Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live

“እከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ”ይናገራል

$
0
0

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዩን አካባቢ አንቀጸ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ በልጅነቱ ከገጠር በእንግድነት ወደ ቤታቸው የሚመጡ ሰዎችን ያነጋገር ዘይቤ ለማስመሰል በመጣር ለቤተሰብና ለት/ቤት ጓደኞቹ ሲያሳይ ጎበዝ በርታ የሚል አስተያየት በማግኘቱ ወደ ኪነ ጥበቡ እንዲሳብ ምክንያት እንደሆነው ይገልፃል፡፡ የዚህ እትም የመሿለኪያ አምድ እንግዳችን ሁለገብ አርቲስት የሆነው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ንብረት ገላው ነው፡፡
nibret gelaw
በፈረንሳይ ኪነት ውስጥ የገጠሩን የሀገራችንን የቋንቋ ዘዬ ሲሰራ ያየው አንድ ሰው ከአብረሃም አስመላሽ ጋር እንዲገናኝ ያደርገውና ኢትዩጲያ ሬዲዩ ገብቶ ለመስራት እድሉን ይከፍትለታል፡፡ ከዚህ በኋላ በበርካታ በቴሌቭዥንና ሬድዮና የማስታወቂያ ስራዎች ላይ በድርሰት፣ አዘጋጅነትና በትወና ሰርቷል፡፡ ለአብነትም ሬድዮ ፋና ላይ በራሱ የቴአትር ፕሮሞሽን ስር በሚያቀርበው ‹ብሩህ ተስፋ› በተሰኘ አካል ጉዳተኞች ላይ በሚያተኩር ፕሮግራም ላይ ‹ጅረት› የተሰኘ ሃምሳ ሁለት ተከታታይ ክፍል ያለው ድራማ ደራሲ፣አዘጋጅ፣ተዋናይ በመሆን ፣ፖፕሌሽን ሚዲያ ሲያስተላልፈው በነበርው ‹መንታ መንገድ› የሬድዮ ድራማ ላይ በትወና፣ ኢትዮጲያ ሬድዎ የቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ከአብረሀም አስመላሽ ጋር ለረጅም ዓመት ጭውውት በማቅረብና በለያዩ የሲኒማ ፊልሞችና የመድረክ ቲያትሮች ላይ ሰርቷል፡፡

ንብረት ገላው በተለይም በህዝብ ዘንድ በደንብ ያስተዋወቀውና ተወዳጅ ያደረገው በአሁኑ ወቅት ማክሰኞ ማታ በኢትዮጲያ ቴሌቨዥን በሚቀርበው ‹ቤቶች› የቤተሰብ ኮሜዲ ድራማ ላይ በሚጫወተው ‹እከ› የተሰኘ ገፀ ባህሪ ነው፡፡ መጽሔታቸንም ‹ከእከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ› ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡

ቁም ነገር፡- አንድ ሰው ምች መታኝ ቢልህ ምን ትመክረዋለህ?
ንብረት፡- ምስክር ነበር? ብዬ እጠይቀዋለሁ፡፡ ለመክሰስ! /…ሳቅ/፤ ወይም ከቻልከው ሂድና ግጠመው ነው የምለው ፤እና እኔ ሄጄ ልጣላለት ኖሯል!

ቁም ነገር፡- በሀገራችን የቤት ሰራተኞችና የጥበቃ ሠራተኞች የሚገባቸውን ያህል ቦታ ተሰጥቷቸዋል ብለህ ታምናለህ ?
ንብረት፡- በፍጹም! እኔ እንደውም አንዳንድ ጊዜ አረብ ሀገር ከፎቅ ላይ ተጣሉ ምናምን እያልን ስናማርር አንድ ቀን ግን ለምን ራሳችንን ዞር ብለን አናይም እላለሁ፡፡ እዚህም አገር ላይ እንኳ በገዛ ወገኖቻቸው ሰራተኛቸው ላይ ምግብ ቆልፈው የሚሄዱ፣የሚደበድቡና እንደውም ሰራተኛ ሊቀጥሩ ሲሉ ትማራለች ከተባሉ የማይፈልጉ ሞልተዋል፡፡ በጣም የሞላና የተረፋቸው ውሻቸውን በቂቤ እያሻሹ በጣም በሚያሳፍር ሁኔታ ለዘበኛቸው ከውሻ ያነሰ ምግብ የሚሰጡ አሉ፡ ፡ በዛው ልክ ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ሰዎች እንደውም ለቤተሰባቸው እስከ መዳር የደረሱ ጥሩ ሰዎችም ገጥመውኛል፡፡ አሁን እኔ የምናገረው እንደ ሙያዊ አስተያየት አይወሰድብኝና ቤቶች ላይ የምናየው ግንኙነት ትንሽ ለቀቅ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው የሚሰራው የኮሜዲ ስራ ስለሆነ በታሪኩ ውስጥ የሰራተኞቹ ከቤተሰቡ ጋር ያላቸው ግኑኙነት እንደዚህመሆኑ ወሳኝ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ እንጂ እንደዛ መሆን አለበት ማለት አይደለም፡፡

