Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic Âť Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live
↧

“በጣም ደህና ነኝ…ምንም አልሆንኩም”–ወንድም ጥበቡ ወርቅዬ (Video)

↧

ሜሮን ጌትነት በሚኒሶታ የልጅ እናት ሆነች

$
0
0

Meron Getenet
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂዋ አርቲስት ሜሮን ጌትነት በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ የልጅ እናት ለመሆን መብቃቷን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመከተ::

ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ላይ የተቀየረች መሆኑን እና ኑሮዋም አሜሪካ እንደሆነ ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ ጽፋ የነበረ መሆኑ ይታወቃል::

ሜሮን ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ 2 ጊዜ የልጅ እናት ትሆናለች በሚል ሆስፒታል ስትመላለስ መቆየቷን የጠቆሙት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ትናንት ማምሻውን ወደ ኢመርጀንሲ ክፍል ተወስዳ የሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች::

ዘ-ሐበሻ ሜሮንን እንኳን ደስ ያለሽ ትላለች::

The post ሜሮን ጌትነት በሚኒሶታ የልጅ እናት ሆነች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

እኛው ነን!! “ –በጌትነት እንየው

$
0
0

እኛ ነን እኛው ነን እኛ የዛሬዎች…
በአጭር የተቀጩ ሩቅ መንገደኞች
ሰላሳ ህልመኞች፣ ሰላሳ ተስፈኞች፣ ሰላሳ ወጣቶች
ሀገር እንደሌለው በሰው ሀገር ምድር ሲቀላ አንገታቸው
ወገን እንደ ሌለው ከሰው ሀገር ባህር ሲቀየጥ ደማቸው
በአገር ቁጭ ብለን ከአለም ጋራ እያየን
ከሬት የመረረ ከቋጥኝ የሚከብድ
ከቶን የሚያቃጥል ከብራቅ የሚያርድ
ሀገር ያህል መርዶ በሰንበት አመሻሽ በአገር የተሸከምን
በገዛ ሞታችን እዝን የተቀመጥን፡፡
ካሳለፍነው ህይወት ካለፈው መከራ
መማር የተሳነን ደመና ወራሾች፣
የሞትነውም እኛ ያለነውም እኛ
ከፋይም ተቀባይ እኛው ነን ባለእዶች፡፡
እኛው ነን….

ከቅጣትም ቅጣት ከመርገምትም መርገት፣
የገዛ አንገታችን በስለት ሲቀላ
የገዛ ደማችን ባህሩን ሲያቀላ
የራሳችንን ሞት ቆሞ መመልከቱ፣
ምን ያህል ነው ፍሙ ምን ያህል ይጠብሳል ሰቆቃው እሳቱ?
ምን ያህል ነው ሸክሙ? ምን ያህል ይደፍቃል? መከራው ክብደቱ
ምን ያህል ይጠልቃል? ምን ያህል ይሰማል? መጠቃት ስለቱ
ሀዘን ነው? ቁጣ ነው? ቁጭት ነው? ጸጸት ነው? ምንድነው መጠሪያው? ምንድነው ስሜቱ?
እውን ይህን መአት ይኼን የእኛን መቅሰፍት
ቋንቋዎች በቃላት ችለው ይገልጹታል?
እውን ይህ ስቃይ፣ ይህንን ሰቆቃ፣ እናትና ሀገር ሸክሙን ይችሉታል?
እኛው ነን እኛው ነን…
ለዚህ ክፉ እጣችን ለዚህ መርገምታችን
ለአለም ለፈጣሪ አልፈታ ላለው እንቆቅልሻችን
መነሻም መድረሻም ጥያቄዎች እኛ መልሶችም እኛው ነን፡፡
እኛው ነን የገፋን፣ እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን ፣እኛው ነን ያጠፋን፡፡
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ አገር ይዘን በሀሳብ እየጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመዱ አቀበት የሆነን
ቂም እየቆነጠርን፣ ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትናንቱን ድርቆሽ የምናመነዥግ
በዛሬ ምድጃ የትናንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
ባንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ ምንደፍቅ
እኛው ነን እኛው ነን….
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን፡፡
እኛው ተጋፊዎች፣ እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች፣ እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካለፍነው መከራ
መማር የተሳነን ደመና ወራሾች
እኛው ነን እኛው ነን እኛ የዛሬዎች
የነገ፣ የታሪክ ያገር ባለእዳዎች፡፡
እኛው ነን….
በንፍገት በስስት በስግብግብ መዳፍ
ከድሆች ጉሮሮ ካፋቸው መንጭቀን
ሌሎችን ረግጠን ሌሎችን ጨፍልቀን
በሌሎች ጀርባ በሌሎች ጫንቃ ላይ ወደ ላይ መሳቡ ቅንጣት የማይጨንቀን
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ የሰለጠን
ከብዙዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ላንድ ለራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንጻ ላይ ህንጻ
ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን፣
የመንፈስ ድውዮች የንዋይ ምርከኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመን የስጋ ብኩኖች
የራሳችን ሀጢያት የራሳችን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች
እኛው ነን!
በዚህ ሁሉ ግና …..
መቼም ቢሆን መቼ ሰው ይሞታል እንጂ ተስፋ አይሞትምና
በመንገድ የቀሩት ወጣቶቻችን
በአጭር የተቀጨው ሀሳብ ምኞታቸው
ተስፋ አለን ተስፋቸው፡፡
በአገራቸው አፈር በታናሾቻቸው
ነገ ውብ ይሆናል ለምልሞ ይጸድቃል በዛሬው ደማቸው
ዛሬ የመከነው ውጥን ርዕያቸው
በጊዜና በአገር ነገ እውን ይሆናል ይፈታል ህልማቸው
ይህ ነው መጽናኛችን ይህ ነው መዕናኛቸው፡፡

ethiopia

The post እኛው ነን!! “ – በጌትነት እንየው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ኣባ ይፍቱኝ(በዉቀቱ ስዩም)

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)
ኣባ ይፍቱኝ !
ሲኦል ኣለ ሲሉኝ፤ የለም ብየ ክጀ
የባልቴት ተረት ነው፤ በማለት ቀልጀ
ኣውቄ በድፍረት፤ በድያለሁና
ያንጹኝ በንስሃ፤ ያንሱኝ በቀኖና
ሲኦል ከነጭፍራው፤ በጉም ተሸፍኖ
እንዴት ሳላየው ኖርኩ፤ ካጠገቤ ሆኖ?
ኣባ ይፍቱኝ
ሰይጣን ብሎ ነገር፤ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው፤ ብየ ኣስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፤ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያብሎስን ኣየሁት፤ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ፤ ቸብቸቦ ጨብጦ፡፡
ኣባ
ልክ እንደ ብርሌ ፤ኣጥንት ሲከሰከስ
ኣባይን ኣዋሽን፤ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
ለምለም ፍጥረት ሁላ፤ ወደ ኣመድ ሲመለስ
ልክ እንደ ጧፍ ሃውልት፤ ምስኪኖች ሲጋዩ
ምድጃው ዳር ሆነው፤ ይሄንን እያዩ
ገሃነም ከላይ ነው፤ ብለው መሳትዎ
እስዎ እንደፈቱኝ ፤ እግዚሃር ይፍታዎ

The post ኣባ ይፍቱኝ(በዉቀቱ ስዩም) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አነጋጋሪው በጥላሁን ገሠሠ ዙርያ የወጣው መጽሐፍ –‹መፅሐፉ የተዛቡ የጥላሁን ገሠሠን ታሪኮች ያጠራል› –ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ

$
0
0

tilahun gesese

ቁም ነገር ቅጽ 13 ቁጥር 201 ሚያዝያ 2007

ዘከርያ መሐመድ ይባላል፡፡ ጋዜጠኛ ነው ለረጅም ዓመታት በጋዜጦችና በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ላይ ሰርቷል፡፡ በ1984 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቲያትር ጥበባት የተመረቀው ዘከርያ ቢላል መፅሔት፣ ህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት፣ ልዩ አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን በመሳሰሉ ተቋማት በጋዜጠኝነት እና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አገልግሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በግሉ የዶክመንተሪ ፊልሞችን በመስራትና በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ላይ በማማከር ተግባር ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
በጋዜጠኝነት ህይወት ውስጥ ረጅም ጊዜ ያሳለፈው ዘከርያ ከቀናት በፊት ጥላሁን ገሠሠ የህይወቱ ታሪክና ሚስጢር በሚለው ርዕስ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ መፅሐፉ በጥላሁን ገሠሠ ህይወት ዙሪያ እስከ ዛሬ የምናውቃቸውንና በመገናኛ ብዙሀን ሲነገሩ የነበሩትን ሀቆች የተዛቡ እንደነበሩ ያስረዳናል፡፡ ከአዳዲስ ሀቆች ጋር ያስተዋውቀናል፡፡ እነዚህን አዳዲስ ሀቆች ጥላሁን ገሠሠ በህይወት በነበረበት ወቅት ለአንዴም ቢሆን በይፋ ተንፍሷቸው አያውቅም፡፡
ጋዜጠኛው ዘከርያ እድለኛ በሚያስብለው ሁኔታ በጥላሁን አጎት በአቶ ፈይሳ ሀሰና ሐይሌ የተፃፈውን የቤተሰብ ማስታወሻ አግኝቷል፡፡ መፅሐፉ የያዛቸው ጥሬ ሀቆች ከዚህ ማስታወሻ ላይ የተቀዱ ናቸው፡፡ ‹‹በጥላሁን ገሠሠ ዙሪያ ለዓመታት ሲተላለፉ የነበሩ የተዛቡ እውነታዎች በማያዳግም ሁኔታ መልስ ያገኛሉ›› የሚለው ዘከርያ መሐመድ ከፍስሃ ጌትነት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ቁም ነገር፡- የጥላሁንን ታሪክ ለመጻፍ ምን አነሳሳህ?
ዘከርያ፡- በአጋጣሚ ነው ወደዚህ ስራ የገባሁት፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ አፍቃሪ ጥላሁንን እወደዋለሁ፤ በቤተሰባችን የእሱን ሙዚቃዎች እየሰማን ስላደግን ለጥላሁን ልዩ ስሜት አለኝ፡፡ ጥላሁን ህይወቱ ካለፈ ከሁለት ወር በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ሬዲዮ እየሠማን ነበር፡፡ ስለ ጥላሁን ይወራል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ያልዘፈነበት ርዕስ የለም እየተባለ ነው፡፡ ትክክል ነው በብዙ ርዕሶ ላይ ጥላሁን ዘፍኗል፡፡ ነገር ግን ስለጥላሁን ያ ብቻ ነው ወይ የሚወራው የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡ 68 ዓመት ረዥም እድሜ ነው፡፡ የጥላሁን ህይወት በብዙ ክስተቶች የተሞላን ነው፤ ጥላሁን ከህዝብ ጋር የኖረ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ጥላሁን በብዙ ጎን ሊዘገብ የሚገባው ሠው ነው፡፡ መባል የሚገባውን ያህል አልተባለም፡፡ ሊጻፍ የሚባውን ያህልም አልተጻፈለትም፡፡ በዚህ መነሻነት ከጓደኛዬ ሲሳይ ገብረጻድቅ ጋር አንድ ነገር ለመስራት ተነጋገርን፡፡ መጽሐፍ ልጽፍ፤ እሱ ደግሞ ዶክመንተሪ ፊልም ሊሠራ በዚያ ቀን ወሰንን፡፡ መሳይ ምትኩ የተባለ ሌላ ጓደኛችን ደግሞ ዌብሳይት አዘጋጃለሁ አለ፡፡ ከዚያ ይሄንን ካነሳን በኋላ 3 ቀን ቆይቶ አንድ ነገር ተከሠተ፡፡ አንድ ሠው ሲሳይ ጋ ደውሎ አባታቸው ስለጥላሁንና ስለቤተሰቡ የጻፈው ማስታወሻ እጁ ላይ እንዳለ ነገረው፡፡
ቁም ነገር፡- የአቶ ፈይሣ ልጅ ማለት ነው?
ዘከርያ፡- አዎ የአቶ ፈይሣ ልጅ ነው የደወለው፡፡ ሳምሶን ይባላል፡፡ አቶ ፈይሣ ሃይሉ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ ጥላሁን ከተወሰደበት ጊዜ አንስቶ የቤተሰቡን ታሪክ በማስታወሻቸው ጽፈው አስቀምጠው ነበር፡፡ ከሳምሶን ጋር ተገናኝተን ለመጀመርያ ጊዜ እነዚህን አስገራሚ የሆኑ የቤተሰብ ታሪክ የያዙ ማስታወሻዎች አየኋቸው፡፡ እነዚህን ማስታወሻዎችና ራሳቸው አቶ ፈይሣ ያነሷቸው ፎቶ ግራፎችን በእምነት ሰጠኝ፡፡ ማታውኑ ሳነበው አደርኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ወደኋላ ተመልሼ ማጥናት የጀመርኩት፡፡ የጥላሁን ታሪክ ላለፉት ዓመታት ተዛብቶ ሲቀርብ የነበረበትን ምክንያት ለመመርመር የተለያዩ ጽሑፎችን ተመለከትኩ፡፡ አቶ ፈይሣ በጻፉት የቤተሰቡ ማስታወሻና በመገናኛ ብዙሐን ሲነገረን የነበረው መረጃ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ የልዩነቱ ምንጭ ሌላ ሰው ሳይሆን ጥላሁን ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ጥላሁን የራሱን ታሪክ አዛብቶ ሲነግረን ነበር ማለትህ ነው?
ዘከርያ፡- ለምሳሌ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ያሳተመው መጽሐፍ ላይ የተጻፉ ታሪኮች ተመልከት፡፡ በቀጥታ ከሱ የተገኘውን ነገር ነው ያሰፈሩት፡፡ ስለ መጀመሪያ ሚስቱ ሲናገር ወ/ሮ አስራት እንደሆነች ይገልጻል፡፡ እውነታው ግን እሱ አይደለም፤ የመጀመሪያ ሚስቱ ወ/ሮ ፈለቀች እንደሆነች የሚያስሳየውን እውነት ታገኛለህ፡፡
ቁምነገር፡-ስለዚህ አሁን አንተ ያወጣከው ጥላሁን በሕይወት በነበረበት ዘመን የደበቀን ታሪኮች ናቸው ማለት ነው?
ዘከሪያ፡- ይህ መፅሐፍ የተፃፈው እንደነገርኩህ ነው፡፡ እንዲሁ ዝም ብለን ጥላሁን ቡቡ ነበር፣ ያለቅስ ነበር እያልን ማውራት ብቻ ልክ አይሆንም፤ ለምን ብለን መጠየቅ አለብን፤ የጀርባ ታሪኩን ማጥናት አለብን፡፡ ልንረዳው ይገባል፡፡ ያላወቅንለት ነገር ነበረ ማለት ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ያላወቅንለት ነው ወይስ የደበቀን?
ዘከሪያ፡- እኛም አላወቅንለትም፤ እሱም ልክ ነህ ደብቆናል፡፡ ሁለቱም ነው የሚባለው፤ እሱ ስለደበቀን ነው እኮ እኛም ያላወቅነው፡፡ ነገር ግን ስለደበቀንና ሌላ ታሪክ ስለነገረን ውሸታም ነው ልንለው አንችልም፡፡ በርግጥ ውሸት ነው፡፡ ግን ለህልውናው ሲል እራሱን ለማቆየት ሲል ስሜቱን ለማጠገግ ሲል በሰቀቀን ላለመሞት ሲል አንድ ሰው ይዋሻል፡፡ ይሄ የሁላችንም ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ እኮ የጥላሁንን ታሪክ ለመናገር የወጣም አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎችን ያክማል ብዬ አስባለሁ እኔ፡፡ ጥላሁን ያደረገውን ማድረግ ጉዳትም ጥቅምም ይኖረዋል፡፡ ወደኋላ ያሉ መጥፎ ትውስታዎችን እንሸሻቸዋለን፡፡ ማስታወስ አንፈልግም ስለዚህ ከዚያ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ማውራት ካለብን ከዚያ ሸሽተን ሌላ ታሪክ ጨምረንበት እንናገራለን፡፡ ጥላሁን ዝነኛ ባይሆን ኖሮ እኮ ሁሉም ሰላም ይሆን ነበር፡፡ ዝነኛ የሆነውም ያንን ታሪክ በመሸሹ ነው፡፡ ጥቅምም ጉዳትም ነበረው፡
፡ ጥላሁን ደስተኛ ሰው አልነበረም፤ ለራሱ ተርፎ አይደለም የኖረው፡ ፡ እነዚያ የሚጎዱት
ነገሮች ደግሞ በቀላሉ የሚታረቁት አይደሉም፡፡ እና ለምን ለህዝብ ያንን ታሪኩን አልተናገረም ልል አልችልም፡ ፡ ግን ስነልቦናውን ጎድቶታል፡፡ የተረጋጋ የትዳር ሕይወት እ ን ዳ ይ ኖ ረ ው አድርጎታል፡፡ የሆነ አቅሙን ነስቶታል፡ ፡ የሚፈጠሩ አደጋዎችን የመጋፈጥ አቅሙን ሸርሽሮታል፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተሰቡ ይፈርሳል፡፡ ምክንያት አለው ሰዎች እንዲረዱት እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ለምሳሌ ጥላሁን ብዙ ስለማግባቱ
አንስተው በመጥፎ ሁኔታ የሚተረጉሙት አሉ፡፡ ለምንድነው ብለው ግን አይጠይቁም፡፡ ዝም ብለው ‹አለሌነት › አድርገው ይወስዱታል፡፡ አይደለም / ላይሆን ይችላል፡፡ መጀመሪያ ለምንድ ነው ብለን ጠይቀን ትክክለኛውን ነገር መረዳት አለብን፡፡
ቁም ነገር፡- በመፅሐፍህ ውስጥ የልጅነት ሕይወቱ ለዚህ እንደዳረገው ነው የምትነግረን?
ዘከሪያ፡- አዎ ቤተሰባዊ ዳራው ነው ዋናው ምክንያቱ፤ በመፅሐፉ ውስጥ በደንብ ተቀምጧል፤ በሽሽት ውስጥ ስትኖር እውነተኛውን ነገር ስትሸሸው ጠንካራ ስብዕና ታጣለህ፡፡ ደካማ ኢጎ ይቆጣጠርሀል፡፡ እንደዚህ ስትሆን ደግሞ መደረግ ያለበትን ትተህ መደረግ የሌለበትን ታደርጋለህ፡ ፡ ችግሩ የሚከሰት መሆኑን እያወክ እንኳ የለም
ይቅርብኝ ብለህ ፊትህን አታዞርም ፡፡ ዝም ብለህ ትገባበታለህ፡፡ ስለጥላሁን ያናገርኳቸው አንድ ሦስት ሰዎች ‹‹ ጥላሁን የቦይ ውሃ ነው›› ብለውኛል ቃል በቃል፡፡ ካንተ ጋር ተቀጣጥሮ ሌላ ሰው መንገድ ላይ ካገኘው ከሱ ጋር ሊሄድ ይችላል፡፡ ጥላሁን ያንን አቅም ነው ያጣው፡፡ በዚህ ምክንያትና ሌሎች ከሱ ውጪ የሆኑ ተፅእኖዎች ተደምረው የኖረውን
አይነት ህይወት ውስጥ ከትተውታል፡፡ ይሄንን ልንረዳለት ይገባል፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ አንፃር የመፅሐፉ መፃፍ አላማ ምንድ ነው ማለት ነው?
ዘከርያ፡- የተዛቡ ታሪኮችን ማስተካከል፤ የተዛቡ እይታዎችንና ግንዛቤዎችን ማስተካከል፣
ሰውዬውን መረዳት ፣ ከሱ ህይወት መማር እንድንችል ነው፡፡ለኛም እኮ ይጠቅመናልየ የሱ
ህይወት ምን አይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደነበር እናያለን፡፡ ዝም ብሎ ከሆነ ታሪክ መሸሽ አያዋጣም፤ ምን አይነት ጥፋት እንደሰራ ላታውቅ ትችላለህ፡ ፡ ስነ አእምሮአዊ ጉዳይ ስለሆነ በምን መልኩ እየተጎዳህ እንደሆነ አታውቀውም ፡፡ ሌላኛው ነገር ግን እኔ ጥላሁን ገሰሰ ዝም ብሎ ተረት እንዲሆን አልፈልግም፡፡ ማንም የሚፈልግ አይመስለኝም፡ ፡ ጥላሁን የተለያየ ሰው በሚያነሳው ብጥስጣሽ አሉባልታ መካከል እንዲቆም አልፈልግም፡፡ ይሄ
ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተናጠል ስናውቀው ነው፡፡ ምን አይነት ስብዕና ነበረው፤ ከህዝቡ ጋር ምን አይነት መቀራረብ ነበረው፤ የልጅነት ህይወቱ ምንድነው የሚሉትን ነገሮች መለስ ብለን ብናውቅ እንማ ርበታለን፤ እንጠቀምበታለን፤ እሱንም ደግሞ ከተዛቡ ግንዛቤዎች እናጠራዋለን፡፡
ቁም ነገር፡- ስለጥላሁን ከወጡት የተዛቡ ታሪኮች ውስጥ በምሳሌነት ማንሳት የምንችላቸውን ንገረኝ?
ዘከሪያ፡- ለምሳሌ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ካ የ ኋ ቸ ው ፅሑፎች መካከል የጥላሁን ስም
ደንዳና አያና ጉደቱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሌላ ቦታ ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ የንጉሴ ልጅ
መሆኑን ይፅፋል፡ ፡ የአባቱ ስም ኩምሳ አንጋሱ ነው የሚልም አለ፡፡ እናቱ ድሀ
ነች የሚልም አ ን ብ ቤ ያ ለ ሁ ፤ ዝም ብሎ አ ፈ ታ ሪ ክ ይወራል፡፡ አቶ
ፈይሳ ሀሰን ሀይሌ የፃፉት የቤተሰብ ማስታወሻ ግን ይሄን ሁሉ ነገር ያጠራልናል፡፡
ቁም ነገር፡- በጥላሁን ገሠሠ ታሪክ ውስጥ ስንሰማቸው ከነበሩት እውነታዎች መካከል አሁን ባንተ መፅሐፍ ውስጥ ፍፁም ተቃራኒ ሆነው የመጡ አሉ፤ የውልደት ቦታው፣ የመጀመሪያው የትዳር ህይወቱ እና የ1985ቱ የግድያ ሙከራን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል?
ዘከሪያ፡- እነዚህ ነገሮች ላይ በመፅሐፉ ጥሩ መልስ ተሰጥቷል ብሎ ማለፍ ይሻላል፡፡ በእውነትና በጥንቃቄ ተተንትኖ በምክንያታዊነት የተሰራ መፅሐፍ ነው፡፡ አሁን ባልካቸው ነገሮች ላይ ይሄ መፅሐፍ ክፍተት የለበትም፡፡ አሻሚ የነበሩ ታሪኮች በጠቅላላ
መልስ ተሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ከትውልድ ቦታው ጋር የተገናኘውና ከቤተሰቡ ጋር እና ከናትና አባቱ ትዳርና ማንነት ጋር፣ ከራሱ ትዳር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከዚያም ደግሞ ከ1985ቱ የግድያ ሙከራ ጋር ያሉት ነገሮች በሙሉ በበቂ ሁኔታ ተተንትነው፣
ተብራርተው ቀርበዋል፡፡ የማያዳግም ምላሽ ተሰጥቷል ብዬ አስባለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- የጥላሁን ቤተሰቦች ስለ መፅሐፉ ያውቃሉ?
ዘከሪያ፡- የግል ታሪክ መፅሐፍ እራሱ ነው የሚመራህ፤ የሰውየውን የህይወት ምዕራፍ ነው
የምትከተለው፡፡ የአቶ ፈይሳ ሐሰና ሀይሌ የቤተሰብ ማስታወሻ ከተመለከትኩ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ታሪኮችን ለማሰባሰብና ለመተንተን የጥላሁንን ቤተሰቦችና የሱን የቅርብ ወዳጆች አነጋግሪያለሁ፡፡ ከወዳጆቹና የስራ ባልደረቦቹ መካከል እነ መሐሙድ አህመድ፣ ደበበ እሸቱ፣ አቶ ከበደ ወጋየሁ፣ ወ/ሮ ቆንጅት፣ ወ/ሮ አድባሪቱ የመሳሰሉትን አነጋግሪያለሁ፡

ቁም ነገር፡- ከቤተሰቦቹስ? ዘከሪያ፡- ወ/ሮ ማርታ፣ ወ/ሮ ሒሩትን
እንዲሁም ልጆቹንም አግኝቻቸዋለሁ፤ ይህን ስራ እየሰራሁ እንደሆነ የማያውቁ አሉ ብዬ አላስብም፡፡ ልጆቹንና የትዳር አጋሮቹን አግኝቻቸዋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- የመፅሐፉን የህትመት ወጪ ማነው የሸፈነልህ?
ዘከሪያ፡- ከቤተሰቦቼ ተበድሬ ነው፡፡
ቁም ነገር ፡- አመሠግናለሁ፡፡

The post አነጋጋሪው በጥላሁን ገሠሠ ዙርያ የወጣው መጽሐፍ – ‹መፅሐፉ የተዛቡ የጥላሁን ገሠሠን ታሪኮች ያጠራል› – ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የምስጢራዊው ድምፃዊ ‹አዳዲስ› ምስጢሮች

