ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአቡነ ዓቢየ እግዚእ ታቦተ ህግ በትናንትናው ዕለት ከበሯል። ይህ ጻዲቅ አባት በጎንደርና በትግራይ ብቻ ነበር የሚከብረው። ትናንት ግንቦት 19 እረፍቱ ስለነበረ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ ደብር ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።
ዲያቆን ሉኡልሰገድ ጌታቸው እንደገለጸው ለዚህ ክብረ በዓል መሳካት አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ ወሮ አፀደ ሥላሴ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በተለይ ወሮ አፀደ የጻድቁን ገድል በማጻፍ፣ ታቦተ ሕጉም በደብሩ እንዲኖር ከአባቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት ያደረገች ታላቅ ሴት ነች። አጋጣሚው ደግሞ እጅግ ደስ ይላል፣ ለእነዚህ ለተባረኩ ጥንዶች ይህ ግንቦት ወር የተጋቡበት ወር መሆኑ ነው። ስለዚህ 8ኛ ዓመታቸውን በታቦቱ ስር አስበውት ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሩት መልካም ትሩፋት ደብሩ ያዘጋጀላቸውን የክብር ካባ ብጹዕ አቡነ ሰላማ ባርከው ደርበውላቸዋል ሲል ዲያቆን ልዑልሰገድ ጌታቸው ዘገባውን አጠናቋል::
The post አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ 8ኛ ዓመት የትዳር ሕይወታቸውን አከበሩ appeared first on Zehabesha Amharic.