ቁም ነገር፡- ገበጣ ፣ዳማ ፣ካርታ ልዩነታቸው ምንድ ነው ?
ንብረት፡- ምን አይነት የሚገርም ጥያቄ ነው የምጠይቂኝ? ገበጣና ዳማ የኢትዩጵያ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ በቅርቡ እንደውም አንድ ጥናት ላይ ተሳትፌ ነበር ፤‹የባህል ስፖርቶቻችን ለምን ቀሩ?› የሚባል እና ዳማም ኢትዮጵያ ውስጥ ጥንት ነገሥታቶች ይጫወቱት ነበር የሚልነገር አለ፤ ስለ ካርታ ግን አላውቅም፤ የሚመስለኝ የፈረንጆቹ ጨዋታ ነው ፡፡ እኔ እንደውም ካርታ ሲነሣ ቁማር ቀመስነቱ ነው ትዝ የሚለኝ (ይቅርታ ይደረግልኝና) /…..ሳቅ/፤ልዩነታቸው ካርታ በወረቀት ነው፡፡ ገበጣ በድንጋይ ነው በጠጠር፤ዳማም ጠጠር አለው፡፡

ቁም ነገር፡- ከቤቶች ድራማ ጋር በተያያዘ የገጠመህ ነገር አለ?
ንብረት፡- ምን የማይገጥመኝ ነገር አለ ?ብዙ ነው፡፡ ድንገት ስጠየቅ አይመጣልኝም እንጂ፤አሁን እኔ ቤቶች ድራማ ላይ ልክ በቀረፃ ወቅት ልብሱን አንዴ ከለበስኩ በኋላ እራሱን እከን የዘሩ ሞላ ዘበኛ ነኝ፤ ማንም ይምጣ ማንም
ትዕግስት ታደለ
በዚያ ገፀ ባህሪ ውስጥ ሁኜ ነው የማዋራው፡፡ እና አንዳንዴ በቀረፃ ወቅት ሐያት አካባቢ ነው የምንቀረጽበት ቤት፤እየሰራን እንዳለ ቁራሌው የሚሉ ይመጣሉ፣ ልዋጭ የሚል ይመጣሉ፤ የዛኔ ድምጹ ይረብሸናል፤ እኔ እረፉ ልል እወጣለሁ፤‹እባካችሁ ሥራ ይዘን ነው ዝም በሉ› ስላቸው ‹ባክህ አንተም ዘበኛ ነህ እኛም ቁራሌው› ይሉኛል፡፡ እንዲሁም እከን ሲያዩ በጣም የሚገረሙ ሰዎች አሉ፤በቅርቡ መኪናዬን አስነስቼ ስሄድ አንዲት ልጅ የእውነት በመገረም ዘበኛው እኮ ነው፡፡ በሚል ስትገረም አየኋት፤ ልክ ዘበኛ ሁኜ የባለቤቱን መኪና ሰርቄ እንደምነዳ አድርጋ ነው የቀወጠችው፤ እንደዚህ አይነት ነገሮች በተደጋጋሚ ይገጥሙኛል፡፡

ቁም ነገር፡- ሰዎች ወሽመጤን በጠሰው፤ ወሽመጤ ተበጠሰ ሲሉ እንሰማቸዋለን ፤ለመሆኑ ወሽመጥ የትኛው የአካላችን ክፍል ነው?
ንብረት፡- ብዙ ቦታ ወሽመጥ እንዳለ ላስብና፤ አንደኛው ብብት ላይ አለ ወሽመጥ /….ሳቅ/፤ ሁለተኛው ደግሞ እግርና እግር መካከል ውስጥ ወሽመጥ አለ፡፡
ቁም ነገር፡- በምድር ላይ ስትመለከተው እጅግ የሚያስደንቅህ ነገር ምንድ ነው?
ንብረት፡- ሰው ነው የሚያስደንቀኝ ነገር፡፡ እግዚአብሔር ሰውን እንዴት አድርጎ ፈጠረው የሚለው ነገር ያስደንቀኛል፡፡ በነገራችን ላይ እኔ ይሄ ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው የሚል ሳይንስ አይመቸኝም ፡፡ እንደዚህ አይነት ሳይንስን ሲያንስ ነው የምለው፤እግዚአብሔር ሰውን ምን ያህል ቢወደው ነው እንዲህ አድርጎ የፈጠረው እላለሁ፡፡ ከፈጠረው በኋላ ጥበብን ጥግ ድረስ ሰጠውና፤ አሁን አውሮፕላን ላይ ሆነን ስናይ አቤት የሰው ልጅ ስራ እንላለን፡፡ ግን ሰው መፍጠርና አንዲት ጣታችን እንኳን ተቆርጣ መልሶ መፍጠር አልቻልንም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው መፍጠር ያስደንቀኛል፡፡