$
0
0

ጥላሁን ገሠሠ የዛሬ ስድስት ዓመት በፋሲካ ዋዜማ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ህዝብና መንግስት እንደ አንድ ሆነው ቀብሩን እንዳደመቁትና በጋራ እንደሸኙት እናስታውሳለን፡፡ጥላሁን በህይወት በነበረባቸው ዘመናት በህይወቱ ውስጥ ያሉ ብዙ አነጋጋሪና ምስጢራዊ ጉዳዮችን ሳያብራራና ግልፅ ሳያደርግ ማለፉን ተከትሎ በዓመቱ የወጣው የህይውት ታሪኩን የያዘው መፅሐፍ ነገሮችን አፍረጥርጦ ይፋ ያደርጋል የሚል ግምት ነበር፡፡ ያም ሆኖ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ‹ደራሲያን› በቡድን ተፅፎ የታተመው መፅሐፍ በጥላሁን ዙሪያ ያሉና የሚነገሩ ምስጢሮችን ሳያፍታታም ሆነ ሳይነካ የወጣ መፅሐፍ መሆኑ በወቅቱ አነጋጋሪ ነበር፡፡ ጥላሁን ገሠሠ በሕይወት በነበረበት ወቅት ለመጨረሻ ጊዜ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቶ ተዘጋጀ የተባለው መፅሐፍ አንድ የህይወት ታሪክ መፅሐፍ መያዝ ያለበትን መሠረታዊ ደንቦችን ያልተከተለና ጥላሁን ገሠሠን የማይመጥን መፅሐፍ መሆኑን ቁም ነገር መፅሔት በወቅቱ አስተያየቷን አስፍራለች፡፡
tilahun
ጥላሁን ገሠሠ የሚሊዮኖችን ስሜት የመቆጣጠሩን ያህል፤ ከ50 ዓመታት በላይ የማንጎራጎሩን ያህል፤በሀገር ፍቅር ስሜት ህዝቡን ያነደደ ሰው የመሆኑን ያህል የግል ህይወቱና ማንነቱም ለብዙዎች ምስጢር ነው፡፡ በትውልዱ፤ በዕድገቱ፤ በቤተሰቦቹ ፤ በትዳር ህይወቱና በልጆቹ ዙሪያ የሚታወቁ ነገሮች የጠለቁ አይደሉም፡፡ይህንኑ መነሻ በማድረግ ይመስላል ሰሞኑን በጥላሁን ገሠሠ ዙሪያ አንድ መፅሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምስጢር› በሚል ርዕስ በጋዜጠኛ ዘከሪያ መሐመድ የተፃፈው መፅሀፍ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ በቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ በተገለፀው መፅሐፍ ላይ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ ከአስተዳደጉ፤ከቤተሰቡ ማንነት፤ከሙዚቃው ስራው አንፃር ሳይንሳዊ የህይወት ታሪክ አፃፃፍን ተከትሎ እንደተዘጋጀ የሚናገረው ጋዜጠኛ ዘካሪያ ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ከሁለት ወራት በኃላ ስራውን መጀመሩንና አምስት ዓመታት እንደፈጀበት ይናገራል፡፡ በአራት ምዕራፎች የተከፋፈለው መፅሐፉ 448 ገጽ ያለው ሲሆን ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በተፃፈው መፅሀፍ ላይ የተገለፁ የሀቅ መፋለሶችን እንደሚያስተካክልና ለዓመታት ምስጢር የነበሩ ጉዳዮችን ‹ሆድ ይፍጀውን › ጨምሮ ለአንባቢያን ይፋ ያደርጋል፡፡ ከቤተሰቡ በተገኘ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ይህ መፅሐፍ እስከዛሬ ድረስ በየትኛውም ሚዲያ ላይ ያልታዩ ጥላሁን ገሠሠ የአንድ ዓመት ህፃን ሳለ ጀምሮ ያሉ ፎቶግራፎችን አካቶ ይዟል፡፡
ያልተፈቱት ምስጢሮች
በጥላሁን ህይወት ብዙ ያልተፈቱ ምስጢሮች አሉ፡፡ በ1985 ዓ.ም ከተፈጸመበት የግድያ ሙከራ ጀምሮ የቤተሰባዊ ህይወቱና የውልደት ቦታው ምስጢር ሆነው ወይም በተዛቡ መረጃዎች ታጅበው አመታትን ዘልቀዋል፡፡
የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ጋዜጠኛ ዘከርያስ መሃመድ ከአቶ ፈይሣ ሃሰና ሃይሌ ማስታወሻ ላይ ያገኛቸውን መረጃዎች መነሻ በማድረግ እውነቱን ላሳያችሁ ይለናል፡፡ በመጽሐፉ እንደቀረበው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ የሚል ካባ የተደረበለት ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የተወለደው አዲስ አበባ ሳይሆን ወሊሶ አካባቢ ሶየማ በተባለ ቦታ ነው፡፡ ከአቶ ፈይሣ ሃሰና ማስታወሻ የተገኘው ጽሑፍ እንዲህ ይላል፡-
‹‹በወረራው ምክንያት ተበታትኖ የነበረው ቤተሰባችን ሶየማ በሚገኘው የቤተሰብ ርስት ላይ ዳግም ተገናኘ፤ በዚህ ጊዜ ጌጤነሽ (የጥላሁን እናት) መውለጃዋ ተቃርቦ በጣም ከብዳ ነበር፡፡
… መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም የመስቀል በዓል ዕለት መላው ቤተሰባችን በወላጅ አባቴ በአቶ ሃሰና ቤኛ እልፍኝ ተሰብስበን ነበር፡፡ ከዕኩለ ቀን በኋላ በትልቁ እልፍኝ ጌጤነሽ በምጥ ተያዘች፤ ፅንሱ በሆድዋ ውስጥ ፋፍቶ ስለነበር ምጧ ረጅም ሰዓት ወሰደ፤ በዚህም ምክንያት ጌጤነሽ ደካክሟት ምጧ በተራዘመ ቁጥር ድካምዋ በርትቶ አቅም እያጣች በመሄድዋ ለእሷም ሆነ ለልጅዋ ህይወት በጣም ሰጋን፤ ቤተሰቡ በሙሉ ፀሎትና ልመና ያደርግ ጀምር፤ በመጨረሻም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን ጌጤነሽ ወንድ ልጅ ተገላገለች፤ የጌጤነሽ እናት ነገዬ አብደላ ዲንሳሞ ለተወለደው ልጅ ደገፋ ስትል ስም አወጣችለት፡፡›› (ገፅ 29-30)

ጥላሁን ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ጋብቻ የፈፀመ ሲሆን የመጀመሪያ ባለቤቱ መሆናቸው የሚነገረው ወ/ሮ አሥራት አለሙ ቢሆንም ጋዜጠኛ ዘከሪያ በአዲሱ መፅሐፉ ይህንን እውነት ያፈርሰዋል፡፡ የመጀመሪያ ባለቤቱ ፊት በር አካባቢ ትኖር የነበረች ፈለቀች ማሞ የተባለች ሴት ናት ይለናል፡፡ ከፈለቀች ጋር በሰርግ መጋባታቸውም ይነገራል፡፡ በወቅቱ ካሳ ተሰማ፣ እሳቱ ተሰማ እና ሸዋንዳኝ ወልደየስ የጥላሁን ሚዜዎች ነበሩ፡፡ (ገፅ 352)፡፡

ይሁን እና ከወ/ሮ ፈለቀች ጋር ረጅም አመታትን በትዳር አልቆዩም፡፡ በቅናት ምክንያት ፈለቀች ጥላው ጠፋች፡፡ ከዚያ በኋላ ሁለቱ ሰዎች ለረዥም ጊዚያት በአካል እንኳ ተገናኝተው አያውቁም ነበር፡፡ ዘከርያ የፈለቀች ጥላሁንን ባዶ ቤት ጥላው መጥፋት ከሌላ የልጅነት ታሪኩ ጋር አዛምዶ ይተነትነዋል፡፡

አቶ ፈይሳ ማናቸው?

አቶ ፈይሳ ሃሰና ሐይሌ የጥላሁን ገሠሠ አጎት ናቸው፡፡ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ የግል ታሪካቸውን ጨምሮ የጥላሁን እና የቤተዘመዶቹን ታሪኮች በመፃፍና ፎቶግራፎቹን በማንሳት ታሪክን ለትውልድ ያስቀመጡ ታሪከኛ ሰው ናቸው፡፡ ጋዜጠኛው ዘከርያ መሐመድ አሁን በመፅሐፍ መልክ ላሳተመው አዲስ የጥላሁን ታሪክ መነሻ የሆኑት እርሳቸው ናቸው፡፡ ይህ የአቶ ፈይሳ ማስታወሻ በጥላሁን ዘንድም የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እና እሱ በሕይወት እያለ እንዲታተም አይፈልግም ነበር፡፡ ለአመታት ከጋዜጠኞች ደብቋቸው የነበሩት ታሪኮች ተገልጠው ከአዲሱ እውነት ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥን አይፈልግም ነበር፡፡ ይሁን እና ህይወቱ ካለፈ በኋላ እንደሚታተም እርግጠኛ ነበር፡፡ ለአቶ ፈይሳ ልጆችም ማንቂያ የሚመስል ሀሳብ ሹክ ብሏቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ስሞት ይህን ታሪክ አትተኙበትም›› የሚል፡፡

የ22 ዓመታት እንቆቅልሽ

ጥላሁን ‹‹ሆድ ይፍጀው›› በሚል ያለፈው የ1985ቱ የግድያ ሙከራ በማን እና ለምን እንደተፈፀመ ጥርት ያለ መረጃ አሁንም ድረስ ባይገኝም ዘከርያ በመፅሐፉ ውስጥ ያስቀመጣቸው ትንታኔዎች ሁለት ድምዳሜዎች ላይ ሊያደርሱን ይታትራሉ፡፡ የመጀመሪያው ድምዳሜ ጥላሁን እራሱን ለማጥፋት ሙከራ አድርጓል የሚል ነው፡፡ አደጋው ከደረሰበት በኋላ ለንደን ለህክምና በሄደበት ወቅት ከቅርብ ጓደኛውና የጀርመን ሬድዮ ጋዜጠኛ ከነበረው ጌታቸው ደስታ ጋር ሲያወሩ እንደቀልድም ቢሆን ራሱን ለመግደል መሞከሩን ነግሮታል፡፡ ‹‹ስማ ጥላሁን ያኔ የጀመረህ ሰውዬ ሳይጨርስ አይተውህም፤ ወንድምህ ነኝ፡፡ ነገ ብትሞት በሚቻለው በማንኛውም መንገድ ገዳይህን እፋረደዋለሁ…. ንገረኝ… ማነው የወጋህ?››
‹‹ ራሴ ነኝ››
‹‹ሂድ ባክህን… ይሄን ሂድና ለምታወራለት አውራ እኔ አለቀበልህም›› (ገፅ 290)

ጌታቸው የጥላሁንን መልስ ያመነ አይመስልም፡፡ ነገር ግን ከዚህ የጥላሁን መልስ ተነስተን ሊሆን የሚችልበትን እድል ስንገምት አንድ ጥያቄ ማንሳት ጥሩ ይሆናል፡፡ ጥላሁን በርግጥ የመግደል ሙከራ የተደረገበት በሰው ከሆነ ከዚያ በኋላ በነበሩት እነዚያ ሁሉ አመታት ያ ሰው ጥላሁንን ለምን አልተተናኮለውም፡፡ መቼም አንድ ሰው በጊዜያዊ ንዴት ያን ያህል ጥቃት ይፈፅማል ተብሎ አይታሰብም፤ ከዚያ በተጨማሪ ግን በፖሊስ የምርመራ ውጤት ሊረጋገጥ አልቻለም፡፡ ወይም ተረጋግጦ ቢሆን እንኳን በድብቅ ቀርቷል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ጥላሁን እራሱን ለማጥፋት ሞክሯል ወደሚል ጫፍ ይወስዱናል፡፡ ዘከርያ በመጽሐፉ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበሩትን የጥላሁን ህይወት በሰፊው በመተንተን እንቆቅልሾቹን ሊፈታልን ሞክሯል፡፡

በሌላኛው ጫፍ ደሞ ጥላሁን ላይ ጥቃት የፈፀመ ሰው እንዳለ እንድናስብ ይገፋናል፡፡ ሰውዬው አቶ አወቀ መንገሻ ይባላል፡፡ ከገፅ 292 – 293 ድረስ በሰፈረው ፅሁፍ የቀደሙ መፅሔቶች ላይ የወጡትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ ስለ ጉዳዩ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡

ጥላሁንና አቶ አወቀ የሚቀራረቡ ጓደኛሞች ቢሆኑም በመጨረሻ ግን ተኮራርፈው ነበር፤ በዚህ ምክንያት አቶ አወቀ ወይም በአቶ አወቀ የታዘዘ ሰው ጥላሁን ላይ ጥቃቱን ፈፅሞ ሊሆን ይችላል ወደሚል ሀሳብ ይገፋናል፡፡ ተከታዩን ፅሁፍ እንመልከት፡-
‹‹ በ1990ዎቹ አጋማሽ አካባቢ አንድ እለት መሻለኪያ በሚገኘው የጥላሁን ሼል ነዳጅ ማደያ ቢሮ የስልክ ጥሪ አቃጨለ፡፡ የጥላሁን ፀሐፊ ስልኩን አንስታ ‹‹ጤና ይስጥልኝ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ቢሮ›› አለች፡፡

… ‹‹አወቀ የሚባል ሰው ሞቷል፡፡ እንኳን ደስ አለህ በይው፡፡››
‹‹እንዴ! ሰው ሲሞት እንዴት ለሰው እንኳን ደስ ያለህ ይባላል?!››
‹‹ግዴለም ለእርሱ ስትነግሪው ይገባዋል፡፡ አንቺ የማታውቂው ነገር ስላለ ነው፡፡››
በማግስቱ ይሁን በሳልስቱ ጥላሁን ከአሜሪካ ስልክ ደወለ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ፀሐፊዋ ሌሎች መልዕክቶችን አስቀድማ ‹‹አወቀ የሚባል ሰው ሞቷል የሚል መልዕክትም ተቀብያለሁ›› አለችው፡፡ የቀረውን መልእክት ግን ማስተላለፍ አልፈለገችም፡፡ … ምንም እንኳ በዛች ሰዓት የጥላሁን ገፅታ ባይታያትም ፀሐፊዋ ከምትሰማው የጥላሁን ድምፅ ሁለመናው ወለል ብሎ ይታያት ነበር፡፡ ከዚያ ለራሱ የሚያወራ ያህል ‹‹ ህም እርሱ ሞተና… እኔ ነዋሪ ሆንኩኝ?!›› አለ፡፡ (ገፅ 297)

መጽሐፉ ለምን?

የመጽሐፉ አዘጋጅ ዘከርያ መሐመድ በመቅድሙ ላይ እንዳሰፈረው እስካሁን በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን የሰማናቸውና ያነበብናቸው እንዲሁም የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በ2002 ዓ.ም ለህትመት ባበቃው መፅሐፍ የሰፈሩት የጥላሁን ገሠሠ ታሪኮች በመሠረታዊ ሀቅ ደረጃ ጉድለት አለባቸው፡፡ ‹‹ ጥላሁን ወደ ሙዚቃ ዓለም ከገባበት ዘመን አንስቶ እስከ ህልፈቱ ማግስት፣ ሕይወትና ሥራዎቹን የሚመለከቱ አያሌ ዘገባዎች በመገናኛ ብዙሀን ቀርበዋል በ2002 የህልፈቱ 1ኛ ዓመት በተከበረበት ወቅት ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉስ የሚል ርዕስ ያለው መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል፡፡ ነገር ግን በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የምናነበው የጥላሁንን የሕይወት ታሪክ እና ርዕሱ ከተጠቀሰው መፅሐፍ መሆኑ ከዚህ ቀደም ሲል በመገናኛ ብዙሀን ሲተረክ የኖረው የጥላሁን ሕይወት ታሪክ በመሠረታዊ ሀቅ ደረጃ ለየቅል ናቸው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ የህይወቱ ታሪክ እና ሚስጢር የተሰኘውን ይህን መፅሐፍ የወለደው ከዚህ ልዩነት ጀርባ ባለው በጥላሁን ህይወት እና በስብዕናው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ በምንም አጋጣሚ ያልተነገረ ቤተሰባዊ ክስተት ነው፡፡
ባለፉት 50 ዓመታት ስናነብና ስንሰማ የኖርነው የጥላሁን የትውልድ፣ የልጅነትና የቤተሰቡ ታሪክ ጥላሁን እስከ ሕይወቱ ፍፃሜ ድረስ ሚስጥር አደድጎ የያዘው የልጅነት ዘመን ቤተሰባዊ ጠባሳ የወለደው የተቀየረ ታሪክ ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ በጥላሁን የሕይወት ታሪክ ውስጥ ያሉ መሠረታዊ ሀቆች እንዴትና ለምን እንደተቀየሩ፣ እንዲሁም በጥላሁን ስብዕና ላይ ያሳደረው አንድምታ ምን እንደሚመስል ይተርካል፣ ይተነትናል፡፡›› ይላል፡፡
ዘከርያ መጽሐፉን ለማዘጋጀት የተነሳበትን አላማ ሲገልጽም፡- ‹‹ የተዛቡ ታሪኮችን ማስተካከልና የተዛቡ እይታዎችንና ግንዛቤዎችን ማስተካከል፣ ሰውዬውን መረዳት፣ ከሱ ህይወት መማር እንድንችል ነው፡፡ ለኛም እኮ ይጠቅመናል የሱ ህይወት ምን አይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደነበር እናያለን፡፡ እኔ ጥላሁን ገሰሰ ዝም ብሎ ተረት እንዲሆን አልፈልግም፡፡ ማንም የሚፈልግ አይመስለኝም፡፡ ጥላሁን የተለያየ ሰው በሚያነሳው ብጥስጣሽ አሉባልታ መካከል እንዲቆም አልፈልግም፤ ይሄ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ምን አይነት ስብዕና ነበረው፤ ከህዝቡ ጋር ምን አይነት መቀራረብ ነበረው፤ የልጅነት ህይወቱ ምንድነው የሚሉትን ነገሮች መለስ ብለን ብናውቅ እንማርበታለን፤ እንጠቀምበታለን፤ እሱንም ደግሞ ከተዛቡ ግንዛቤዎች እናጠራዋለን፡፡››ይለናል፡፡

ጥላሁን በህይወት ዘመኑ የደበቀን የግል ምስጢሮች እንዳሉትም ዘከርያ ይናገራል፡- ‹‹ እኛም አላወቅንለትም እሱም ደብቆናል፡፡ ሁለቱም ነው የሚባለው እሱ ስለደበቀን ነው እኮ እኛም ያላወቅነው፡፡ ነገር ግን ስለደበቀንና ሌላ ታሪክ ስለነገረን ውሸታም ነው ልንለው አንችልም፡፡ በርግጥ ውሸት ነው፡፡ ግን ለህልውናው ሲል እራሱን ለማቆየት ሲል ስሜቱን ለማጠገግ ሲል በሰቀቀን ላለመሞት ሲል አንድ ሰው ይዋሻል፡፡ ይሄ የሁላችንም ጉዳይ ነው ይሄ መፅሐፍ እኮ የጥላሁንን ታሪክ ለመናገር የወጣም አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎችን ያክማል ብዬ አስባለሁ እኔ፡፡ ጥላሁን ያደረገውን ማድረግ ጉዳትም ጥቅምም ይኖረዋል፡፡ ወደኋላ ያሉ መጥፎ ትውስታዎችን እንሸሻቸዋለን፤ ማስታወስ አንፈልግም፤ ስለዚህ ከዚያ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ማውራት ካለብን ከዚያ ሸሽተን ሌላ ታሪክ ጨምረንበት እንናገራለን፡፡ ጥላሁን ዝነኛ ባይሆን ኖሮ እኮ ሁሉም ሰላም ይሆን ነበር፡፡ ዝነኛ የሆነውም ያንን ታሪክ በመሸሹ ነው፡፡ ጥቅምም ጉዳትም ነበረው፡፡ ጥላሁን ደስተኛ ሰው አልነበረም፤ ለራሱ ሆኖ አይደለም የኖረው፡፡ እነዚያ የሚጎዱት ነገሮች ደግሞ በቀላሉ የሚታረቁት አይደሉም፡፡ እና ለምን ለህዝብ ያንን ታሪኩን አልተናገረም ልል አልችልም፡፡ ግን ስነልቦናውን ጎድቶታል፡፡ የተረጋጋ የትዳር ሕይወት እንዳይኖው አድርጎታል፡፡ የሆነ አቅሙን ነስቶታል፡፡ የሚፈጠሩ አደጋዎችን የመጋፈጥ አቅሙን ሸርሽሮታል፤ በዚህ ምክንያት ቤተሰቡ ይፈርሳል፡፡ ምክንያት አለው ሰዎች እንዲረዱት እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ለምሳሌ ጥላሁን ብዙ ስለማግባቱ አንስተው በመጥፎ ሁኔታ የሚተረጉሙት አሉ፡፡ ለምንድነው ብለው ግን አይጠይቁም፡፡ ዝም ብለው ‹አለሌነት› አድርገው ይወስዱታል፡፡ አይደለም / ላይሆን ይችላል፡፡ መጀመሪያ ለምንድ ነው ብለን ጠይቀን ትክክለኛውን ነገር መረዳት አለብን››

Source: ቁም ነገር ቅጽ 13 ቁጥር 201 ሚያዝያ 2007

The post የምስጢራዊው ድምፃዊ ‹አዳዲስ› ምስጢሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የጌትነት ሀለሐ እና ልማታዊ ሥነ ጥበብ

$
0
0

(ማስረሻ ማሞ)

ከኻያው ክፍለ ዘመን ታላላቅ ፈላስፎች የሚመደበው ኦስትሪያዊ ቪትገንስታይን፦ ፈላስፎችን ከማኅበረሰብ የተነጠሉ የየትኛውም “አገር” ዜጋ ያልኾኑ አድርጎ ይመስላቸዋል። የቪትገንስታይን ሐሳብ አከራካሪ ቢኾንም አስደንጋጭ አይደለም። በታሪክ ጀግኖች ፈላስፎች ብለን ከምንጠራቸው መካከል በርካቶቹ ከሚኖሩበት ማኅበረሰብ ሥር ነቀል በኾነ መንገድ የተነጠሉ (radical detachment) እና ማኅበረሰባቸውን ከውጭ የሚያዩ፣ የሚሄይሱ እና የሚተነትኑ ናቸው። ስለ አርቲስቶች ግን እንዲህ ዐይነት አስተያየት ሲሰጥ ብንሰማ ያስደነግጠናል። እንዲያውም ታዋቂው አንግሎ-አሜሪካዊ ገጣሚ እና ጸሐፊ ኦውደን እንዲህ ሲል ያስምጣቸዋል፤
A poet’s hope:
to be, like some valley cheese
local, but praised elsewhere
getenet eneyew
ማይክል ዋልዘር እንደሚለው አርቲስት ሊገፈተር፣ ከራሱ ማኅበረሰብ ጋራ ሊጣላ፣ እንደ ነቢይ ባገሩ ላይከበር እና ሊንገላታ ይችላል። ይኹንና ራሱን ከማኅበረሰቡ አይገነጥልም፤ እንደ ቪትገንስታይን ፈላስፋ አየር ላይ ሊንሳፈፍ አይቻለውም። ለዚህም ይመስለኛል አርቲስቶች በሚሠሩት እና በሚናገሩት በብዙዎቻችን ውስጥ ጠንካራ የኾነ አዎንታዊ እና አሉታዊ ስሜት የሚጭኑብን። በቅርቡ ጌትነት እንየው በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በሊቢያ የደረሰውን ዘግናኝ ግድያ አስመልክቶ ስለ ስደተኝነት እና ተጠያቂነት ያቀረበውን “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” ግጥም ስመለከት እና የፈጠረውን ነውጥ ስከታተል የተሰማኝ ይህ ዐይነት ስሜት ነው። ጌትነት እንዲህ ዐይነት ነገር ሲፈጥር የመጀመርያው አይደለም። ከጥቂት ዓመታት በፊት አንዳንዶቻችን የአሁኑ ዘመን የኢትዮጵያ አምባገነንነት ኢንጂኒየር እና አንቀሳቃሽ ናቸው ብለን እየኮነንናቸው የነበሩትን አቶ መለስ ዜናዊን ግነት በበዛባቸው ቃላት በማንቆለጳጰስ ክፉኛ ድብርት (depression) ውስጥ ከቶን ነበር፤ አስቆዝሞን ነበር። ይኸው ጌትነት በምርጫ 97 ወቅት በሌላ መንፈስ እና በሌላ ነፍስ “ወይ አዲስ አበባ” የሚል መንግሥትን የሚተች ሙዚቃዊ ቴአትር ደርሶ እና አዘጋጅቶ ሊያሳይ ሲል “ተንኮለኛ” ተብሎ የመቀስ ሰለባ ኾኗል። ጌትነት ሀ፣ ጌትነት ለ፣ ጌትነት ሐ፤ ጌትነት ሲናጥ እኛን ሲያናውጥ። በጌትነት የ“ሀለሐ” ጉዞ ውስጥ የኢትዮጵያን ሥነ ጥበብ እና ግንኙነትን መዳሰስ እንችላለን።

በልጅነቴ ምራቅ የዋጡ እና ኮሌጅ የበጠሱ ታላላቆቼ የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ መርኾ “ሶሻሊስት ሪያሊዝም ነው” ሲሉ አደምጥ ነበር። ለእኔ አእምሮ ልክ እንደ ኮሚዩኒዝም፣ ዲያሌክቲካል ማቴሪያሊዝም እና ወዘተ እነዚህ ቃላት “ከአምስት በላይ” ተብሎ የሚጠራውን ደማቅ ሰማያዊ ልብስ የሚለብሱ ሰዎች በወሬ መካከል ጣል የሚያደርጉት እና ለመናገር የሚያኮለታትፍ ከባድ የፈረንጅ ቃል ከመኾን ያለፈ ትርጉም አልነበረውም። በኋላ አድጌ በጋዜጦች የሥነ ጥበብ እና የፊልም ሂስ ጸሐፊ መኾን ስጀምር ደርግ ከተቀናቃኞቹ ዱላ ተንፈስ ባለበት ከ1972 እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት የኢትዮጵያን ሥነ ጥበብ ቀስፎ የያዘ ሐሳብ መኾኑን ተረዳሁ። ትንሽ ገፋ አድርጌ ስመረምር ደግሞ የሐሳቡን መፍለቂያ አገኘሁት።

እ.ኤ.አ በ1934 የሶቭየት ኅብረት ጸሐፍት የአንድነት-ኅብረት ኮንግረስ የመጀመርያው ስብሰባ ሲደረግ፤ የባህል አዛዡ አንድሬ ዛህዳኖቭ “ጓድ ስታሊን ጸሐፍቶቻችንን ‘የሰው ነፍስ መሐንዲሶች’ ይላቸዋል” ብሎ ነበር። ይህ ምን ማለት ነው? ይህ በጸሐፍት ላይ ሊጫን የተፈለገው “አክሊልስ” ምን ዐይነት ግዴታዎችን ያስከትላል?
ዛህዳኖቭ በጊዜው ሊያስቀምጥ የፈለገው ሐሳብ ማንም በስታሊን አመራር እና አስተዳደር ውስጥ ከፈጠራ እና ከሥነ ጥበብ ሞያ ጋራ ራሱን ያጣመረ ሰው የሶሻሊስት ሪያሊዝምን ትእምርት ተግባራዊ ማድረግ አለበት የሚል ነው። ሶሻሊስት ሪያሊዝም የዘመኑ የሶቭየት ኅብረት የባህል ፖሊስ ነበር። ማንኛውም አርቲስት እውነታውን ማሳየት ያለበት ከደረሰበት አብዮታዊ ዕድገት ጋራ በተጣጣመ መንገድ ነው። ሥነ ውበትን (aesthetics) እና ርዕዮተ ዓለማዊ ወጥነትን (Ideological uniformity) በሥነ ጥበብ ላይ ይጭናል። በርግጥ ይህ በሕግ የተደነገገ አልነበረም፤ ይኹንና በስታሊን አስተዳደር ዙሪያ ‘ሥነ ጥበብ በዘዬው ሪያሊስቲክ በግቡም ፕሮፖጋንዳዊ ነው’ የሚል ዶግማዊ እምነት ግን በእጅጉ ይቀነቀን ነበር።

የደርግ መርኾ የተቀዳውም ከዚያ ነው። ሶሻሊዝም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ እና የማኅበራዊ ሐሳቦችን የያዘ ታላቅ የፖለቲካ ፍልስፍና እና ርዕዮተ ዓለም በመኾኑ የሶሻሊስት ሪያሊዝም ቴንታክሎች በዕለት ተዕለት (mundane) ሕይወት ላይ የሚያተኩሩ ሥነ ጥበባትን ሁሉ ይመለከት ነበር። ይኹንና እንደ ታላላቅ ፍልስፍናዎች ሁሉ ሐሳቡ ሰፊ እና ብዙ ትርጓሜ ስለነበረው ለአርቲስቶች ለመተጣጠፍ ያመቻቸው ነበር።

