Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live

የኡዛዛ አሌይና ዘፋኞች ሔለን በርሔና ናዳ አል ቃላ –ሊያዩት የሚገባ (Video)

$
0
0

የኡዛዛ አሌይና ዘፋኞች ሰሞኑን ተገናኝተዋል:: ታዋቂዋ የሱዳን ድምጻዊት ናዳ አል ቃላ ከኢትዮጵያዊቷ ሄለን በርሄ ጋር በተገናኙበት ወቅት እርስ በራሳቸው ያላቸውን አድናቆትና ፍቅር የተገለለጹት በሚከተለው መልኩ ነበር:: ሁለቱም ይህን ተወዳጅ ዘፈን በአንድ ላይ ዘፍነውታል:: ይመልከቱት::

Helen Berhe and Nada El- qalaa

The post የኡዛዛ አሌይና ዘፋኞች ሔለን በርሔና ናዳ አል ቃላ – ሊያዩት የሚገባ (Video) appeared first on Zehabesha Amharic.


‹‹የጥላሁን ገሠሠ ሚስትነት ከሕግ የበላይ አያደርግም.. ወ/ሮ ሮማንን በሕግ እፋረዳታለሁ!›

$
0
0

በቅርቡ በዘከርያ መሀመድ ተጽፎ ለንባብ የበቃውን ‹ጥላሁን ገሠሠ የህይወቱ ታሪክና ሚስጥር› የሚለውን መጽሐፍ ተከትሎ የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ‹ከመጽሐፉ መታተም ጀርባ ሌላ ታሪክ አለ› በሚል በቁምነገር መጽሔት ቅጽ 14 ቁጥር 203 አስተያየቷን ሰጥታ ነበር፡፡ በቃለምልልሱ ላይ ስማቸው ከተጠቀሱ ሰዎች መካከል የአቶ ፈይሳ ልጅ የሆነው ሳምሶን ፈይሳ ‹ወ/ሮ ሮማን ስሜን ስላጠፋች በህግ እፋረዳታለሁ› ይላል፡፡ ሳምሶን የሰጠው ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
Tilahun Legend
ቁምነገር፡- በቅርቡ ለህትመት በበቃው አዲሱ የጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ የአንተ ሚና ምንድን ነው?

ሳምሶን፡ በአባታችን በአቶ ፈይሣ ኃይሌ ሐሰና ከ1934 ጀምሮ የተጻፈ የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ አለ፡ ፡ ያን ማስታወሻ መነሻ በማድረግ የጥላሁን የሕይወት ታሪክ እንዲጻፍ ቤተሰቤን ወክዬ ባለሙያ ፍለጋ የተንቀሳቀስኩት እኔ ነኝ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ጋዜጠኛ ሲሳይ ገብረጻድቅን አነጋገርኩት፡፡ በእርሱ አማካይነት ከዘከሪያ ጋር ተዋወቅሁና የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻዎቹን፣ ተዛማጅ ሰነዶችን እና የጥላሁን የሕጻንነት ፎቶዎችን ጨምሮ የቤተሰብ ፎቶግራፎችን አሳየኋቸው፡፡ ዘከሪያ ማስታወሻዎቹን ጊዜ ወስዶ ማየት እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ልሰጠው እችል እንደሆን ጠየቀኝ፡፡ ሰጠሁት፡ ፡ በዚሁ የመጽሐፉ ሥራ ሂደት ተጀመረ፡፡

ቁምነገር፡- የመጽሐፉ ዝግጅት ሥራ ከተጀመረ በኋላ የአንተ ሚና ምን ነበር?
ሳምሶን፡ ዘከሪያ ሥራውን ከጀመረው በኋላ የእኔ ሚና ከጥላሁን ጋር በተያያዘ ያሉኝን የግል ትውስታዎች ማካፈል፣ ለሚያቀርብልኝ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እና መረጃ ሊሰጡት የሚችሉ ሰዎችን መጠቆም የመሳሰለ ነበር፡፡

ቁምነገር፡- ከወ/ሮ ሮማን ጋር ከመቼ ጀምራችሁ ነው የምትተዋወቁት? ቅርርባችሁስ ምን ያህል ነበር?

ሳምሶን፡ ከወ/ሮ ሮማን ጋር የተዋወቅነው ከአሜሪካ መጥታ ጥላሁን ቤት ከገባች በኋላ ነው፡ ፡ ቅርርባችሁስ ላልከው፣ የተለየ ቅርርብ የለንም፡ ፡ በእንግድነት ቤታቸው ስሄድ፣ በመልካም ሁኔታ ታስተናግደኛለች፡፡ በወቅቱ ጥላሁን ቤት የምሄደው ለጉዳይ ፈልጎ ሲጠራኝ ብቻ ነበር፡፡ ከወ/ሮ ሮማን ጋር የምንገናኘውም በእንደዚህ ያሉት አጋጣሚዎች ነው፡፡
ከዚያ ውጪ እኔ እና ወ/ሮ ሮማንን የሚያገናኝ ወይ የሚያቀራርበን ነገር አልነበረም፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን ግን አንተ እነርሱ ቤት ትኖር እንደነበር ተናግራለች፡፡

ሳምሶን፡ እውነት አይደለም፡፡ ወ/ሮ ሮማን ከአሜሪካ መጥታ ጥላሁን ቤት ከመግባቷ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ፣ ጥላሁን ለራሱ ጉዳይ ሲፈልገኝ፣ ወይም ቤት መጥቼ አብሬው እንድውል ሲጠራኝ ወይም ልጠይቀው ሄጄ ለአንድ፣ ለሁለት ወይም ግፋ ቢል ለሦስት ቀናት ያህል አድሬ ይሆናል፡፡ እንጂ፣ እኔ በየትኛውም ዘመን በቋሚነት ጥላሁን ቤት ኖሬ አላውቅም፡፡
ቁምነገር፡- ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት በአንተ እና በወ/ሮ ሮማን መካከል የተፈጠረ ግጭት ነበረ? ከነበረ የግጭታችሁ መንስዔ ምንድን ነው?
ሳምሶን፡ ከወ/ሮ ሮማን ጋር ምንም ዓይነት ግጭት የለንም፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን ጥላሁን ቤት ጥሎ የወጣውና ከእኔ ጋር የተለያየው በሳምሶን ምክንያት ነው ትላለች፡፡ ለዚህ አንተ የምትሰጠው ምላሽ ምንድን ነው?
ሳምሶን፡ ጥላሁን በጋብቻም ሆነ ከጋብቻ ውጪ በአብሮ መኖር ጎጆ ከተጋራቸው ሴቶች ወ/ሮ ሮማን ሰባተኛ ወይም ስምንተኛዋ ነች፡፡ ከእርሷ በፊት ከአምስት ወይ ስድስት ቤቶች ሻንጣውን ይዞ መውጣቱ ይታወቃል፡ ፡ ወ/ሮ ሮማን ከአሜሪካ መጥታ አብራው መኖር ከጀመረች በኋላ ቤቱን ትቶ የወጣውም በራሱ ውሳኔ እንጂ፣ የ30 ዓመት ታናሹ በሆንኩት በእኔ ምክንያት አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም፡፡ ወ/ሮ ሮማን ከምን ተነስታ ይህን ልትል እንደቻለች ለእኔ ግልጽ አይደለም፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን ከጥላሁን ጋር በተለያዩበት ወቅት አካባቢ ልብሶችና ወርቆች ጠፍተውባት እንደነበረ፣ ከዚያ ጋር በተያያዘም አንተ ፖሊስ ጣቢያ ታስረህ እንደነበርና፣ ፖሊሶች ደብረ ብርሃን ይዛ ሄዳ ‹‹ሰባት ሻንጣ ልብስና ወርቆቼ ሳይቀር ተገኙ›› ብላለች፡፡ ለዚህ ያንተ ምላሽ ምንድን ነው?

ሳምሶን፡ እቃ ጠፍቶኛል ብላ እኔን እና የጥላሁንን ልጅ ዳንኤልን በተጠርጣሪነት ፖሊስ ጣቢያ አሳስራን ነበር፡፡ በተጠርጣሪነት ተይዞ መመርመርም ሆነ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ መቆየት ጥፋተኝነትን አያሳይም፡፡ በፍርድ ቤት ክስ አልተመሰረተብንም፤ አልተመሰከረብንም፤ በጥፋተኛነትም አልተፈረደብንም፡፡ ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ፣ ወ/ሮ ሮማን በቁም ነገር መጽሔት (14ኛ ዓመት፣ ቅፅ 14፣ ቁጥር 203) የሥርቆት ወንጀል እንደፈፀምኩ አድርጋ ተናግራለች፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን፣ ሳምሶን ‹‹ጥላሁንን ገና በሕይወት እያለ ሊሸጠው ሊለውጠው የፈለገ ሰው ነው››፣ ሳምሶን ማለት ‹‹ጥላሁንን ትብትብ አድርጎ የተጫወተበት ሰው ነው››፣ ‹‹ፖሊሶች ከሳምሶን ኪስ ውስጥ ‹ጥላሁንን እንዲህ አድርግልኝ … ምናምን› የሚል የጥንቆላ ነገሮችን አግኝተዋል›› በማለት በአደባባይ ስሜን አጥፍታለች፡፡ የጥላሁን ገሠሠ ሚስትነት ከሕግ የበላይ አያደርግም፡፡ ስለዚህም፣ በአደባባይ ስሜን በማጥፋቷ ወ/ሮ ሮማን በዙን በሕግ እፋረዳታለሁ፡፡

ቁምነገር፡- በዚሁ ምክንያት ከዚያ ጊዜ በኋላ ከጥላሁን ጋር ተነጋግራችሁ እንደማታውቁ፣ ሌላ ቀርቶ በለቅሶው ላይ እንኳ እንዳልተገኘህ ወ/ሮ ሮማን ተናግራለች፡፡ እውነት ከጥላሁን ጋር ተጣልታችሁ ነበር? በለቅሶውስ ላይ አልተገኘህም?

ሳምሶን፡ ወ/ሮ ሮማን፣ ጥላሁን ገሠሠ ታላቅ ወንድሜ መሆኑን የዘነጋችው ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው እኔም፣ በወንድሜ ለቅሶ ላይ መገኘቴን ታውቅልኝ ዘንድ ወ/ሮ ሮማንን እጅ ነስቼ መውጣት እንደነበረብኝ ዘንግቼ ይሆናል፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ለጥቅም እና የእኔን ስም ለማጥፋት ተብሎ ነው የተጻፈው፤ ሳምሶን ከደራሲው ጋር በጥቅም ተደራድሮ ነው ያስጻፈው፣ ከመጽሐፉም ጀርባ ሳምሶን አለ የሚል ስሞታ አቅርባለች፡፡ በዚህ ላይ የአንተ ምላሽ ምንድን ነው?
tilahun Gesese
ሳምሶን፡ መጽሐፉ ለጥቅም እና የሰው ስም በማጥፋት መናኛ ዓላማ እንዳልተጻፈ ያነበበ እና የሚያነብ ሁሉ በቀላሉ የሚረዳውና አፍ አውጥቶ የሚመሰክረው ነው፡፡ እኔም ሆንኩ ሌላ የቤተሰቤ አባል ከደራሲው ጋር ምንም ዓይነት የጥቅም ድርድር አላደረግንም፡፡ ያደረግነው ነገር ቢኖር፣ አባታችን ከ1934 ዓ.ም. ጀምሮ ጽፈው ያኖሩትን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ መነሻ በማድረግ የጥላሁንን የሕይወት ታሪክ በራሱ ጥረት አዳብሮ እንዲጽፍ ሙሉ ፈቃደኝነታችንን የሚገልጽ ሰነድ ፈርመን ሰጥተነዋል፡፡ ያም ሰነድ ዘከሪያ ጋ ይገኛል፡፡ እኔም ሆንኩኝ ወንድም እና እህቶቼ ጥላሁንን በተመለከተ በዉሱን ደረጃ የየግል ትውስታዎቻችንን ከማካፈልና በሥራው ላይ ሳለ ደራሲውን ከማበረታታት ባለፈ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ‹‹ይህን ጻፍ፣ ይህን አትጻፍ›› ያልንበት አንድም አጋጣሚ የለም፡፡ ደራሲው በዚህ መጽሐፍ ላይ ስድስት ዓመት ገደማ ለፍቶበታል፡ ፡ የልፋቱ ውጤትም እጅግ ያማረ መሆኑን ብዙዎች በአደባባይ እየመሰከሩ ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ደራሲው ወ/ሮ ሮማንን በተመለከተ ከእኔ የወሰደው አንድም መረጃ የለም፡፡ ከ2003 በኋላ ከደራሲው ጋር በስልክ ካልሆነ በቀር በአካል የተገናኘንባቸው ጊዜያት በጣም ውሱን ናቸው፡፡ በእነዚህም ጊዜያት “መጽሐፉ እንዴት እየሄደልህ ነው? አይዞህ በርታ” ከማለት በቀር አንድም ጊዜ በመጽሐፉ ይዘት ዙርያ አላወራንም፡፡ ስለዚህ፣ የወ/ሮ ሮማን ስሞታ በጭፍን የተሰነዘረና መሠረተ ቢስ እንደሆነ አረጋግጥልሃለሁ፡፡ ይህን ደግሞ ማንም መጽሐፉን ያነበበና ወደፊትም የሚያነብ ሰው እንደሚመሰክር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ቁምነገር፡- ወላጅ አባትህ አቶ ፈይሣ ኃይሌ የጻፉትን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ ለደራሲያን ማኅበር ለምን አልሰጠህም?