ቁም ነገር፡- እከን ብዙ ህፃናት ይወዱታል፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስልሀል?
ንብረት፡- አዎ እኔ ብዙ ጊዜ ሕፃናት ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ አውቃለሁ፤ ልክ ስገባ ይጮኻሉ፤ ይህንን እንግዲህ እኔ ክብር ለእግዚያአብሔር ብዬ ማለፍ ነው የምችለው፡፡ ምክንያቱም የእከን ገፀ ባህሪ አይተሽው እንደሆን የሚጮህ ነገር ነው፣ ጀው ጃዋ ዓይነት ነገር ነው፡፡ ሕፃናት ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰውን የመፍራት ነገር ነው ብዙ ጊዜ የሚታይባቸው፤ የግርቢጥ ብዬ ልገልጸው እችላለሁ በአማርኛ እከን ወደውታል፡፡ እውነቱን ለመናገር ልጆች ላይ በትወና ግብት ማለት ይከብዳል፤እንደ አዋቂዎቹ አይደለም ነገሩ፤ማለት የምችለው ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ፕሮዳክሽኑን የጀመረው ጥላሁን ጉግሳ ወዳጄ በጣም ጀግና ሰው ነው ለኔ፤ወቅታዊ ኮሜዲ ተከታታይ ድራማን በድፍረት የጀመረ ሰው ነው፡፡ ከዛ ውጭ አዘጋጁ ይታገሱ ገስጥ ተጫኔና ሌሎችም ከፕሮዳክሽን ጀርባ ያሉት በሙሉ የነሱ አስተዋጽኦ እከን እንዲወደድ አድርጎታል፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወትህን የምትመራው በዕቅድ ነው? ወይስ እንደ አመጣጡ?
ንብረት፡- እኔ ምን አስዋሸኝ? እንዳመጣጡ ነው የምኖረው /….ሳቅ/፤ የምን ዕቅድ ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ከሞት በኋላ ቀጣዩ ምዕራፍ ምን ይመስልሀል?
ንብረት፡- እኔ ሰማያዊቷን እየሩሳሌምን እወርሳለሁ፡ ፡ ምክንያቱም እየሱስ ሞቶልኛል፡፡
ቁም ነገር፡- ከሰማኸው ውሸት ውስጥ በጣም ያስገረመህ ውሸት አለ ?
ንብረት፡- እንዴ ብዙ ውሸት፤እኔም እራሴ ስኖር ውሸታም ነኝ፤ዓለም እንዳለች በውሸት የተሞላች ነች፤ ስለዚህ የትኛውን ውሸት ለይቼ ልንገርሽ?
ቁም ነገር፡- አይዶል ላይ ተወዳደር ብትባል በምን ብትወዳደር ይሳካልኛል ትላለህ ?
ንብረት፡- በድብድብ! /….ሳቅ/ የሚችለኝ ካለ ይምጣ ፡፡