ከደርግ መውደቅ በኋላ ኢሕአዴግ እንደዚህ ዐይነት የሥነ ጥበብን ሚና የሚመለከት ፍልስፍናን ለመፍጠር ጥቂት ዓመታት ፈጀመበት። ኢ-መደበኛ ሳንሱሩ እና ክልከላው የሚደረገው በመርኾ ላይ ተመሥርቶ ሳይኾን በወፍ በረር ነበር። ይህ የሥነ ጥበብን ነጻነት ቢያሰፋውም የፈቃዱን ድንበር ለመገመት እና ለማወቅ እንዲያስቸግር አድርጎታል። እንደ ሶሻሊስት ሪያሊዝም ዐይነት መርኾ እንደሚመጣ ፍንጭ ያገኘነው አቶ መለስ በ1992 በፓርቲያቸውን ውስጥ ያመጹባቸውን ባለሥልጣናት ለማጥቃት በጻፉት በተለምዶ “ቦናፓርቲዝም” ተብሎ በሚጠራው ጽሑፋቸው ነው። በዚያ ጽሑፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ሰው ሁሉንም የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሐሳብ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚሰጠው ጠበቅ ያለ የፍልስፍና ዐፅመ ሕንጻ (framework) ውስጥ ብቻ እንዲመሠረት፣ እንዲያሳድግ እና እንዲተረጉም ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።

እኔ እንደዚህ ዐይነቱን የሚያቅለሸልሽ ዕይታ መጀመርያ ያነበብኹት በቼስላቭ ሚሎዥ The Captive Mind በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ነበር። መጽሐፉ የምሥራቅ አውሮፓ ኮሚኒስት ሥርዐቶች እንዴት አድርገው የአርቲስቶችን እና የምሁራንን አእምሮ ጠፍረው እንደያዙ ይተነትናል። አቶ መለስ ይኼንም አድርገው “በሐይል ሳይኾን በውድ ነው” ሲሉ ደነገጥኹ። በዴሞክራሲ ተፎካክሬ የአርቲስቶችን ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያውያንን አእምሮ በቅጡ እንኳ ባልተተነተነው አደናጋሪ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ፍልስፍና አስረዋለሁ አሉ። “የሐሳቤ ጉልበት ፍላጎቴን ያስፈጽማል” ሲሉ ተከራከሩ። ይህን ጽሑፋቸውን ሳየው የትዕቢቱ ደረጃ ያስገርመኛል። የኖዓም ቾምስኪን Propaganda Model ያለነበበ እንኳ በዴሞክራሲያዊ ሥርዐት እንዲህ የምናብ እስራት ማምጣት ይቻላል ብሎ ለማሰብ ይቸገራል። ምርጫ 97 ደርሶም ይህን መሰከረ። አቶ መለስም በዴሞክራሲ እና በአእምሮ እስር መካከል ያላቻ ጋብቻ መመሥረት እንደሚያዳግታቸው ሲያውቁ ብዙ ጊዜ ተሞክሮ እንደሚሠራ ወደተረጋገጠው ወደ አምባገነን “ካሮት እና ልምጭ” ሄዱ። በመጀመርያ ቡትቶውን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጥለው በደቨሎፕመንታል ስቴት ሐሳብ ተኩት። ከዚያ ሥነ ጥበብ የደቨሎፕመንታል ስቴት ሐሳብ ፕሮፖጋንዳ መሣርያ እንዲኾን ከራዳር ውጭ ደነገጉ። ድንጋጌው ሥነ ጥበብ በሚሠራባቸው ቦታዎች በሙሉ ገዢ ኾነ።

“ኢሕአዴግ ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ይዞት የመጣው የልማታዊ ሥነ ጥበብ ስልት እጅግ ጽንፈኛ እና የሥነ ጥበብን ጉልበት ለማሽመድመድ ተሰልቶ የተቀመረ ነው” ይላሉ አንድ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴአትር ዲፓርትመንት መምህር። እንደ መምህሩ አባባል አዲሱ የሥነ ጥበባት ዩኒቨርስቲዎች አወቃቀር አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከዚህ በፊት በራሳቸው ቆመው ይሠሩ የነበሩት የቴአትር ዲፓርትመንቱ፣ የሥዕል ትምህርት ቤቱ እና የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በአንድ ላይ ተዋቅረው “እስክንድር ቦጎስያን ኮሌጅ ኦፍ ፐርፎርሚንግ ኤንድ ቪዡዋል አርትስ” በሚለው ሥር ተጠቃለዋል። ይህ ተግባራዊ እንዲኾን ያደረጉት የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አንድርያስ እሸቴ ናቸው። “ይህ ሐሳብ አምባገነናዊ ቁጥጥር የሌለው እና ሁሉም ነገር ወደ ልማት ያተኩር የሚል ጫና ባይኖርበት ኖሮ ሠዓሊው፣ ቴአትረኛው እና ሙዚቀኛው በነጻነት አንዳቸው ከአንዳቸው ጋራ የሐሳብ ፍጭት እና ልውውጥ የሚያደርጉበት ቢኾን መልካም ነበር፤ እየኾነ ያለው ግን በተቃራኒው ነው። በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ በዋነኛነት ፈንድ የሚደረጉት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥር ሲኾን ዋነኛ ተግባር እና ዓላማቸው ደግሞ ሥራዎቹ በሙሉ ልማት ላይ ብቻ ያተኮሩ እንዲኾኑ ማድረግ ነው። ይህን ለማስፈጸም ትልቁን ሚና የሚጫወቱት የእስክንድር ቦጎስያን ኮሌጅ ዲን የኾኑት አቶ ነቢዩ ባዬ ናቸው። እርሳቸው ያልፈቀዱት እና ያልፈረሙበት የትኛውም ፕሮጀክት ወደ ተግባር አይለወጥም። አቶ ነቢዩ ደግሞ የአገሪቱ የባሕል ፖሊሲ ተደርጎ የተወሰደው የልማታዊ ሥነ ጥበብ ቀንደኛ አቀንቃኝ ናቸው።” ይላሉ። አቶ ነብዩ ባዬ እንደ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን እና እንደ አባይ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች ላይ የሚያተኩሩ ድራማዎችን፣ ቴአትሮችን እና ሙዚቃዎችን በመሪነት ይጽፋሉ፤ ያሠራሉ። ኢሕአዴግ ሥነ ጥበብ ያላትን ጉልበት በመረዳት በሕዝቡ ውስጥ ተቀባይነቱን ለማስረጽ ቴአትሮቹ በየክልሉ እንዲዞሩም ያደርጋል።

ፖለቲካ እና የሙዚቃ ሥነ ውበት ላይ ጥናት የሚያደርጉት ዶክተር ሉዊስ ፐላስኮ ፕፍላዉ “ራሳቸውን ከአብዮት ጋራ አቆራኝተው መንግሥት የሚመሠርቱ አምባገነኖች ሁለት ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች አሉ። አንደኛው፦ ብሔርተኝነትን የተላበሰ ባህላዊ ማንነት መፍጠር ነው። ሁለተኛው፦ በሥነ ጥበብ ውስጥ ፖለቲካዊ ተቀባይነታቸውን በማሰናሰል በአገር ውስጥም ኾነ ከአገር ውጪ የመንግሥታቸውን ስክነት ለማሳየት አገራዊ ጉዳዮችን በማስረግ ተቋማዊ እንዲኾን ማስቻል ነው።” ይላሉ። እንደ አቶ ነብዩ ባዬ ያሉ በሐላፊነት ቦታ የተቀመጡ ሰዎች ጠቅላይ አምባገነንነት እንዲፋፋ ሥነ ጥበብን እንደ መሣርያ በመጠቀም ማኅበረሰብን ለአንድ ዓላማ እና ለአንድ ግብ በማሰለፍ፤ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በማሳለጥ፤ የሚሠሩትን የሥነ ጥበብ ውጤቶች በሙሉ የስኬቱ ማረጋገጫ ለማድረግ ቀን ቀሌት የሚታትሩ ናቸው። “ለምሳሌ አቶ ነብዩ ከዲንነት ባሻገር በቀድሞው ኢቲቪ ባሁኑ ኢቢሲ የሚተላለፉ ድራማዎችን የመገምመገም ሥልጣን የተሰጣቸው ሰው ናቸው። ድራማው የእርሳቸውን ልማታዊ ሚዛን ካላስጎነበሰ አያሳልፉትም” ይላሉ።

እንደ አቶ ነብዩ ባዬ ያሉ ሰዎች አንገታቸውን ደፍተው የሚያገለግሉት ዴቨሎፕመንታል ስቴት እንደ ሶሻሊዝም ታላቅ የፖለቲካ ፍልስፍና ሳይኾን የተጋነነ የኢኮኖሚክ ፖሊሲ (glorified economic policy) ነው። በዴሞክራሲ አገር የምንኖር ቢኾን ኖሮ በየጊዜው ለምርጫ እንየቀረበ በመራጮች ራይት እና ኤክስ ይሰጠው ነበር። ስለዚህ በዚህ አስተሳሰብ አርቲስቶቻችን የኢኮኖሚክ ፖሊሲ ፕሮፖጋንዲስቶች ኾኑ ማለት ነው። ነፍሳችንን ይመረምሩታል፤ መንፈሳችንን ይፈታተኑታል ስንል የአቃቤ ነዋይ ሥራ ተሰጣቸው። ስለ ግድብ እና ትራንዚስተር መግጠም፣ ቴአትር መድረስ፣ ድራማ መሥራት እና መዝፈን ጀመሩ።

አልበርት ካሙ The Rebel በተሰኘ መጣጥፉ አርቲስቶች በየማኅበረሰቡ ጀግንነት እንደሚጠበቅባቸው ነገር ግን ይህ ተስፋ ሩቅ መኾኑን ታሪክን እያጣቀሰ ያወጋናል። ብዙ አርቲስቶች የጨቋኞች ጋሻ እና የፕሮፖጋንዳ መሣርያ ኾነው አገልግለዋል። ከማመጽ ይልቅ ማደርን የሚመርጡ ናቸው- እንደ ካሙ። እንዲያውም የካሙ ትችት ከዚህም ያየለ ነው፤ ዱላ አላብዛ ላለስልሰው ብዬ እንጂ። ስለዚህ “ሁሉም ነገር ወደ ዴቨሎፕመንታል ስቴት” የሚለውን መርህ ለጥ ብለው ቢቀበሉም፣ ድሮ የነበራቸውን አቋም ቀይረው ለመንግሥት ቢያጫፍሩ ለካሙም (አፈር ይቅለለውና) የሥነ ጥበብን ታሪክ ለሚያወቅም አይገርመውም። ጌትነት ሀ ወደ ጌትነት ለ ቢሸጋገር ምክንያቱ በዙርያው ያለው ያለው የፖለቲካ ኢኮኖሚ መዋቅር መለወጡ ነው። ይኹንና አርቲስቶች ላይ አብዝቶ ተጠራጣሪ መኾን ማለት ሥነ ጥበብ ላይም ተስፋ መቁረጥ ማለት አይደለም። አሪስቶትል እንደሚለው የሥነ ጥበብ መጎልበት የሰው ልጅ ማበብ ዋነኛ መለኪያ ነው። የሥነ ጥበብ መጎልበት ጥራትን፣ ብዛትን እና ስብጥርን ያካተተ ነው፤ ስለ ግድብ እና ትራንዚስተር መግጠም የሚፈልገውም፤ ትልልቅ ሐሳቦች እያነሳ ነፍሳችንን የሚጎነትለውም፤ የቀን ተቀን ሕይወታችንን የሚዳስሰውም፤ ስውሩም- ስውር ያልኾነውም፤ ሁሉም ሥነ ጥበብ የሚፋፋበት የአንድ ሺሕ ጽጌሬዳዎች ዓለም። የቴአትር ዲፓርትመንት መምህሩ እንደሚሉት “አርቲስቶች እና የሥነ ጥበብ መምህራን የራሳቸው የኾነ ግለሰባዊ ፍላጎት እና የፖለቲካ ግብ ይኖራቸዋል።” ይኹንና በግለሰብ እና በማኅበረስብ መካከል ለመምረጥ የሚያስችለው ግብ የሚመረጠው በአንድ ፓርቲ እምነት እና ዓላማ ላይ ተመሥርቶ ከኾነ “ማበብ” ገደል ገባ፤ “ይህ እንዴት ያለ አሰቃቂ እውነታ እንደኾነ እያየነው ነው።” ይላሉ መምህሩ።
teddy afro
ይኹንና በዚህ አሰቃቂ ኹኔታም ውስጥ አፈትልከው በመውጣት የሚያብቡ እና የሚያፈሩ የሥነ ጥበብ ሥራዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በፊት በነበረችው ሶቭየት ኅብረት ውስጥ ፈክተው እና አብበው መውጣት የቻሉ ሥራዎች ነበሩ። በደርግ ጊዜም በየቀበሌው ከተቋቋሙት የኪነት ቡድኖች መካከል የወጡ ግለሰቦች እና የቡድን ሥራ ውጤቶችን መጥቀስ ይቻላል፤ በሥዕል፣ በሙዚቃ፣ በቴአትር፣ በልቦለድ፣ በግጥም እና በመሳሰሉት። አሁንም የበእውቀቱ ስዩም ዐይነት አፈንጋጭ ገጣምያን፣ የቴዲ አፍሮ ዐይነት ለደቨሎፕንታል ስቴት ጽንሰ ሐሳብ የማያደገድጉ አቀንቃኞች፣ ሠዐልያን እና ሌሎች አርቲስቶች አሉ። የእነዚህ አርቲስቶች ፈተና ከባድ ነው። እንደ እነ ጌትነት ጊዜን ተገን እያደረጉ ሥነ ጥበብን የጊዜው ሥልጣን እና ሐይል (power) መሣርያ ማድረግ ቀላል ነው። ሃላፊነትን በተመለከተ ሁሉም ድርሻ ድርሻውን እንዳያነሳ “ጥፋተኞች ሁላችንም ነን” ለሚል መደበቂያ ይዳርጋል እንጂ። ይህ ደግሞ በሥነ ጥበብ ሊያብብ የሚገባውን ሕይወት ያቆረፍደዋል።

Source: 7-killo Magazine

The post የጌትነት ሀለሐ እና ልማታዊ ሥነ ጥበብ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አነጋጋሪው የጥላሁን ገሰሰ መጽሐፍና የባለቤቱ ሮማን በዙ ምላሽ

$
0
0

Tilahun and Roman Bezu
በጋዜጠኛ ዘከርያ መሀመድ የተጻፈውና ‹‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ምስጢር›› በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃውን መጽሐፍ አስመልክቶ የተለያዩ ሀሳቦች እየተነሱ ነው፡፡ ዘከርያ በቁም ነገር መጽሔት 202ኛ እትም ላይ በሰጠው ቃለምልልስ መጽሐፉን ለማዘጋጀት ዋና ምክንያት የሆነው በጥላሁን ገሠሠ ዙሪያ የሚነሱ የተዛቡ ታሪኮችን ማጥራት መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁንና የጥላሁን ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ‹ከመጽሐፉ መታተም ጀርባ ሌላ ታሪክ አለ› ትላለች፡

ቁም ነገር፡- ጋዜጠኛ ዘከርያ የጻፈው መጽሐፍ ለንባብ ከመብቃቱ በፊት እየተጻፈ እንደሆነ ታውቂ ነበር?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንድ ጊዜ በጥላሁን ዙሪያ ኮሚቴውን ለማመስገን አንድ ዝግጅት ቤታችን ውስጥ ተዘጋጅቶ በነበረበት ወቅት ንጉሤ የሃረሩ መጥቶ ነበር፡፡ እሱ ነው መጀመሪያ የነገረኝ፡፡ ‹ዘከርያ የሚባል ሠው እኔን አነጋግሮኛል፤ በጥላሁን ዙሪያ መጽሐፍ እያዘጋጀ ነው ለምን ባለቤቱን አታነጋግራትም ብየው ነበር› አለኝ፡፡ ከዚያ ወዲያው ደወለለትና ከኔ ጋር አገናኘን፡፡ እኔም ‹‹ከበፊቱ መጽሐፍ የተለየ ነገር አለኝ የምትል ከሆነ በአካል እንገናኝና እናውራ፤ ጥላሁን ሠፊ ነው፤ ብዙ የምንልለት ነገር ይኖራል፡፡ የጥላሁን ነገር በአንድ
መጽሐፍ የሚያልቅ አይደለም፤ ስለዚህ አዲስ ነገር ካለህ እንገናኝና አብረን እንሰራለን›› አልኩት፡፡ እሽ ተባብለን ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ጠፋ፡፡

የሚሆነው ይመስለኛል፡፡ ንጉሤ በትክክል ጊዜውን ያስታውሰው ይሆናል፡፡ በንጉሴ ስልክ ነው ያወራነው፡፡ ከዚያ በኋላ አንድ ቀን ንጉሤን ‹ያልከኝ ሰውዬ የታለ› አልኩት፡፡ እሱም እኔም ጋ መረጃ ከወሰደ በኋላ ጠፍቷል፡ ከአንች ጋር በስልክካወራችሁ በኋላ ደውሎልኝ አያውቅም አለኝ፡፡ ከዚያ በኋላ መጽሐፍ እየተጻፈ ነው.. ሊያልቅ ነው የሚለውን ወሬ መስማት ጀመርኩ፡፡

ቁም ነገር፡- መጽሐፉን መቼ ነው ያየሽው?
ወ/ሮ ሮማን፡- መጽሐፉ ውስጥ ያነጋገራቸው አንዳንድ የጥላሁን ወዳጆች እየደወሉ ይጠይቁኛል፡፡ አንች ጋር አልመጣም እንዴ? እኛን እኮ መጥቶ አነጋግሮናል፤ እሷ ጋ መሄድ አለብህ ብለነዋል ብለው ሲነግሩኝ እኔ ጋ አልመጣም ብዬ እመልስላቸዋለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ መጽሐፉ ታትሞ ወጣ፡፡
መፅሐፉ ከወጣ በኋላ የእሱ ጓደኞች አንጋፋዎቹ ተናደው ምንድነው አሁን የሞተን ሠው አንስቶ ዋሽቷል እንዲህ ብሏል ማለት፣ እንዴት ዝም ትያለሽ ብለው ይደውሉልኛል፡፡ እኔ ደግሞ መጽሐፉን ገና አላነበብኩትም ነበር፡፡ መጽሐፉን ላንብበውና የምንለውን እንላለን አልኳቸው፡፡

ቁም ነገር፡- እነ ማናቸው ?
ወ/ሮ ሮማን፡- የጥላሁን ወዳጆች ናቸው፤ ጥላሁንን ከስር ከመሠረቱ የሚያውቁ ወዳጆቹ ናቸው፡ ፡ ነይ ብለው ብሔራዊ ቴአትር ቤት ጠርተው ቁም ነገር መጽሔት ላይም ወጥቷል፤ መጽሐፉንም ነይ አንብቢ ብለውኝ እዚያ ሄጄ ነው መጀመርያ ያየሁት፡፡ ከዚያ ወዲያው ነው መጽሐፉን ይዤ ቤቴ ሄጄ ማንበብ
የጀመርኩት፡፡
ቁም ነገር፡- መጽሐፉን ካነበብሽ በኋላ ልክ አይደሉም ያልሻቸው ሃሳቦች የትኞቹ ናቸው?
ወ/ሮ ሮማን፡- ከሀሉም በፊት መነሳት ያለበት ይሄ መጽሐፍ ለምን ተጻፈ የሚለው ነው፡፡ ስለ መጽሐፉ ይዘት ከማውራታችን በፊት ሌላ ማወቅ ያለብን ነገር አለ፡፡ መጽሐፉን ካነበብኩ በኋላ ስደርስበት ከደራሲው በስተጀርባ ያለው ሠው ነው ዋና ምክንያቱ፡፡ መነሻው የአቶ ፈይሣ ልጅ የሆነው ሳምሶን ነው፡፡ በመጽሐፉ ላይ የሳምሶን እጅ እንዳለ ሳውቅ መጽሐፉ በምን ደረጃ እንደሚጻፍ ይገባኛል፡፡ እያንዳንዱን ገጽ እንኳ ማንበብ አይጠበቅብኝም፡፡

አቶ ፈይሳን አውቃቸዋለሁ፡፡ ደብረብርሃን ወስዶ ጥላሁን አስተዋውቆኛል፡፡ የእሳቸው ልጅ ሳምሶን ደግሞ እኛ ቤት ይኖር የነበረ ሠው ነው፡፡ እኔና ጥላሁን በትዳራችን መሃል ለተፈጠረው ግጭት ዋናው መሳሪያ ሳምሶን ነበር፡፡ ለጥላሁን የሆነ ያልሆነ ነገር ይነግረው ነበር፡፡ እንዲህ እያደረገች… እንዲህ ልታስደርግህ…ብዙ ነገር…በቃ እኔ ልናገረው የሚዘገንነኝን ነገር ሁሉ እያለ ጥላሁንን ከቤት እንዲወጣ አደረገው፡፡ ከዚያ ጥላሁን ወጣ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ እቃዎቼን ስመለከት ብዙ ነገር ጠፍቷል፡፡ በሻንጣ የነበሩ ልብሶቼና ወርቅ ሁሉ ሳይቀር ይጠፋል፡፡ ላንቻ ፓሊስ ጣቢያ አመልክቼ ሰራተኞቹ ሁሉ ሲመረመሩ ሳምሶን ነው የወሰደው ብለው ተናገሩ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ እሱ ግን ሊያምን አልቻለም፡፡ ታሪኩ በጣም ረዥም ነው፡፡ በኋላ ፖሊሶቹን ደብረብርሃን እንሂድ አልኳቸውና እዚያ ስንሄድ በሙሉ ከአሜሪካ ሀገር ያመጣኋቸው 7 ሻንጣ ልብስና ወርቆቼ ሳይቀር ተገኙ፡፡

ጥላሁን ይህን ሲያውቅ ፖሊሶቹ ሲነግሩት መሬት ላይ ነው የተደፋው፡፡ ‹‹የልጄ እናት ይቅርታ አድርጊልኝ፣ ለዚህ ያበቃኝ እሱ ነው፤ ብዙ ነገር እየነገረ››
ብሎ አለቀሰ፡፡
በአጭሩ ሳምሶን ማለት ይሄንን ያደረገ ሰው ነው፡፡ ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ብትጠይቁ መረጃውን ታገኛላችሁ፡፡ ፖሊሶች ከሳምሶን ኪስ ውስጥ ብዙ የጥንቆላ ነገሮችን ሁሉ ነው ያገኙት፡፡ ‹‹ጥላሁንን እንዲህ አርግልኝ…ምናምን›› የሚል እንዲሁም ደግሞ ጥላሁን ከተለያየ ሠው እንደተበደረ አስመስሎ ያዘጋጀው ወረቀት ሁሉ ተገኝቶበታል፡፡ ጥላሁንን ትብትብ አድርጎ የተጫወተበት ሰው ነው ሳምሶን ማለት፡፡

ቁም ነገር፡- ከጥላሁን ጋር ምንድነው ዝምድናቸው?
ወ/ሮ ሮማን፡- አቶ ፈይሳ ለጥላሁን እናት አጎት ናቸው፡፡ ሳምሶን ደግሞ የእሳቸው ልጅ ነው፡፡ አቶ ፈይሳ ስለጥላሁን ሊያውቁ የሚችሉት ብቸኛው ነገር ምናልባት የተወለደበትን ቦታ ነው፡ ፡ እሱንም ቢሆን የጻፉትን መረጃ ማየት አለብን፡፡ አቶ ፈይሳ በዚያ ዘመን የረቀቁ ሰው ሆነው ጥላሁን ወደፊት እዚህ ደረጃ እንደሚደርስ ታይቷቸው ነው የጻፉት? ጠንቋይ ናቸው? የወደፊቱ ይታያቸዋል? የጥላሁንን ብቻ ነው ወይስ የልጆቻቸውን ታሪክ ጽፈዋል? ምንድነው? በማስረጃ መረጋገጥ አለበት፡፡

ቁም ነገር፡- መጽሐፉ ለሆነ የተለየ አላማ የወጣ ነው ብለሽ ታምኛለሽ?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንደኛ ሳምሶን ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ አውቃለሁ፡፡ ጥላሁን ገና በህይወት እያለ እንኳ ሊሸጠው ሊለውጠው የፈለገ ሠው ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ መጽሐፍ ጀርባ ከደራሲው ጋር በምን እንደተደራደረ ባላውቅም የተወሰነ ሳንቲም ሊገኝበት ይችላል፡፡ ትልቁ አላማው ሳንቲም ነው፡፡ ሳምሶንን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ መጽሐፉ ምንድነው ያመጣው አዲስ ነገር? ትንሽ የተለየ አገኘሁ ብል የት ተወለደ የሚለውን ነው፡፡ ሌላው ግን የቃላት ጨዋታ ነው እንጂ ምንም የተለየ ነገር የለውም፡፡ ‹‹አንድን መጽሐፍ ሽፋኑን አይተህ ግምት አትስጥ›› የሚባለው እውነት ነው፡፡ ‹‹ምስጢር›› ይላል ግን ምንም አዲስ ምስጢር የለም፡፡ በእርግጥ ስለሙያው ጥሩ አድርጎ ጽፏል፡፡ እሱም ቢሆን ግን ከዚህ በፊት ያልተባለ ነገር አይደለም፡፡ የትዳሩን ጉዳይ በተመለከተ ግን ዝም ብለህ ቁጭ ብለህ የምትጽፈው አይደለም፡፡ የስሚ ስሚ ልትጽፍ አትችልም፡፡ በትዳር ውስጥ ስላለው ጉዳይ የሚያውቁት ባለቤቶቹ ብቻ ናቸው፡፡ እኔ እንኳን ልናገር ብል እኔን በተመለከተ ያለውን እንጅ ከዚያ በፊት ስለነበረው የትዳር ህይወት ግን ማንም ገብቶ ከሁለቱ ባልና ሚስት ውጭ እውነቱን ሊናገር አይችልም፡፡ ልትጽፍ የምትችለው ባለቤቱ ራሱ የተናገረውን ነው፡፡

ስለእኔ ተጽፏል፡፡ ግን ፀሐፊው እኔ ጋ አልመጣም፡፡ አውቃለሁ፡፡ ሳምሶን ዘከርያ ወደእኔ እንዲመጣ አይፈልግም፡፡ ምክንቱም እኔ ምን እንደምል ያውቃል፡፡ ግን ፀሐፊው መጽሐፉ ውስጥ ስለኔ የሚያወራ ከሆነ መጥቶ ሊያነጋግረኝ ይገባ ነበር፡፡ ስለ አንድ ሰው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ
ነገር ስትጽፍ ባለቤቱን ማናገር ያስፈልጋል፡፡

ቁም ነገር፡- ያ ችግር ከተፈጠረ በኋላ ሳምሶን ከጥላሁን ወይም ከአንቺ ጋር ተገናኝቶ ያውቃል?
ወ/ሮ ሮማን፡- በፍፁም፡፡ ከጥላሁን ጋር ራሱ አስራ ምናምን አመት ይሆናቸዋል፡፡ ሕይወቱ ካለፈ በኋላም ለቅሶ እንኳ እኔ ጋ መጥቶ
አልደረሰም፡፡
roman bezu

ቁም ነገር፡- የደራሲያን ማህበር በጻፈው መጽሐፍ ላይ ጥላሁን የተወለደው አዲስ አበባ መሆኑን ይገልፃል፤ በአዲሱ መጽሐፍ ደግሞ የጥላሁን የትውልድ ቦታ ወሊሶ መሆኑ ተጽፏል፤ ያሄን እንዴት ነው ማስታረቅ የሚቻለው?

