንያዎች የመፈላለጊያ መንገድም በዝቷል። ታዲያ ተቋሞችም ፈላጊዎቻቸውንና አድናቂዎቻቸውን ላለማጣት እና ላለማስቀየም ብሎም ተሽሎ ለመገኘት ሌት ተቀን በመልፋት እና የተሻለ እና አዳዲስ ነገር በማቅረብ ገበያውን ሲቆጣጠሩት ይስተዋላል።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
በተለይም በዚህ ዘመን የኤሌክትሮኒክስ ገበያውን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ኩባንያዎች ይህን ያደርጋሉ፤ የአሜሪካው አፕልም ከእነዚህ ድርጅቶች አንዱና ተጠቃሹ ነው። ይህ ኩባንያ በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎቹ በተለይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልኮችና ሰዓቶቹ ይታወቃል፤ አሁን ደግሞ እጅግ በዘመነ ተሽከርካሪ ወደ ገበያ ልመጣ ነውና ጠብቁኝ እያለ ነው።
ኩባንያው በኤሌክትሪክ የምትሰራ አነስተኛ እና ዘመናዊ ተሽከርካሪን በፈረንጆቹ 2019 መንገድ ላይ እሞክራታለሁ ማለቱን ወል ስትሪት ጆርናል ላይ የወጣ መረጃ ያትታል።
በአራት አመታት ውስጥ ተገጣጥማ መንገድ ላይ ትወጣለች ያላትን ተሽከርካሪ ጉዳይን በተመለከተም ከካሊፎርኒያ ባለስልጣናት ጋር መምከሩም ነው የተነገረው።
ታይታን የሚል ሚስጥራዊ መጠሪያ በተሰጠው ፕሮጀክት ያለውን ስራ ለማቀላጠፍም ተቋሙ የሰራተኞቹን ቁጥር ለመጨመር ማሰቡም ተነግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም የዘርፉን ኢንጅነሮች የቀጠረ ሲሆን ይህ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ፕሮጀክቱም የተቋሙ ትልቁና ዋናው አጀንዳ ነው ተብሏል።
አዲሷ ተሽከርካሪ ያለ ሾፌር ላትሰራ እንደምትችል ተጠቅሷል፥ ምናልባትም ከዚህ እጅግ የዘመኑትና ራሳቸውን ችለው የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች የኩባንያው የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሆኑም ነው የተነገረው።
ከዚህ ቀደም ጎግል ተመሳሳይ ተሽከርካሪን ያመረተ ሲሆን፥ የመኪና አምራች ኢንዱስትሪውን ከመቀላቀል ይልቅ ለተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና አምራች ኩባንያዎች ሶፍትዌሮችን አሻሽሎ ማቅረብ ቀጣይ ተግባሩ መሆኑን ኩባንያው መግለጹም ይታወሳል።
ምንጭ፥ fossbytes.com