ቁም ነገር፡- የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ ሲባል ምንድን ነው ወደ አዕምሮህ የሚመጣው?
ንብረት፡- ማድረግ ይቻላል፤ በጣም ቀላል ነው፡፡ እኔ ክርስቲያን ስለሆንኩ እግዚያአብሔር ሟችን በገነት አኑርልኝ እላለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ምን ይመጣብኛል መሰለሽ? ሰው አይደለሁ! ተንኮልም ወደ አዕምሮዬ ይመጣብኛል፡፡ በአካባቢሽ ያሉ ሰዎች ሀሳብሽን ሊሰርቁት ይችላሉ፤አንዳንዱ የሆነ ተመስጦ በራሱ ሙድ ውስጥ የሚገባ ሰው አለ፣ሀሜት የሚጀምርም ሰው አለ፤እነዚህ እነዚህ ነገሮች ሳይ ሐሳቤ ሊሰረቅ ይችላል፤ከራሴ ህሊና ጋር ስሆን ግን የሞቱትን ነፍስ ይማር እላለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የዝና ጥቅሙ ይታወቃል፤ ጉዳቱስ ምንድን ነው?
ንብረት፡- እንደፈለጉ አለመሆን ፤ሰው በመሆን የምትፈጽሚያቸው ስህተቶች አሉ፤ አንዳንድ ጊዜ፤ያን ማድረግ አይቻልም፡፡ እኔ ግልፍተኛ ነበርኩኝ፤ያንን አሁን እህ….. ብዬ እተወዋለሁ፤ እንደምንም ችዬ እና ተወጣጥሬ፤ ይቺ በጣም ከባድ ነች፡፡ አንድ ጊዜ ከመገናኛ ጀምሮ አንድ መኪና መንገድ እየዘጋብኝ እየዘጋብኝ ይመጣል፤እኔም ችዬ ዝም አልኩት፡፡ መጨረሻ ላይ አልፌው ወደ ባልደራስ ጋር ልዞር ስል መልሶ ከፊቴ መጣና ተናገረኝ፤ተናድጄ የሆነ ኃይል ቃል ስናገረው በአካባቢው ከነበሩት ጎረምሶች መካከል አንዱ ‹ኧረ እከዬ አንተም ስድብ› ሲለኝ ‹ሂድ እኔ ሚካኤል ነኝ› አልኩት /..ሳቅ/ ይቺ ይቺ ናት ጉዳቷ፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወት ምን አስተማረችህ ?
ንብረት፡- ብዙ ነገር፡፡ እኔ ነገን አላውቃትም ፤በእግዚያአብሔር ቸርነት እዚህ እንደደረስኩ አውቃለሁ፤ ተንገላትቼ ነው ያደኩት፤የረሐብ ጥጉን አውቀዋለሁ፤ከዛ ደግሞ አግኝቼ በግል ሄሊኮፕተር አልሄድኩም እንጂ የመዝናናት ጥጉንም አይቻለሁ፤ ስለዚህ ህይወት ከዚህ በላይ ምንም ልታስተምረኝ አትችልም፡፡ ከዚህ በኋላ ከኔ ምን ይጠበቃል የሚለውን ለማድረግ ነው የምጥረው፤ እንደሰው ስህተት ብሰራም አሁን ለህይወት ዋጋ እሰጣለሁ፤ታላላቆቼን አከብራለሁ፣ማህበራዊ ጉዳይ ላይ በደንብ እሳተፋለሁ፣እንደ አንድ አርቲስት በአካል ጉዳተኞች ላይ የኢትዮጵያ የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ብሔራዊ ማህበር አምባሳደር ነኝ፤እንደውም በዚህ አጋጣሚ መጽሔታችሁን የሚያነቡ ሁሉ ብሔራዊ ማህበሩን እንዲጎበኙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው የአዕምሮ እድገት ውስንነት የሌለበት ልጅ ላለመውለድ ዋስትና የለውም፤ማንም ሰው ደግሞ ባጋጣሚ
ድንገተኛ አደጋ ይህ እንደማይከሰትበትም ዋስትና የለውም፤ ስለዚህ ብሔራዊ ማህበራችን ከዘሪሁን ህንፃ ጀርባ ይገኛል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መስራት የሚፈልጉ ሰዎች መጥተው እንዲያናግሩኝና አብረን እንድንሰራ እላለሁ፡ ፡ እና ህይወት እነዚህን እነዚህን ኃላፊነቶቼን እንድወጣ አስተምራኛለች፡፡

ቁም ነገር፡- የመጀመሪያ ፍቅር ከሁለተኛው በምን ይለያል?
ንብረት፡- አዎ! ብዙ ሰው እንደዚህ ይላል፡፡ ስለዚህ እንደዚህ የሚሉትን ጠይቂያቸው እኔ አላውቅም /..ሳቅ/ ስለሁለቱም ፡፡

ቁም ነገር፡- በልጅነትህ በባህሪህ ምን አይነት ልጅ ነበርክ ?
ንብረት፡- በልጅነቴ ቀይ ልጅ ነበርኩ /…ሳቅ/፤በባህል ታንፆ የማደግ ነገር ነበር ቤተሰባችን ውስጥ፤ይህ ማለት ስማር እራሱ የመጀመሪያ ትምህርቴ ሀ. ሁ ነው ፤ፊደል ተማርኩት ለጥቆ አቦጊዳ ከዚያ መልዕክተ ከዚያ ደግሞ ዳዊት ደገምኩኝ፤ እንደዚህ እያልኩ መደበኛ ትምህርት ቤት ስገባ እንደ አሁኑ ዕውቀት ተኮር መመዘኛ ሳይሆን እጄን ጭንቅላቴ ላይ አድርጌ በእጄ ተቃራኒ በኩል ያለውን ጆሮዬን ንካ ተብዬ በቃ ደርሷል ተብሎ ነው የገባሁት፡፡ በባህሪዬ የተረጋጋሁ ልጅ አይደለሁም ፤ቶሎ አኩራፊ ነኝ፣ትንሽ ደግሞ ተደባዳቢ ቢጤም ነበርኩኝ፤ቶሎ ውጤት ፈላጊ ልጅ፣ ብዙ የምጠይቅ ነበርኩ በአጭሩ /..ሳቅ/፡፡

ቁም ነገር፡- ከዘሩ ሞላና አዛሉ ለቤተሰቡ ይበልጥ የሚያስበው ማነው?
ንብረት፡- ለኔ ሁለቱም እኩል ናቸው ፡፡ ዘሩ ሞላ ስናየው ዝም ብሎ ቋጣሪ ስግብግብ ይመስላል፤የሚንገበገበው ግን ለልጆቹ ነው ፡ ፡ ዘሩ በአሳማኝ ወጪ ብቻ የሚያምን ሰው ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን አሳማኝ ወጪዎችን ጭምር መሸወድ የሚፈልግ ሰው ነው /..ሳቅ/ ፤ለመኖር ደግሞ ይሄ አስፈላጊ ነገር ነው ፡ ፡ አሳማኝ ያልናቸውን ነገሮች ትተን ወደፊት ደግሞ በርከት ብሎ ከዛ ይበልጥ አሳማኝ ነገሮች ሲመጡ ለነዛ ልናውላቸው እንችላለን፤እና ዘሩ ሞላ እንደዚያ አይነት ሰው ነው ፡፡ ደግም ነው፡፡ እከን ያህል እንቅልፋም ሰውዬ፣ትርፌን ያህል ሆዳም ሴትዮ፣ሻሼን ያህል ምላሳም ይዞ መኖር እንደቤተሰብ አባል፤ የዘሩን ደግነት ነው የሚያሳየው፡፡ አዛሉንም ካየናት ቀለል ያለች እናት ነች፡፡