ወ/ሮ ሮማን፡- እኔ አሁን በሁለቱም ጎን ሆኜ ጥላሁን አዲስ አበባ ነው የተወለደው ወይም ወሊሶ ነው የተወለደው ማለት አልችልም፡ ፡ ለምሳሌ አቶ ፈይሳ ለጥላሁን በእናቱ በኩል ባላቸው ዝምድና ስለጥላሁን ማስታወሻ ጽፈው እዚያ ላይ የገለጹት ወሊሶ እንደተወለደ ነው ተብሏል፡፡ ማስረጃ ካለ ላምን እችላለሁ፡፡ ግን ይቅርታ አድርግልኝና እሳቸው ጽፈዋል በሚል ሳምሶን ያን ሊያደርገው አይችልም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሳምሶን ጥላሁንን በቁም እያለ ሊሸጠው የነበረ ሠው ነው፡፡

ዞሮ ዞሮ ወሊሶ ነው የተወለደው ወይም አዲስ አበባ ያንን የሚያውቀው ራሱ ባለቤቱ ነው፡ ፡ በነገራችን ላይ ጥላሁን የውልደት ቦታ ወይም የብሔር ነገር የሚያሳስበው ሰው አልነበረም፡ ፡ በተለያዩ ቦታዎች የሆነ ፎርም ሲሞላ እንኳ ብሔር ሲባል ኢትዮጵያዊ ብሎ ነበር የሚሞላው፡፡ ጥላሁን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዚያ ላይ አዲስ አበባ መወለድም ሆነ ወሊሶ መወለድ የሚያሰፍርም ሆነ የሚያኮራ ነገር የለውም፡፡ ስለዚህ ሊደብቅ የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የደራሲያን ማህበሩ መጽሐፍ ላይ ጥላሁን አዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ ሠፈር እንደተወለደ ነው የገለጸው፡፡ የተቀረጸና ከሰውዬው አንደበት የተሰማ ነው፡፡ ነገር ግን በማስረጃ እስከተጻፈ ድረስ በዚህኛው መጽሐፍ ላይ የሠፈረውንም ቢሆን አምነዋለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ስለዚህ በአጠቃላይ መጽሐፉ የተጻፈው በሳምሶን ግፊትና ለጥቅም ሲባል ነው ብለሽ ነው የምታምኚው?

ወ/ሮ ሮማን፡- ለጥቅምና ስም ለማጥፋት ተብሎ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ እኔ እንዳጋጣሚ በጥላሁን የትዳር ህይወት ውስጥ መጨረሻ ላይ ሆንኩኝ፡፡ ማንም ሠው የህይወቱን አጋጣሚ አያውቅም፡፡ የእኔ ከሱ ጋር የመጨረሻ መሆን የሰሞኑ አጀንዳ ሳምሶንና የሳምሶን አጃቢዎችን ስላናደዳቸው ‹‹ጥላሁን እሷ ጋር በነበረበት ወቅት ተጎድቷል በጥሩ አታስታምመውም ነበር›› ብለዋል፡፡ ይሄ እኮ ስም ማጥፋት ነው፡፡ ይሄ ባይሆን እኔ ጋ መጥቶ ይጠይቀኝ ነበር፡፡ አንድ ሶስቱን የቀድሞ የትዳር ጓደኞቹን መርጦ አነጋግሮ እነሱ ጋ እንክብካቤው ከፍ ያለ እንደነበር አድርጎ፤ እኔ ግን እንደበደልኩት አድርጎ ነው የጻፈው፡፡ እኔን ግን አላናገረኝም፡፡ በተጨማሪ የሞተን ሰው አሁን አንስተህ ዋሽቶ ነበር፤ በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም፤ እያሉ መጻፍስ ምን ይጠቅማል፡፡ እሱ ታዋቂ ስለሆነ ማንም ተነስቶ እየዘለፈ መጻፍ ያለበት አይመስለኝም፡፡

ቁም ነገር፡- ጥላሁን ራሱን ለማጥፋት እንደሞከረ በመጽሐፉ ተገልጾዋል፤ በዚህ ጉዳይ ምን ትያለሽ?
እየተባለ ነው የተፃፈው፡፡ የሠው ስምም ተጠቅሶ እከሌም ይጠረጠራል ተብሎ ተጽፏል፡፡ አሁንም በ‹ሆድ ይፍጀው› ዙሪያ ነው እንጅ የተቀመጠው መፍትሔ አልሰጠውም፡፡ መፍትሔ የሚሰጠው ማስረጃ ሲኖረው ነው፡፡ ለጥርጣሬ ለጥርጣሬማ ሠው እቤቱ ቁጭ ብሎ እኮ ‹‹ራሱን ሊያጠፋ ሞክሮ ይሆን እንዴ? ለምንድነው ሆድ ይፍጀው ያለው?›› እያለ ሊነጋገር ይችላል፡፡

ቁም ነገር፡- አቶ ፈይሳ የቤተሰብ ማስታወሻ እንደሚጽፉ ታውቂ ነበር፤ ከጥላሁን ጋር ሲያወሩ ሰምተሸ ይሆን ?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንድ ሁለት ጊዜ ነው ደብረብርሃን ሄጄ ያገኘኋቸው፡፡ ምንም የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡ በጣም በቅርብ የማውቀው ልጃቸው ሳምሶንን ነው፡፡ እሱ እኛ ቤት ነው ይኖር የነበረው፡፡

ቁምነገር፡- ደራሲያን ማህበር የፃፈው መጽሐፍ ጥላሁንን በበቂ ሁኔታ ገልጾታል ብለሽ ታምኛለሽ?
ወ/ሮ፡- ጥላሁን በህይወት እያለ ነው መጽሐፉ የተጀመረው፡፡ ከትውልዱ አንስቶ ትዳሩ ደረጃ እስኪገባ ድረስ ራሱ የተረከው ነገር ነው፡፡ እርግጥ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ያለው ሲጻፍ በጥልቀት ሊኼድበት ይገባ ነበር የሚለውን አስባለሁ፡፡ እንጅ በህይወቱ እያለ ለተጠየቀው ሁሉ ጥላሁን እሱ ያመነበትን መልስ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ እኔ ሁሌ እንደምለው ጥላሁን በእያንዳንዱ ሠው ህይወት ውስጥ የገባ ሠው ነው፡፡ ሁሌም ብትጽፈው አያልቅም፡፡ ይኼኛው መጽሐፍ ግን ሆነ ተብሎ ለተለየ አላማ የተጻፈ ነው፡፡ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የደራሲያን ማህበር በጥላሁን ዙሪያ መረጃ ያላችሁ ስጡን ሲል ነበር፡፡ ለምን ያኔ ሳምሶን የአባቴ ማስታወሻ አለ ብሎ አልመጣም፡፡ ‹‹በህይወት እያለሁ እንዳይወጣብኝ›› ብሏል አይደል የሚሉት፡ ፡ ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ከሞተ በኋላ ለደራሲያን ማህበር መረጃውን አልሠጡም፡፡

ቁምነገር፡- በመጨረሻ ከጥላሁን ገሠሠ አደባባይ ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ?
ወ/ሮ፡- የአደባባዩ ጉዳይ ሁሉም የሚያነሳውም ነገር ነው፡፡ በመንገዱ ስራ ምክንያት ነው እንደዚያ የሆነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ከኢንጅነር ፈቃደ ሃይሌ ጋር ተገናኝተን ተነጋግረናል፡፡ ሌላ ቦታ፣ የማይነካ ቦታ ላይ አደባባይ ለመሰየም ታስቧል፡ ፡ ሐውልቱን ለማቆም ከቀራጺያን ጋር መነጋገር ጀምረን ሁሉ ነበር፡፡ አሁን ተለዋጭ አደባባይ ለማግኘት በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡
ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

The post አነጋጋሪው የጥላሁን ገሰሰ መጽሐፍና የባለቤቱ ሮማን በዙ ምላሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ድምጻዊት ራሔል ዮሐንስ

$
0
0

አንጋፋዋ ድምፃዊ ራሔል ዮሐንስን በሃበሻ ልብስ ደምቃና አምራ ነበር ያገኘኋት- ባለፈው ረቡዕ ምሽት፡፡ በተንጣለለው ግቢዋ ጋራዥ ቤት ውስጥ ሽንጣም ኒሳን መኪናዋ ቆሟል:: ግራውንድ ፕላስ ዋን መኖርያ ቤቷ በአካባቢው ካሉ መኖሪያቤቶች እጅግ ማራኪና ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ ሳሎን ቤት ስገባ ትልቅ ድግስ የተዘጋጀ ይመስል ነበር፡፡ ጥሬ ስጋው ጠጁ፣ ጠላው ተደርድሮ ነው የደረስኩት፡፡ ራሔል እንደነገረችኝ ማክሰኞ ዕለት ቤቷ ማህበር ነበር፡፡ የስድስት ልጆች እናት ብትሆንም አሁን ልጆችዋ አብረዋት የሉም – በአሜሪካና በካናዳ ነው የሚኖሩት፡፡ እሷ ከዘመድ ልጆች ጋር ትኖራለች፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደሙዚቃ ሙያ ከገባችው ራሔል ዮሐንስ ጋር በህይወቷና በሙያዋ ዙሪያ ያላወጋነው ነገር የለም፡፡ በቤተመንግስት አጉራሽ እንደነበረች፣ በጊዮንና በሂልተን ሆቴል በዋይን ገርልነት መሥራቷን፣ አንዳንዴ ዘፈኗን በእንግሊዝኛ እንደኮሜዲ ታቀርብ እንደነበረ ወዘተ— ነግራኛለች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር ስላላት ማህበር እንድትነግረኝ በመጠየቅ ነው ወደ ጭውውታችንን የገባነው፡፡
ድምጻዊት ራሔል ዮሐንስ
ማህበሩ የጓደኞች ነው የቤተሰብ?

የት/ቤት ጓደኞቼም የቤተሰብም አለኝ፡፡ ከ40 ዓመት በፊት የተጀመረ ነው፡፡ አንዳንድ ጓደኞቼ፣ እህቶቼ ቢያልፉም እስከዛሬ ይሄው ማህበሩን እንጠጣለን፡፡ ዛሬ አንቺም ወደ ቤቴ የመጣሽው የመድሃኒያለም ማህበር ትናንት አውጥቼ ነው፡፡ በጣም የተለየ ፍቅር አለን፡፡
የትምህርት ቤት ጓደኞችሽ—የት ነው የተማርሽው?
የቄስ ትምህርት አባታችን አስተማሪ በቤታችን ቀጥረው ነው ያስተማሩን፡፡ ከ1ኛ- 8ኛ ክፍል ደግሞ አስፋው ወሰን ት/ቤት ነው የተማርኩት፡፡ ከትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር በ21 እና በ27 ማህበር አለን፤ ማህበር ሲኖር በየቤታችን አዝማሪ ይቆማል፤ ማስንቆ የሚጫወት፡፡ ወንጂና ናዝሬትም እህቶቼ አሉ፤እዛም እየሄድን እንዝናናለን፡፡ እረ እንደው ተይኝ አልኩሽ —- የተንፈላሰሰ ዘመን ነበር፡፡ በማህበራችሁ ቀን የሚጫወቱት አዝማሪዎቹ የሚታወቁ ነበሩ?
አዎ፡፡ እነ ወረታው፣ ባይረሳው—- እንዴት ቆንጆ ድምፅ አላቸው መሠለሽ፡፡ እነሱ ወደ ቤታችን ሲመጡ ታዲያ ሁሉም ግጥም ሰጪ ነው፤ ሁሉም ተቀባይ ነው፡፡ ቤትም ባይመታም:: ማሲንቆዋቸውን ይዘው ይመጣሉ፤ ጨዋታው ሌላ ነው አልኩሽ፡፡ ደሞዝ እኮ የላቸውም ግን በየወሩ ፅዋ የገባበትን ቤት ስለሚያውቁ ማህበሩ በሚወጣበት ቤት ይመጣሉ፡፡ መጀመሪያ ፀሎት ይደረግና ምሳ ይበላል፣ ከምሳ በኋላ የንስሃ አባቶቻችን ያሳርጋሉ፡፡ ከዛ በኋላ አሸሸ ገዳሜ ነው የእኔ እናት፡፡
ግጥም ከመስጠት ወደ ዘፋኝነት ገባሽ ማለት ነው?
ያን ጊዜ ዘፋኝነትን አልሜው አላውቅም ነበር፡፡ ድምፃዊ ሰይፉ ዮሐንስ የሚባል ወንድም ነበረኝ፡፡ ወላጅ አባታችን ዘፋኝ ሆነ መባልን ሲሰሙ የሞተ ያህል ነው ያለቀሱት:: አለማወቅ እኮ ነው— ማን ያውቀዋል ይሄንን:: አባቴ በጣም አዘኑ…የወንድሜን መታመም ሲሰሙ ግን ድንጋጤአቸው ባሰ፡፡ በጣም በጣም ደግ ልጁ ነበረ፡፡ እርሱም ሞተ፤ አባቴ በጣም ተፀፀቱ — ምን ታደርጊዋለሽ? አለማወቅ ይጎዳል፡፡ ወንድሜ በሞተ በዓመቱ ነው አባታችን የሞቱት፤ በእርሱ ሃዘን (እንባ) ወንድሜ ከሞተ ከአስር ዓመት በኋላ ነው ሙዚቃ የጀመርኩት፡፡
አባቴ ዘፈን አይወዱም ነበር፡፡ ግን በገና ነበራቸው፤ የቅዳም ሱር እለት በገናቸውን አውጥተው ሲደረድሩ ፤የገና ዕለት ጌታን እያመሰገኑ ሲጫወቱ የድምፃቸው ማማር ልዩ ነው —- እናቴም ጥጥ ስትፈትል እያንጎራጎረች ነበር፡፡ ‹‹… ባለድሪ›› የሚለውን ዘፈን ከእርስዋ ነው የወሰድኩት፡፡ ‹‹… ገዳማይ —- ገዳማይ —ገዳማይ›› እያለች ታንጎራጉራለች:: የእናቴን ድምፅ ወንበር ስር ተደብቀን ወይም ግድግዳ ተከልለን ነው የምንሰማት፡፡ እማዬ ድምፅዋ በጣም ነበር የሚያምርው፡፡ አሁን በህይወት የለችም፡፡
እናትሽ የሙዚቃ ስራ ስትጀምሪ በህይወት ነበሩ?
አዎ! ድምፄን የሞረድኩበትን ‹‹አንተ ባለድሪ” የሚል ዘፈን እናቴ ትወደው ነበር፡፡ በአባትዋ ጎንደሬ ስለሆነች ጨዋታው ይስባታል:: የመጀመሪያ የካሴት ስራዬንም እናቴ እንዴት ትወደው ነበር መሰለሽ፡፡
ከዘፈን በፊት ምን ነበር የምትሰሪው?
“ፎር ሽፕ ትራቭል ኤጀንት” የሚባል ድርጅት ውስጥ ትኬት ኤጀንት ሆኜ እሰራ ነበር፡፡ ራስ ሆቴል ዴስክ ነበረችኝ፡፡ እዛ እንግዳ ይመጣል፡፡ እንግዶችን ተቀብሎ
የሚፈልጉትን መረጃ መስጠት፣ መኪና ማከራይት፣ ፎርም ማስሞላት፣ ዲፖዚት መቀበል ነበር ሥራዬ፡፡ ድርጅቱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተዘጋ፡፡ በወቅቱ የልጆች እናት፤ የቤተሰብ ሃላፊ ነበርኩ—‹‹ምን ሆኜ ነው የምኖረው..›› ብዬ ሳስብ፣ ጓደኞቼ “እነ በቀለች ክትፎ ከትፈው እየሸጡ ይኖሩ የለ፡፡ ክትፎ ክተፊ›› አሉኝ፡፡
ክትፎ ግን ሞያ ይጠይቃል አይደል–
ሞያ ለእኔ!! እኔ እናትሽ እኮ አንቱ የተባልኩ ባለሞያ ነኝ:: የወላጆቼ ቤት እዚህ ካዛንቺዝ ነበር፡፡ እዛው ጊቢ ውስጥ አንድ ክፍል ተሰጥቶኝ እኖር ነበር፡፡ ክትፎ ቤት ከፈትኩ:: አንድ ቀን ታዲያ ሰዎች ክትፎ ሊበሉ ቀብረር ያለውን ድምፃዊ ከተማ ይፍሩን ይዘውት መጡ፡፡ ያን ቀን አንድ ዕቃ ጠፍቶብኝ ተበሳጭቼ ነበር:: ይሄን ያህል የተበሳጨሽው ምን ቢጠፋብሽ ነው?

አንድ ሙሉ ካርቶን ውስኪ፡፡ አንድ ዘመድ ነበር— አውጥቶ ሽጦብኝ ብስጭት ብዬ ነበር፡፡ አልቅሼ ፊቴን ስጠራርገው የልጅነት መልክ ጥሩ ነው፣ ወለል ‹‹ፏ›› ነው የምለው፡፡ እነ ከተማ ክትፎውን እየበሉ ይጨዋወታሉ:: ከዚያ ከተማ መዝፈን ማንጎራጎር ጀመረ፡፡ እኔም ከጎኑ ቁጭ ብዬ አንጎራጉራለሁ:: ከዛ ከተማ ድንገት ብድግ ብሎ ‹‹እዚህ ቤት ሁለተኛ ክትፎ እንዳይከተፍ›› አለ፡፡
‹‹ምነው አመምዎት?›› አልኩኝ ያልተስማማቸው፣ አለርጂ የሆነባቸው መስሎኝ፡፡
‹‹ይሄን ቆንጆ ድምፅ ይዘሽ በምን ምክንያት ነው የማትዘፍኝው?›› አሉ፡፡
‹‹ድምፅ አለኝ እንዴ?›› አልኩኝ ለራሴ
‹‹ምንድን ነው የምትጠጭው?›› አሉኝ፡፡
እኔ ግን እንኳን በዛ ጊዜ ዛሬም መጠጥ የሚባል አልቀምስም፡፡
‹‹እረ እኔ ምንም አልፈልግም… አልጠጣም›› አልኳቸው፡፡ ሲያስጨንቁኝ
‹‹ኮካ ይሻለኛል›› አልኩኝ፡፡ ያን ጊዜ ግሩም ነበር ኮካኮላ- –ከኮካኮላው ውስጥ ሳላይ ውስኪ ጨምረውብኝ….እንደ ውሃ ጭልጥ አደረኩት፡፡ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ደስ አለኝ… ‹‹እንዴ ምን ሆኜ ነው ደስ ያለኝ…ምን አገኘሁ›› እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ለካ ለብታ ማለት ይሄ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ሰንጥቄ ሰንጥቄ ለቀቅኩት ዘፈኑን፡፡
የማንን ዘፈን እንደዘፈንሽ ታስታውሺያለሽ?
ከተማ እኔ ቤት የተጫወተውን ባቲ፣ ትዝታን፣ ተይ ማነሽን ተጫወትኩ — ከአሁን በኋላ ‹‹አምቦ ውሃሽን አቀዝቅዥ፣ ቆንጆ ውስኪ አቅርቢ — እኛ እንግዳ ይዘን እንመጣለን —- አበቃ ክትፎ ቤት›› አሉኝ፡፡ ከዛ ምን አለፋሽ — ከአለም አንደኛ ሆንኩኝ፡፡
በማግስቱ የምሽት ክበብ ተጀመረ?
መጀመሩስ ተጀመረ፡፡ መጥተው “በይ ተጫወቺ” ሲሉኝ ከየት ይምጣ፡፡ ያቺ የለችማ የተለመደችው ብረት ለበስ…. ታዲያ ወሰድ አታደርጊም ነበር—
እኔ ምኑን አውቄው—-በፊትም እኮ ወኔዬን ያመጣው ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ በኋላ እኮ ነው የነገሩኝ፡፡ ግን እየለመድኩ መጣሁ —- ሌላ ሆነ እንግዳው፣ ደንበኞቼ በዙ—የብር አቆጣጠሬን ብታይ አስቅሻለሁ፡፡ እንግዶቼን ሸኝቼ ስጨራርስ—-.ብር እቆጥራለሁ፡፡ ‹‹..አንድ.. ሁለት…ሶስት..አራት.. እባካችሁ ተኙ እናንተ ልጆች— መሸ እኮ– ነገ ትምህርት ቤት ወየውላችሁ..›› ብሩ ከእጄ ይንጠባጠባል፡፡
የሽልማቱ ብር ነው?
ሽልማቱ ተይኝ ይረግፍ ጀመር፡፡ ማን አውቆት ቁጥሩን — -ከትራሴ ስር አድርጌው ነው የማድር — ልጆቼ በጠዋት ሲነሱ —-ገንዘቡን ለቃቅመው እየሳቁ ‹‹..አንቺን ብሎ ቆጣሪ›› ብለው ይሰጡኛል፡፡
መኖሪያሽም የስራ ቦታሽም አንድ ቦታ ነበር ማለት ነው? መጀመርያ አዎ፡፡ በኋላ ግን ሃብት መጣ — ካሳንቺዝ እርሻ ሚኒስቴር አካባቢ ቤት ገዛሁ፡፡ ዛሬ ንብ ባንክ ሆኗል:: ታሪኩ ብዙ ነው ባክሽ…በመሃል ታመምኩ፡፡ ሶስት ወር ሙሉ እጅና እና እግሬ ተይዞ ፓላራይዝድ ሆኜ ተኛሁ:: የቤት ስልክ ጮኸና ጨዋታችንን አቋረጠን፡፡ ከካናዳ ወንድ ልጅዋ ነበር የደወለው) ከዚያልሽ — በጠበሉም በምኑንም ብዬ ተሻለኝ፡፡

በመሃል ስራሽን አቁመሽ ነበር?

አዎ ሙሉውን አቁሜ ቤቱን አከራየሁት፡፡ መጨረሻ ላይ ያከራየኋት ሴት እገዛዋለሁ ብላ ስሙን አዛውሬላት ነበረ– -በቼክ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ሰጥታኝ ነበር— ከዚያ እዛ ዱባይ የሚባል አገር ተነስታ ሄደች፡፡ ቤቱ በሃራጅ ተሸጠና ለእኔ ስድስት መቶ ሺ ብር ተሰጠኝ፡፡ ከባንክ በቀኝ እናበግራእጄሶስትመቶሺ፣ሶስትመቶሺብርይዤ ስወጣ በጣም ከበደኝ:: ‹‹ፈጣሪዬ በአቅሜ ነው የሰጠኸኝ.. ያንን አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር..አግኝቼ ቢሆን እንዴት ነበር የምይዘው..ተመስገን ጌታዬ ይሄንኑ በረከቱን ረድዔቱን ስጠው›› ብዬ— (በድጋሚ የቤት ስልክ ጮኸ:: አሁንም ከካናዳ ሌላኛዋ ልጅዋ ደወሎ፤ ሰላምታ ሰጥታ ቆይቶ እንዲደውል ነግራው ዘጋች)

የካሳንቺሱ ስራ ቆመ ማለት ነው —

አንድ ዓመት ይህል ቁጪ አልኩኝ ያለ ስራ፡፡ ከዛም ለምንድን ነው ቁጪ የምትይው ብሎ ቁምላቸው የሚባል የፋሲካ ባለቤት ተቆጣኝ፡፡ ከዛ ኦርጋኔንና የራሴን ባንድ ይዤ እዚያ ሄድኩኝ፡፡ አብረውኝ የሚጫወቱትን ሳክሲፎኒስትና ኦርጋኒስት ይዤ ማለት ነው፡፡ ‹‹ራሄል እዚህ ገብታለች›› ሲባል…ተይኝ አልኩሽ — ሰው እንደጉድ ይጎርፍ ጀመር፡፡

ደንበኞችሽ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለሥልጣናትና ባለሃብት— ነበሩ ይባላል፡፡ እንደውም አንዴ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ቃለ መጠይቅ ስናደርግላቸው—.የአንቺን የምሽት ክበብ በጣም ይወዱት እንደነበር ነግረውናል — እጣ ክፍሌም እንደዛ ነገር ነው፡፡ የአዲስ አበባ መሳፍንት መኳንት፣ የራስና የደጃዝማች ልጆች፣ ማን ይቀራል…እገሌ ከእገሌ አልልሽም፡፡ የጨዋ ልጆች ይመጡ ነበር፡፡ ስርዓት ለሌለው እንኳን ስርዓት አስተምሬ ነው የምለከው፡፡ በጃንሆይም ጊዜ ከቤተመንግስት ሰዎች ጋር ነበር ቅርበቴ፡፡ በቃ ይወዱኛል፡፡ ዘፋኝ ሳልሆንም እኮ ነው፡፡

እንዴት ወደ ቤተመንግስት ለመቅረብ ቻልሽ?

ያኔ ቤተመንግስት ቱሪስቶች ሲመጡ አጉራሽ ይፈለግ ነበር:: ቤተ-መንግስት ሄደን እንጀራ እናጎርሳለን፡፡ የቤተመንግስት እንጀራ እንደዚህ ሶፍት ነጭ ነበረ(በእጅዋ የያዘችውን ሶፍት እያሳየችኝ) ፈረንጆቹ ናፕኪን እየመሰላቸው እንጀራውን እንደ ሶፍት ይጠቀሙበታል፡፡ ቤተመንግስት ውስጥ በጣም ስለተቸገሩ— እስኪ ቆነጃጅትን ፈልጉ ተባለ፡፡ አንድ እኔን በጣም የሚያውቅ ሰው ነበረ…ነፍሱን ይማርና ኮማንደር እስክንድር ‹‹ዋይን ገርል ራሄልን ጥሩ›› አለ፡፡
ዋይን ገርል ነበርሽ እንዴ?
አዎ፡፡ ዋይን ስፔሻሊስት ነኝ፡፡
እንዴት— የት ተማርሽው?
ታሪኬ ብዙ ነው አላልኩሽም፡፡
እስቲ አውጊኛ —-
ዛሬ እንግዲህ አብረን ማደራችን ነው፡፡
ግዴለም አጫውቺኝ —-
ስሚ—-.ድሮ ሁለቱን ልጆቼን እንደወለድኩ ባሌን ፈታሁ ከዛ ‹‹ራስ ሆቴል ኮርስ መውሰድ አለብኝ›› ብዬ አሰብኩና ለሶስት ወር ያህል የገበታ ዝግጅት (tabel set up) የእንግዳ መስተንግዶ አሰጣጥ (how to serve the guest) ሰለጠንኩ፡፡ እንግሊዝኛውም ሌላ ነው— እንደ አሜሪካን ነው የምናወራው:: የእኛ ትምህርት ቤት እንደአሁኑ ቀላል መስሎሻል—ከሶስተኛ ክፍል በኋላ በእንግሊዝኛ ነው የምታወሪው፡፡ በተለይ በእንግሊዝኛ አስተማሪ በኩል- —እኛ የተማርንበት ዘመን ሌላ ነበር፡፡ በጣም ቆንጆ ትምህርት ቤት ነው የተማርነው ግን አልሰራንበትም፡፡ እኔን ያልሽ እንደሆነ ግን በጣም የገባኝ አራዳ ስለነበርኩ በወቅቱ ሰርቼበታለሁ፡፡ እና የ‹‹ዋይን ገርል›› ኮርስ ስጨርስ ምርጫ ተሰጠኝና ጊዮንን መረጥኩ፡፡ ያኔ የነበሩት ሆቴሎች በጣም ትንሽ ናቸው፡፡ ዋቢ ሸበሌ ገና እየተጠናቀቀ ነበር:: በተረፈ ጊዮን ሆቴልና ኢትዮጵያ ሆቴል ናቸው፡፡ እኔ ጊዮን ሆቴል ገባሁ፡፡

በአስተናጋጅነት ነው?

