(ዘ-ሐበሻ) የላፎንቴኑ ብርሃኑ ተዘራ (ያምቡሌ) ከጃኪ ጎሲ ጋር የሰራው ነጠላ ዜማ ለድል በዓል እንደሚለቀቅ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
የአደዋ ድል በዓልን ተከትሎ የሚለቀቀው ይሄው ነጠላ ዜማ በሕዝብ ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል:: ብርሃኑ ተዘራ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሲሆን ይህን ነጠላ ዜማ ለመስራት ረዥም ጊዜ እንደፈጀበትም ታውቋል::
በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ይኸው አዲስ ነጠላ ዜማ ስለሃገር ፍቅር የሚገልጽ እንደሆነም ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቋል:: በቅርቡ የአሜሪካ “ሰላ” ኮንሰርቱን አጠናቆ ወደ አውሮፓ ያቀናው ጃኪ ጎሲ በዚሁ የብርሃኑ ተዘራ አዲስ ነጠላ ዜማ ላይ የተሳተፈ ሲሆን ስራው የተዋጣ እንደሆነም ያደመጡ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል:: ሙዚቃውን ያቀናበረውም ሄኖክ ነጋሽ መሆኑን ምንጮቻችን አስታውቀውናል::
ይህ ዘፈን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሚለቀቅ ሲሆን ዘፈኑ እንደደረሰን በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እናስደምጣችኋለን:: ይጠብቁት::
The post ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ነጠላ ዜማ ሊለቀቅ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.