ቁም ነገር፡- ሀገራችን በቀላሉ ከድህነት መውጣት ያልቻለችው ለምን ይመስልሀል ?
ንብረት፡- ለምዳው ነዋ! /…ሳቅ/ ፤ ለምዳው ነው የሚለው ቃል ከማሳቅ አንፃር ይታይልኝና፤እኔ ትልቁ ምክንያት ብዬ የማስቀምጠው ሰው ላይ አልተሰራም ፡፡ ከድህነት ለመውጣት ሰው አለማም ፡፡ የመስራት ባህላችን የደከመ ነው፡፡ ድሮ ይህችን ሐገር ቅኝ ግዛት ሊያደርጓት የፈለጉ ፈረንጆች ስለቱን የሚሰራውን ቀጥቅጦ ጎራዴውን የሚያበጀው፣መቆፈሪያውን ፣ማልሚያውን የእርሻ መሳሪያውን የሚሰራውን ቀጥቃጭ እያሉት፣ ሸማ የሚሰራውን ቡዳ ነው እያሉ፣ሸክላ የሚሰሩትንም እንደዛው እያሉ ማንነታችንን ወሰዱት፤ እኛም እስካሁን ቁጭ ብለናል ስንሰዳደብና ስንጣላ እንዲሁ አለን፡፡ አሁን ያለው ትውልድ ደግሞ በዘመናዊ እውቀት ሄደዋል ለመረጃም ቅርብ ናቸው፤ግን የማንነት ችግር በጣም አለ፡፡ ኢትዩጵያዊ የሚባለው ነገር በጣም ያሰጋል፤ በኪ ነጥበብ ስራዎቻችን ላይም የራሳችን የሆኑ ብዙ የሚሰሩ ታሪኮች እያሉን የውጭ አድናቂ ሆነናል፡፡ ሙዚቃችን ፣ፊልሞቻችን ፣የመድረክ ቴአትሮቻችን በውርስ ትርጉም እየተጨናነቁ ነው ያሉት፡፡ እና እነዚህ ነገሮች ተንከባለው ተንከባለው የሆነ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳይደርሱ እፈራለሁ፡፡ ክፉ ትንቢትም እየተናገርኩ አይደለም ስለዚህ ሰው መልማት አለበት እላለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- በመጨረሻ የጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄ ነው የቀረን፤ የመጀመሪያው የአጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ደራሲ ማናቸው?
ንብረት፡- አላቃቸውም፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡

The post “እከ ደከ ማን ችሎት በብልጠቱም ሆነ በጉልበቱ ከወንድ በላይ አበጀ” ይናገራል appeared first on Zehabesha Amharic.


ቤዛዊት ገሰሰ እንደጃፓኗ ቆንጆ ሆና ለጥላሁን ገሰሰ በዘፈን የሰጠችው ምላሽ (ያድምጡ)

$
0
0

ነብሱን ይማርና “ሩቅ ምስራቅ ሳለው” ሲል የሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ ጃፓን ላለችው ቆንጆ ፍቅሩን በዘፈኑ ገልጾ ነበር:: ለዚህ ተወዳጅ ዘፈን ቤዛዊት ዘለቀ እንደጃፓናዊቷ ሆና ለጥላሁን ገሰሰ በ2011 አካባቢ ምላሽ ሰጥታው ነበር:: ይህን ምላሽ ብዙ ሰው ጆሮ አልደረሰ ይሆን በሚል ከ4 ዓመታት በኋላ ለ እሁድ ረፍት ቀንዎ መዝናኛ እንዲሆን ጋብዘናችኋል:: ያድምጡና አስተያየትዎን ያስፍሩ::

tilahun

The post ቤዛዊት ገሰሰ እንደጃፓኗ ቆንጆ ሆና ለጥላሁን ገሰሰ በዘፈን የሰጠችው ምላሽ (ያድምጡ) appeared first on Zehabesha Amharic.