ስለ በቬሬጅ (መጠጥ) ነበር ያጠናሁት፡፡ ስለ ኮክቴል አሰራር አውቃለሁ — አንድ መጠጥ ከአንድ መጠጥ ጋር ኮክቴል ይደረጋል፡፡ አፕሬቲቩ፣ ዳይጄስቲቩ—-የተለያዩ የዋይን ዓይነቶች አሉ— ሬድ፣ ዋይት፣ ሮዜ፣ ድራይ፣ስዊት፣ ሚዲየም… ከምን ከምን ምግብ ጋር እንደሚወሰዱ አውቃለሁ፡፡ ካስተመሮቹ በጣም ይደነቁ ነበር፡፡ የት ነው የተማርሽው፤ የት አወቅሽው ይሉኛል፡፡

ስንት ዓመት ሰራሽ በዋይን ገርልነት?

አራት ዓመት ከስድስት ወር ነው የሰራሁት፡፡ ስራውን ብወደውም እየሰለቸኝ መጣ፡፡ አንድ ቀን አኩርፌ ተቀምጬ አንድ ደንበኛችን አዩኝ፡፡ የአርጀንቲና አምባሳደር ነበሩ፡፡ ስሚ—-ብዙ ካስተመሮቼ የሚያውቁኝ በጣም ሳቂታ፣ ደስተኛ፣ ተጫዋች መሆኔን ነው፡፡ የሚያኮርፍም ሰው አልወድም፡፡ ኩርፊያም አልወድም፡፡ ስለዚህ ‹‹ምነው ዛሬ አልሳቅሽም?›› አሉኝ፡፡
‹‹ደከመኝ የሌሊት ስራ ደከመኝ›› አልኳቸው፡፡
“So?” አሉኝ፡፡
‹‹በቃ ሰለቸኝ አስጠላኝ…›› መለስኩላቸው
“Why don’t you come to my embassy, I am go- ing to move by next week.” (ለምን ወደ እኔ ኤምባሲ አትመጪም? በሚቀጥለው ሳምንት እገባለሁ)
እሽ ብዬ ሄድኩ፡፡ እቃ ግዢ ክፍል (ፐርቼዘር) አደረጉኝ:: ከዚያ የጣሊያን ክልስ ፀሃፊና አራት ዘበኞች ቀጠርኩለት፡፡ ሁለት የማታ፣ ሁለት የቀን፡፡ የዘበኞች
ዩኒፎርም(የቤተመንግስት ልብስ ሰፊ ነበር) እሱ ጋ ሄጄ አሰፋሁ፣ ባርኔጣቸውን አሰራሁ:: ሁለት ሾፌሮችም ቀጠርኩ፡፡ የኤምባሲ ሾፌሮች የሚለብሱትን አውቃለሁ:: ወጥ ቤትም ቀጠርኩ—የፅዳት ባለሙያ (ሃውስ ኪፐር) እንዲሁም አትክልተኛ ሁሉ ቀጠርኩ፡፡
ሥራ ብቻ ነው ወይስ ሌላም ግንኙነት ነበራችሁ? ኦኦ—ባለትዳር እኮ ነው፡፡ እኔ ስራውን ነው የፈለግሁት፡፡ (የቤቷ ስልክ ለሦስተኛ ጮኸ…)
እንግዲህ ቻይው—- ልጆቼ አሜሪካና ካናዳ ነው ኑሮዋቸው…ልክ ሲነጋ የኔን ድምፅ ሳይሰሙ ቀናቸውን በስመዓብ አይሉም…(ከአሜሪካ ሴት ልጅዋ ነበረች የደወለችው)—ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የአምባሳደሩ ሚስት መጣች፡፡ ይሄኔ ችግር ተፈጠረ፡፡
‹‹ምንድን ነች?›› ብላ አፈጠጠች፡፡
‹‹ይሄን ሁሉ የሰራችው እስዋ ናት›› አሏት፡፡
‹‹ሰዎችን ከመቅጠር ጀምሮ..ፈረስ ቤቱን፣ አበባውን … የቤቱን ቀለም..ይሄን ሁሉ የሰራች እስዋ ናት›› በማለት አስረዷት፡፡ በጣም ሃርድ ወርከር ናት…ብላ ብታደንቀኝም ከጥቂት ጊዜ በኋላ አልተመቸኋትም መሰለኝ—ደሞዜም በጣም ብዙ ነበር፡፡

ምን ያህል ይደርሳል?
2ሺ ብር—
ይሄ ሁሉ ከሙዚቃው በፊት ነው አይደል–

ሙዚቃ ባልታሰበበት ጊዜ እኮ ነው የማወራሽ፡፡ እዚህና እዚያ አስረገጥሺኝ እኮ፡፡ እንዳልኩሽ የሰውየው ሚስት አልተመቸኋትም፡፡ ስርዓት አለኝ—ሰው አከብራለሁ— ሰው ስነሥርዓት ከሌለው አልወድም—ወዲያውኑ ነው የማስወግደው:: ሁለተኛ ማየት አልፈልግም፡፡ እናም‹‹.. በቃ ወደ ውጪ መሄዴ ነው ….›› ብዬ ስነግረው አምባሳደሩ በጣም ደነገጠ፣ ተጨነቀ፡፡ እኔ ግን ትዕግስቴና ፍላጎቴ ተዘግቶ ስለነበር ትቼው ወጣሁ፡፡
ይሄን ሁሉ ያስታወሰን እኮ ለአጉራሽነት ወደቤተመንግስት መግባትሽ ነው—-.የአጉራሽነቱስ ጉዳይ
— አጉራሽነትማ—-ጃንሆይ ጥሩ ጥሩ ልጆችን አምጡ ብለው አዘዙ:: ‹‹እንደውም ጊዮን ሆቴል ሁለት ዌይትረስ አሉ አምጡዋቸው›› ተባለ፡፡ ቤተመንግስት ገብተን ፈረንጆችን እናጎርስ ጀመር፡፡ ፈረንጆቹ..
“Oh my God. What is this? Is this napkin or what?…’” እያሉ ይወናበዱ ነበር፡፡ ስናጎርሳቸው ደስ እንዲላቸው ብለን ፊታቸው እጃችንን እንታጠብ ነበር—-ከዛ ስናጎርሳቸው ተደስተው ሊሞቱ፡፡

ቆንጆ ነሽ—-አድናቆት ምናምንስ አልነበረም?

“you have a beautiful smile, you Ethiopians are beautiful” ይላሉ (ውብ ፈገግታ አለሽ–እናንተ ኢትዮጵያውያን ውብ ናችሁ) —-ምን ልበልሽ— አድናቆት በአድናቆት ነው—-ልዕልቶቹም ያዩናል፡፡ የሆነ ዝግጅት ሲኖር በመካከላቸው ካናፒ እናዞራለን፡፡ ‹‹እንዴት ቆንጆ ናት›› ይሉኝ ነበር፡፡ የአልጋ ወራሽ ሚስት በጣም ያደንቁኝ ነበር፡፡ ልዕልት ተናኘ ወርቅ ነፍሳቸውን ይማረው፡፡ …አረ ተይኝ—አድናቆታቸው ራሱ ገንዘብ ነው፡፡ አክብሮታቸው…ሰላምታቸው…አመለካከታቸው.. ነገረ ስራቸው ሌላ ነበር፡፡

በነገስታቱ ተሸልመሽ ታውቂያለሽ?

እጅግ በጣም ብዙ ሽልማት እንጂ…የአንገት ወርቅ፣ የእጅ ወርቅ አምባር፣እንዲሁም ሰንጋ መግዣ ተብሎ 500 ብር ተሰጥቶኛል:: .የእኔ ልጅ—- ባሳለፍኩት ዕድሜ ቁጭ ማለትን አልወድም፣ የሰው እጅ መጠበቅን አልወድም፣ ስራ መስራት ያስደስተኛል፣ መጫወት መደሰት ቁምነገር መስራት—እጅግ ሰው እወዳለሁ.. ስራ አልንቅም፡፡ የሚገባኝን ነገር አውቃለሁ፡፡ የሰው ነገር አልነካም፡፡ ለዚህም ነው ያልነካሁት የስራ ዓይነት የለም የምልሽ—-.ቆይ ልቁጠርልሽ አርጀንቲና ኤምባሲ፣ ታንዛኒያ ኤምባሲ፣ ፊሊፕስ… ሾው ሩም ውስጥ ሁሉ እሰራ ነበር፡፡ የዋቢሸበሌ ፐርሶኔል አንዴ መብራት ሊገዙ መጥተው ‹‹ምን ልትሰሪ ያለ ፊልድሽ መጣሽ?›› ብለው ዋቢሸበሌ
ወሰዱኝ..እዚያ ስሰራ ደግሞ የሂልተን ሆቴል ..“ፉድና ቤቨሬጅ ማኔጀር” መጡ፣ የውጪ ዜጋ ዋናው የሂልተንን ሃላፊ ጭምር ይዘው፡፡

‹‹ምንድን ነው የምትበሉት?›› አልኳቸው፡፡

‹‹አዘናል›› አሉ፡፡ ያዘዙትን ጠየቅሁ – ስጋ፣ ዶሮ፣ አሳ ነበር ያዘዙት፡፡ ሁለት ዓይነት ወይን ማዘዝ አለባቸው፡፡ አንድ ቀይ ዋይን፣ አንድ ነጭ ዋይን አልኩኝ፡፡ አለበለዚያ ሁለቱንም የሚያባላ ሮዜ ዋይን..አልኩና ሄጄ ጠየቅኋቸው፡፡

‹‹ምንድን ነው የምትጠጡት? ምን ዓይነት ዋይን ላምጣላችሁ?›› አልኳቸው፡፡

‹‹የምንበላውን ካወቅሽ አንቺ ጠቁሚን ምን ይሻለናል?›› አሉኝ፡፡ ሞያዊ ትንታኔ ሰጠኋቸው፡፡ በጣም ተገረሙ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ባለሞያ አለ ብለው ተደንቀዋል፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ‹‹ፈቃድሽ ከሆነ..ሰኞ ጠዋት ሂልተን ሆቴል እንድትመጪ›› አሉኝ፡፡

‹‹የት ነው ሂልተን ሆቴል?›› ብዬ ጠየኳቸው፡፡
‹‹እዚህ እዚህ ቦታ….›› ብለው ነገሩኝ፡፡
‹‹እኔ የሆቴል ስራ ሰልችቶኛል..ሆቴል እንዳይሆን ስላቸው..›› ‹‹ኖኖ እንደዚህ አይባልም..ስራ እንደዚህ አይባልም እንድትመጪ..›› አሉኝ፡፡
ሂልተን ሆቴል ሄድኩኝ—“.አይዞሽ ሲደክምሽ ማረፊያ ክፍል እንሰጥሻለን” አሉኝ፡፡ “መቼሽ ቲፑ ሌላ ነው—-በጣም ቆንጆ ቦታ ነው፡፡ የተወሰነ ቦታ ነው የምትሰሪው” ብለው አግባቡኝ፡፡ አሒአ(አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል) የሚል እንዴት ያለ የሚያምር የአበሻ ቀሚስ ተሰራልኝ መሰለሽ —ላይት ብራውን እንደ ጎልዲሽ ዓይነት — አቤት መልክ—አቤት ቁመና…፡፡
ሂልተንስ ስንት ዓመት ሰራሽ?
ከአራት ዓመት በላይ ሰርቻለሁ፡፡

በዘፈኖችሽ ላይ ንጉሶችን ማነሳሳት ትወጂያለሽ —.የጣይቱ ጠጅ ነው…የምኒልክ እልፍኝ– ትያለሽ?
እኔ የሰርቶ አደር ልጅ ነኝ፡፡ ግን እነዚህ አብሬያቸው ያሳለፍኳቸው እንግዶች..ክብር ያላቸው፤ ለሰው ልጅ ጥሩ የሚመኙ፤ ደጎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው አንድ ነገር ይሰጠዋል…ሁሉን በፕሮግራም ነው የሚፈጥረው፡፡ እግዚአብሄር እኮ እኔን አድሎን ነው እንጂ—እኔ ማን ነኝ I am no body af- ter all. ከማንም አልበልጥም:: ሰው ስለምወድና ስለማከብር… አባቴ ሰርቶ አደርም ቢሆን አስተዳደጋችን እንዴት ሸጋ ነበር — ልጆቼንም በዛ መንገድ ነው ያሰደግኋቸው፡፡

ውጪ አገር ስራዎችሽን አቅርበሽ ታውቂያለሽ?

በፍጹም፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ አምባሰል የሚባል ሙዚቃ ቤት ዋሺንግተን ናይት ክለብ ነበረው፡፡ ለስድስት ወር ለመስራት ተስማምቼ ሄጄ —.ለአራት ወር ያህል ከሰራሁ በኋላ ኢትዮጵያኖች እርስ በእርስ ሊጋደሉ ሲሆን ስራውን ትቼ ወደ አገሬ መጣሁ፡፡ ብዙም እንደዚህ ዓይነት ቦታ አይመቸኝም—

የትዳርሽ ጉዳይስ—

ልጆቼን ብቻዬን ነው ያሳደግሁት.— ጠንካራ እናት ነኝ፡፡ .ባሎች ትንሽ አስቸጋሪዎች ነበሩ፡፡ ምን ይጎለኛል—ልጆቼን ለማሳደግ ብዬ ልውሰድም ቢሉ እሽ አልልም—.ይሄው ልጆቼን አሳደግሁኝ ዳርኩኝ–እግዚአብሄር ይመስገን፡፡

የዘመኑን ዘፈኖች ትሰሚያለሽ? እንዴት ነው ዘፈን ድሮ ቀረ ትያለሽ ወይስ —-

ድምፁ የወጣው አሁን ይመስለኛል፡፡ ወጣቶቹ ቆንጆ ቆንጆ ድምጽ አላቸው፡፡ ሲዲውን ስሰማው ጥሩ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምሰማው ወይ ስለ ሃገር፣ ስለ አንድ ታሪክ፣ ወይም ስለኢትዮጵያ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ታሪክዋ ሰፊ ነው፡፡ አንዳንዱን እያነሱ አንስቶ መስራቱ ጥሩ ነው፡፡ የፍቅር ነገር መቼም እንዳለ ነው አያረጅም፡፡ ፍቅር ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜ ግን ስለ ፍቅረኛ፣ ስለ ባል፣ ስለ ሚስት— ተጣላኝ ታረቀኝ አባረርከኝ…መለስከኝ… እንደዚህ ዓይነት በጣም ሲበዛ ጥሩ አይደለም፡፡ አንችዬ አርጅቼ ይሆን እንዴ? ግን አይደለም…ድሮም ይሄው ነው ስሜቴ…ሁሉም ይቅር እያልኩ አይደለም፡፡ በየመሃሉ ቁምነገር ቢገባበት ማለቴ ነው፡፡ እንጂ ድምፅማ የመጣው አሁን ነው፡፡
በድሮና በአሁን ዘፈኖች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ትያለሽ?

ምርጫቸውና የደረሱበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በአብዛኛው የፈረንጅ መዚቃ፤ የፈረንጅ ሲኒማ፤ የፈረንጅ ዘፋኞች የሚሆኑትን ነው የሚሆኑት፡፡ ከአሁኑ ዘፋኞች ቴዲ አፍሮን —- ጎንደር ብዙ የተጫወቱ ልጆች አሉ –ማዲንጎ እስከ ወንድሙ…ግሩም ናቸው:: ማዲንጎን ያየሽ እንደሆን የበላይን ታሪክ አስቀምጦታል— በደንብ — ታምር ነው መቼም፡፡ እኔማ ያሳዝነኛል ያንን ሲጫወት:: እነዚህ ቁም ነገር ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ባህል እኮ ተወርቶም አያልቅ፡፡ መጸሐፍም አይችለው፡፡ አስተማሪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እኛ እኮ ድሮ ትምህርት ቤት አሁን ማን ያስተምራል….እዚህም አገር አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እየታየ ነው፡፡ እኛ ድሮ በትምህርት ቤት ውስጥ ባንዲራ አውርደን ክፍል እንደገባን ፀሎት እናደርጋለን፤ ከፀሎት በኋላ የሚገባው አስተማሪያችን የግብረገብ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ነው ትምህርቱ የሚቀጥለው፡፡
ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ ናት ብል—-.አላፍርም፡፡ስለ ሃገሬ ተናግሬም አልጨርሰው፤አቅሜም አይችለው፡፡ አገራችን፣ ህዝባችን፣ አለባበሳችን፣ ምግባችን፣ አየሩ…በክረምቱ ሰዓት ክረምቱ የታወቀ ነው፤ በበጋው ሰዓት በጋው የታወቀ ነው፣ በበልግ ሰዓት በልጉ የታወቀ ነው፤ አለቀ፡፡ አየራችን ደግሞ ልዩ ነው፡፡ የምታኮራ አገር የሚያኮራ ህዝብ ነው ያለን..ይሄ ራሱ ቢዘፈንለት አይበቃም፡፡

ስንት ካሴት በነጠላ እና በጋራ ሰራሽ..

ወደ 12 ካሴቶችን ሰርቻለሁ፡፡ “ምኒልክ” የሚለው ዘፈኔ ዜማውን የሰራሁት እኔ ነኝ፡፡ የሁሉም ካሴቶቼ ግጥም ድርሰት የይልማ ገብረ አብ ናቸው፡፡
የድምፅሽን ለዛ ስለሚያውቀው በይልማ መርጦ የሚሰጥሽ
አዋ፡፡ ይልማ በአንድ ወቅት አንድ ስራ ገጥሞት አንድ ካሴቴ ላይ ብቻ ሶስት ዘፈኖች የሌላ ሰው ነበሩ፡፡ ከይልማ ጋር ስንሰራ ግጥሞችን መክረንባቸውና ተነጋግረን ነው – ይሄ ይውጣ ይሄ ይግባ ብለን፡፡ አንድ ጊዜ ምን ሆነ…‹‹በደሳሳ ጎጆ ቁጭ ብዬ ብቻዬን ሳለቅስ..›› ምናምን የሚል ግጥም ..መጣልኝ…እኔ እንደዚህ አይነት ነገር …ምንድን ነው በፍፁም አልዘፍንም አልኳቸው፡፡ ችግርም የለብኝ..ይቅርታ አድርጉልኝ የእኔ ስሜት ለእንደዚህ ዓይነት ነገር አይሰራም አልኳቸው፡፡ በጣም ሳቁ..ጭንቅ አልወድም ሌግዠሪ ነገር ነው የምወደው…ዝም ያለ ቆፍጠን ያለ…ለሰውም ቀለል ሲል.. ነው፡፡ የእኔን ለቅሶና ሃዘን ህዝብን ስማልኝ ማለት ምንድን ነው:: የሆነ ድባብ እኮ ይፈጥራል፡፡ ይቅርታ እንግዲህ እኔ እንደዚህ አይነት ታይፕ የለኝም፡፡ ከተሸመ አሰግድ፤ ጋሽ ባህሩ፣ ጋሽ ይርጋ፣ ከተማ መኮንን፣ ዳምጠው…ኡፍ ለዛ አላቸው እኮ፡፡ my God!! የማይሰለቹ እኮ ናቸው፡፡ ስሚ የዛን ዘመን ዘፋኞች..እነ ወረታው… የወረታው ድምፅ እኮ..ራሱ ጊታር ነው፤ ራሱ ሳክስፎን ነው፤ራሱ ቤዝ ጊታር ነው፤ በጣም ጎልደን ድምፅ እኮ ነው ያለው:: ከብዙዎች ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ልረሳ ነው እንዴ..እረ አንቺ ልጅ ይሄ ነገር ያሰጋል- — እርጅና መጣ መሰለኝ
ዕድሜሽ ግን ስንት ሆነ?
63 ዓመቴን ባለፈው የፋሲካ ዕለት አከበርኩ.—.ገና ልጅ እኮ ነኝ፡፡ መልካም ልደት፣ ረጅም ዕድሜ ተመኝተንልሻል፡፡ በሶስት መንግስታት ውስጥ በአርቲስትነት ትታወሻለሽ–
የደርግ ጊዜን ሳልነግርሽ፡፡ በምሽት ክበቤ ውስጥ ..እረ ገዳዬ፣ እንደው ዘራፌዋ፣ እንደ ኮሜዲ አድርጌ የምጫወተው ስራ ነበረኝ:: እረ ገዳዬ የሚለውን በእንግሊዝኛ እለው ነበር—

እስኪ አሁን በይልኝ–
Oh killer oh killer
The useless goat give birth to nine
She is died and her children
I love the killer I love the killer
As well as the shooter
When I feel tired I rest under the umberella of ጀግናዬ hair. ብታይ ሰው ይሄን እንደ ኮሜዲ ነው የሚሰማው—-. ትርጓሜው ደግሞ ትክክል ነው፡፡
እረ ገዳዬ አረ ገዳዬ
የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች
ልጆችዋም ያልቃሉ እስዋም ትሞታለች፡፡
ስሚ እኔ ጀግና እወዳለሁ፡፡ ዘፋኝ ባልሆን ወታደር ነበር የምሆነው፡፡ በጣም በጣም ነው ወታደር መሆን.. ለመዝመት አስበሽ አታውቂም ታዲያ–
አይ ልጄቼን ከወለድኩ በኋላ ..ሃላፊነቱም አለ..፡፡
የአሁኑ አልበምሽ..ከስንት ጊዜ በኋላ ወጣ?
ከ7 ዓመት በኋላ…ሰርቼው ቁጭ አድርጌው ነበር…ኮፒ ራይቱም አስጨናቂ ስለነበረ..ሰርቼ ቁጭ አደረኩት:: የምገዛ ሲጠፋ:: አቶ ቁምላቸው ገብረስላሴ የፋሲካ ባለቤት/ የሚሞ ባለቤት…የተፈጠረውን አጫወትኩት፡፡ ከፈቃደ ዋሬ የአምባሰል ሙዚቃ ቤት ባለቤት ጋር እንደ ወንድም ነው የሚተያዩት፡፡ ተነጋገሩና ይሄው ባለፈው ለሰው አፍ አበቁልኝ፡፡
ምን ያህል ገቢ አገኘሽበት ?
እሱን ተይው
ከአሁን በኋላስ ምን ታስቢያለሽ?
አገሬ ላይ ቁጪ ብዬ እግዚአብሄርን ማመስገን ነው… የምስጋና መዝሙር ነው ሃሳቤ፡፡ ደስተኛ ነኝ…እንምታይው ሁሉ ሙሉ ነው..ተመስገን ለእግዚአብሄር ምን ይሳነዋል፡፡ አይንሽን አሞሽ ነበር?
አዎ… ሼክ ሙሃመድ አሊ አሙዲ ናቸው ያሳከሙኝ… የምዘፍነው:: የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ እወዳቸዋለሁ::
(አዲስ አድማስ ጋዜጣ በ2013 ዓ.ም. ከአርቲስቷ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ)

The post ድምጻዊት ራሔል ዮሐንስ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ጆሲ ኢንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ጻፈ “ከግንቦት 30 ጀምሮ በእናንተ አስገዳጅነት ፕሮግራማችንን እናቋርጣለን”

$
0
0

jose in ze house1
ጆሲ እንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን በላከው ግልጽ ደብዳቤ በቴሌቪዥን ጣቢያው አስገዳጅነት ፕሮግራሙን ከግንቦት 30 ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ:: ሙሉ ደብዳቤውን ያንብቡት::

ጉዳዩ፡ፕሮግራም ስለማቋረጥ

ድርጅታችን ከጣቢያችሁ የአንድ ሰዓት የስርጭት ጊዜ በመውሰድ በ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላለፉት ሁለት ዓመታት “ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው ” የተሰኘ ፕሮግራም እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ፕሮግራሞቻችን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው፤ ትውልድን የሚያንጹና የሚያስተምሩ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በተመልካች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ለማግኘት የቻሉ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ቀደም ባለው ጊዜ በተፈቀደልን የአየር ሰዓት የሠራናቸውን ፕሮግራሞች ለማቅረብ የነበሩት ሁኔታዎች የተመቻቹ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን አየር ላይ እንዲውሉ ከላክናቸው ፕሮግራሞች አንዳንዶቹ በተፈቀደልን የአየር ሰዓትና ጊዜ እንዳይተላለፉ ተደርገዋል፡፡

ጆሲ መልቲሚዲያ የሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች የአየር ሰዓት ለመሸፈን ብቻ ተብለው የሚዘጋጁ ሳይሆን እያዝናኑ የሚያስተምሩ ኢትዮጽያዊ አንድነትን የሚያጠነክሩ ፤የትላንትን ታሪክ የሚያውሱና ትውልድ የሚቀርጹ፤ መረዳዳትንና መተጋገዝን የሚሰብኩ ናቸው ፡፡

በአብዘኛው የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ አገዛዝ መዳፍ ውስጥ በነበሩት ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የጣልያንን ወራሪ ጦር ያሸነፈችበት የአድዋ ድል 119ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በድሉ እንደሚኮራ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በያገባኛል ስሜት ደክመን የሠራነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮግራም በተፈቀደልን ቀንና የአየር ሰዓት እሁድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ሰአት እንዳይተላለፍ ተደረጎብናል ፡፡ይህ ያልተለመደ ነገር ሲከሰት ብናዝንም ቀደም ሲል የነበረንን መልካም የሥራ ግኑኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ወደፊትም እንደማይደገም በማመን ነገሩን በትዕግስት አልፈን አብረን ለመስራት ሞክረን ነበር፡፡