ሳምሶን፡ ይህን ያላደረግሁት የጥላሁን የሕይወት ታሪክ ከማንኛውም ዓይነት ተፅዕኖ ነፃ፣ ሚዛናዊና ገለልተኛ በሆነ ባለሙያ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ስላመንኩኝ ነው፡፡ እንዲህ ስል የደራሲያን ማኅበርን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ ለመክተት አይደለም፡፡ ነገር ግን፣ በደራሲያን ማኅበር የሚጻፈው የጥላሁን የሕይወት ታሪክ የአንድ አካል ተፅዕኖ ሊያርፍበት ይችላል የሚል ሥጋት ነበረኝ፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ከተለያዩ ትዳሮችና የአብሮ መኖር ግንኙነቶች ሰፊ ቤተሰብ ያፈራ ሰው እንደመሆኑ፣ የሕይወት ታሪኩ ከአንዱ ወይም ከሌላኛው ቤተሰብም ሆነ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነጻ በሆነ ፕሮፌሽናል መንገድ ቢሠራ የጥላሁን አፍቃሪ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሩ ሥራ ይቀርብለታል ከሚል እምነትም ነው፡፡ በአጋጣሚ ከዘከሪያ ጋር ተዋወቅን እና ሥራውን እርሱ ጀመረው፡፡ ላለፉት ስድስት ዓመታት በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት፣ ሥራውን በፍቅር ሲያከናውን ከርሞ ‹‹ለሌሎች ፀሐፍያን አዲስ ጎዳና የቀደደ›› ተብሎ በምሁራን የተሞገሰ አስገራሚ እና መሳጭ መጽሐፍ ጽፎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቀረበ፡፡ ማስታወሻዎቹን ለደራሲያን ማኅበር ሰጥቼ ቢሆን ኖሮ፣ የጥላሁን ታሪክ እንዲህ ተተንትኖ ይቀርብ ነበር ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህም፣ ባለመስጠቴ አልቆጭም፡፡ የሚገርመው፣ ዘከሪያ አራት ምዕራፍ ጽፎ እንደጨረሰ፣ ‹‹እውነተኛውን የጥላሁን ገሠሠ የትውልድ፣ የልጅነትና የቤተሰብ ታሪክ ከፎቶግራፍ ማስረጃዎች ጋር ልስጣችሁ›› ብሏቸው ነበረ፡፡ ‹‹አራቱ ምዕራፎች፣ የአቶ ፈይሣ ኃይሌን ማሥታወሻዎች መነሻ በማድረግ በእኔ የተጻፉ መሆኑን ጠቅሳችሁ ተጠቀሙበት›› ሲላቸው እምቢ አሉ፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን በዙ ጥላሁን ደብረ ብርሃን ወስዶ ከአቶ ፈይሣ ጋር እንዳስተዋወቃት ተናግራለች፡፡… እውነት ነው?
ወ/ሮ ሮማን እና አቶ ፈይሣ ይተዋወቁ ነበር?

Roman Bezu

Roman Bezu


ሳምሶን፡ በቁም ነገር መጽሔት (14ኛ ዓመት፣ ቅፅ 14፣ ቁጥር 203) ላይ ወ/ሮ ሮማን በዙ ከተናገረቻቸው ንግግሮች ውስጥ እጅግ በጣም የሚያስገርሙ ሦስት ተከታታይ ዓረፍተ ነገሮችን ቃል በቃል እንዳነብባቸው ፍቀድልኝ፡ … ‹‹አቶ ፈይሣን አውቃቸዋለሁ፡፡ ደብረ ብርሃን ወስዶ ጥላሁን አስተዋውቆኛል፡፡ የእሳቸው ልጅ ሳምሶን ደግሞ እኛ ቤት ይኖር ነበር፤›› ብላለች፡፡ እነዚህ ሦስቱም ዓረፍተ ነገሮች ውሸቶች ናቸው፡፡ ወ/ሮ ሮማን አባቴን (አቶ ፈይሣን) አታውቃቸውም፡፡ ጥላሁንም ደብረ ብርሃን ወስዶ ከአባቴ ጋር አላስተዋወቃትም፡፡ እኔ ሳምሶን ደግሞ እነርሱ ቤት አልኖርኩም፡፡ … እነዚሁ የሐሰት ንግግሮች በቀጣዩ ገጽ ላይም ይደገማሉ፡፡ ‹‹[አቶ ፈይሣን] አንድ ሁለት ጊዜ ነው ደብረ ብርሃን ሄጄ ያገኘኋቸው፡፡ … በጣም በቅርብ የማውቀው ልጃቸው ሳምሶንን ነው፡፡ እሱ እኛ ቤት ነው ይኖር የነበረው፤›› ብላለች፡፡ ወ/ሮ ሮማን ከጥላሁን ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ደብረ ብርሃን የመጣችው፣ ሄሎም የምትባል እህታችን ባረፈችበት ወቅት፣ በሚያዝያ 1989 ነው፡፡ አባቴ አቶ ፈይሣ በዚያን ጊዜ በሕይወት የሉም፡፡ እርሳቸው በሐምሌ 1985 ዓ.ም. ነው ያረፉት፡፡ ወ/ሮ ሮማን፣ ይህን መጽሐፍ ጭቃ ለመቀባት ቸኩላ አደባባይ ከመውጣቷ በፊት መጽሐፉን ከመጀመርያ እስከ መጨረሻው በእርጋታ አንብባው በነበረ፣ እንዲህ ያለ ዓይን ያወጣ የሐሰት ንግግር በአደባባይ ከመናገር ትድን ነበር፡፡ ጨርሳ ስላላነበበችው ነው’ንጂ መጽሐፉ ውስጥ አባቴ ያረፉበት ቀን በግልጽ ተጽፏል፡፡ … ወ/ሮ ሮማን በቃለ ምልልሱ ላይ ‹‹አንድን መጽሐፍ ሽፋኑን ዓይተህ ግምት አትስጥ›› የሚል ጥቅስ ጠቅሳለች፡፡ መልሳ ግን እዚያው ቃለ ምልልስ ላይ፣ “‹በመጽሐፉ ላይ የሳምሶን እጅ እንዳለ ሳውቅ፣ መጽሐፉ በምን ደረጃ እንደሚጻፍ ይገባኛል፡፡ እያንዳንዱን ገጽ እንኳ ማንበብ አይጠበቅብኝም፤›› አለች፡፡ ይህ ‹አንድን መጽሐፍ ሽፋኑን ብቻ ዓይቶ ግምት ከመስጠት› በምን ይለያል? … በመጽሐፉ ውስጥ የሳምሶን እጅ እንዳለ እና እንደሌለ ለማወቅም’ኮ መጽሐፉን ገጽ በገጽ ማንበብ ነበር የሚጠቅማት፡፡ ቃለ ምልልሱን ከመስጠቷ በፊት መጽሐፉን ብታነብ ኖሮ፣ ደራሲው ከአባቴ ማስታወሻዎች በተጨማሪ የጥላሁን የረጅም ዘመን ወዳጆችን፣ የወሊሶ የትምህርት ቤት ጓደኞችን፣ በሶየማ የጥላሁን የትውልድ መንደር የሚገኙ የቤተሰብ አባላትን እና በተለያዩ ዘመናት ከጥላሁን ጋር የጓደኝነት ወይም የሥራ ቅርበት ከነበራቸው ሰዎች በቃለ መጠይቅ መረጃ በመሰብሰብ፣ እንዲሁም ከ1950 ገደማ ጀምሮ በሚዲያ የወጡ ዘገባዎችን እና መጻሕፍትን በማገላበጥ በከፍተኛ ጥረትና ድካም የሠራው መሆኑን መረዳት ትችል ነበር፡፡ ይህን በቅን ልቡና መመልከት ብትችል ኖሮ ደግሞ በመጽሐፉ ከልብ ልትደሰትና ደራሲውንም ልታመሰግነው ነበር የሚገባት፡፡ ከዚያ በተቃራኒ መጽሐፉን ያነበቡትና ወደፊትም የሚያነቡት ሰዎች ይታዘቡኛል እንኳ ሳትል፣ መጽሐፉን ማጣጣል መሞከሯ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡

ቁምነገር፡- ወ/ሮ ሮማን በቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻው ተዓማኒነትም ላይ ጥያቄ ታነሳለች፡፡ በዚህ ላይ አንተ ምን ትላለህ?

ሳምሶን፡ በቅን ልቡና የቀረበ ቢሆን ኖሮ፣ ይህ ጥያቄ በራሱ ምንም ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን፣ ለእኔ እንደሚገባኝ፣ ወ/ሮ ሮማን የዚህን መጽሐፍ ለህትመት መብቃት ተከትላ ወደ መገናኛ ብዙኃን የወጣችው፣ በቀጥታ በመጽሐፉ ላይ አሉታዊ ዘመቻ ለመክፈት፣ መጽሐፉን ለማጣጣል ነው፡፡ በዚህ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይህን መጽሐፍ ገዝተው ካነበቡ ብዙ ሰዎች ጋር ተገናኝቻለሁ፡፡ ከወጣት እስከ ጎልማሳ ስለ መጽሐፉ የሚያደንቅና የሚያሞግስ እንጂ፣ አንድም መጽሐፉን የሚተች የሚያጣጥል ሰው አልገጠመኝም፡፡ ሐያሲያንም መጽሐፉን በማድነቅ እየጻፉ ነው፡፡ እንዳውም አንድ ጋዜጠኛ በመጽሐፉ ዙርያ የጻፈውን በሳል ትንተና በዚሁ በቁም ነገር መጽሔት ላይ ነው ያነበብኩት፡፡ በአንፃሩ፣ ከማንም አስቀድማ ይህን መጽሐፍ ማድነቅ እና ደራሲውንም ማመስገን የሚጠበቅባት ወ/ሮ ሮማን፣ መጽሐፉን፣ ያውም ሙሉ በሙሉ ሳታነበው፣ [ብታነበው ኖሮ ‹‹አቶ ፈይሣን አውቃቸዋለሁ›› ባላለች] በአደባባይ ስታጣጥለው መስማት በጣም ያስገርማል፡ ፡ ያላነበበውን መጽሐፍ በአደባባይ የሚያጣጥል ሰው፣ ይህን ያደረገው ከቅን ልቡና ነው ለማለት ይከብደኛል፡ ፡ ስለዚህም፣ ወ/ሮ ሮማን አባቴ ከ1934 ጀምሮ ጽፈው ባኖሯቸው የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻዎች ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ ለማንሳት የሞራል ብቃት አላት ብዬ አላምንም፡፡ ይህን ካልኩ በኋላ ግን፣ በወላጅ አባታችን የተጻፉትን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻዎች እና ሌሎችም በርካታ ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሰነዶች፣ ለጥናት እና ምርምር ይውሉ ዘንድ ለተገቢው የጥናትና ምርምር ተቋም መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት እንደምናነጋግር በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ቁምነገር፡- በመጨረሻም ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት፣ ወይም በአቶ ፈይሣ ማስታወሻዎች ላይ ተመስርቶ ስለተጻፈው የጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ “ሰዎች ሊያውቁት ይገባል” የምትለው ነገር አለ?