“የምኖረው ለልጆቼ ነው”–አርቲስት ገነት ንጋቱ

$
0
0

የዛሬዋ እንግዳ በሀገራችን አሉ ከሚባሉ ሁለገብ አርቲስቶች መካከል አንዷ የሆነችው አርቲስትና ጋዜጠኛ ገነት ንጋቱ ነች፡ ፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ በጋዜጠኝነት ፣ በትወናና ዝግጅት በርካታ ስራዎችን ሰርታለች፡፡ በይበልጥ ግን በብዙዎች ልብ ውስጥ ለመግባት ያስቻላት ‹ውሳኔ› የተሰኘው ፊልም ሲሆን በ ‹ሰው ለሰው› ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማም ድንቅ ብቃቷን አሳይታለች፡፡ ጋዜጠኛና አርቲስት ገነት ንጋቱ ‹ገነት የኪነጥበብ ፕሮሞሽን› የተሠኘ የማስታወቂያ ድርጅት ያላት ሲሆን በFM 96.3 ሬድዮ ጣቢያ ይተላለፍ የነበረ ‹አሸወይና› የተሠኘ ፕሮግራም ታቀርብ ነበር፡፡ ከቁምነገር መጽሄት ጋር ተጨዋውታለች::
Genet
ቁም ነገር፡- ከተጫወትሻቸው ገጸ-ባህሪያት ውስጥ ውስጥሽ የቀረ ንግግር የቱ ነው?
ገነት፡- ውሳኔ ፊልም ላይ ልጆቼን (የፊልሙን ልጆች ) ለተለያዩ አሳዳጊዎች ለመስጠት የወሰንኩበት ምሽት ላይ የነበረውን ንግግርን ከትወናው በጣም አስታውሰዋለሁ፡፡ ልጆቹ በጋራ ምግብ እየበሉ ሁለቱ ወንዶች ልጆች በአጥንት ሥጋ ይጣላሉ ፤ ያንን ያየችው እናት ‹እኔ በህይወት እያለሁ እንደዚህ የሆናችሁ ሳልኖር ምን ልትሆኑ ነው? › ስትል የት ልትሄድ እነንደሆነ ከልጆቿ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ‹‹ እሩቅ ሀገር ፤ ሁላችሁም አንድ ቤት ትሄዳላችሁ ፤ በጣም የሚወዷችሁ እናትና አባት ፡፡ ጥሩ ቤት ፣ጥሩ ልብስ፣ ጥሩ ተውምህርት…….›› እያለች በእንባ ስርቅርቅ የሚቋረጥበት ቦታ ሁሌም በውስጤ አለ፡፡

ቁም ነገር፡- ወላጆች ለልጆቻቸው ማውረስ አለባቸው የምትይው ትልቁ ነገር ምንድነው?
ገነት፡- በራስ መተማመን ፤ፍቅርና ትምህርት ፡፡ ልጆች ሦስቱን ነገር በሚገባ ከያዙ የራሳቸው ጌቶች ይሆናሉ፡፡ ፍቅር ቤተሰባዊና ማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ ቀስ በቀስ የሚገነባ ነው፡፡ ወንድምና እህቶች እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱና እንዲተሳሰቡ ከተደረገ ከማህበረሰቡ ጋርም ሲቀላቀሉ ፍቅር እንጂ ሌላ ተቀጽላ ባህሪ አያሸንፋቸውም ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ከቤት ከጓዳ ይጀምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ትርፉ ብዙ ይሆናል ፡፡ይህ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ቢቀርብ ለድርድር የማይቀርብ ነገር ነው፡፡ ብርሃን ፈንጣቂ አማራጭ የሌለው በራስ የመተማመን መሰረት ነው፡፡ ትምህርትና ፍቅር በለጋ ዕድሜያቸው ላይ ከመገብናቸው በስተእርጅናቸውም አይቸገሩም፡፡ ከእግዚያብሔር ጋር ሁሌም አሸናፊ ይሆናሉ፡፡ ቀና ብለው መሄድም ይችላሉ፡፡

ቁም ነገር፡- የሴት ልጅ ዕድሜና የወንድ ልጅ ደሞዝ አይጠየቅም የሚባለው ለምንድን ነው?
ገነት፡- እም…. ምናልባት ስለምንፈራ ይሆን? አንዳንዴ ከእግዜር ጋር ሁላ የሚያጣላ ይመስለኛል፡፡ ‹ይሄን ያህል ዕድሜ ስለሰጠኸኝ አመሠግናለሁ› ማለትን የምንፈራ ሁላ ይመስለኛል፡፡ ዕድሜ ሰጭና ነሺም እሱ እያለ ፣እኛ የሱን ሀብትና ስጦታ ለመናገር አለመፈለግ ሁሌም ነው እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ! እንደሚታወቀው በእያንዳንዱ ዓመት አንድ አንድ ዓመት እድሜአችን ላይ መደመራችን እንደሆነ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ የወንድ ልጅ ደመወዝ አይጠየቅም ላልሽኝ እኔም “ለምን አይጠየቅም ?” የሚል ጥያቄ ነው የማነሳው፡፡ በነገራችን ላይ ይህን አባባል ማን እንዳለው ባውቅ ኖሮ መልሼ
እሱን /እሷን እጠይቅ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- መጀመሪያ የትወና ሥራ የጀመርሽው የት ነበር?
ገነት፡- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዬን በምሰራበት ጊዜ ነው የሰራሁት፡፡