ይህ መፈጠሩ እያሳዘነን እያለ ሌላ ነገር ተከሰተ፡፡ ድርጅታችን በጣቢያቸሁ ፕሮግራም ማስተላለፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በሀይማኖታዊና በዘመን መለወጫ በዓላት ላይ በተለያየ ጊዜና ሙያ ሀገራቸውን ያገለገሉ ግን ደግሞ የተዘነጉ የሀገር ባለውለታዎችን መጠየቅና የተቻለውን ያህል ድጋፍ ማድረግ የተለመደ ነበር፡፡በእዚህም መሰረት የ2007 ዓ.ም የትንሣኤን በዓልን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀነው ፕሮግራም በቂና አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እንዳይተላለፍ ተደርጎብናል፡፡
jossy gebre
ፕሮግራማችን በተደጋጋሚ በተለመደው የአየር ሰዓት እንዳይተላለፍ መደረጉ እያሳዘነን እያለ ፤በየመን ፤በደቡብ አፍሪካ በተለይም በሊቢያ አይ.ኤስ የተባለው ፅንፈኛ ቡድን በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እንደ ኢትዮጵያዊ አዝነን ፤ቤተሰቦቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን በሞት ከተነጠቁ ሀዘንተኞች ጎን ሆነን ሀዘናችን ገልጸንና የሀዘናቸው ተካፋይ ሆነን ድጋፍም አድርገን በተጨማሪም በኢትዮጵያዊ አንድነት ፤በሀይማኖት እኩልነት ፤ተፈቃቅሮ ፤ተቻችሎና ተከባብሮ በመኖር፤ እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም ዜጎቻችንን ለእንግልትና ለሕልፈተ ሕይወት እየዳረገ ባለው ሕገ ወጥ ስደትና ሕገ ወጥ ደላሎች ዙሪያ ደክመን የሰራነው አስተማሪ ፕሮግራም ከጣቢያው በወሰድነው የአየር ሰዓት ላይ በተደጋጋሚ እንዳይተላለፍ መደረጉ ወደፊት አብሮ የመስራታችንን ነገር በጥርጣሬ እንድንመለከተው አድርጎናል ፡፡

ፕሮግራማችን በጣቢያችሁ ላይ መቅረብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለነበረን መልካም ግንኙነት ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ከላይ ከጠቀስናቸው ችግሮች በተጨማሪ ሌሎችም ምክንያቶች ቢኖሩም የስራ ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ስምምነት ለማድረግ ብንሞክርም አልተሳካም ፡፡ በእናንተ በኩል እየተከናወነ ያለው ያልተለመደ ተግባር የስራ ግኑኝነታችን እንዲቋረጥ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ እንደሆነ እንድናምን ስላደረገን በእኛም በኩል ይህንን በአጽንኦት እንድንመለከተው አስገድዶናል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ውል ተፈራርመን መስራት ሲገባን በድርጅታቸሁ አሰራር መሰረት ያለፈውን አንድ ዓመት ያለ ውል መስራታችን ይታወቃል ፡፡ ከአሁን በኋላ ግን በእዚህ አሰራር መቀጠል አንችልም ፡፡ ስለሆነም ከስፖንሰሮቻችን ጋር እስከ ሲዝን 4 የመጨረሻ 13ኛ ክፍል ድረስ የተደረገውን ውል ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከ ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ፕሮግራማችን በጣቢያቸሁ እንዲተላለፍ በእኛ በኩል አስቀድመን ዝግጅታችንን የጨረስን መሆናችንን እያሳወቅን፤ ከግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በጣቢያቸሁ ሲተላለፍ የነበረው “ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው” የተሰኘው ፕሮግራማችን በእናተው አስገዳጅነትና ተገቢ ያልሆነ አሰራር እንደምናቋርጥ አስቀድመን እናሳውቃለን ፡፡
ከሰላምታጋር

The post ጆሲ ኢንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ጻፈ “ከግንቦት 30 ጀምሮ በእናንተ አስገዳጅነት ፕሮግራማችንን እናቋርጣለን” appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ዝነኛው አርቲስት ሠይፈ አረአያ አረፈ

$
0
0

seyfe areaya
(ዘ-ሐበሻ) የቢትዮጵያ ትያትር እና ፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቁን ድርሻ ያበረከተው አንጋፋው አርቲስት ሠይፈ አረአያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች እንዳሉት ዝነኛው አርቲስት ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በመጨረሻም ይህችን ምድር ተሰናብቷታል:: ብራቸውም ነገ በጉርድ ሾላ ሳሊተምህረት ቤተክርቲያን ይፈፀማል።

በብሄራዊ ትያትር እና በሌሎችም ትያትር ቤቶች በማገልገል በርከታ የመድረክ ሥራዎችን ያቀረበው ሰይፈ አረአያ በተለያዩ የአማርኛ ፊልሞችም ላይም ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል::

ዘ-ሐበሻ በአርቲስቱ ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸች ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን::

The post ዝነኛው አርቲስት ሠይፈ አረአያ አረፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በዘፋኝነት; በሙዚቃ አቀናባሪነትና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት የሚታወቁት ታዋቂው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ::

በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ የትራንፔት ሙዚቃ ተጫዋች የነበሩትና “አደሉላ (የዘማች እናት)” በሚለው ታዋቂ ዘፈናቸው የሚታወቁት ሻምበል ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የወርቅ ሰራተኛ ነበሩ:: ሻምበሉ በአንድ ወቅት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደገለጹት ወርቅ ሰሪነት የተቀጠሩት በወቅቱ 15 ብር ነበር::

ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ዛሬ የተለዩት እኚሁ ባለጥምር የሙዚቃ ክህሎት ባለሙያ ሻምበል መኮንን ለሂሩት በቀለና ለተለያዩ የሙዚቃ ሰዎች ሙዚቃ አቀናብረዋል:: ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ዓለም ቆይታቸውም በርከት ያሉ ሥራዎችን ሰርተዋል:: ሃመልማል አባተ ከሃረር መጥታ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ሥራ እንድትሰራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ሲሆን የቴዲ አፍሮ አባት አቶ ካሳሁን ገርማሞ የቴዲ አፍሮን እናት ባገባ ጊዜ ሚዜም ነበሩ::

የእኚሁ ታዋቂ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በኖሩበት ኮልፌ አካባቢ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ነገ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል::

ቭዲዮውን ይመልከቱ::

shambel Mekonen Mersha

The post ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው

$
0
0

teddy afro and ameslet
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሆስፒታሎችን ንፁህና ፅዱ /Clean and save Hospital- CASH/ በማድረግ
ለታካሚዎች፤ለጤና ባለሙያዎችና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል የጤና ተቋማትን ምቹ የማድረግ ዘመቻ የጀመረ ሲሆን ለዚሁ ዘመቻ በሙያዋ ቅስቀሳ እንድታካሂድ የዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ባለቢኤት አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩን አምባሳደር አድርጎ መርጧል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህንን ትግበራ ከጀመረባቸው ሆስፒታሎች መሀከል አንዱ የሆነው በራስ ደስታ ሆስፒታል ሲሆን የአዲስ አባባ ጤና ቢሮ ከአብት አሶስየት ፕሮጀክት Abt project Associate-HSFR/HFG project ጋር በጥምረት የሚያካሂደው ዘመቻ ሆስፒታሎችን ንፅህና ፅዱ በማድረግ ምቹ አካባቢን የመፍጠር ዓላማ አለው፡፡ አዳዲስና ዘመናዊ ሆስፒታሎች እስከሚገነቡ ድረስ ያሉትን ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ንፁህና ምቹ በማድረግ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ የመስጠት እቅድም ተይዟል፡፡
ባለፈው ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላትና የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ሃላፊዎች እንዲሁም አርቲስት አምለሰት ሙጩ በተገኘችበት የጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡ ፡ የራስ ደስታ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ ጨመዳ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር አርቲስት አምለሰት ሙጩ በራስ ደስታ ሆስፒታል የተጀመረውን የህክምና አካባቢን ንፁህና ምቹ የማደርግ ዘመቻ ላይ ለመሳተፍና በአምባሳደርነት ሀላፊነቷን ለመወጣት ፍቃደኛ መሆኗን አድንቀው ሆስፒታሉ ንፅህና ምቹ መሆኑ ሆስፒታሉ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ አጋዥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ameleset
የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሉዑልሰገድ አገዘ እንደተናገሩት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ዳምጠው ቤተሰቦች፤የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ የጤና ቢሮ የስራ ሀላፊዎች፤ የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንትና የአስተዳደር ሰራተኞች በሚገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ አምለሰት አምባሳደር ሆና እንድትሰራ ሃላፊነቱ እንደሚሰጣትና ይኸውም ለህዝቡ በይፋ እንደሚገለፅ ተናግረዋል፡፡ አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩ በበኩሏ ይህንን ሀላሀፊነት ከፍ ባለ አክብሮት እንደምትቀበል ገልፃ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደየሆስፒታሎች ስትንቀሳቀስ ከንፅህና ጋር ተያያዞ ጉድለቶችን በማየቷ በዚሁ ዘመቻ ላይ የተቻላትን ያህል እንደምትሰራ ተናግራለች፡፡

አምለሰት ቀደም ሲል በአካባቢ ጥበቃ ላይ የራሷን እንቅስቃሴ ማድረጓና በውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ባላት ተሳትፎ ሳቢያ ለዚህ ሀላፊነት መመረጧ ታውቋል፡፡

ምንጭ – ቁምነገር መጽሔት ከአዲስ አበባ

The post የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

(አሁንም ስለአነጋጋሪው የጥላሁን መጽሐፍ) ሁለት ማንነት በአንድ ራስ –ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃው ንጉሥ

$
0
0

tilahun

ርዕስ፡ ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር
ጸሐፊ፡ ዘከሪያ መሐመድ

ሲሳይ ጫንያለው እንዳነበበው
ďżźďżź

የመጀመሪያ ስሜት እንደመንደርደሪያ “እንዲህ ካለ መራራ የሕይወት ገጽ ውስጥ ኮኮብ ሆኖ መፈጠር ፤ ንጉሥ ተብሎ መዘከር እንደምን ይቻላል?” የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬ ውስጥ ብቅ ያለው የጥላሁን ገሠሠን የሕይወት ታሪክና ምሥጢር የሚተርከውን የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ ነው፡፡ ከጨቅላ ዕድሜው አንስቶ የሐዘን አንቀልባ እንዳዘለ ሃምሳ አመታትን በኢትዮጵያ ኪነት ውስጥ በክብር ለኖረ ሰው 69 ዓመት ትንሽ ዕድሜ ነው፡፡ ኅልፈተ ሕይወቱ በሚዲያ ሲነገር አገር በዕንባ ታጥቧል፡፡ ያኔ እኔም እርሜን አውጥቻለሁ፡፡ ከስድስት ዓመታት በኋላ የጥላሁንን ሁለት የማንነት ገጾች በፍካሬ ለማሳየት የተጋውን የዘከሪያን መጽሀፍ ሳነብ ደግሞ በስኬቱ ተገርሜ በስቃዩ ታምሜያለሁ፡፡

ጋሽ ጥላሁን የምር አሳዝኖኛል፡፡

በገጾቹ ምን ይዟል?

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምስጢር” በዘከሪያ መሐመድ ተጽፎ ለንባብ
የበቃ አነጋጋሪ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ነው፡
፡ መጽሐፉ አቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና የተባሉ የጥላሁን ቅርብ የስጋ ዘመድ ከ1934 ጀምሮ ያሰፈሩትን የቤተሰብ ማስታወሻ ቀዳሚ የመረጃ ምንጩ አድርጓል፡፡ ጸሐፊው የትውልድ ሥፍራው ሶየማ ድረስ ተጉዞ የባለታሪኩን ዘመድ አዝማዶች ፣ አብሮ አደጎች እና ጎረቤቶች ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃዎቹን አጠናክሯል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እና የህትመት ሚዲያው ስለ ጋሽ ጥላሁን የዘገቡትን ፣ በሙዚቃው ንጉሥ ሕይወት ውስጥ የነበሩ ሌሎች ግለሰቦች የነገሩትን በመተንተንና በመፈከር በአራት ክፍሎች እና በሃያ ዘጠኝ ምዕራፎች የጥላሁንን ሕይወት ከልደቱ እስከ ኅልፈቱ ተርኳል፡፡

በአምስትምዕራፎችየተደራጀውና“መሠረት” የሚል ርዕስ የተሰጠው የመጀመሪያው ክፍል ከአቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና ዳራ ተነስቶ የጥላሁንን ልደት እና ቤተሰባዊ መሠረት የሚቃኝ ነው፡፡ ሁለተኛው ክፍል የጥላሁን የሙዚቃ አጀማመር ከኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ጋር በማስተሳሰር ሙያዊ እና ግለሰባዊ ሕይወቱ ተሰናስለው በአስራ ስድስት ምዕራፎች ቀርበውበታል፡፡ ሰፋ ያለውን ገጽ የሸፈነውም “የሕይወቱ ሕይወት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይኸው ክፍል ነው፡ ፡ ክፍል ሶስት በጥላሁን የመጨረሻ አልበም መጠሪያ የተሰየመ ነው ፤ አንዳንድ ነገሮች፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ጥላሁን ከግል ሕይወቱ ጋር የሚገናኙ ዜማዎች ፣ ስለሌሎች ድምጻውያን ያደነቀባቸውን ስሜቶች ፣ ስለድምጽ አጠቃቀሙና ብቃቱ ፣ ከመደበኛ መድረክ ውጪ ስለተጫወተባቸው አጋጣሚዎችና ስለግለሰባዊ ባህርይው የሚተርኩ አጫጭር ሁነቶችን የያዙ ሦስት ምዕራፎችን አካቷል፡፡ ክፍል አራት የሚተርከው የልጅነት ሕመሙ የፈጠረው ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበትን የፍቅር ሕይወቱን ነው፡፡ ከመጀመሪያ የልጅነት ባለቤቱ ወ/ሮ ፈለቀች ማሞ አንስቶ በመጨረሻው የሕይወቱ ምዕራፍ ላይ አብራው እስከነበረችው ወ/ሮ ሮማን በዙ ድረስ አስራ ስድስት ልጆች ያፈራባቸውን ሰባት የትዳር ሕይወቶች ይቃኛል (ከፈለቀች ማሞ እና ከብርሃኔ ዘለቀ ብቻ ነው ጥላሁን ልጅ ያላገኘው)፡፡

tilahun Gesese
ደራሲው የጥላሁንን ሕይወት እንዴት ቀረበው የሕይወት ታሪክ እጅግ ጥንታዊ መሠረት አላቸው ከሚባሉ የስነጽሁፍ ዘሮች አንዱ ነው፡፡ በይዘቱ ኢ-ልቦለዳዊ ይሁን እንጂ የባለታሪኩን ሕይወት በመልሶ ፈጠራ በውብ ቃላት እየሳለ ከትክክለኛው የታሪክ እውነት ጋር በማይቃረን መልኩ አቀራረቡን ልቦለዳዊ ሊያደርግ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ግን በባለታሪኩ የሕይወት ታሪክ አካሄድ እና በደራሲው ምርጫ የሚወሰን ነው፡ ፡ በዘመናዊ የሕይወት ታሪክ አጻጻፍ ውስጥ ደራሲው በአቀራረቡ ስነልቦናዊ ፣ ምግባራዊ እና ስነውበታዊ አካሄዶችን ሊያጤን እንደሚገባ ፖልሙራይን የመሰሉ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ፡ ፡ ባለታሪኩን የተመለከቱ ታሪካዊ መረጃዎችን በቅደም ተከተል መደርደር ብቻ የሁነቶችን ቢጋር እንጂ የግለሰቡን ሕይወት አያሳዩም፡፡ ስለዚህ ደራሲው አስፈላጊ የሚላቸውን መረጃዎች ከሰበሰበ በኋላ ጥልቅ የሆነ ስነልቦናዊ ፍተሻ በማድረግ መረጃዎቹን እያዛመደ በመተንተን እና በመተርጎም የባለታሪኩን ሰብዕና መገንባት ይጠበቅበታል፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥ ዘመናዊ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊ የሚጋፈጠው ምግባራዊ ፈተና አለ፡፡ የተለያዩ የስነልቦና ንድፈ ሀሳቦችን ተግባራዊ አድርጎ በትርጓሜ ያገኘውን እውነት ሁሉ እንዲታተም ያደርግ ይሆን? ምን ያህሉን አውጥቶስ ምን ያህሉን ይተወው? እነዚህ ጥያቄዎች ከ18ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ በሕይወት ታሪክ ጥናት ውስጥ ሲነሱ የኖሩ ምላሽ አልባ ጥያቄዎች ይመስላሉ፡፡

ሌላው የሰበሰባቸውን ፣ የተነተናቸውንና የተረጎማቸውን ጥሬ መረጃዎች ሕይወት አከል እንዲሆኑ ምስል የመፍጠር እና ቅርጽ የማበጀቱ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ጋር ሽግግር አለ በቅደም ተከተል የተሰደሩ የታሪክ እውነታዎችን የባለታሪኩን ሰብዕና ወደሚያሳይ ውብ ትረካ ማሸጋገር ያስፈልጋል፡፡ ጥሬ ሐቆቹን ልቦለዳዊ አድርጎ ሲያቀርብ ከእውነታው ሊጋጭ ይችላል፡፡ ልቦለዳዊ አቀራረቡን ትቶ ጥሬ ሐቆቹን ቢደረድር የሕይወት ታሪኩ ኪነት አልባ ይሆናል፡፡ አንድ የሕይወት ታሪክ ደራሲ የሚመዘነውም በዋናነት ለእነዚህ ጥያቄዎች በሚሰጠው የተመቻመቸ ምላሽ (compromised response) ነው፡፡
Tilahun Legend
ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ የነበረው ዘከሪያ መሐመድ እንደ ደራስያን ማህበሩ የደቦ ድርሰት ገራገር አቀራረብ ይዞ አልመጣም፡ ፡ ያገኛቸውን መረጃዎች በሙሉ በቅደም ተከተል ሲሰድር ታሪካዊ እና ስነልቦናዊ አንድነታቸውን እየፈከረ ነው፡፡ ልቦለዳዊ ውበቱ እና ታሪካዊ እውነቱም እርስ በእርስ እንዲደጋገፉ እንጂ አንዱ ከአንዱ ጋር እንዲቃረኑ አላደረገም፡፡ አልያም እንደ ደራስያን ማህበሩ ድርሰት የተነገረውን ብቻ የሚተፋ በቀቀን አልሆነም ፤ በፍጹም !

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” በዋናነት ሦስት የማህበራዊ ሳይንስ ዲሲፕሊኖች ( ሙዚቃ ፣ ስነልቦና እና ታሪክ) እንደየአስፈላጊነቱ ተዛምደው የቀረቡበት መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ ዳሰሳ አቅራቢ ይበልጡን የተሳበው ግን በስነልቦናዊ ፍከራው ላይ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስነልቦናዊ ፍካሬ ያላቸው የሕይወት ታሪኮች ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ምክንያቱም ባለታሪኩ አውቆም ይሁን ሳያውቅ የደበቃቸውን ስውር የታሪክ ገጾች የማሳየት አቅም አላቸው፡፡ በዚህ ረገድ የሊዎናርዶ ዳቬንቺን እና የልጅነት ትዝታውን በፍካሬ ልቦና (psycho analysis) ያሳየው የሲግመን ፍሩድ መጽሐፍ ፈር ቀዳጅነቱ ይጠቀሳል፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ የነበረውን የአዶልፍ ሂትለርን ሰብዕና የሚተነተነው የዶ/ር ሙራይ መጽሐፍም ከሚጠቀሱ ስነልቦናዊ የሕይወት ታሪኮች አንዱ ነው፡፡

የእኛው ዘከሪያ መሐመድ ከእነዚህ መጽሐፍት ጋር የቅርብ ዝምድና ያለው ይመስለኛል፡፡ የአቶ ፈይሳ ኃይሌ ሀሠና የቤተሰብ ማስታወሻ ያዘለውን የጥላሁንን የልጅነት ቀውስ የበዛበት ታሪክ መሳሪያ በማድረግ የጥላሁንን ሙሉ ሰብዕና በፍካሬ ለማሳየት የተጋው በእነዚህ መጽሐፍ ተጽዕኖ ይሆን ? መልሱን ለደራሲው ትቻለሁ፤

ሁለት ማንነት ለምን ?
መሳቁን ይስቃል ጥርሴ መቼ አረፈ፣
ልቤ ነው በጣሙን እጅግ ያኮረፈ፡፡
አልጠፋልህ ብሎኝ የልቤ ውስጥ እሳት፣
ጥርሴ እንዲያምር ብዬ ተወጋሁ ንቅሳት፡፡
ይሄ ነው ጥላሁን ማለት ! ልቡ ውስጥ የቀበረውን እውነት በአንደበቱ

ይሽራል፡፡ በአስታወሰው ቁጥር እሳት ሆኖ ይፈጀዋልና አርቆ ጥሎታል፡፡ በጨቅላነት ዕድሜ የእናቱን ጉያ እየሞቀ ማደግ ቢፈልግም ፣ በአባቱ መዳፍ እየተዳበሰ ልጅነቱን ማየት ቢሻም አልቻለም፡፡ እናቱ ስድስት ዓመት ሳይሞላው ጥላው ኮበለለች፡፡ አባቱ የእናቱን ፈለግ ተከትሎ አድራሻውን ሳይናገር ጠፋ፡ ፡ ጥላሁን በአያቱ እጅ ለማደግ ተገደደ፡፡ ይህን የልጅነት ቁስል ነው ላለፉት 50 ዓመታት ሲደብቅ የኖረው እና የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ይፋ ያደረገው፡፡ ጥላሁን መዘንጋት ፣ መተው ያመዋል፡፡ በልጅነቱ የተከሰተው ስነልቦናዊ ቀውስ በትዳሩም የተረጋጋ ሕይወት እንዳይኖረው አድርጎታል፡፡ እናት እና አባቱ እሱን ጥለውት እንደኮበለሉ ሁሉ እሱም ሻንጣውን እየያዘ ያለበትን ሳይናገር የትዳር አጋሮቹን እስከነልጆቻቸው ጥሎ ሸሽቷል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ትንታኔ መሠረት ጥላሁን ከሰባት ሴቶች ጋር የፍቅር ሕይወት የመሠረተው ሴት የመቀያየር አባዜ ይዞት ሳይሆን የተዳፈነው የልጅነት ቁስል ውጤት ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ትልቁ ትሩፋትም ይህን በትንታኔ ማሳየቱ ነው፡፡

ከጥላሁን አንደበት ያገኙትን በሙሉ በተዝረከረከ ቋንቋ የጻፉት የደራስያን ማህበር ጸሐፍት (ይህ ወቀሳ የሠርጸ ፍሬስብሐትን መጣጥፍ አይመለከትም) ከዘከሪያ መሐመድ ! ከአንዱ ግለሰብ ! ጥረት የሚማሩት በርካታ ነገር አለ፡፡

እንደ ደራስያን ማህበር መጽሐፍ ቢሆን ኖሮ ጥላሁን የተወለደው ጠመንጃ ያዥ ሠፈር ነው ፤ የጥላሁን ሕጋዊ ሚስቶች ቁጥር አምስት ብቻ ነው ፤ የመጀመሪያ ሚስቱም ወ/ሮ አስራት አለሙ ናት ፤ የእናቱ ሙሉ ስምም ወ/ሮ ጌጤነሽ ጉርሙ ነው፡፡ በዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ እነዚህ ስህተቶች እርማት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ የተወለደው ከወሊሶ 12 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ጉሩራ እልፍ ብሎ በሚገኘው ሶየማ የገጠር ቀበሌ ነው፡፡ እናቱም ወ/ሮ ጌጤነሽ ኢተአ ትባላለች፡፡ የጥላሁን ሕጋዊ ሚስቶች ቁጥር ስድስት ሲሆን የመጀመሪያ ባለቤቱ በአስራ ሰባት ዓመት ዕድሜው ያገባት ወ/ሮ ፈለቀች ማሞ ናት፡፡ በ1970ዎቹ አጋማሽም አራተኛ ሚስቱን ፈሪያል መሐመድን ከፈታ በኋላ ከወ/ሮ ብርሃኔ ዘለቀ ጋር ከሁለት ዓመት በላይ አብሮ ኖሯል፡፡ ይህም የሚስቶቹን ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ያደርጋል፡፡ እነዚህን ሁሉ አሳማኝ የታሪክ ሐቆች ነው የደራስያን ማህበሩ መጽሐፍ የገደፈውና የዘከሪያ መሐመድ መጽሐፍ ይፋ ያደረገው፡፡

ለሃምሳ ዓመታት ሲተረክ የነበረው የጥላሁን ተለጣፊ ማንነት በስነልቦናዊ ትንታኔ ሽሮ የእውነተኛውን የሙዚቃ ሰው ታሪክ ለአስኮመኮመን ዘከሪያ በእውነት ክብር ይገባዋል፡፡

የሆድ ይፍጀው ነገር

“ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” የተሰኘውን መጠሪያ የተመለከተ ሰው ሁሉ የዚህ መጽሐፍ ትልቁ ምሥጢር አድርጎ የሚወስደው የሆድ ይፈጀውን ትረካ ይመስለኛል፡፡ ለእኔ ግን ከሆድ ይፍጀውም በላይ ትልቁ ምሥጢር ለሃምሳ ዓመታት ተደብቆ የኖረው የጥላሁን የልጅነት እና የትዳር ሕይወት ነው፡፡
ሚያዝያ 10 ቀን 1985 ዓ.ም የፋሲካ ዕለት የጥላሁን ገሠሠን በስለት የመወጋት ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ጥላሁንን ሦስት ቦታ ወግቶ የመግደል ሙከራ ያደረገው ማን እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም ነበር፡፡ ዘከሪያ መሐመድ ለዚህ ጥያቄ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል ፤ ወንጀሉን የፈጸመው እና የፈጸመበትን መንስኤ በትርጓሜ ጠቁሟል፡፡ አብዛኛውን አንባቢ ምን ያህል ያረካል ? እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

የመጨረሻው ቃል

በአንድ ኢትዮጵያዊ የኪነት ሰው ላይ በዚህ ደረጃ የሕይወት ታሪክ ተጽፎ ያነበብኩት የዘከርያ መሐመድን “ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክ እና ምሥጢር” የተሰኘውን መጽሐፍ ነው፡፡ የጥላሁን ገሠሠ ውስጣዊ ዓለም በቃላት ስሎ አሳይቶናል፡፡ ስነልቦናዊ ፍካሬው አንጀት ያርሳል ቅደም ተከተላዊ ታሪኩን የገለጸበት ቋንቋ ጥቃቅኖቹን ሁነቶች ሳይቀር ልቦና ውስጥ እንዲቀሩ ያደርጋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ፈቃደኛ የሆኑ መረጃ አቀባዮችን ካገኘ የበለጠ እየፋፋና እየጎለበተ መሄድ የሚችል ይመስለኛል፡፡ ለአገራችን የሕይወት ታሪክ ጸሐፍትም ዘከሪያ መሐመድ “የተገኘውን ጥሬ መረጃ እንደወረደ መጻፍ ጸሐፊ አያሰኝም ፤ ጥሬውን መረጃ ከተለያዩ ዲሲፕሊኖች በተገኙ ንድፈ ሐሳቦች መተንተንና መፈክር ነው የስኬታማ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊ ብቃት መታያው፡ ፡” ያለ ይመስለኛል ፤ በሥራው፡፡