ሳምሶን፡ ይህን ዕድል ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ እንደ ጥላሁን ቤተሰብ ሆኜ፣ ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው አንድ ነገር ቢኖር፣ ‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር› በሚል ርዕስ ታትሞ የወጣው መጽሐፍ ከመሠረቱ ጀምሮ በፍፁም ቅንነት፣ በእውነት፣ በፍቅር እና በከፍተኛ ትጋት ነው የተጻፈው፡፡ የመጽሐፉን መሠረት በቃላት የተከሉት ወላጅ አባቴ አቶ ፈይሣ ኃይሌ ሐሰና ሲኾኑ፣ በዚህ መሠረት ላይ ዘከሪያ ለጥላሁን ገሠሠ ድንቅ የሆነ ሐውልት በውብ ቃላት አዋቅሮ አንጾለታል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ለመጽሐፉ ግብዓት የሚሆን መረጃ ለደራሲው በመሥጠት የተባበሩትን የጥላሁን ወዳጆች፣ የሥራ ባልደረቦች እና የቤተሰብ አባላት በመላው የአቶ ፈይሣ ልጆች ስም ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡

ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡

ምንጭ – ቁምነገር መጽሔት

The post ‹‹የጥላሁን ገሠሠ ሚስትነት ከሕግ የበላይ አያደርግም.. ወ/ሮ ሮማንን በሕግ እፋረዳታለሁ!› appeared first on Zehabesha Amharic.

የማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ተከበረ * አላሙዲ 5 ሚሊዮን ብር ሸለሙት

$
0
0

 

(ዘ-ሐበሻ) የትዝታው ሙዚቃ ንጉሥ የሚል የክብር ስያሜን ከኢትዮጵያውያን የተጎናጸፈው ዝነኛው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመኑ ተከበረ::

ማምሻውን በሸራተን አዲስ በተከናወነው በዚሁ የማህሙድ አህመድ የሙዚቃ ዘመን 50ኛ ዓመት ልደት ላይ ድምፃዊውን የሚዘክሩ የተለያዩ ፕሮግራሞች ከመቅረባቸውም በላይ ድምፃዊውም ሥራዎቹን ለሕዝቡ ማቅረቡን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቆሟል::

በዚሁ ምሽትም ለ50 ዓመት የሙዚቃ አገልግሎቱ ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የ5 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደተበረከተለት ለማወቅ ተችሏል::

የማህሙድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ ሕይወት በራሱ አንደበት እንደሚከተለው ዘ-ሐበሻ አሰናድታዋለች:: ይከታተሉት::
Mahamud Ahemed 2

ትውልድና ዕድገት
ቤተሰቦቼ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ የተወለድኩት አሜሪካ ግቢ በ1933 ዓ.ም ነው፡፡ እስከ ሶስት ዓመቴ ድረስ አሜሪካ ግቢ ካደኩ በኋላ በሶስት ዓመቴ ወደ ጉለሌ አርበኞች ት/ቤት ፊትለፊት ያለው ኦሎምፒያ ኳስ የሚባል የግሪክ ክለብ ነበር እዚያ ውስጥ አባቴ ይሰሩ ነበር፡፡ በዚያ ስፖርት ክለብ ውስጥ እየሄድኩ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ ሜዳ ስፖርተኞች ከተጫወቱበት በኋላ ሜዳውን ውሃ እያጠጣሁ እየደመጥኩ አስተካክል ነበር፡፡ አባቴ በሌሉበት ጊዜ የዚያ ስራ ሀላፊነት የኔ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት

ትምህርት ቤትን በተመለከተ ብዙ ባይገባኝም መማር ጀምሬ ነበር፤ ትምህርት ቤት ስገባ ምናልባት 8 ዓመት 9 ዓመት ይሆነኝ ይሆናል፡፡ ቄስ ት/ቤትም ከጓደኞቼ ጋር ገብቼ ነበር፤ መጀመሪያ በእርግጥ ሙስሊም ት/ቤት ነበርኩ፡፡ ወደ 15 ዓመት ሲሆነኝ አባቴ የሚሰሩበት የግሪክ ክለብ ሲዘጋ ስራ ፈቱ፡፡ ከእናቴ ጋር ሆኜ የቤተሰቡን ህይወት ለማገዝ ከእናቴ ጋር ብታምኑም ባታምኑም ጉሊት ቁጭ ብዬ እንጀራ እሸጥ ነበር፡፡ ወደ ጫካ ሄጄ ጭራሮ ና ማገዶ ለቅሜ በማምጣት ለእናቴ እንጀራ መጋገሪያ አቀርብላት ነበር፡፡
በዚህ ሁኔታ ለ6 ዓመት ያህል ትምህርት ቤት እየሄድኩ ስመለስ ሊስትሮ ሆኜ ጫማ እጠርግ ነበር፡፡ ከጓደኞቼ መሀከል ሰነፉ ተማሪ እኔ ነበርኩ፡: ጥያቄ ሲቀርብ ግን የምመልሰው እኔ ነበርኩ፡፡ ግን ፈተና ላይ ስንቀመጥ ነርቨስ ስለምሆን መስራት አልችልም ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ መማር መቀጠል አልቻልኩም፡፡

ሊስትሮና ሙዚቃ

ማታ ማታ እናቴ ዘፈን ታንጎራጉር ስለነበር ስሜቴ ሁሉ ወደ ሙዚቃ ሆነ፤ በ1949 ዓ.ም የንጉሰ ነገስቱ የክብር ዘብ ግቢ ውስጥ የጠቅል ሬዲዮ የሚባል ነበረ፤ ማክሰኞና ሀሙስ ዘፈንና አንዳንድ ፕሮግራሞች ይለቀቁ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ በሬዲዮ ቀርበው ይዘፍኑ የነበሩት እነ ካሳ ተሰማ፣ ተዘራ ሀ/ሚካኤል፣ መቶ አለቃ ኑር ወንዳፍራሽ (የብዙነሽ በቀለ የልጆቿ አባት የነበረው) ብዙነሽ በቀለ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ አየለ ማሞ፣ እሳቱ ተሰማ ወዘተ ነበሩ፡፡ የዚያን ጊዜ እነዚህ ድምፃውያን በሳምንት ሁለት ቀናት ሙዚቃቸውን እየመጡ ያሰሙ ስለነበር እኔ ቡና ቤት በር ላይ ሊስትሮ ሳጥኔ ላይ ቁጭ ብዬ ዘፈናቸውን አዳምጥ ነበር፡፡ የሚገርማችሁ ማታ የሰማኋቸውን ዘፈኖች ጠዋት ት/ቤት ከመግባታችን በፊት ለክፍል ጓደኞቼ እዘፍንላቸው ነበር፡፡

በወቅቱ ሞዴሌ አድርጌ የምቆጥረው ትልቁ ወንድሜን በአሁኑ ወቅት በዚህ ዓለም ላይ የሌለው ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ ሌላ ደግሞ በወቅቱ ከውጪ ሀገር የሚመጡ ፊልሞችን እመለከት ስለነበር በተለይ የኤልቪስ ፕሪስሊንን ዘፈን አዳምጥ ነበር፡፡ ኤልቪስ ፕሪስሊን ሲዘፍን እግሩን እንዴት ያንቀጠቅጥ እንደነበር በፊልም ላይ እመለከት ስለነበር እኔም ወደፊት መድረክ ላይ ስወጣ እግሬን አንቀጠቅጣለሁ እል ነበር፤ የኤልቪስ ፕሪስሊንን ብቻ ሳይሆን የነ ሳምኩክን፣ የነ ጀምስ ብራውንን ዘፈኖች አዳምጥ ነበር፡፡
ወደ ሙዚቃው እየተሳብኩ ስመጣ የትምህርቱ ነገር እየቀረ መጣ፤ ከ8ኛ ክፍል በላይ ማለፍ አልቻልኩም፡፡ ጎረቤታችን ወ/ሮ የሺሀረግ ለእኛ የሰጡን አራት በአራት የምትሆን አንድ ክፍል ነበረችን፡፡ ጎረቤታችን አንድ ግብፃዊ ጠበቃ ነበር፤ ያ ጠበቃ ሹፌሮች ቡና ቤት ከሚባለው ቤት ባለቤት ጋር በመሆን ራስ ሀይሉ ቤት ውስጥ ናይት ክለብ ሊጀመር ነው የሚል ወሬ ስሰማ ለእናቴ ሄጄ ሥራ እንዲያስገባኝ ለምኚልኝ አልኳት፡፡ እሷም እሺ አለችና ሄዳ ስትጠይቀው ጥሩ ይምጣና ከአናፂዎች ጋር እመድበዋለሁ አለ፡፡ እሺ አልኩና ሄድኩ፡፡ ከአናፂዎች ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ከቀለም ቀቢዎች ጋር ሠርቻለሁ፡፡ ቡና ቤቱ ለናይት ክለብ በሚሆን መልኩ ይሰራ ስለነበር ከነሱ ጋር ሰራሁ፤ በየግድግዳው ላይ ሰዎች ሲጨፍሩ ሁሉ የሚያሳይ ስዕል ተሰርቶ ተጠናቀቀ፡፡

ምሽት ክለብ

በ1954 ዓ.ም ገደማ የሚገርማችሁ ምሽት ክበቡ ተሠርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ሲከፈት እኔ ወደ ወጥ ቤት ነበር የገባሁት፡፡ ወጥ ቤት ስገባም የወጥ ቤት ረዳት ተደርጌ ነበር የተመደብኩት፡፡ ረዳት ሆኜ እየሰራሁ ማታ ማታ ምሽት ክለቡ ውስጥ እየመጡ የሚዘፍኑትን እነ እሳቱ ተሰማ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ ተፈራ ካሳ፣ ታምራት ሞላ፣ አባይ በለጠ (ነፍሳቸውን ይማረውና) እመለከት ነበር፡፡

እነሱ ዘፍነው ለእረፍት ሲቀመጡ እኔ ሳንድዊችና ሻይ አቅራቢ ነበርኩ፡፡ እነሱን ስር ስር ጉድ ጉድ እያልኩ ዘፈናቸውን በደንብ ነበር የማደምጠው፤ ታዲያ በአንድ አጋጣሚ እነ ጥላሁን ድሬዳዋ ለስራ ታዘው ሲሄዱ ሙዚቀኞች ብቻቸውን ቀሩ፡፡