ቁም ነገር፡- ቆጮ እንዴት ይዘጋጃል
ገነት፡- በነገርሽ ላይ የቆጮ አፍቃሪ ናቸው ከሚባሉት ሰዎች መሃል አንዷ ነኝ፡፡ በልጅነቴ አሰላ እያለሁ በግቢያችን ውስጥ ይዘጋጅ ነበር፡፡ እድሜ ጠገብ የሆነ የኮባ ተክል መረጣ ጀምሮ ፣ አቆራረጡን፣ እግር ሰቅሎ በመክተፊያ ላይ የሚደረገውን የአፋፋቅ ሁኔታ ፣ የጉድጓድ አዘገጃጀት እና አቀባበር ፣ የተብላሎት እድሜውን፣ ለመጋገር ሲፈለግ ከጉድጓድ ወጥቶ እንዴት ተከፍቶ እና ቃጫው ወጥቶ ንፁህ ሊጥ የሚገኝበትን ጊዜ በሂደት ልነግርሽ እችል ነበር፡፡ ጊዜ ስለሌለን እንለፈው እንጂ፡፡ ሊጡ ከወጣ በኋላ በሚገባ ውሃ ጠብ እየተደረገ ከታሸ በኋላ በኮባ ወይም በገጠር አካባቢ በራሱ የቆጮ መጋገሪያ ስጋጃ ላይ ተጠፍጥፎ ወይ በኤሌክትሪክ ምጣድ አልያም በብረት ምጣድ የሚጋገርበት ሂደትን በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ገነትን ምን ያዝናናታል?
ገነት፡- ከልጆቼ ጋር የማሳልፈው ጊዜ ለእኔ ዓለምን የጨበጥኩ እስኪመስለኝ ድረስ በደስታ፣ በእርካታ የምቦርቅበት ጥዑም ጊዜዬ ነው፡፡ ከወላጆቼ፣ ከወንድምና ከእህቶቼ ጋር የማሳልፈውንም ጊዜ እደሰትበታለሁ፡፡ አረንጓዴ የበዛበት ተፈጥሮአዊ ቦታ መኪና ነድቼ በመሄድ ብቻዬን በተመስጦ በሃሳብ የማሳልፈውን ጊዜ ማን ይቀማኛል? . . . . በጣም እወደዋለሁ፡፡ በወረቀት መሀል ተከብቤ መቀመጥም እንዲሁም መዝናኛዬ ነው፡፡ ትወናም እግዜር ለመዝናኛዬ አስቦ የሰጠኝ ሌላው መክሊቴ መሆኑ እግዜርን የማመሰግንበት አጋጣሚ ይፈጥርልኛል፡፡

ቁም ነገር፡- ልጆቼ ባይጠይቁኝ እመርጣለሁ የምትይው ጥያቄ አለ?
ገነት፡- ልጆቼ የፈለጉትን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው የማምንና በወቅቱም በደስታ መልስ የምሰጥ እናት ነኝ፡፡ ነገር ግን ከጥያቄ ከምትይኝ እርስ በእርሳቸው እየተጣሉና እየተደባበደቡ ለስሞታ ወደ እኔ የሚመላለሱበት የድግግሞሽ ሰዓት አጥብቄ እጠላዋለሁ፡፡ ልጅ ሆኜ ከወንድሞቼ ጋር እየተደባደብኩኝ እናትና አባቴን ምን ያህል እንዳታከትኳቸው እንዳስብና ለትዕግስታቸውም ክብርና አድናቆትን እንድሰጣቸው ያስገድደኛል፡፡ በተለይ ሐሳቤን በሰበሰብኩበትና በንባብ ወይም በድርሰት ፅሁፍ ላይ እያለሁ ሲሆን፤ ንዴቴ በእጥፍ ይጨምራል፡፡ ግን በቃ እናት አይደለሁ! የመቻል ሞራላዊና ፍቅራዊ ግዴታ ስላለብኝ ለማቻቻል እሞክራለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ስምንተኛው ሺህ ሲገባ ዓለም ትጠፋለች በሚለው ታምኛለሽ?
ገነት፡- እሱ ነገር ልጅ ሆኜ ጀምሮ ስሰማው ነው ያደግኩት! እስካሁን አላለፈም እንዴ? መቼም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ ስምንተኛው ሺህ ማለት የዓለም መጨረሻ ነው፡፡ ለእኔ እንደገባኝ የዓለም መጨረሻ ማለት ደግሞ የምድራዊው ዓለም መጨረሻ ነው፡፡ ከዛ ሰማያዊው ዓለም ይቀጥላል፡፡ እንደሚመስለኝ ሰዎች ስምንተኛው ሺህ የሚሉት የምድራዊ ዓለም መጨረሻን ጊዜ ነው፡፡ የክርስቶስ መምጣትን፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ድንገት እንደ ሌባ ነው የምመጣው ስላለ ስምንተኛው ሺህ መቼ እንደሆነ ማወቅም መገመትም አይቻልም፡፡ ያኔ ግን ዓለም ትጠፋለች ማለት ሳይሆን አሁን የምንንኖረው ምድራዊ ህይወት አይኖርም ማለት ነው፡፡ ይሄ የዓለም መጥፋት ከሆነ ትርጉሙን አንቺ እንደዛ በይው፡፡