የዘከሪያን መጽሐፍ ማንበብ መታደል ነው ፤ ትርፉ ብዙ ነውና፡፡

ቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ

The post (አሁንም ስለአነጋጋሪው የጥላሁን መጽሐፍ) ሁለት ማንነት በአንድ ራስ – ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃው ንጉሥ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አሜሪካ ውስጥ ርካሽ እና ውድ የቤት ኪራይ ያለባቸው ከተሞች ተለይተው ታወቁ

$
0
0

(Admas Radio)
ካሊፎርኒያ፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሃዋይ፣ ኒውዮርክ እና ኒውጀርሲ ውድ ቤት ኪራይ ያለባቸው ከተሞች መሆናቸውን ሰሞኑን የወጣ ሪፖርት አሳይቷል።
new-york-city
አንድ በኒውጀርሲ ከተማ ለመኖር የፈለገ ተከራይ ባለሁለት መኝታ ቤት ተከራይቶ ለመኖር አንድ በሰዓት 25 ዶላር የሚከፈልበት የሙሉ ሰአት ሥራ መስራት ይኖርበታል። በኒውጀርሲ በአማካይ የሁለት መኝታ ቤት ዋጋ 1300 ዶላር በወር ነው። አንድ ሰው የቤት ክፍያው ከደሞዙ ከ 30 በመቶ መብለጥ አይኖርበትም – አቅም አለው ለመባል። በዚህ መሰረት 1300 በወር ከፍሎ ለመኖር ቢያንስ በወር አንድ ሰው 4ሺ 500 ዶላር ገቢ ሊኖረው ይገባል።

በኒውጀርሲ የቤቶችና ማህበረሰብ እድገት አጥኚ የሆኑት አርኖልድ ኮህን በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ነዋሪዎቻቸው ሁለት መኝታ ቤት አፓርትመንት የመከራየት አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችል ክፍያ የላቸውም ይላሉ። በተለይ የኒውጀርሲን ሲያስረዱ “ልጆቻችንን የሚጠብቁልን፣ አዛውንቶቻችንን የሚንከባከቡልን፣ ግሮሰሪና ሌላም ቦታ የሚያስተናግዱን፣ ለየለት ለት ጉዳዮቻችን ተስፋ የምንጥልባቸው ሁሉ ፣ ለራሳቸው መኖሪያ ለመክፈል ግን አይችሉም” ሲሉ ይናገራሉ።

በኒውጀርሲ ግዛት መካከለኛ የሰአት ክፍያ 17 ዶላር ሲሆን፣ በሰአት 17 ዶላር የሚከፈለው ሰው ፣ ሁለት መኝታ ቤት አፓርትመንት መከራየት እንዲችል በሳምንት ቢያንስ 59 ሰአት መስራት ይኖርበታል። የግዛቱን ዝቅተኛ የሰአት ክፍያ ማለትም 8.38 ዶላር በሰ አት የሚከፈለው ሰው ሁለት መኝታ ቤት ካማረው ሶስት የሙሉ ሰአት ሥራ ያስፈልገዋል። ያ ማለት ደግሞ 24 ሰአት በቀን መስራት አለበት ማለት ነው።

በአንዳንድ የኒውጀርሲ አካባቢዎች ፣ ለምሳሌ በሃንተርደን፣ ሚድልሴክስ እና ሶመርሴት አካባቢዎች ሁለት መኝታ ቤት እስከ 1500 ዶላር ይደርሳል። በአንጻሩ በሱሴክስ፣ ኬፕ ሜይ እና ግላክስተር የሚባሉ ካውንቲዎች ኪራዩ የሚቀንስ ቢሆንም፣ በዚያ አካባቢ የሚኖሩ ደግሞ በአብዛኛው በሰአት 10 ዶላር አካባቢ የሚከፈላቸው ናቸው።

ለዚህም ነው ባሳለፍነው ሳምንት በኒውጀርሲ የሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ፣ እንደ ሰዉ አቅም የሚሆኑ ቤቶች እንዲሰሩ ግፊት የሚያደርግ ስብሰባ ያካሄዱት: በዚህ ስብሰባ የኒውጀርሲ ባለሥልጣናት ሁሉም እንዳቅሙ የሚኖርባቸው ቤቶች እንዲሰሩ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

በኒው በርንስዊክ ከተማ ነዋሪ የሆነው ፖል ሜየርስ በወር 1500 ዶላር እየከፈለ በተከራየው ሁለት መኝታ ቤት አፓርታማ ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር ነበር። በመካከል ይስራ የነበረው የሽያጭ ሥራ ተቋረጠ። ለቤት ኪራይ የሚከፍለውም አጣ። በዚህ ጊዜ የቤት ዕቃዎቹን እያወጣ መሸጥ ነበረበት። “እንደዚያም ሆኖ መኖር አልቻልኩም፣ የምሸጠው አለቀ፣ የቤት ኪራይ ግን እየጠበቀኝ ነበር” ነው ያለው።
ከዚያ በኋላ ምርጫ አልነበረውም ከነቤተሰቡ ወጥቶ በመቆያ ጣቢያ (ሼልተር) መኖር ጀመረ። ስምንት ወር እዚያ ከቆየ በኋላ እሱ ሚስቱና አንድ ልጁ ከዚያ ወጥተው ኪልመር ሆምስ የተባለው ድርጅት በመንግስት ድጋፍ በሚገነባቸው አፓርታማዎች መኖር ጀመረዋል። እነዚህ አፓርታማዎች ሰዎች እንደገቢያቸው ልክ የሚከፍሉባቸው ናቸው። ሆነም ቀረ፣ ያቺንም ቢሆንም ለመክፈል ፖል ቀን ከሌሊት መስራት ነበረበት።

በሰሞኑ ጥናት መሰረት ውድ የአፓርታማ ኪራይ የተመዘገበባቸው ከተሞች መካከል ሃዋይ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በሃዋይ ሁለት መኝታ ቤት አፓርታማ 1700 ዶላር ሲደርስ፣ በዲሲ 1500 ዶላር አካባቢ፣ በካሊፎርኒያ 1389 ፣ በኒውርዮክ 1335፣ እንዲሁም ኒውጀርሲ 1309 ዶላር በአማካይ ናቸው።

በሌላ በኩል ርካሽ የሚባል ባለሁለት መኝታ ቤት አፓርታማ ከሚገኝባቸው ከተሞች መካከል ፖርቶሪኮ 547 ዶላር ፣ አርካንሳ 673 ዶላር ፣ ኬንታኪ 683 ዶላር፣ ዌስት ቨርጂኒያ 687 ዶላር እንዲሁም ሳውዝ ዳኮታ 698 ዶላር ይጠቀሳሉ።

The post አሜሪካ ውስጥ ርካሽ እና ውድ የቤት ኪራይ ያለባቸው ከተሞች ተለይተው ታወቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ 8ኛ ዓመት የትዳር ሕይወታቸውን አከበሩ

$
0
0

Gosaye Tesfaye

Gosaye tesfaye 2

Gosaye tesfaye2
ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአቡነ ዓቢየ እግዚእ ታቦተ ህግ በትናንትናው ዕለት ከበሯል። ይህ ጻዲቅ አባት በጎንደርና በትግራይ ብቻ ነበር የሚከብረው። ትናንት ግንቦት 19 እረፍቱ ስለነበረ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ ደብር ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።

ዲያቆን ሉኡልሰገድ ጌታቸው እንደገለጸው ለዚህ ክብረ በዓል መሳካት አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ ወሮ አፀደ ሥላሴ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በተለይ ወሮ አፀደ የጻድቁን ገድል በማጻፍ፣ ታቦተ ሕጉም በደብሩ እንዲኖር ከአባቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት ያደረገች ታላቅ ሴት ነች። አጋጣሚው ደግሞ እጅግ ደስ ይላል፣ ለእነዚህ ለተባረኩ ጥንዶች ይህ ግንቦት ወር የተጋቡበት ወር መሆኑ ነው። ስለዚህ 8ኛ ዓመታቸውን በታቦቱ ስር አስበውት ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሩት መልካም ትሩፋት ደብሩ ያዘጋጀላቸውን የክብር ካባ ብጹዕ አቡነ ሰላማ ባርከው ደርበውላቸዋል ሲል ዲያቆን ልዑልሰገድ ጌታቸው ዘገባውን አጠናቋል::

The post አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬና ባለቤቱ 8ኛ ዓመት የትዳር ሕይወታቸውን አከበሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“የአባዬ ስልክ እና ባዮሎጂ”–ተራኪ ፈቃዱ ተክለማርያም (በጣም አስቂኝ)

$
0
0

በየወሩ የመጀመሪያው ሮብ በራስ ሆቴል ‹‹ጦቢያ ግጥምን በጃዝ›› የስነፅሁፍ ፕሮግራም ይካሄዳል:: የግንቦት ወር 2007 ዓ/ም ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ ለታዳሚው አንድ ፅሁፍ እንዲተርክ ወደመድረክ የወጣው ደግሞ አርቲስት ፈቃዱ ተክለማሪያም ነበር:: ዶ/ር አሸብር ከሚለው የአሌክስ አብርሃም አጭር ልብወለድ መጽሐፍ “የአባዬ ስልክና ባዮሎጂ” የሚለውን መጣጥፍ ተርኮታል:: ለመሳቅ ከፈለጉ ይመልከቱት::

fekadu

The post “የአባዬ ስልክ እና ባዮሎጂ” – ተራኪ ፈቃዱ ተክለማርያም (በጣም አስቂኝ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የኤፍሬም ታምሩ አልበም ጥያቄ አስነሳ * ይልማ ገብረአብ 250 ሺህ ብር ይገባኛል አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቀድሞ ዘፈኖቹን በአዲስ መልክ አስተካከሎ ለገበያ እንደሚቀብ በተለያዩ ጊዜያት ሲዘገብ እንከንም እያጋጠመው ሲዘዋወር ቆይቷል:: ለመጨረሻ ጊዜ ይወጣል በተባለበት ሰዓት የእናቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት አልበሙን አዘግይቶታል::

ውስጥ አዋቂ እንደዘገበው ኤፍሬም በቅርቡ አልበሙን ለመልቀቅ በቤቱ ትልቅ የምስጋና ፓርቲ አዘጋጅቶ ቢጨረስም በዚህ በዓል በኋላ ታዋቂው የዘፈን ግጥም ደራሲ ይልማ ገብረአብ ጥያቄ አንስቷል:: “ከዚህ ቀደም እነዚህን ዘፈን ግጥሞች ለካሴት ሥሰራ የተከፈለኝ በአንድ የዘፈን ግጥም አንድ ሺህ ብር ብቻ ነው:: አሁን ግን በዚህ አዲሱ የአፌሬም አልበም ውስጥ ለተካተቱት 10 ዘፈን ግጥሞቼ ለ እያንዳዳቸው 25 ሺህ ብር ጠይቄያለሁ” ብሏል:: ይህም 250 ሺህ ብር መሆኑ ነው:: ዝርዝሩን ያድምጡ::

Ephrem Tamiru

The post የኤፍሬም ታምሩ አልበም ጥያቄ አስነሳ * ይልማ ገብረአብ 250 ሺህ ብር ይገባኛል አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

$
0
0
“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

“ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች”
ዳዊት ፍሬው ኃይሉ

ትዕግስት ታደለ

የአንጋፋው ድምጻዊ የፍሬው ሀይሉ ልጅ ነው፡፡ የአባታቸውንን ፈለግ ተከትለው ወደ ሙዚቃ ዓለም ከተቀላቀሉ የአንጋፋ ሙዚቀኛ ልጆች መሀከል የተሳካለት የክላርኔት ተጫዋች አንዱ የሆነው ዳዊት ፍሬው ኃይሉ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሁለት ሲዲዎችን ለእድማጭ አቅርኋዋል፡ ፡የሙዚቃ ትምህርቱንም በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ተምሯል፡፡ ‹የሰው ልጅ በአብዛኛውን በምሳ ሰዓትም ሆነ ማታ ወደ እንቅልፉ የሚሄደው በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ በተቀነባባሩ ሙዚቃዎችን እየሰማ ነው፡፡› የሚለው ዳዊት እስካሁን በሰራሁት ስራ የሚገባኝን ያህል ገቢ አግኝቻለሁ ለማለት ባልችልም ሲዲዬን ገዝቶ ያዳመጠ ሰው ግን ነፍሱን አስደስቷል ብዬ አምናለሁ› ይላል፡፡እኛም የመሿለኪያ አምዳችን እንግዳ አድርገነው እንዲህ አውግቶናል፡፡

ቁም ነገር፡- የደስታና የሐዘንን ስሜት አውጥቶ ከመግለጽና ተቆጣጥሮ ከማለፍ የትኛው ይሻላል?

ዳዊት፡- ሁለቱም ስሜቶች መደበቅ የለባቸውም፤ ግን ደስታ ላይ ገደብ ሊኖረው ይገባል፣ ሐዘንም ላይ እንዲሁ ገደብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሲለቀስም አልቅሰው ሲመጣላቸው ፤ሲደሰቱም መደነስ የሚችለው ደንሶ፣ መጨፈር የሚችለውም ጨፍሮ ጨፍሮ ሲወጣለት ደስ ይላል፡፡ ድብቅ መሆንን አልደግፍም፡፡

ቁም ነገር፡- የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ሲባል ወደ አዕምሮህ ምንድን ነው የሚመጣው?

ዳዊት፡- እኔ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎትን ሳስብ መድረክ መሪዎቹ ላይ ነው የማዝነው፤ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ ይባልና ሰውን አስነስተው ማስቀመጣቸውን እንጂ የሚያዩት በትክክል ደቂቃውን አያዩትም፡፡ የአንድ ደቂቃ የሚሰጠው ሰው እዛ ጋር ቁሞ ሀሳብን ሰብስቦ ጸሎት የሚደረግለትን ስው ለማሰብ ነው፡፡ እነሱ ግን አስራ አምስተኛው ሰኮንድ ላይ ተቀመጡ ይላሉ፤ ያ ይረብሻል፡፡ መድረክ መሪዎቹ ይህን የሚያደርጉት ዝም ብለው ለፎርማሊቲ ነው፡፡ እኔ ግን አዕምሮዬ ውስጥ የሚመጣው ያረፈውን ሰው ነፍስ በገነት ያኑርልኝ የሚለው ነው፡፡

ዳዊት፡- እንግዲህ እኔ ፍቅር ይዞኝ ያውቃል፤ የእውነተኛ ፍቅር ምክንያታዊ ነው፡፡ ወይ በአይንሽ በምታይው ነገር ተማርከሽ አለበለዚያ በተግባር ከምታየው ባህሪ ሊሆን ይችላል፤ በምክንያት ነው ፍቅር የሚዝሽ እንጂ ምክንያታዊ

ሳይሆን ፍቅር አይኖርም፡፡ ፍቅር ፈጣን ሎተሪ አይደል /ሳቅ/

ቁም ነገር፡- የዛሬ መቶ አመት ኢትዮጵያ በአንተ አመለካከት ምን አይት ገጽታ የሚኖራት ይመስልሃል?

ዳዊት፡- የዛሬ መቶ ዓመት በጣም ረጅም ጊዜ ነው፡፡ ምን ትሆናለች?

የሚለውን ሳይሆን የኔን ምኞት ብናገር ይሻለኛል፡፡ ምክንያቱም መገመት ይከብዳል፤ የዛሬ መቶ ዓመት የእኔ ምኞት የአፍሪካ ዋና ከተማ ሳይሆን የዓለም ዋና ከተማ እንድትሆን ነው፡፡ በአይናችን የምናያቸው ነገሮች አሉ የሚካድ ነገር አይደለም፤ ይሄ ነገር በመቶ ሳይሆን በመቶ ሺህ ተባዝቶ ተባዝቶ ሰዉ የሚሰጥ

እንጂ የሚቀበል እንዳይሆን እመኛለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቅ ለምንድን ነው የሚባለው?

ዳዊት፡- ይሄ የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ሰው መኖርን ስለሚፈልግ ፖለቲካው ለመጥፊያው ምክንያት እንዳይሆንበት ከመፍራት ነው፡፡ ኤሌክትሪክ የሚሸሸው እንዳያጠፋን ነው አይደል፤ ፖለቲካም ለመጥፊያችን ምክንያት እንዳይሆን ነው፡፡

ቁም ነገር፡- ሙዚቃ ባይኖር ኖሮ የሰው ልጅ ህይወት ምን ይመስል ነበር?

ዳዊት፡- በሙዚቃ እኮ ነው ስሜት የሚገለፀው፤ ዓለም ጎዶሎ የምትሆን ነውየሚመስለኝ፡፡ሙዚቃባይኖርሰውደስሲለውሲያዝንስሜቱንየሚገልጽበት ያጣል፡፡ በንግግር ከሚነገረው መልዕክት እኮ በዜማ የሚሰማው መልዕክት ብቃቱ የትየለሌ ነው፡፡ አሁን የጥላሁን ‹‹ዳግመኛ ቢፈጥረው›› ዘፈን ስትሰሚ ሰው ደጋግሞ በንግግር ከሚነግርሽ ሁለቷን የጥላሁንን ስንኝ

‹‹ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው››
‹‹ምናለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው›› የሚለውን በዜማ ብትሰሚ

ትልቅ ጉልበት አለው፡፡ ሙዚቃ ሁሉ ነገራችን ውስጥ አለ፡፡ ሲሸለል ሲፎከር ሁሉ ሙዚቃ አለ፤ ስለዚህ ሙዚቃ ባይኖር ብዙ ነገር ይጎልብናል፡፡ ሙዚቃ የዓለም የልብ ምት ነች፡፡

ቁም ነገር፡- በሰው በሀገራት ስም የሚጠሩ የከተማችን ሰፈሮች የትኞቹን ታውቃለህ?
ዳዊት፡- ሪቼ የሚባል አለ አይደል? ሪቼ የሰው ሀገር ስም ነው እንዴ? እኔ ምን እንደሆነም አላውቅም፤ የሰው ሀገር ስም ይመስላል /ሳቅ/፤ ካሳንችስ ምንድን ነው? ምናልባት ሩዋንዳ የሚለው በሰው ሀገር ስም ነው መሰለኝ /እ…. እንደማሰብ / እንግዲህ የሩዋንዳው ብቻ ነው የመጣልኝ፡፡

ቁም ነገር፡- መጋኛ ምንድን ነው?

ዳዊት፡- መጋኛ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ይመስለኛል፡፡ በፊት ጠዋት ላይ ሆዴን ይቆርጠኝ ነበረ፤ ስጠይቅ በር ከፍተህ ስለወጣህ ነው፡፡ መጋኛ መቶህ ነው ይሉኛል፡፡ ቁርጠት ነው በሽታ ያመጣብኝ፣ በሽታ ደግሞ ሰይጣን ነው፡፡ ስለዚህ

መጋኛ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ነው ወይም ደግሞ የሰፈሩ ልጅ /ሣቅ/ ፡፡

ቁም ነገር፡- ስዕል ፣ ሙዚቃ፣ ቴአትር እና ፊልም ከነዚህ ላንተ የትኛው ነው ህይወትን በደንብ የሚገልፅልህ? ለምን?

ዳዊት፡- ሙዚቃ ጉልበት አለው፡፡ እኔ ሙዚቀኛ ስሆንኩ አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ የኛ ያልሆኑ ሙዚቃዎችን ከፍቼ ሳዳምጥ የማላውቀው ቦታ ይዞኝ ይሄዳል ፣ የሚፈጥረው ስሜት አለው፡፡ ለዚህ ነው ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው የሚባለው፤ አሁን ለምሳሌ የቻይና ሙዚቃ ብንሰማው የማናውቀውን ዓለም ነው የሚያሳየን፡፡ ቋንቋውን የማናውቀውን ፊልም ወይም ቴአትር ብናይ ግን ዝም ብለን ምስሉን፣ እንቀስቃሴውን እናያለን እንጂ አይገባንም፡፡ ሙዚቃ ግን ኖታ ነው፡፡ ስትሰሚው ሌላ ዓለም ይዞሽ

ይሄዳል፡፡ቁም ነገር፡- ጫማው ከጠበበው ሰው እና ሽንቱ ከወጠረው ሰው የትኛው ይሻላል?

ዳዊት፡- እንዴ ጫማው የጠበበው ሰው ነዋ! የሚሻለው /ሣቅ/ ፤ጫማው የጠበበው ሰው ምን ቢጠበውም እግሩ አይቆረጥም ምንም አይሆንም ፡፡ሽንቱ የወጠረው ሰው ግን መንገድ ላይ ቢሆን የወጠረው ምን እንደሚፈጠር ማወቅ

አያዳግትም፡፡ በተፈጥሮ መያዝና በሰው ሰራሽ መያዝ ምን አንድ አደረገው /ሣቅ/፡፡

ቁም ነገር፡- ሀገራችን ከድህነት በቀላሉ መላቀቅ ያልቻለችው ለምንድን ይመስልሃል?

ዳዊት፡- ይህ እንግዲህ ሰፊ ነው ጉዳዩ ፤አንደኛ መናበብ ካለመቻል ነው፡ ፡ ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ

ሀገራችን ታድጋለች፡፡ ችግሮችና ቢኖሩም ሁሌም ማስቀደም ያለብን ኢትዮጵያን ነው፡

፡ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡

ቁም ነገር፡- በአሁኑ ወቅት የወጣቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ምንድን ነው ትላለህ?

ዳዊት፡- ለስራ የተዘጋጀ ስነ ልቦና አለመኖር ይመስለኛል፤ ለስራ ዝግጁ

አለመሆን ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ባህላችን ሆኖ የበታችነትን እንጠላለን፤ አንድ ሰው

ራሱንበአካዳሚዕውቀትሳያዳብርሥራአጣሁብሎቢያወራምንይገርማል፡፡ ለስራ

ዝግጁ አለመሆን ይመስለኛል አንገብጋቢው ነገር፡፡

ቁም ነገር፡- ነገረኛ ጎረቤት ምን አይነት ነው?

ዳዊት ፡- ምነሻ ሃሳብ የሚፈልግ ነዋ ! /ሳቅ../ ሙዚቃ እንኳን ብትከፍቺ

ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ አረ ድምጹን ቀንሱ እንተኛበት የሚል! ያው አንዳንዴ

ትደበሪበታለሽ! የሚለውን እየሰማሽ! እንደዚህ ነው ከልምዴ የማቀው፡፡

ቁምነገር ፡- አመሰግናለሁ፡፡

The post “ሁሉም ሰው ከብሔሩ ወይም ከሰፈሩ ይልቅ ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ ቢሰጥ ሀገራችን ታድጋለች” ዳዊት ፍሬው ኃይሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የኤፍሬም ታምሩ አልበምና ውዝግቡ –ያልተሰሙ አንዳንድ አዳዲስ መረጃዎች

$
0
0

Ephriem Tamriu

መነሻ አንድ

ለማለት መዘጋጀታቸው ሲሰማ ወጣቱ ድምፃዊ ራሱን ለማጥፋት እስከመወሰንየዛሬ ሶስት ዓመት ሳሚ በየነ የተባለ ወጣት ድምፃዊ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የቅጂና የተዛማጅ መብቶች አዋጅን የዘነጋ አንድ አልበም አውጥቶ ነበር፡፡ አልበሙ መሉ ለሙሉ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩን ቀደምት ተወዳጅ ዘፈኖች መሀከል 12 ያህሉን መርጦ በድጋሚ በማቀንቀን ለህዝብ ሲያቀርብ ድምፁ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር ከመመሳሰሉ ጋር በተያያዘ በብዙዎች ዘንድ ተደማጭነትን ያገኘው በአጭር ቀናት ነበር፡፡ በየመገናኛ ብዙሃኑ ብቻ ሳይሆን በየታክሲውና በየሆቴሉ መደመጥ የጀመረው የሳሚ በየነ አልበም ተቃውሞ የመጣበት ግን ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡

ተቃውሞው የመጣው ቀደምት ስራዎቹን በአዲስ መልክ ለማውጣት እንቅስቃሴ በጀመረው በድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ብቻ ሳይሆን ከግጥምና ዜማ ደራሲያኑ ፤አሳታሚው ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤትና ከሙዚቃ አቀናባሪውም ጭምር ነበር፡፡ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ አስር ሺህ ያህል ሲዲዎችን ማሰራጨት የቻለው ሳሚ በየነ ብቻ ሳይሆን ዘፈኖቹን መርጦ እንዲያቀነቅነው ያደረገው አሳታሚውና ፕሮውዲውሰሩ ኢቫንጋዲ ሪከርድስም ከቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ የቀረበበት ወዲያውኑ ነበር፡፡ ያለ ምንም ፈቃድ ዘፈኖቹን ዘፍኖ ያወጣው ሳሚ በየነ በአዋጁ መሠረት በፍትሐብሔር ብቻ ሳይሆን በወንጀልም ከፍተኛ ሊባል የሚችል ቅጣት እንደሚጣልበት መነገር ሲጀምር ድምፃዊው ያልጠበቀው ችግር ውስጥ ገባ፡፡

ወጣቱ ድምፃዊ የኤፍሬም ዘፈኖችን አቀንቅኖ ካገኘው እውቅና የበለጠ ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ወደቀ፡፡ በቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጁ መሠረት የፈጠራ ስራዎቹ ባለቤቶች ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድና ‹አቤት›የሚደርስ ከባድ ወሳኔ ላይ መድረሱ ተነገረ፡፡ ከቀናት በኋላም ዘፈኖቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበስብ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ተከትሎ አሳታሚውና ድምጻዊው ታትመው ህዝብ እጅ ያልገቡ ሲዲዎችን ከከተማ ላይ በመኪና ተዘዋውረው መሰብሰብ ጀመሩ፡፡ ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስም በግጥም ደራሲው ይልማ ገ/አብ፤ እንዲሁም በዜማ ደራሲው አበበ መለሰ ወኪልና በኤፍሬም ታምሩ ማናጀር፤በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤትና በሙዚቃ ቅንብሩ መሪ በነበረው ዳዊት ይፍሩ መኖሪያ ቤት ሳሚ በየነ አዛውንት እናቱንና ነፍሰ ጡር ባለቤቱን ይዞ በማለዳ በመገኘት ‹የይቅርታ› ምልጃ አቀረበ፡፡

ሁሉም ባለሙያዎች የነገሩን ከባድነት ባለመረዳት የተሰራ ስራ መሆኑንና የወጣቱን ድምጻዊ የወደፊት ህይወት ላለማበላሸት በሚል ሁሉም ይቅርታ አደረጉለት፡፡ እርግጥ ነው መኪናውን ሸጦ የተወሰነ ክፍያ ለደራሲያኑ መክፈሉ በወቅቱ ተዘግቧል፡፡
Ephrem 28