ሙዚቀኞቹ የተፈራ ካሳን አልጠላሽም ከቶ ዘፈን መጫወት ሲጀምሩ ከወጥ ቤቴ ሹልክ ብዬ ወጥቼ ‹‹ይህቺን ዘፈን እሺ ልዝፈናት›› አልኳቸው፡፡ ቀጭን ስለነበርኩ አይተውኝ ‹‹ትችያዋለሽ እንዴ›› አሉኝ፡፡ እሞክራሁ አልኳቸውና መድረክ ላይ ወጥቼ ስጫወት እንደአጋጣሚ እዚያ ቤት ከምድር ጦርም ከጦር ሰራዊትም የኮንጎ ዘማቾች ነበሩና ሰምተው ተገረሙ ስጨርስ ቢስ ብለው አስደገሙኝ፤ ስጨርስ እንደገና ለሶስተኛ ጊዜ አስደገሙኝ፤ ‹ይህም አለ ለካ› የተሰኘውን የተዘራ ኃ/ሚካኤልን ስጫወትም ይደገም ተባለ፤ ደገምኩ፤ ያንን ዘፍኜ ከመድረክ ልወርድ ስል የምሽት ክለቡ ባለቤት ፊት ለፊቴ ቆሞ ‹‹ያ አላህ፤ ለመሆኑ መዝፈን ትችላለህ እንዴ?›› አለኝ ‹‹እሞክራለሁ›› ስለው ከነገ ጀምሮ ወደ ወጥ ቤት አትመለስም እነ ጥላሁን እስከሚመጡ ድረስ እዚሁ ትዘፍናለህ›› አለኝ፡፡ በማግስቱም መርካቶ ወሰደኝና ሙሉልብስ፣ ጫማና ሸሚዝ ከነልዋጩ ገዛልኝ፡፡ እነ ጥላሁን ከድሬዳዋ ሲመለሱ መድረኩ ላይ ቄብ ብዬ ጠበኳቸው፡፡ መድረክ ላይ ቆሜ ስዘፍን ሲያዩኝ ተገረሙ፡፡ ‹‹መዝፈን ትችያለሽ እንዴ›› እያሉ ሲጠይቁኝ ‹‹እሞክራሁ›› ነበር መልሴ፤ ከዚያ ብታምኑም ባታምኑም አንድ ሙሉ ግጥም የያዘ ደብተር አመጡልኝና አጥና አሉኝ፡፡ እየመረጥኩ የጥላሁንን፣ የእሳቱን፣ የተዘራን፣ የካሳን ዘፈኖች ግጥሞች ማጥናት ጀመርኩ፡፡

Mahamud Ahemed

ምሽት ክለቡ እየተሟሟቀ ብዙ ደንበኞች እየመጡ ሳለ በ1954 ዓ.ም እቴጌ መነን ያርፋሉ፡፡ በዚሁ ሰበብ ምሽት ክለቡ ተዘጋ፡፡ ግን ከሁለት ወራት በኋላ ሀዘኑ ይበቃል ብለው ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ‹‹ህዝቤ ሀዘኔን ከኔ ጋር ተካፍለሀልና ከዚህ በኋላ ወደ ስራህ ግባ›› ባሉት መሠረት የሙዚቃ ሥራ ዳንስ ቤቱ ሁሉ ሲከፈት የእኛም ምሽት ክለብ ተከፈተ፡፡ የዚያን ጊዜ ያው የሰው ዘፈን እያጠናሁ ስለነበር የምዘፍነው የመጀመሪያዋን የራሴ ዘፈን፡-
‹‹ካንቺ በቀር ሌላ ብሞት አልመኝም
ግን እስካሁን ድረስ አላወቅሽልኝም››

የተባለችው ዘፈን ተሰጥታኝ የጉሮሮዬ ማሟሻ ሆና ተጫወትኳት፡፡ ይህቺ ዘፈን አሁን ድረስ አብራኝ አለች፡፡

ጉዞ ወደ ክቡር ዘበኛ

ወደ ክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ ፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል ነበር ለመግባት የፈለግሁት፡፡ በዚህም መሠረት ለምን ሄጄ አልጠይቃቸውም ብዬ ሄጄ ስጠይቅ ‹‹የማንን ዘፈን ነው የምትዘፍነው?›› ሲሉኝ የነ ጥላሁን ገሠሠ፣ የነ እሳቱ ተሰማ ስላቸው ‹‹የሙዚቃ ትምህርት ተምረሃል ወይ›› አሉ፣ አልተማርኩም ስል ካላወቅህ አንፈልግም አሉኝና መለሱኝ፡፡ ከዚያ እንደገና ወደ ምድር ጦር ሙዚቃ ክፍል ሄድኩ፡፡ እዚያ ደግሞ ‹‹መጀመሪያ ደብረ ብርሃን ሄደህ ወታደርነት ተቀጥረህ ስትመጣ ነው ወደዚህ ክፍል የምትገባው›› አሉኝ፡፡ አይ እንግዲህ ዕድሌ አይደለም ብዬ ዝም ብዬ እዚያ ምሽት ክለብ ውስጥ ማታ ማታ ስሰራ ቆይቼ ለምን ክቡር ዘበኛ አልሄድም ብዬ ሻለቃ ግርማ ሀድጎ ስሄድ በዚያን ወቅት የፊደል ሠራዊት የሚባል ተቋቁሞ ለነሱ እርዳታ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት የክቡር ዘበኛ፣ የጦር ሠራዊት፣ የፖሊስ እና የቀዳማዊ ሀይለስላሴ የሙዚቃ ክፍሎች ባሉበት ዝግጅት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እነ ተሾመ ምትኩን ይዞ ተሳትፏል፡፡ በዚህ የሙዚቃ መድረክ ላይ ነው እንግዲህ ተፈትነህ ካለፍክ ትቀጠራለህ የተባልኩት፡፡ በዕለቱ ትዝ ይለኛል የመድረክ አስተዋዋቂ በዚያን ወቅት የ10 አለቃ ገዛኸኝ ደስታ ነበር፡፡ የተናገረው ነገር አሁን ድረስ አይረሳኝም፡፡ ‹‹አንድ አዲስ ልጅ ዛሬ እናቀርብላችኋለን፡፡ ልጁ ምናልባት የጥላሁን ገሠሠ ደቀመዝሙር ይሆናል ብለን እንገምታለን፡፡ ይሁን ካላችሁ ይቀጥላል›› ነበር ያለው፤ አስቦት ይሁን የተናገረው ታይቶት ይሁን አላውቅም፡፡ እንደዚህ አስተዋውቆኝ መድረክ ላይ ወጣሁ፡፡ ይዤ የነበረው የታምራት ሞላን፣ የገላን ተሰማን፣ የጥላሁን ገሠሠንና የራሴን የተሰጠችኝን ካንቺ በቀር ሌላን ተጫወትኩ፡፡ ከታምራት ዘፈን ቀጥሎ የራሴን ስዘፍን አቀባባሉ ልዩ ነበር፡፡ ስጨርስ ይደገም ተባለ፡፡ ደገምኩ፡፡ የሚገርማችሁ ሶስተኛውን ዘፈን ስጫወት ልክ ያኔ ኤልቪስ ፕሪስሊን እንደሚያደርገው እግሬን እያንቀጠቀጥኩ ነበር፡፡ ህዝቡም በልዩ አድናቆት አጀበኝ፡፡

ከመድረክ ስወርድ በክቡር ዘበኛ ውስጥ ልቀጠር እንደምችል አውቅ ነበር፡፡ ምክንያቱም የህዝቡ አቀባበል ልዩ ነበር፡፡ ታዲያ ሻለቃ ግርማ ሀድጎ ምን አሉኝ ‹‹ስማ አንተ ልጅ በወታደርነት እንቅጠርህ ቢሉ እሺ እንዳትላቸው፤ በሲቪል ግን ካሉህ እሺ በላቸው፡፡›› አሉኝ፡፡ እሺ አልኳቸውና በወታደርነት እንቅጠርህ ሲሉኝ አልፈልግም በሲቪልነት ነው የምፈልገው አልኳቸው፡፡ ከዚያ የዚያን ጊዜ ደሞዝ 60 ብር ስለነበር በሲቪልነት በ60 ብር በወታደርነት ደግሞ በ60 ብር በድምሩ በ120 ብር እንቅጠርህ አሉኝ፡፡ አልፈልግ ስል በሲቪልነት በ60 ብር ደሞዝ ታህሳስ 15 ቀን 1955 ዓ.ም ክቡር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል ተቀጠርኩ፡፡

ለ11 ዓመታት ያህል በክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ውስጥ ሳገለግል የመጀመሪያው መምህሬ የአፍ አከፋፈትና የድምፁ አወጣጥ ያስተማረኝ ወንድሜ ጥላሁን ገሠሠ ነበር፡፡ ሌሎችም ጓደኞቼ የየራሳቸውን ምክር ሰጥተውኛል፡፡ እነ እሳቱ ተሰማ፣ ተዘራ ሀ/ሚካኤል፣ ብዙነሽ በቀለ ሁሉም መክረውኛል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ እጠቀምበታለሁ፡፡
በ1955 ዓ.ም ለ1956 ዓ.ም አዲስ ዓመት መግቢያ የምድር ጦር የንጉሰ ነገስቱ የክብር ዘብ ሙዚቀኛ፣ ፖሊስ ሠራዊትና ኪነ ጥበባት መምሪያ የሚባል ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለው ልዩ ዓመታዊ የሙዚቃ ውድድር ያካሂድ ስለነበር ሁላችንም ተዘጋጅተን ነበር የምንሄደው፡፡ የዚያን ጊዜ እያንዳንዳችን አራት ወይም አምስት አዲስ ዘፈን ይዘን ነበር የምንቀርበው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለኔም ሌሎች አዳዲስ ዘፈኖች ተሰጡኝ፡፡ በደንብ መዝፈን ጀመርኩ፡፡ በ11 ዓመታት ቆይታዬ ብዙ ዘፈኖች ተጫውቻለሁ፡፡ ከዚያ ክቡር ዘበኛን ለቅቄ ወደ ናይት ክለብ ስራ ራስ ሆቴል ገባሁ፡፡

ወደ ናይት ክለብ ስራ ልገባ የቻልኩት ክቡር ዘበኛ የሚከፈለኝ 250 ብር እያነሰኝ መጣ፡፡ ቤታችን ውስጥም 3 ወንዶች ሶስት ሴቶች ስላለን ለማስተዳደር በቂ አልሆን አለ፡፡ አባቴም ስራ ስላቆመ እናቴም እንጀራ ጉልት ብቻ ስለነበር የምትሸጠው የኔ ደሞዝ እያነሰ ሲመጣ ለቅቄ በ1966 ዓ.ም ራስ ሆቴል አይቤክስ ጋር ናይት ክለብ ገባሁ፡፡ ከዚያ ጊዜ ወዲህ ህይወቴም እየተሻሻለ መጣ፤ አሁን ለደረስኩበት ደረጃ መሠረት የሆኑኝን ዘፈኖች ሰራሁ፡፡

በኛ ዘመን ከነበረው አንፃር እናንተ በጣም እድለኞች ናችሁ፡፡ ምክንያቱም በኛ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰጠን ድምፅ ፀጋ በቀር ሌላ እውቀት አልነበረንም፡፡ እናንተ ግን አሁን ሙዚቃን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ነው እየተማራችሁ ያላችሁት፡፡ በዚህም ልትኮሩ ይገባል፡፡ ሙዚቃ በዓለም ላይ ትልቅ ደረጃ ደርሷል፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ የማድረስ ሀላፊነት እናንተ ላይ ነው የተጣለው፡፡ ለመጪው ትውልድ እናንተ መብራቶች ናችሁ ተጠቀሙበት፡፡
ስለ ፍራንሲስ ፋልሴቶ

በኔ በኩል የኢትዮጵያን ሙዚቃን ከራሴ አልፌ በዓለም እንዳስተዋውቅ ያደረገኝ አንድ ሰው አለ፡፡ ፈረንሳያዊው ፍራንሲስ ፋልሴቶ ይባላል፡፡ ይሄ ፈረንሳዊ ፕሮሞተር ነው፡፡ ፍራንሲስ ፋልሴቶ የኢትዮጵያ ሙዚቃን የሚወድ፣ ልቅም አድርጎ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡

የኔን ዘፈን በሬዲዮ ሰምቶ ነው ከፈረንሳይ ወደ አዲስ አበባ የመጣውና ያገኘኝ፡፡ ራስ ሆቴል ድረስ መጥቶ ካንተ ጋር መስራት እፈልጋለሁ፤ አለኝ፡፡ የዚያን ጊዜ ያው እንደ ማንኛውም ሰው አይ ይሄ ፈረንጅ እውነቱን ነው ብዬ ነበር የተጠራጠርኩት፡፡ ከዚያ ከአይቤክስ ሙዚቀኞች ጋር ሆነን የመጀመሪያ ጉዟችን ወደ ፈረንሳይ ሄድን፡፡ የዚያን ጊዜ ትዝ የሚለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሪስ ውስጥ እኔ ስሰራ ከኛ አዳራሽ ፊት ለፊት ባለ ሌላ መድረክ ላይ ማይክል ጃክሰን ይዘፍን ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ እኔ ስጫወት ሙላቱ አስታጥቄ ትልቁ ሙዚቀኛ አብሮን ነበር፡፡ ሙላቱ የኢትዮጵያ ሙዚቃን በከፍተኛ ደረጃ ያስተዋወቀ ሰው ነው፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈረንሳይን ረግጨ ብዙ ስራዎችን አብረን ከፍራንሲስ ፋልሴቶ ጋር ሰርተናል፡፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አልበምን አሳትሟል፡፡ የኔ ብቻ ሳይሆን የጥላሁን ገሠሠ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ አለማየሁ እሸቴን የሌሎችንም በልዩ ሁኔታ አስቀርፆ አውጥቷል፡፡

በነገራችን ላይ እኔ ይህ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከተማሪዎች ፊት ቁጭ ብዬ የሕይወት ልምዴን ሳካፍል፤ ለናንተ ይህንን ነገር ከተናገርኩ በኋላ እኔ ዛሬ ማታ ብሞት ቅር አይለኝም፡፡
የአንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ገለፃ እንዳበቃ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከተማሪዎች ቀርቦለታል፡፡ ከቀረቡት ጥያቄዎች መሀከልም የመጀመሪያ አልበምህ ያሳተምከው መቼ ነው? የሚለው ይገኝበታል፡፡ ማህሙድ ሲመልስ ‹‹በካሴት ደረጃ ያወጣሁት የመጀመሪያ ካሴት በ1972 ገደማ ነው፤ ከዚያ በፊት ሸክላ ነበር፤ በዚህ ካሴት ላይ አሽቃሩ የሚለው ዘፈን ያለበት ሲሆን ደራን ጨምሮ 10 ዘፈኖችን ይዟል፡፡ የሚገርማችሁ በዚያን ወቅት ጥላሁንም ካሴት አውጥቶ ነበር፡፡ የሱ በሎ የሚለውን የኦሮሞኛ ዘፈን የያዘ ሲሆን የኔ ደግሞ አሽቃሩ የሚለው የጉራጊኛ ዘፈንን የያዘ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ እሱ አሽቃሩ ሲለኝ እኔ በሎ በሎ ነበር የምለው፡፡››

በትዝታ ዘፈኖችህ ላይ ልዩ ድምፅ አለህ? ይህንን ችሎታህ እንዴት አዳበርከው ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ‹‹እኔ ከሌሎች የተሻለ ድምፅ አለኝ ለማለት አልችልም፤ ከሌሎች ተሽዬ ሳይሆን ባለኝ አቅም እግዚአብሔር በሰጠኝ ፀጋ እዚህ ደርሻሁ፡፡ የድምፅ አወጣጥ ወይም ስለ ድምፅ የተሰጠኝ ትምህርት የለም፡፡ በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው የምንዘፍነው ካንዳችን አንዳችን የምንማረው ነገር አለ፡፡ አሁን እናንተ እድለኞች ናችሁ የምለው በኖታ ተፅፎ እያነበባችሁ ነው ሙዚቃ የምትጫወቱት፡፡ በኮንዳክተር የሚዘፍኑ ድምፃውያን አሉ፤ ከኖታ ላይ የሚዘፍኑ አሉ፤ እኛ ግን የዚህ ዕድል ተጠቃሚዎች አልነበርንም፡፡ ለዚህ ነው እኔ ችሎታ አለን ብዬ የማልናገረው፡፡ ሀይል አለኝ አልልም፤ ሀይል የእግዚአብሔር ነው››
በሙዚቃ ህይወትህ ያጋጠሙህ ፈተናዎች ምን ይመስላሉ? እንዴትስ አለፍካቸው? ለወጣቶችስ ምን ትመክራህ? ‹‹በሙዚቃ ህይወቴ ብዙ ነገሮችን አሳልፌያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ስቀጠር በሙዚቀኛ ደረጃ አልነበረም የምንጠራው፤ ያንን ጊዜ በትዕግስት አልፈናል፡፡ አዝማሪ ነበር የምንባለው፤ ግን በዚያን ወቅት አዝማሪ እንደስድብ የሚቆጠር ቢሆንም በኋላ ግን ክብር መሆኑን ነው ያወቅሁት፡፡ ምክንያቱም አዝማሪ ይዘምራል የሚል ነገር ስላለ ስድብ ሳይሆን ክብር መሆኑን ነው ያወቅሁት፡፡ ያንን ዘመን አሳልፈናል፤ ግን በፀጋ ነው ተቀብለን ያሳለፍነው፤ በውጪው ዓለም አሁን የሙዚቃ ሰው ያለውን ክብር እያያችሁ ነው፤ ይህንን ይዞ ወደፊት መሄድ ያስፈልጋል፡፡ እናንተ ናችሁ ሙያችሁን የምታስከብሩ፤ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ነው የምለው፤ ችግር ቢመጣም መቻል ነው ያለባችሁ፡፡ መሠረታችሁን ሳትለቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃን ለማሳደግ ነው መጣር ያለባችሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የውጪ ሀገር ሙዚቃዎችን ስታሰሙ እንዴት አድርገው ነው የሰሩት ልትሉት ትችላላችሁ፤ ግን በትምህርት የተሰራ በመሆኑ ትምህርታችሁን ጠንክራችሁ ልትማሩ ይገባል››

በ1968 እና 1968 ገደማ በነበረው የሀገራችን ሁኔታ ውስጥ የሰራሃቸው ስራዎች መሠረታዊ ለውጥ ያመጡ እንደሆኑ ይታወቃል፤ በተለይ የዕድገት በህብረት ዘመቻ ጊዜ የወጡት ስራዎች ማለት ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ትችት የሰነዘሩባቸው ሥራዎች አሉ፤ ስለ እነዛ ሥራዎችና ስለወቅቱ እስኪ አንዳንድ ነገሮችን ንገረን? ተብሎም ተጠይቆ ነበር፡፡
‹‹ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ራስ ሆቴል ከአይቤክስ ባንድ ጋር እሰራ ነበር፤ በዚያን ወቅት እነ ኩሉን ማን ኳለሽ፣ እነአምባሰል፣ እነትዝታ፣ እነችቦ አይሞላም ወገቧ፣ አልማዝ ምንዕዳ ነው የሠራሁበት ወዘተ ነው፡፡ ክቡር ዘበኛ ሆኜ ነበር በራስ ሆቴል ማታ ማታ የምሠራው፡፡ ታዲያ በዚህ የተነሳ ምን አየሠራህ ነው ተብዬ ተጠይቄ ነበር፤ እነዛን ዘፈኖች የተቀረፀበት ብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ነበር፡፡ታዲያ እነኩሉን ማንኩሎሻል ስጫወት ከፍተኛ ዝና ነበር ያገኘሁት፡፡ ጋዜጠኛ ግን ምንአለኝ ፍራሽ አዳሻ አለኝ፡፡ ‹‹ፍራሽ አዳሽ ስልህ ከፋህ ወይ›› ሲለኝ ለምን ይከፋኛል አልከፋኝም አልኩት፤ ፍራሽ አዳሽ የተበላሸ ፍራሽ ጥጥ እንደገና አስተካክሎ ሰው እንዲተኛበት የሚያደርግ ባለሙያ ነው፡፡ ፍራሹ ከመቆርቆር ወደ ምቾት ይቀይረዋል፡፡ እኔ ደግሞ የተረሱትን ዘፈኖች በማደሴና ፍራሽ አዳሽ በመባሌ ምንም ቅር አይለኝም ነው ያልኩት፡፡

በዕድገት በህብረቱ ዘመቻ ወቅት ተማሪው በሙሉ ወደ ገጠር ዘመቻ ሲሄዱ እኔ አታውሩልኝ ሌላ፣ ነይ ደኑን ጥሰሽ፣ መላ መላን፣ አባይ ማዶን ነበር የዘፈንኩት፤ እንደውም የአባይ ማዶን ግጥም የገጠመልኝ ሰው እዚህ መሀከላችሁ ይገኛል፡፡ ሸርፈዲን ሙሳ ይባላል፡፡ አባይ ማዶን ብቻ ሳይሆን ሌላም ዘፈን ፅፎልኛል፡፡ በቅርቡ ትሰማላችሁ ‹‹አብራኝ ናት›› የተባለ ግጥም ፅፎልኛል፡፡ አብራኝ ናት የሚለው አሁን አብራኝ ላለችው ባለቤቴን ነው፡፡ ድሮም ነበረች፤ አልማዜ ብዬም ዘፍኜላት አውቃለሁ፡፡ አብራኝ ናት ያልኩት ለምንድንነው? ከልጅነት እስከ እውቀት አብራኝ ናት፣ በሞራል አብራኝ ናት፣ በስራዬ አብራኝ ናት፣ የምታማክረኝ ናት፣ የኑሮ ደረጃዬ ከፍ እንዲል እየሠራች እዚህ ደረጃ ያደረሰችኝ እሷ ናት፡፡ አልማዝ አልማዝዬ ብዬ ዘፋኜላታለሁ፡፡ አሁን ደግሞ አብራኝ ናትን እዘፍንላታለሁ፡፡ አልማዝ አልዝዬ ግጥምና ዜማ የሰጠኝ ነፍሱን ይማረውና ፍሬው ሀይሉ ነበር ዛሬ ልጁ ደግሞ ፍሬው እዚሁ ት/ቤት ተምሮ ራሱን ለትልቅ ደረጃ ያበቃ የራሱን ካሴት ያወጣ ልጅ አፍርቷል፡፡ እናንተንም ለዚህ ደረጃ ያብቃችሁ ነው የምለው ፡፡
ታዲያ እነዛን ዘፈኖች በዕድገት በህብረት ዘመን ወቅት በመዝፈኔ በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ባልገባም ብሔራዊ ቴአትር የነበሩ ሠራተኞችና ሙዚቀኞች አድማ አድርገው ታፍሰው ነበር፡፡ በአድማው በታሰሩበት አንድ ካድሬ መጥቶ ሊያስፈታቸው ሲል ‹‹እኛ ትግል እየታገልን እንደገና አንዳንዱ አታውሩልኝ ሌላ ከሷ ዜና በቀር አያለ ይዘፍናል፡፡ እኛ ትግል እየታገልን ነይ ደኑን ጥሰሽን ይዘፍናል›› ብለው ወደሌላ ነገረ ቀይረው ሊያስመቱኝ ነበር፡፡ በወቅቱ ብዙ ችግሮችን አልፌያለሁ፤ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ያንን ሁሉ አልፌ ለዚህ ደረጃ በቅቻለሁ፡፡

የት የት ሀገራት የሙዚቃ ስራዎችህን አቅርበሃል? በሚል ለተጠየቀው ጥያቄ ‹‹መጀመሪያ ጊዜ ከፍራንሲስ ፋልሴቶ ጋር ፈረንሳይ ላይ ሙዚቃዎቼን ካቀረብኩ በኋላ ያልሄድኩበት ቦታ የለም ልል እችላለሁ፤ እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት በትክክል የማላውቃቸው ሀገሮች ጃፓንና ብራዚል ብቻ ናቸው ልል እችላለሁ፤ ከዚህ ውጪ ያሉ ሀገሮችን አይቻለሁ፡፡ በእንግሊዝ ሀገርም የቢቢሲ ሚውዚክ አዋርድ ተሸልሜያለሁ፡፡ በመላው ዓለም ዛሬ የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሼ ሀገሬን አስተዋውቄያለሁ ብል የዋሸሁ አይመስለኝም፡፡››
የህይወት ታሪክህን የተመለከተ መፅሐፍ እየተዘጋጀ እንደሆነም ይነገራልና መቼ ለአንባብያን የሚደርስ ይመስልሃል? በሚል ለቀረበለት የመጨረሻ ጥያቄም‹‹ታሪኩ በረድፍ በረድፉ እየተሠራ ነው፤ ግን ማነው በጥሩ ሁኔታ የሚፅፈው የሚለውን እያፈላለግሁ ነው፡፡ የራሴን ገጠመኞች እኔ ነኝ የምፅፈው ወይስ ለሌላ ሰው ተናግሬ ነው የማፅፈው የሚለው ገና ነው፡፡ ግን በህይወት እያለሁ መፅሐፌ ታትሞ ባየው ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ላልፍ እችላለሁ፤ ግን ታሪኬን በመፅሐፍ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ምኞት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚያሳካው እምነት አለኝ፤ ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር አመሠግናለሁ፡፡››

The post የማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ተከበረ * አላሙዲ 5 ሚሊዮን ብር ሸለሙት appeared first on Zehabesha Amharic.

የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሼህ መሃመድ አላሙዲ ከአርቲስት ማህደር አሰፋ ጋር ግንኙነት ጀምረዋል የሚለው ወሬ ሲወራ ከቆየ ሰንበትበት ብሏል:: በተለይም ማህደር ለትዳር ከምታስበው ጓደኛዋ ጋር ከተለያየች በኋላ ብዙ ጊዜ ከሼኩ ጋር ታይታለች:: በትናንትናው ዕለት ደግሞ ይህን የሁለቱ ግንኙነት በአደባባይ ታይቷል:: የአርቲስት ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመን ሲዘከር አላሙዲና ማህደር በሕዝብ ፊት ወጥተው እየተቃቀፉ ሲደንሱ ታይተዋል:: ይህም ፎቶ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል – በጨለማ ውስጥ የተነሳ በመሆኑ ለፎቶው ጥራት ይቅርታ::
alamudi

alamudi

alamudi and mahder

alamudi and mahder asefa

 

 
Mahder asefa

The post የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ጎሳዬ ቀለሙን ምን ነካው ?

$
0
0

jacki gossee
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
እዚህ ሀገር ድንገት ተነስተው አየር ምድሩን ሁሉ መሙላት የሚፈልጉ አሉ ። ቢችሉ እሰየው ። ግን ክፋቱ ደግሞ ሀገሪቱ ለዚህ አትመችም ። በወጡበትየሚጨብጡ የሚረግጡትን አጥተው በወጡበት ፍጥነት ሲወርዱ አይተናል ። ድምፃዊ ጎሳዬ ቀለሙም ከእነዚህ አንዱ እንዳይሆን እሰጋለሁ ። በግሌ እንደነ አብርሀም አፈወርቂ ፣ ሄለን መለስ ፣ የማነ ባሪያ ለመሳሰሉት የኤርትራ ድምፃውያን (ለድምፃቸው) ያለኝ አክብሮትና ፍቅር ከኤርትራውያኑ የሚያንስ አይመስለኝም ። እዚህ ሀገር ያሉ የኛ ድምፃውያን የኤርትራውያኑን ተወዳጅ ስራዎች አምጥተው ሲጫወቱባቸው ( እነሱ ዘፈንን ነው የሚሉት) በእጅጉ እበሽቃለሁ ። የአብርሀም አፈወርቂን ዘፈኖች ከነጎሳዬ ጥቃት ለመከላከል ኤርትራዊ መሆን ወይም ቋንቋውን ማወቅ ግዴታ አይደለም ።ጎሳዬም የአብርሀም አፈወርቂን ” መለይ” የተባለ ዘፈን (የፍቃድ ነገር መቸም አይነሳም) ወስዶ መዝፈኑ ሳያንስ ያለፍቃድ የዘፈነውን ዘፈን ይዞ ” የሌባ አይነ ደረቅ ” እንዲሉ “አስመራ ሄዶ በመዝፈን የመጀመሪያው” ለመሆን መመኘቱ ዘ ይገርም ነው ። ወዳጆቹ ካላችሁ አብርሀምን የበላ የኤርትራ ባህር ዳርቻ አሸዋ ውጦ እንዳያስቀረው ብትመክሩት ይበጀዋል ። ለነገሩ እዚያ የሚያደርሰውም አይኖርም ። ልጁ ግን ምን ነካው ?

The post ጎሳዬ ቀለሙን ምን ነካው ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የጆሲ ኢን ዘሓውስ ምክር ለጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) – Video

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

ጃኪ ጎሲ ከለቀቃቸው በጣት የሚቆጠሩ ዘፈኖች ውስጥ በጣት የሚቆጠሩትን ከሌሎች ዘፋኞች ካለፈቃድ ወይም ደግሞ አትውሰድ እየተባለ በጉልበት ወስዶ በመስራት ስሙ ይጠራል:: የተሾመ አሰግድ “የኔ አካል”, የኤርትራዊው ፍጹም ዮሐንስ ‘ፊያሜታ’ (ከዩቲዩብ እስከመታገድ ደርሶ ነበር)… እንዲሁም አሁን የአብርሃም አፈወርቂ ‘መለይ’ ዘፈኖች ክርክር አስነስተውበታል:: በርግጥ ጃኪ ምርጥ ድምጽ እና ስታይል ያለው ዘፋኝ ሆኖ ሳለ በሰው ዘፈኖች ላይ ሙጥጥ ማለቱን ብዙዎች እየወደዱለት አይደለም:: እያስተቸውም ይገኛል:: ለዚህም ነው ጃኪ መልካም የሆነ አማካሪ ቢኖረው ከነዚህ ትችቶች ሊያመልጥ ይችላል የሚባለው:: ቀጣዩ ቭዲዮ ጆሲ በአንድ ወቅት ከተሾመ አሰግድ ወስዶ በሠራው ሥራ ክርክር ውስጥ በገባበት ወቅት የመከረው ምክር ነው:: ጃኪ ያን ምክር በፊያሜታ እና በመለይ ላይ ባይተገብረውም አሁን ግን ከዚህ የበለጠ መካሪ የሚያስፈልገው ግዜ ላይ ይገኛል:: ያድምጡና የ እርስዎን አስተያየት ያስቀምጡ::


Jackey and Jossey

The post የጆሲ ኢን ዘሓውስ ምክር ለጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) – Video appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ –ኮርኩማ አፍሪካ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ አፍሮ አዲሱን ነጠላ ዜማ ለሕዝብ ለቀቀ:: ቴዲ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሐሙስ ጁላይ 2 ያለው ሲሆን አዲሱ ነጠላ ዜማው ከወዲሁ የሶሻል ሚዲያውን አጥለቅልቆታል::

በስጋት ቀፎን ተይዞ እስራት
አዋቂው ሸሽቶ ረሃብ ነግሶ ርዛት
በምድሯ ሊቆይ ማንስ ይደፍራል
ታንኳ ላይ ወጥቶ ወንዝ ይሻገራል
አለቀ ሰዋ ባህር ገብቶ ሄዶ(4×)
………

ውሃ ቢገባ በአፍሪካ መርከብ
አቤት ቢል ተጓዥ ሃሳብ ለማቅረብ
ይሰምጣል እንጂ ከባህር አብሮ
ቀዛፊው ላሳብ አይሰጥም ቶሎ
……….

ዮንጂ ከረ
ቤቴ ኖረ
ወጥቶ ቀረ
ግዶ ግዶ
ወይ ግዶ ወይ ግዶ
………..

ኮርኩማ ኮርኩማ ወንዝ አሻገረችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የንን የሰው ጫካ
ኮርኩማ አፍሪካ
ባዶ አደረገችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የሚለውን አዲሱን የቴዲ ነጠላ ዜማ ዘ-ሐበሻ እነሆ ትላለች::

teddy afro

The post ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ – ኮርኩማ አፍሪካ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለመሆኑ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ማን ነዉ? የሕይወት ታሪኮቹና የፍቅር ሕይወቱ ምን ይመስል ይሆን?

$
0
0


ለመሆኑ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ማን ነዉ? የሕይወት ታሪኮቹና የፍቅር ሕይወቱ ምን ይመስል ይሆን?
ለመሆኑ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ማን ነዉ? የሕይወት ታሪኮቹና የፍቅር ሕይወቱ ምን ይመስል ይሆን?
Zehabesha.com


በሕወሓት $5 ሺህ ዶላር የተደለለው ድምፃዊ ደረጀ ደገፋው በዲሲ ከፍተኛ መገለል እየደረሰበት ነው

$
0
0

Dereje Degefaw
ቢሆነኝ ከዋሽንግተን ዲሲ

የሕወሓት መንግስት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ላይ አንጃ በመፍጠር በስርዓቱ ደጋፊ በሼህ መሀመድ አላሙዲ ሌላ ፌዴሬሽን አቋቁመው በኢትዮጵያውያን ቦይኮት መደረጋቸው ይታወሳል:: ከአንድ ዓመት በፊት የወያኔ መንግስት በሚኒሶታ ባዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ትናንት ሃገር ወዳድ በመምሰል ስለታማኝ በየነ ጀግንነት እያወደሰ ሲዘፍን የነበረው ድምፃዊ ደረጀ ደገፋው ከአላሙዲ የተከፈለው 5 ሺህ ዶላር በልጦበት ሃገር ወዳዱን ኢትዮጵያዊያን ክዶ ተገኝቶ ነበር::

ይህ ድምፃዊ ለገንዘብ ራሱን በማስገዛቱ እጅጉን በ”መጸጸቱ” በዲሲ ባሉ ራድዮኖችና ዲሲን መሠረት ባደረጉ ሚድያዎች እንዳይዘገብበት አርቲስት ታማኝ በየነ እና አበበ በለው እግር ስር መውደቁ ይነገራል:: በወቅቱ የደረጀ ደገፋው ለገንዘብ ሲል ለወያኔ ፌስቲቫል ማድመቂያ መሆኑን እነዚሁ ሚድያዎች ዝም ብለውለት አለፉ:: ሆኖም ግን ሕዝቡ ዝም አላለም:: ይበላበት የነበረበት ሬስቶራንትና የሚውልበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለገንዘብ ሲል ለወያኔ ራሱን የሸጠ እያሉ ማግለል ጀመሩ::

ድምፃዊው ቀጥሎም የአምናው ሳያንስ ዘንድሮም ሕወሓት በአላሙዲ ስፖንሰርነት ዴንቨር ላይ ባደረገውና ቦይኮት በተደረገው ኳስ ጨዋታ ላይ ዘፍኖ ተመልሷል:: ትናንት እነ አቦነሽ አድነውን ቦይኮት አስደርገው ሬስቶራንቷን እንድትዘጋ ያደርጉ የዲሲ ራድዮ ጣቢያዎችና አክቲቭስቶች ደረጀ ደገፋውን ዝም ቢሉትም ሕዝቡ ግን ድምፃዊውን ከማግለል አልተመለሰም:: በዲሲ ብዙ ጊዜ ከሚዝናናበት ካፌ ከሕዝቡ በሚደስበት ተቃውሞ ለመቅረት ተገዷል:: በአሁኑ ወቅት ይህ ድምጻዊ ራሱን ከኢትዮጵያውያን እየደበቀ ለታማኝ ዘፍኖ ያገኘውን ክብር በሕወሓት $5 ሺህ ዶላር ሸጦታል::