መነሻ ሁለት

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በብስራት ኤፍ ኤም ላይ በሚቀርብው ‹ሁሉ አዲስ› በተሰኘው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ በእንግድነት የቀረበው አንጋፋው ገጣሚ ይልማ ገ/አብ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር ስለነበረው ጓደኝነትና ስለ ስራዎቹ ተጠይቆ ሰፊ ጊዜ ወስዶ ነበር ያብራራው፡፡ በድምፁ ከሚያደንቃቸው አርቲስቶች መሀከል አንዱ ኤፍሬም እንደሆነ የጠቀሰው ይልማ ገና በ23 ዓመቱ ሲያገባም ሚዜው ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ‹ወንድሜ› ነው ሲል ነበር የገለፀው፡፡ ይህንን የይልማን ገለፃ የሰሙ አንዳንድ አርቲስቶች ግን የይልማ አባባል የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በ1998 ዓ.ም ኤፍሬም ታምሩ ካወጣው ‹ኋላ እንዳይቆጭሽ› አልበም ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር የማይሄድ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
በወቅቱ ኤፍሬም ታምሩ አዲሱን አልበም ለማውጣት የግጥምና ዜማ ስራዎችን ሲመርጥ እንደቀድሞ ብዙዎቹን የይልማ ገ/አብ ስራዎች አልመረጠም ነበር፡፡ ኤፍ
ሬም ካሴት ማውጣት ከጀመረበት ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በየካሴቶቹ ላይ አብዛኛዎቹን ግጥሞቹን የሰራለትና ለኤፍሬም እውቅናም መሠረት ከሆኑት ሰዎች መሀከል አንዱ የሆነው ይልማ በዚህ አልበም ላይ የተመረጠለት ግጥም አራት ብቻ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን ኤፍሬም ከይልማ ግጥሞች መሀከል የወሰደውን ‹ሰው ነው መሠረቱ› በተሰኘው ግጥም ሃሳብ በመመሰጡ በሲዲው ላይ በልዩ ሁኔታ ጠቅሶ ነበር በስራው እርካታ እንዳለው የፃፈው፡፡ ኤፍሬም የተለያዩ የግጥምና ዜማ ደራሲያን ስራዎችን መርጦ ካቀነቀነና ቅንብሩ ካለቀ በኋላ ፖስተር ታትሞ አልበሙ የሚወጣበት ቀን ተቆረጠ፡፡ ሚያዝያ 1998 ዓ.ም፡፡ ለዚሁ ስራ አሳታሚና አከፋፋዩ ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ሁሌም እንደሚያደርገው የኤፍሬም ካሴት አልበም በወጣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከገበያ ላይ የመጥፋት ልምድ ስላለ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በአንድ ጊዜ በርከት አድርጎ በማሳተም እጥረቱን ለመቀነስ ደፋ ቀና በሚባልበት ሰዓት አልበሙ እንዳይወጣ የሚያደርግ አንድ ነገር ተከሰተ፡፡

በአልበሙ ላይ አራት ዘፈን ብቻ በተመረጠለት በይልማ በኩል ይፋም ባይወጣ ‹ለምን› የሚል ጥያቄ መፈጠሩ አልቀረም ነበርና ቀደም ሲልም ‹ሰላም ልበለው አይንሽ› ከሚለው
አልበም ጀምሮ በ1988 እና በ1992 ዓ.ም ኤፍሬም ታምሩ ባወጣቸው አልበሞች ላይ ለሰራቸው ዘፈኖች የተከፈለው ክፍያ በአሜሪካ የታተመውንና የተሰራጨውን የሲዲ ክፍያ የማይጨምር ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ አዲሱ አልበም ሊወጣና ሊሰራጭ የሚችለው የቀድሞዎቹ ስራዎቼ ክፍያ አንድ ላይ ከተከፈለኝ ብቻ ነው የሚል አቋም ያዘ ይልማ፡ ፡ ለዚሁም ብር ሁለት መቶ ሺ ጠየቀ፡፡ ጥያቄው የቀረበለት ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ጉዳዩን ወደ ኤፍሬም ታምሩ እንደመራው ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የቁም ነገር መፅሄት
ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ኤፍሬም ለማውጣት የተዘጋጀበትን አልበም የግጥምና ዜማ ስራ የመረጠውና ያስቀረፀው አሜሪካ ሆኖ በመሆኑ ከይልማ ጋር በግጥም ስራው ዋጋ ላይ አልተነጋገረም ነበር፡፡ በመሆኑም አልበሙ አልቆ ተባዝቶ ለገበያ ሊቀርብ አፋፍ በደረሰበት ወቅትይልማየሁለትመቶሺብር የክፍያ ጥያቄ ማንሳቱ በኤፍሬም በኩል አልተዋጠለትም፡፡

ያም ሆኖ ኤፍሬም ማስታወቂያ ተነግሮ፤ ፖስተር ተለጥፎ፤ አድማጭ ከዛሬ ነገ ይወጣል እያለ የሚጠብቀው አዲሱ አልበሙ ላይ የተጋረጠውን የ ‹አይወጣም› ክልከላ ላይ አንድ ነገር ማድረግ ነበረበት፡፡ ያም ሆኖ ግን ‹ክፍያው ካልተፈፀመልኝ ግጥሜ በአልበሙ ውስጥ እንዳይካተት› የሚለውን ውሳኔ ለማስቀየር ከይልማ ጋር ተደራድሮ ከስምምነት ላይ መድረስ ኤፍሬም ‹ አልፈለገም› ይላሉ ምንጮች፡፡ ኤፍሬም የይልማ ሀሳብ ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት እንደደረሰው ያሰበው ነገር ቢኖር የይልማን ግጥም በሌላ ግጥም በመቀየር በዛው ዜማ መስራት ነበር፡፡የዚህ አይነት ፍላጎት እንዳለው በመግለፅም በአልበሙ ላይ ሌሎች የዘፈን ግጥሞችን ከፃፉለት ገጣሚያን መሀከል ሃብታሙ ቦጋለን በማስጠራት አዲስ ግጥም እንዲፅፍለት ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ይገልፃል፡፡ ሁኔታውን በቅርበት ይከታተሉ የነበሩ አርቲስቶች የኤፍሬምን ውሳኔ ለይልማ እንዲደርስ በማድረግ ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስ በመሃል ይገባሉ፡፡ ጥረቱ ከቀናት በኋላ ተሳክቶ ይልማ ለዘፈኑ የሃያ ሺ ብር ክፍያውን ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ተቀብሎ ‹ኋላ እንዳይቆጭሽ› የተሰኘው አልበሙ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ‹በወቅቱ የዚህ አይነት ውሳኔ ላይ የደረስኩት የገንዘብ ሰው አለመሆኔን ለማሳየት እንጂ የገንዘብ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ የአራት አልበም የሲዲ ሽያጭ ዋጋ ሳይከፈለኝ ሥራዎቹ ለአድማጭ ሳይደርሱ እንዲቀሩ ማድረግ እችል ነበር› ይላል ይልማ ያንን ወቅት በማስታወሰ፡፡
ephrem22

አዲሱ አልበም

ኤፍሬም ታምሩ እንደ ሌሎቹ አንጋፋ ድምፃውያን በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን ያቀነቀነ ድምፃዊ ይሁን እንጂ እንደ ሌሎቹ አርቲስቶች የጥንት ዘፈኖቹን በሲዲ አሰባስቦ አላሳተምም፡፡ በተለይም ከ1974 ዓ›ም እስከ 1988 ዓ.ም ድረስ የተጫወታቸው ዘፈኖች መሀከል የብዙዎችን ትዝታ የያዙት ዘፈኖቹ በካሴት ብቻ ያሉ በመሆናቸው ብዙዎች በሲዲ ተቀርፀው እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡ ኤፍሬም የጥንት ስራዎቹን ከመስራት ይልቅ አዳዲስ ዘፈኖችን በመስራት ላይ አተኩሮ በመቆየቱና የጥንት ስራዎቹን ችላ ማለቱ እንደ ሳሚ በየነ ላሉ መንታፊዎች ሊያጋልጠው እንደሚችል የጠረጠረ አይመስልም፡፡ በወዳጅ ዘመድ ጉትጎታ የድሮ ዘፈኖቹን በአዲስ መልክ መስራት የጀመረው ኤፍሬም አራት ዓመት ያህል የወሰደበት ሲሆን ዘንድሮ አልቆ ለህዝብ ለማድረስ ዝግጅቱ ተጠናቆ ነበር፡፡ ከሰራቸው ስራዎች መሀከል ›‹የድንገት እንግዳ› የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ከተለቀቀ በኋላ ድጋሚ አልበሙ ለህዝብ ሊደርስ የሚችልበት ሂደት ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰማ፡፡

ይልማ ገ/አብ በአዲስ መልክ ኤፍሬም ከሰራቸው 13 ዘፈኖች መሀከል አስሩ የይልማ ግጥሞች ናቸው፡፡ኤፍሬም በአጠቃላይ ከሰራቸው 130 ያህል ዘፈኖች መሀከል ምርጡን ሰብስቦ እንደገና ለመስራት ሲነሳ አስር ያህሉን ዘፈኖች የይልማ ስራዎችን ማድረጉ የይልማ ግጥሞች ምን ያህል በኤፍሬም ስራዎች ውስጥ ገዢ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ያም ሆኖ ኤፍሬም የድሮ ስራዎቹን ድጋሚ የመስራት ሀሳብ እንዳለው እንጂ የእሱን ስራዎች መርጦ ማቀንቀኑን ይልማ እንደማያውቅና ስራው ከተሰራ በኋላ እንደተነገረው ያስታውሳል፡ ፡ በመሆኑም ይልማ ቀደም ሲልም ያልተከፈለው የውጪ ሀገር የሲዲ ሽያጭ ክፍያ ዋጋ መኖሩን ከግምት በማስገባት አሁን ለመውጣት ከተዘጋጀው ሲዲላይለአንድዘፈንግጥም25ሺህብር በድምሩ 250 ሺህ ብር እንዲከፈለው ይጠይቃል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አልበሙ እንዳይወጣ ማስጠንቀቂያ ለኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት መስጠቱን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ኤፍሬም ከሰራቸው 13 ዘፈኖች መሀከል ቀሪዎቹ ሁለቱ የፀጋዬ ደቦጭ ድርሰት ሲሆኑ አንድ ደግሞ በህይወት የሌለው የተስፋዬ ለሜሳ ድርሰት ነው፡፡ፀጋዬ ግን ከወራት በፊት ለሁለቱ ዘፈኖች ግጥም በድምሩ 14 ሺህ ብር ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት መውሰዱን ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ አንዳንድ ወገኖች የይልማ ገ/አብን ውሳኔ ተገቢና በወቅቱ የቀረበ ሲሉ ሌሎች አስቀድሞ ባልተስማማበት ሁኔታ ስራው አልቆ ለህዝብ ሊደርስ ሲል የዚህ አይነት እንቅፋት መፍጠር ተገቢ አለመሆኑን ይተቻሉ፡፡

ኤፍሬም በዚህ አልበም ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኝበት ስለመሆኑ አያከራክርም፡፡ ቀደም ሲል እነ ይልማ እነዚህን ስራዎች ለካሴት ብቻ በሚል ሲሰሩ የተከፈላቸው ክፍያ ከአንድ ሺህ ብር እስከ ሶስት ሺህ ብር ብቻ ነበር፡፡ ኤፍሬምም በወቅቱ እነዚህን ስራዎች ሲሰራ ክፍያው ያን ያህል የተጋነነ አለመሆኑና ከአስር አስከ ሃያ ሺህ ብር ካሴቱን ይሸጥ እንደነበር ይነገራል፡፡
ከዛሬ ሃያና ሃያ አምስት ዓመታት በፊት የተሰሩት እነዚህ ተወዳጅ ስራዎችን በድጋሚ ኤፍሬም ሲሰራቸው ከፍያው ከ10 እጥፍ በላይ ስለመሄዱ ይነገራል፡፡ ኤፍሬም ይህንን የድሮ
ዘፈኖቹን በድጋሚ ሰርቶ ለማውጣት ከኤሌለክትራ ሙዚቃ ቤት ጋር አደረገ የተባለው ስምምንት በቃል የተደረገ ቢሆንም ኤፍሬም ሙሉ የባንዱን ወጪ ችሎ ዘፈኖቹን መርጦ ሰርቶ ማስተሩን ለማስረከብ ሲሆን ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ማስተሩን ሲረከብ ለግጥምና ዜማ ባለሙዎች ተገቢ የተባለውን ክፍያ እንዲከፍል ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት ኤፍሬም ሙሉ የባንዱን ወጪ ችሎ ስራውን አጠናቆ ሲረከብ ለድምፁ ብር 800 ሺህ ብር ክፍያ እንደሚያገኝና ከሽያጩ ላይም የፕርሰንት ክፍያ እንዲያገኝ ለማድረግ ታስቦ ነበር ተብሏል ፡፡ እንደዛም ሆኖ ኤፍሬም የውጪ ሀገር የሲዲ ሽያጭ ገቢውን ለብቻው ያገኛል፡፡ ግን ይህ ስምምነት ወደ ወረቀት ተቀይሮ ውል ሳይፈረም ኤፍሬም አልበሙን ጨርሶ ማምጣቱ ነው የተገለፀው፡፡
EPHREM ADDIS

አሁን አልበሙ ሊወጣና አድማጭ ዘንድ ሊደርስ የሚችለው ይልማ ያቀረበውን የገንዘብ መጠን በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ወይም በኤፍሬም በኩል የሚሸፈን ከሆነ ብቻ ይሆናል፡፡ ያን ለማድረግ ደግሞ ለኤሌክትራ በኩል አስቸጋሪ ነው፡፡ የህትመት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ባለበትና የኮፒ ካሴቶች ሽያጭ ባልቆመበት ሁኔታ ይህን ያህል ወጪ ለአንድ ዘፈን መክፈል አዋጭነቱ አጠራጣሪ እንደሆነ ነው ስራውን የሚያውቁ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡ በሌላ በኩል ይልማ አሁን ያቀረበውን ክፍያ መክፈል ቢቻል እንኳ ሌሎቹም ባለሙያዎች ተመሳሳይ የክፍያ ጥያቄ ማንሳታቸው ስለማይቀር በማናቸውም መልኩ የአልበሙን ወጪ ያንረዋል፡፡

ከኤፍሬም ታምሩ የድሮ ዘፈኖች በስተጀርባ የነበሩና ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎችን ሲሰሩለት የነበሩት ይልማ ገ/አብና አበበ መለሰ የሙያቸውን ያህል ተጠቃሚ እንዳልነበሩ ግልፅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት ዓመታት በኩላሊት ህመም ሳቢያ ታሞ የነበረው አበበ መለሰ አስቀድሞ በስራዎቹ ጥሪቱን ለመያዝ ባለመቻሉ እጁን ለእርዳታ ለመዘርጋት መገደዱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ለአበበ መለሰ ክብር ሲባል የተለያዩ ድምፃውያን የተሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት ሲዘጋጅ ኤፍሬም ታምሩ የኮንሰርቱ ተሳታፊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አለኝታነቱን አለማሳየቱ በብዙዎች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ ጉዳይ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ኤፍሬም ግን በእነዛ ዘፈኖች በየኮንሰርቱና በውጪ ሀገር በሚዘጋጁ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ በመቅረብ ከፍተኛ ከሚባሉት የኮንሰርት ተከፋዮች መሀከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ አንዳንድ የሙዚቃ ባለሙያዎች እነ ይልማ በሙያቸው ተገቢውን ክፍያ ማግኘት ያለባቸው ሰዓት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ከስራዎቻቸው መሀከል በሲዲ ያልወጡትን ለብቻ መርጠው ከሚሰሩ ድምፃውያን ጋር በልዩ ድርድር የተሻለ ክፍያ በማግኘት ምናልባትም የመጀመሪያ ስራውን ሰርተው ሲሰጡ ያልተከፈላቸውን ክፍያ ሊያገኙ ይችላሉ ይላሉ፡፡

የትርፍና ኪሳራ ስሌት ኤፍሬም ታምሩ የአሁኑን የይልማ ገ/አብን የክፍያ ጥያቄ መነሻ በማድረግ እንደ ከዚህ ቀደሙ ግጥሙን በሌላ ገጣሚ ለመተካት የሚችልበት ዕድል ያለ አይመስልም፡፡ በመሆኑም ከይልማ ጋር ተደራድሮ ችግሩን መፍታት እስካልቻለ ጊዜ ድረስ አልበሙ ህዝብ ጆሮ የመድረስ ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው፡፡ በተለይም ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ከአንድ ነጠላ ዜማ በቀር /ከጎሳዬ ጋር የተሰራው ባላገሩ/ በቀር ከህዝብ ርቆ ለከረመው ኤፍሬም ይህንን አልበም በማናቸውም መልኩ ለአድማጭ ሳያደርስ መቅረት ሁኔታውን አስቸጋ ሪ ያደርግበታል፡ ፡ኤፍሬም አዲስ አልበም ለመስራት የጀመረ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ አዲስ አልበም ከሁለትና ከሶስት ዓመታት በፊት ለማውጣት ከባድ በመሆኑ ሁኔታው ለኤፍሬም ታምሩ አጣብቂኝ መሆኑን የሙዚቃ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የኤፍሬም አልበም በቀድሞ የሮሃ ባንድ አባላት በሀገር ቤት ተገናኝተው የሰሩት ሲሆን ከቀድሞው የባንዱ አባል ሰላም ስዩም ብቻ በሀገር ውስጥ ባለመኖሩ የተቀረፀው ድምፅ ተልኮለት በአሜሪካ ሀገር ለብቻው ሊድ ጊታሩን እንደተጫወተና በጥራት እንደተቀረፀ ታውቋል፡፡ የኤፍሬም አዲስ አልበም ከ70ሺ ኮፒ በላይ ይታተማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ህጉ ምን ይላል?

‹‹የሥነ ጽሑፍ የኪነጥበብ እና ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎች የአንድ ሀገር ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ልማትን በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው፤ የሚበረታቱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የሥነ ፅሁፍ የኪነጥበብና ተመሳሳይ የፈጠራ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ተዛማጅ መብቶችን በህግ እውቅና መስጠትና ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀጽ 55/01 መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ዐዋጅ አንድ የሙዚቃ ስራ ተሰርቶ ታትሞ ለአድማጭ ሲቀርብ የፈጠራ ስራ ባለቤቶቹ እነማን እንደሆኑ የሚያከራክርበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ክርክሩ የሚመነጨው የፈጠራ ስራው አብዛኛውን ጊዜ በድምፃውያኑ ስም ሲጠራ ስለሚሰማ ነው፡፡ በሀገራችን ፀድቆ ስራ ላይ ያለው የቅጂና የተዛማጅ መብቶች አዋጅ ግን የአንድ የሙዚቃ ስራ የፈጠራ ባለሙያዎች እነማን እንደሆኑና የጥቅም ተጋሪነታቸውም እስከምን ድረስ እንደሚሆን በግልፅ ደንግጓል፡፡ በአዋጁ መሠረት የአንድ ዘፈን ዋና ባለመብቶች የግጥምና ዜማ ደራሲያኑና ሙዚቃውን ያቀናበረው ባለሙያ ነው፡፡ድምፃውያኑና አሳታሚው ወይም ፕሮውዲሰውሰሩ የተዛማጅ መብት ተጋሪ መሆናቸውን ህጉ በግልፅ አስቀምጦታል፡፡

የግጥምና ዜማ ደራሲያኑ ስራቸውን ለአንድ ድምፃዊ ሲሰጡ የት የት ቦታና መቼ መዝፈን እንዳለበትም የመወሰንና እንደቦታው የክፍያ ዋጋ ወይም ተመን የማውጣት መብት እንዳላቸው አዋጁ ይፈቅዳል፡፡ ለምሳሌ ኤፍሬም ቀደምት ስራዎቹን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በየኮንሰርቱና በየግብዣው ላይ ሲዘፍንና ዳጎስ ያለ ገቢ ሲያገኝ ለግጥምና ዜማ ደራሲያኑ የከፈለው ገንዘብ የለም ወይም መክፈሉ አልተዘገበም፡፡አሁን ግን ኤፍሬም እነዚህን ዘፈኖች ድጋሚ በሲዲ ለማስቀረፅ ብቻ ሳይሆን መድረክ ላይ ለማቅረብ ልዩ ስምምነት ከግጥምና ዜማ ደራሲያኑ ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ ይህንን ተላልፎ አልበሙን ማውጣት የፍትሐብሔር ብቻ ሳይሆን የወንጀል ተጠያቂነትንም እንደሚያስከትል አዋጁ ደንግጓል፡፡

በሌላ በኩል አዋጁ አንድን የፈጠራ የሰራ ባለሙያ ስራው በካሴት ወይም በሲዲ እንዲወጣ ከመፍቀድ ብቻ ሳይሆን በመገናኛ ብዙሃንም ላይ ሲቀርብ እንደየደራጃቸው ዋና እና ተዛማጅ ባለመብቶቹ ክፍያ የሚያገኙበት ስርዓት እንዳለ ይፋ አድርጓል፡፡ይህንን ለማስፈፀም ይቋቋማል የተባለው የኮፒ ራይት ሶሳይቲ ቦርድ ስራውን በቅርቡ ሲጀምር ዋና ባለመብቶቹ አንድ ጊዜ ለሰሩት የፈጠራ ስራ ክፍያ ከየሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ እንዲሁም ከየሆቴሎቹና ከህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና ባቡሮች ላይ ያገኛሉ፡፡ እነሱ ቢያልፉ እንኳ ወራሾቻቸው ክፍያውን ይቀበላሉ፡፡

የሌሎች ሀገሮች ልምድ

የኪነጥበብ ባለሙያዎችን የፈጠራ ሥራ መዝግቦ በመያዝ ለሙያተኞች ተገቢ የሆነ ክፍያ በማበጀት በር ከፋች ተደርጋ የምትወስደው አሜሪካ ነች፡፡ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ጀምሮ እያደገ የመጣውን የፖፑላር ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ፈር ለማስያዝ የተለያዩ ህጎችን በማውጣት ትታወቃለች፡፡ በአሜሪካ የመጀመሪያ የፌዴራል መንግስት የኮፒራይት copy right Act of 1790 የተባለው የረቀቀና የፀደቀው እ.ኤ.አ በ1790 ነው፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላም በአሜሪካ ጃዝ ሙዚቃ ራሱን ከቤተክርስቲያን መዝሙር በመለየት የተሻለ ተደማጭ መሆን ችሏል፡፡ የአሜሪካ የኮፒራይት ህግ በየጊዜው እየተቀያየሩ ከሚወጡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንፃር የመብት ጥበቃ እየተሻሻለ የሄደ ሲሆን በዋናነት የኮፒራይትና ሮያሊቲ ክፍያው የሚመለከታቸው ወገኖች በግልጽ ተለይተው የተቀመጡበት ነው፡፡
የሙዚቃ ደራሲያን ሮያሊቲ ማንኛውም የሙዚቃ ስራ ከተቀረፀ በኋላ ለአድማጭ በመድረክ ሲቀርብ ወይም በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ሲሰራጭ ክፍያ ለባለቤቶቹ ይከፈላል፤ በዚህ ረገድ ዘፈኑን በተለያየ መልኩ የሚጠቀሙ ወገኖች ይኖራሉ፡፡ የመጀመሪዎቹ ዘፈኑን መድረክ ላይ ደግመው የሚጫወቱ ሲሆኑ የመድረክ ክፍያ (performing right) መክፈል ይጠበቅባቸዋል- በተጫወቱት ቁጥር፡፡

ለዚሁም ተብሎ ከመድረክ ላይ የሚጫወቱ ሰዎችንና ኮንሰርት የሚያዘጋጁ ድርጅቶችን የሚቆጣጠር የመድረክ ክወና ማህበር (the performing Right Society) የሚባል ማህበር አላቸው፡፡ ማህበሩ ከየኮንሰርቶቹ ላይ ለሚቀርቡ ዘፈኖች ፈቃድ በመስጠት፤ ለቀረበው ዘፈን ክፍያ በመሰብሰብ ለሚመለከታቸው ባለቤቶች ክፍያ ይፈፅማል፡፡ ማህበሩ በዋናነት ከሚከታተላቸው የመድረክ ስራ ማቅረቢያ ቦታዎች መካከል የሙዚቃ አዳራሾች፣ የምሽት ክለቦች፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ስታዲየሞች ማንኛውም የመድረክ ሥራ የሚቀርብባቸውን ቦታዎች ይከታተላሉ፡፡

የሬዲዮና የቴሌቪዢን ጣቢያዎችም በቀጥታ የሙዚቃ ስርጭት በሚያቀርቡበት ወቅት ለማህበሩ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡ ማህበሩ አስቀድመው የኮንሰርቱ አዘጋጆች ለመጫወት ፈቃድ የጠየቀባቸውን ሙዚቃ ዝርዝር መሰረት ማቅረባቸውን ከሬዲዮ ወይም ከቴሌቪዢን ላይ በመቅዳት ይከታተላቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፊልምና የቪዲዮ ካምፓኒዎችም ዘፈኖችን በፊልማቸው ውስጥ መጠቀም ከፈለጉ ከማህበሩ ፈቃድ የማግኘት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህ በፊልም ውስጥ የሙዚቃ ሥራን የማቅረብ መብት የጥምረት መብት (Synchronisation right) ተብሎ ይታወቃል፡፡’

ሁለተኛው የመብት አይነት የቀረፃ መብትን (Mechanical right) ይባላል፡፡ ምንግዜም ሙዚቃ ተደማጭ ሊሆን የሚችለው በቀረፃ ባለሙያዎች አማካይነት ተገቢውን ጥራት ጠብቆ ሲቀርብ በመሆኑ ይህንኑ ሥራ በሚሰሩና በማብዛት ሙያ ላይ ከተሰማሩ ሰዎች የሚሰበሰብ ክፍያ አለ፡፡ ይህንን ክፍያ የሚሰበስበው ደግሞ የቀረፃ መብት ጥበቃ ማህበር (The Mechanical Copy right Protection Socity) ነው፡፡

ይህ ማህበር አንድን ወጥ የሙዚቃ ስራ በተለያዩ መንገዶች በማብዛት ለህብረተሰቡ ከሚያደርሱ ድርጅቶች ላይ ተሰብስቦ ለአሳታሚዎች የሚከፋፈል ነው፡፡ ይህ የፈጠራ ስራዎችም የመጠቀም መብት ተግባራዊ ለማድረግ የቴክኖሎጂው በየጊዜው መቀያየር አፈፃፀሙን አስቸጋሪና ውስብስብ አድርጎታል፡፡ በተለይም የሶፍትዌሮች መበራከትና ለቁጥጥር እጅግ አስቸጋሪ ሆነው መውጣት ጋር በተያያዘ ብዙ የአውሮፓ ሀገራት የአርቲስቶቻቸው ዘፈኖች መብት ለማስጠበቅ እየተቸገሩ እንደሆነ ይታያል፡፡

በተለያዩ ድረገፆች ላይ ሙዚቃዎችን የሚሞሉና ለአድማጭ ኮፒ እንዲያደርገው ሁሉ የሚፈቅድ የኢንተርኔት መረቦች የቁጥጥር ስራውን ፈታኝ አድርጎታል፡፡ እንግሊዝ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከድረ ገፆች ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠር European copyright Directive የተሰኘ ማንዋል ያፀደቀች ቢሆንም አሁንም ድረስ በተለይ በእጅ ስልኮች ላይ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ከማባዛት ማቆም አልተቻለም፡ ፡ ይሄ የቴክኖሎጂ ውስብስብነት በአፍሪካምለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑ እየታየ ነው፡፡

The post የኤፍሬም ታምሩ አልበምና ውዝግቡ – ያልተሰሙ አንዳንድ አዳዲስ መረጃዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 261 articles
Browse latest View live