ማሳሰቢያ በተለይ ለዲሲ ራድዮኖችና አክቲቭስቶች:- ከወያኔ ጋር ያበረውን ድምፃዊም ሆነ አርቲስት ቦይኮት ማድረጋችሁን እኮራበታለሁ:: ሆኖም ግን ከአንድ አካባቢ ነው የመጣነው በሚል ከወያኔ ጋር ያበረውን አርቲስትም ዝም አትበሉት:: ዘር ቆጠራ ውስጥ ከገባችሁ እናንተም ከወያኔ አትሻሉም::

የሰው መጽሐፍ ታሪክን በፊልም ካለፈቃድ ወስዶ ሰርቷል በሚል በ10 ሚሊዮን ብር የተከሰሰው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለሐምሌ 23 ተቀጠረ

$
0
0

maxresdefault
በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ “ሦሥት መዓዘን” ፊልም እና በደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ “ፍቅር ሲበቀል” የተሠኘ ረጅም ልብወለድ መፅሐፍ መካከል የነበረው የ10 ሚሊዮን ብር የፍትሐብሔር ክስ ክርክር ለፍርድ ማስፈፀሚያ የሚሆን ብር ማስያዣ ማቅረብ ይችላል የሚል ሀሣብ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ባቀረበው ተቃውሞ መሠረት ከጥቅምት 22/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ሰኔ 24/2007 ዓ.ም የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ ምድብ በዋለው ችሎት የደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ ጠበቃ አቶ አንዱዓለም በእውቀቱ እና የአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ጠበቃ አቶ ኤልያስ ተ/መድህን ያቀረቡትን አቤቱታ ዳኛው ግራ ቀኙን ካዩ በኋላ ብይን የሠጡ ሲሆን አርቲስት ቴዎድሮስ ለሐምሌ 23/2007 ዓ.ም ለተከሰበት ክስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ዉሳኔ ሲሰጡ ከዚህም ጋር አያይዘውም የመፅሀፉን አንድ ኮፒ አብረዉ ሠጥተዋል፡፡

ከሳሽ ደራሲ አትንኩት አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለእይታ ያበቃው “ሦስት ማዕዘን” የተሰኘ ፊልም ታሪክ በ2000 ዓ.ም ካሳተሙት “ፍቅር ሲበቀል” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሃፍ የተወሰደ ነው የሚል አቤቱታ ማሰማታቸውን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም::

አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ –መልካም አመት በዓል (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል)

$
0
0

መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:-

መልካም አመት በዓል – አብዱ ኪያር

ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን
ቤት ለሌሉት ለራቁት በአካል
በያሉበት መልካም አመት በዓል

አንቺ የኢትዮጵያ እናት ይለፍልሽ
ከአመት እስከ አመት ይሙላ ጓዳሽ
አንተ የኢትዮጵያ አባት እሺ ይበልህ
ከሰው እንዳታይ እንዳይጎድልህ

ጀግናዋ እህቴ የናቷ ልጅ
ከብረሽ ቆይልን ውለጅ ክበጅ
ወንድሜ አንበሳው ያባቱ ልጅ
ክፉ አያሳይህ ደጋጉን እንጂ

ከአገር ርቀው ለተሰደዱት
በህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉት
በህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉት
ያድርግላቸው እንደሚመኙት

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ካለም ሚለየን ከማንም ዜጋ
የሚያሳምመን ልክ እንደ አለንጋ
ልብ ውስጥ ታትሞ የማይዘነጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካ
እኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካ
ኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

የወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ
ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙ
የቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ
አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ
የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ABDU_KIAR

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቴዲ አፍሮ ምክንያት 200 ሺህ ዶላር ከሰረ * ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር

$
0
0

· ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር

(ክንፉ አሰፋ፣ ፍራንክፈርት) ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል።
teddy afro
አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው።

አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል። የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት ነበር።

ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በመቃወም ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤትዋ ዘሪሁን ተሾመ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 33ኛ ዓመት በዓል ላይ እነዚህ ድምጻውያን አልተገኙም። ድምጻውያኑ በበዓሉ ያልተገኙበት ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው የኮምፒውተር ሽብር ጥቃት- የቪዛ ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ ቢገለጽም፤ ቪዛ ቢያገኙ ኖሮ እንኳ በደህንነቶች አፈና ከሃገር ሊወጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነበር።

የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን አሸባሪ ተብሎ በነሚሚ ስብሃቱ መፈረጁን የህወህት መንግስት ተቀብሎ በውስጥ አጽድቆታል። ቴዲ አፍሮ ባለቤቱን ለማሳከም ወደ ኬንያ በመጓዝ ላይ እንዳለ በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው ተብሎ በነ ሚሚ ስብሃቱ በደረሰው ጥቆማ ነው አውሮፕላኑ እንዲመለስ የታዘዘው። በዚህ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በተሳፋሪው ላይም ከፍተኛ መጉላላት የደረሰ ሲሆን አየር መንገዱም ለከፋ ኪሳራ ተዳርጓል ሲሉ የአየር መንገዱ ምንጮች ተናግረዋል። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤት ጋር ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የህወሃት ደህንነት አባላት ይህንን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ደካሞች እንደሆኑ ምንጮቹ ተቁመዋል።

ከብዙ መጉላላት በኋላ ቴዲ አፍሮ ፓስፖርቱን አስመልሶ ወደ ጀርመን – ፍራንክፈርት የበረረ ሲሆን በቅዳሜ ምሽት የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቱን ያቀርባል። ከዚያም የጄኔቭ ስዊዘርላንድ ማዘጋጃ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ ልዩ ተጋባዥ በመሆን በመጭው ሳምንት ስራውን ለህዝብ በነጻ ያሳያል።

የቴዲ አፍሮ ባለቤት አለምሸት ሙጬ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ-ቨርጂንያ ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች።
ይህንን እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ወደፊት በስፋት እመለስበታለሁ።

ብዙአየሁ ደምሴ በፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያኑን ሲያዝናና አመሸ (Video)

$
0
0


የኢትዮ-አውሮፓ የ እግር ኳስ እና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮ በፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ስነስርዓት ተደርጓል:: በዚህ በዓል ላይ ከታዩት ደማቅ ፕሮግራሞች መካከል ደግሞ የድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ የሙዚቃ ኮንሰርት ነው:: ደማቅ ሆኖ ባለፈው በዚህ ኮንሰርት ላይ የነበረውን የብዙአየሁ እንቅስቃሴ ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ብዙአየሁ ደምሴ በፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያኑን ሲያዝናና አመሸ (Video)

የበእውቀቱ ስዩም አስቂኝ ጨዋታ (በድምጽ እያደመጡ ይሳቁ)

$
0
0

የበእውቀቱ ስዩም አስቂኝ ጨዋታ (በድምጽ እያደመጡ ይሳቁ)

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)

“ዘፈኑን እየተውኩ ወደ ዝማሬው ዓለም እየገባሁ ነው”–ድምፃዊት(ዘማሪት) ዘሪቱ ጌታሁን [ቃለ-ምልልስ]

$
0
0

ዘሪቱ ከበደ ዘፈን አቁማለች ወይንስ አላቆመችም የሚሉ አናጋጋሪ ጉዳዮች በርካታ ጊዜያት ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ከእርሷ አንደበት ይህ ነው የሚባል ቁርጥ ያለ ምላሽ ሳይሰጥበት በመቆየቱ በበርካቶች ዘንድ አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዘሪቱ በየወሩ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለገበያ በሚበቃው ሪቪል (REVEAL)መፅሄት ባደረገችው ቃለ ምልልስ ከዘፈኑ አለም በመውጣት መንፈሳዊ ጉዞ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡ መፅሄቱ ከቀረበላት ጥያቄዎች መካከል ዋና ዋናዎች አለፍ አለፍ ብይ በመቃኘት ላስነብባችሁ፡፡
zeritu
☞ሪቪል፡ ከመንፈሳዊነት ጋር ተያይዞ መዝፈን አቁመሻል?
☞ዘሪቱ፡ መንፈሳዊነት ሁለገብና የሁለንተናችን ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ከአለማዊነት ስንወጣ የማይነካ የህይወታችን ክፍል የለም፡፡ ሁሉም ነገር እኔ እንደምለውና ዓለም እንደምትሰብከው ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚለው የማድረግና የመሆን ሂደት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ታዲያ እንደ ሁሉ ነገሬ የጥበብ ስራየም ሳይፈተሸ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሙዚቃም ይሁን ፊልም፤ ብቻ ምንም ነገር ልስራ የማደርገው ነገር እግዚአብሄር የሚፈልገውን መለዕክት ያደርሳል ወይ? ሰዎችን ይጠቅማል ወይ? ደሞስ እንደሱ ፍቃድና ልክ ሰዎችን ያሳዝናል? ያስደስታል ወይ ብዪ በመጠየቅና ይልቁንም ከሱ ከራሱ መለዕክትን በመቀበል ወደ መስራት መንፈሳዊነት እያደኩ ነው፡፡ መዝፈን ይሁን መዘመር አላውቅም፡፡ የማውቀው እግዚአብሄር እንደሚከብርበት ነው፡፡

☞ሪቪል፡ ብዙዎች ግን “ዘሪቱ ወይ ትዘምር ወይ ትዝፈን መቁረጥ አቅጧት እየወላወለች ነው” ይላሉ፡፡ በእርግጥ እየወላወልሽ ነው?

☞ዘሪቱ፡ እየሱስ ክርስቶስን ተከትያለሁ ብዪ በማምንባቸው ዓመታት ውስጥ በአካሄዴ ሁሉ እግዚአብሄርን ደስ አሰኝቻለሁ ብዪ አላስብም፡፡ ምንአልባትም በአንዳንድ የህይወቶቼ ክፍሎች እግዚአብሄርን አይፈሩም ተብለው ከሚታሰቡት ሰዎች እንኳን ብሼ አውቃለሁ፡፡ እንደእግዚአብሄር ምህረትና እንደ አባትነቱ ፍቅር ባይሆን ኖር ዛሬ ያለሁበት ቦታ አልገኝም ነበር፡፡ሰ አድርጌ የማላውቅ ግን መወላወል ነው፡፡ ፈርቼ አውቃለሁ፤ ግራ ገብቶኝም ያውቃል፤ ፈርሶ ሲሰራ እንደሰነበተ ሰው ደግሞ በሁሉም ነገር እርግጠኛ ሆኜ ሀሳቤን ሳለውጥ መጥቻለሁም ብዪ ለመናገርም አልደፍርም፡፡ ወላውዪ ግን አላውቅም፡፡

ዘሪቱ ሙዚቃ አቁማለች ብሎ ሚዲያ ጭምር ሲዘግብ ፤ እኔን ጠይቆና አነጋገግሮ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ከሆነች መቆሟ አይቀርም ብለው በራሳቸው በመደምደም ነው፡፡ እኔ ህይወቴን ስቀጥልና ከተነገሩት ዜናዎች በተቃራኒ የሙዚቃስራዎች ወደ አድማጭ ሲደርሱ የወላወልኩ የሚያስመስል መልክ ሊያሰጠኝ ችሏል፡፡
☞ሪቪል፡ ግን ዝናና ገንዘብን መስዋትነት ማድረግ የሚከብድ አይደለም?

☞ዘሪቱ፡ እኔ ለመተው የሚከብድ የገንዘብ ክምችት የለኝም፡፡ዝናንም በተመለከተ ዘማሪዎች ከዘፋኞች ባልተናነሰ ዝነኞች የሆኑበት ዘመን እንደሆነ ነው የማስበው፡፡ ከዝና ወደ ዝና ብሸጋገር አሁን ከምከፍለው ዋጋ የበለጠ እንደምከፍል አውቃለሁ፡፡

☞ሪቪል፡ ቤት መኪናና ሌሎች አያስፈልጉም ብለሽ ነው የምታምኚው?
☞ዘሪቱ፤ እኔ የማምነው ከሆነ ቦታ ተነስተህ የሆነ ቦታ ለመድረስ ትራንሰፖርት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ መኪናው ያንተ ከሆ ጥሩ፤ ካልሆነም መኖርህን ለማታውቅበት ለዛሬ ባለቤትነትህ ያለው ፋይዳ ውስን ነው፡፡ የቤትም አስፈላጊነት መጠለያነቱ፤ትርጉሙም አብረውህ በሚኖሩት ሰዎች እንጂ በባለቤተረነት ካርታው አይደለም፡፡ የባለቤተረነት ዋስትና ለእኔ ትርጉም የለሽ ነው፡፡እግዚአብሄር ወዶ ለሚጨምርልኝ ለእያንዳንዱ ቀን የሚያስፈልገኝን ሁሉ እንደሚያዘጋጅልኝ አምናለሁ፡፡
☞ሪቪል፤ እንደዚህ ያለ ህወት ግን ላገባችና በተለይም ልጆች እናት ለሆነች ሴት አይከብድም?

☞ዘሪቱ፤ እንደዚህ ያለ ህይወት ለማንም ቀላል አይደለም፡፡ በተለይም እንዳልከው፤ቤተሰብ ላለን ሰዎች ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በስጋዊ አቅማችን ስንሞክረው ነው፡፡ ሰው የመሆንን ትርጉም ለመረዳት በፈቀድን መጠን ግን ራሱ እግዚአብሄር በእና ውስጥ ይችለዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ማለት፤ ሰው በሀጢያት ከመውደቁ በፊት ወደ ነበረው ማንነት የመመለስ ጉዞ ማለት ነው፡፡ ያ ማንነት ደግሞ ከእግዚአብሄር የመሆንና ማንነቱን የማንፀባረቅ ህይወት ነው፡፡ በመሬታዊ ገደብ እሱን ማንፀባረቅ አይቻልም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አሰልጣኝነት ከመሬታዊ ገደብ ወደ እሱ ማንነት የሚያሻግረን መመሪያ ሁሉ ደሞ በቅዱስ ቃሉ ወስጥ አለ፡፡ ኢየሱስ ለምን አይነት ክብር እንደጠራን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከንግዳችን፣ ከቤተሰባችንና ከራሳችን ጭምር በላይ እሱን እንድናስቀድም ነው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ደቀመዛሙርቶቹ ልንሆን እንምንችል በግልፅ አስቀምጦልናል፡፡ ስለዚህ እሱን በመከተል ውስጥ ምንም አይነት አቋራጭ አልፈልግም፡፡
☞ሪቪል፤ ባለቤትሽ በዚህ ደስተኛ ነው?

☞ዘሪቱ፤ በጣም ደስተኛ ነው እንጂ፡፡ የምተገዛ ሚስት አድረጎለታል፡፡ ከዚህ ህይወት ጋር በተዋወኩባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በእኔ ላይ ባስከተለው የማንነት መናጋት ተከትለው በመጡ ጥፋቶች ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ሚስትህ ፈርሳ እስክተሰራ መታገስ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ከመጀመሪያዋ የተሻለች ሚስት እንዳለችው እሱ ምስክር ነው፡፡
ጌታ ይባርክሽ ዘሪቱ!!
@የእውነት ቃል


አርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት አዲሱን “መማር”ነጠላ ዜማ አቀነቀነ (ቭዲዮን ይመልከቱት)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኮምፒውተር ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ባችለሩን የተቀበለው አርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት በርከት ያሉ ተመራቂዎች በተገኙበት አዲሱን መማር የተሰኝውን ነጠላ ዜማ አቀንቅኗል:: ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እንኳን ደስ ያለህ እያልን ይህን ታሪካዊ ቭዲዮ ጋብዘናችኋል::

መንግስት በሕዝብ የተመረጠው ቴዲ አፍሮን በስነጥበብ ዘርፍ ለመሸለም ፍላጎት እንደሌለው በይፋ አሳየ

$
0
0

teddy afro
(ዘ-ሐበሻ) በየዓመቱ የሚካሄደና ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚከናወነው ‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት› በየዘርፉ የተመረጡ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎችን መንግስት ልክ እንደምርጫው አጭበርብሮ ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች አስቀመጠ:: ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ የዓመቱ በጎ ሰው በሚል በስነጥበብ ዘርፍ ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ምርጫን ቢያገኝም መንግስት በምርጫው እንደማጭበርበር እንደለመደው በፖለቲካዊ ውሳኔ ከ እጩዎች ዘንድ እንዳይካተት መደረጉ ተጋልጧል:: ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ መሠረት ታሪካቸውና ሥራቸው ተሰብስቦ፣ በበጎ ሰው ሽልማት የምርጫ ሂደት ኮሚቴ የተመረጡት 45 ዕጩዎች ናቸው ብሎ መንግስት ካስቀመጣቸው ሰዎች መካከል ሁሉም መንግስት ራሱ እንዲሸለሙልኝ እፈልጋለሁ ያላቸውን እንዳጨ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: ቴዲ አፍሮ በስነጥበብ የዓመቱ በጎ ሰው ዘርፍ የበርካታ ሕዝብ ድምጽን ቢያገኝም ከ እጩዎች ዝርዝር እንዲወጣ ተደርጓል::

ዘንድሮ መንግስት 9 ሰዎችን በሕዝብ ምርጫ እሸልማለሁ ቢልም ቅሉ ምርጫው ለመንግስት ፖለቲካ ቅርበት ያላቸው ሰዎችን የሚያካትት እንጂ ትክከለኛው የሕዝብ ጥቆማ እንዳልሆነ ታማኝ ምንጮች ይናጋራሉ::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሕዝብ የተጠቆሙ ሰዎችን ትቶ በራሱ መንገድ ሕዝብ መረጣቸው ብሎ ያስቀመጣቸው ሰዎች ዝርዝራቸው የሚከተለው ነው፡፡

በ2007ዓም በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕጩ የሆኑ በጎ ሰዎች

በሳይንስ ምርምር ዘርፍ ዕጩዎች
1. ፕ/ር ኢ/ር አበበ ድንቁ (አአዩ)
2. ኬሚካል መሐንዲስ ጌታሁን ሄራሞ
3. ዶክተር አበበ በጅጋ
4. ፕሮፌሰር አሥራት ኃይሉ
5. ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)

በሥነ ጥበብ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ አለ ፈለገ ሰላም
2. እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ
3. አቶ ተስፋየ አበበ(የክብር ዶክተር)
4. ሰዓሊ ታደሰ መስፍን
5. አባተ መኩሪያ
በበጎ አድራጎት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ወ/ሮ አበበች ጎበና
2. አቶ አስመሮም ተፈራ /ሲኒማ ራስ አካባቢ የተቸገሩትን የሚረዳ/
3. ስንታየሁ አበጀ (የወደቁትን አንሱ) እንጦጦ ማርያም አካባቢ)
4. አቶ አስፋው የምሩ /የአሠረ ሐዋርያት ት/ቤት መሥራች/ ዊንጌት አካባቢ
5. ትርሐስ መዝገበ

በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አባ ሐዊ /አቶ ገብረ ሚካኤል (በትግራይ ክልል ለአብርሃ ወአጽብሐ አካባቢ ገበሬዎች ሥራ የፈጠሩ ገበሬ)
2. ሰላም ባልትና
3. አዋሽ ባንክ
4. ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው
5. ካልዲስ ቡና
በቅርስና ባሕል ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ ዓለማየሁ ፋንታ
2. አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ
3. አቶ ዓለሙ አጋ
4. EMML /HMML(የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ማይክሮ ፊልም ድርጅት)
5. ማኅበረ ቅዱሳን

በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት
2. ደሳለኝ ራሕመቶ
3. ዶክተር ፈቃደ አዘዘ
4. ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ
5. ፕሮፌሰር በላይ ካሣ

በጋዜጠኛነት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ መዓርጉ በዛብህ
2. አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም
3. አቶ ነጋሽ ገብረ ማርያም
4. ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ(ፎርቹን ጋዜጣ)
5. ቴዎድሮስ ጸጋየ

በስፖርት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው
2. መምህር ስንታየሁ እሸቱ (ከበቆጅ ብዙ አትሌቶች እንዲወጡ ያደረገ መምህር)
3. መሠረት ደፋር
4. ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ
5. ዶክተር ወ/መስቀል ኮስትሬ

መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ ግርማ ዋቄ(የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ)
2. አቶ መኮንን ማን ያዘዋል
3. አቶ ሽመልስ አዱኛ
4. ዐማኑኤል የአእምሮ ሕክምና ሆስፒታል
5. ኢንጅነር ስመኘው በቀለ

ቃልኪዳን አለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን “እውነት ማለት”ግጥም እንዲህ ያነበዋል (Video)

$
0
0

የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተማሪ የሆነው ወጣት ቃልኪዳን ዓለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን ተወዳጅ ግጥም እንደሚከተለው አንብቦታል:: ይመልከቱት::


ቃልኪዳን አለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን “እውነት ማለት” ግጥም እንዲህ ያነበዋል (Video)

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

$
0
0

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

“ቴዲ አፍሮ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል”– (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

$
0
0

የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ስጋቱን በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ነበር የገለጸው:: ተካፈሉት::

ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው::
teddy afro
ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ::
ቴዲ ከእናቱ ቤት መሀል አዲስ አበባ እሱ ወደ ሚኖርበት ሲ ኤም ሲ በየጊዜው ሲመላለስ በደህንነቶች ታጅቦ: በመንገድ ላይ እያስቆሙ መከራውን አሳይተው በሚፈትሹት የህወሀት ሰዎች ተንገላቶ መሆኑ አስገራሚ ነው:: ቤቱ በደህንነቶች እጅ ላይ ወድቋል:: ዙሪያውን ይቆጣጠሩታል:: እንዳሻቸው እየጠሩ ያስፈራሩታል:: ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ክብረ ነክ ምርመራ ያደርጉበታል:: በቅርቡ ባለቤቱ ታማ ወደ ኬኒያ ይዟት ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ የጀመረን አውሮፕላን እንዲመለስ አድርገው እንደ ወንጀለኛ በተሳፋሪ ፊት እየገፈተሩ ወስደውታል:: በተደጋጋሚ የውጭ ጉዞዎቹ እንዲሰረዙ አድርገዋል:: በርካታ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽመውበታል:: ለፊታችን አዲስ ዓመት በላፍቶ ያዘጋጀው ኮንሰርትም ሊሰረዝ እንደሆነ ከውስጥ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአዲስ አበባ ለህወሀት የሚጮሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የላፍቶው ኮንሰርት የሚሰረዘው በስፖንሰር እጦት ነው በሚል ቢያራግቡም እውነታው ግን የምንመርጥልህን እንጂ የመረጥካቸውን ዘፈኖች አታቀርብም ብለው ጣልቃ በገቡ የደህንነት ሰዎች ግፊት ነው::

ቴዲን ህወሀት ከሀገር ገፍትሮ ሊያስወጣው እየሞከረ ነው:: መንፈሰ ጠንካራ የሆነው ቴዲ እስከአሁን በትዕግስት እየመከተ ነው:: ሰው ነውና መንግስትን የሚያክል ሃይል ተነስቶበት ብቻውን ይመክታል ማለት አይቻልም:: ከጎኑ መቆም ግድ ይላል:: ህወሀት ቴዲ ላይ አይደለም ሰይፍ የመዘዘው:: ትውልዱ ላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው::

Viewing all 261 articles
Browse latest View live