ቁም ነገር፡- ደስታ እንዴት ይገኛል?
ገነት፡- አንቺ አዕምሮ ውስጥ፡፡ ለኔም አዕምሮዬ ውስጥ ነው፡፡ ለነ እርሱም አዕምሮአቸው ውስጥ ነው ያለው፡ ፡ ደስታን ከገበያ ገዝተሽ አትደሰችበትም፡፡ ሁላችንም ባለን ነገር መደሰት ከቻልን ፣የምንደሰትበትን ቦታና ጊዜ ከመረጥን ደስታ የኛ ነው፡፡ ሁላችንም በመዳፋችን ጨብጠን የምንዞረው የቀና አስተሳሰባችን ውጤት ነው፡፡ ለእንካ ሰላምትያው፣ ለትርኪሚርኪውና፣ ለመንደርተኛው አስተሳሰብ ቦታ ካልሰጠን የደስታችንን አጥር አጥብቀን ከያዝነው ደስታ ከዚያ ነው፡፡

ቁምነገር፡- ምን ያህል ዓመት መኖር ትፈልጊያለሽ?
ገነት፡- የእግዜሩን ለእግዜር ትቼ፤ እኔ መኖር የምሻው ልጆቼን አስተምሬና ለቁም ነገር አብቅቼ ኃላፊነቴን ከትከሻዬ እስከማወርድበት ጊዜ ነው፡፡ እስከዚያ እግዜር ጨክኖ ባይወስደኝ ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ለልጆቼ ነው የምኖረው፡ ፡ ከዚያ ለእናትና አባቴ፤ ለምን ብትይኝ እነሱ ቀደም ሲል ለእኔና ለወንድም እህቶቼ ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ ዕድሜም ለምነዋል፡፡ የእኔ መኖር በእነሱ ዕድሜ ላይ በጎ ተጽእኖ አለው፡፡ አየሽ ልጅ ከመጣ በኋላ መኖር ያጓጓል ፡፡ እነሱ መርጠውኝ ሳይሆን በእኔ ፈቃድ ምድር ላይ ለመጡ ልጆቼ ከእግዜር ቀጥሎ የማኖር ፣የማድረግ ፣ለቁም ነገር የማብቃት የእነዚህ ሁሉ ነገሮች ዋስትና በእኔ እጅ ስላለ ይዤባቸው ቶሎ አልሙትባቸው፡፡

ቁም ነገር፡- በሃገራት ስም የሚጠሩ የሰው ስሞችን የትኞቹን ታውቂያለሽ?
ገነት፡- እ . . . እየሩሳሌም፣ ኢትዮጵያ፣ ኤደን፣ ቻይና፣ አፍሪካ(ይሄ ከአህጉር መሆኑ ነው) አስመራ ወዘተ. . . ይሄ የተናገርኩት አይበቃም? ክፍል ውስጥ ለፈተና የተቀመጥኩኝ አስመሰላችሁኝ እኮ ሆ!
Mogachoch

ቁም ነገር፡- የኔ ድክመቴ ነው የምትይው ነገር ምንድነው ጥንካሬሽስ
ገነት፡- ድክመቴ ለልጆቼ ስል የማላምንበትን ነገር ሁሉ ላደርግ እችላለሁ፡፡ ከወንጀል በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ እነሱን የሚያስደስታቸው ነገር ከሆነ እንደሻማም ቀልጬ ባልቅ ህመሙ የሚሰማኝ አይመስለኝም፡፡ ልጆቼ እንደ ልባቸው የሚያዙኝ እናት ነኝ፤ አንዳንዴ ትዕዛዛቸው የግል እምነቴንና አቋሜን ሁሉ ቀስ በቀስ ሲሸረሽርብኝ ይታወቀኛል ፡፡ በራሴ ላይ በግርምት እስቃለሁ፡፡ በቃ ምን አደርጋለሁ እኔ ደግሞ አንዲት ኢትዮጵያዊ እሩህሩህ እናት ነኝ፡፡ ጠንካራ ጎኔ ነገሮችን እንደ አመጣጣቸው በተለያዩ በጎ በጎ ትርጉሞች በመለወጥ የመመለስ ፍጥነቴን እንደ
አንድ ጥንካሬ አየዋለሁ፡፡ ብዙ ሰዎችን የጎዳ፣ ያቆሰለ፣ ያሳዘነ ነገር ገነት ጋር ሲደርስ ተራና ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ቀለል የማድረግ ብቃቴ ከአባቴ የወረስኩት ባህሪ ይመስለኛል፡፡ አባቴ ጠንካራና ብልሃተኛ ነው፡ ፡ ሁሌም ቢሆን ለነገሮች ትኩረትና ጊዜ በሰጠሽ ልክ ነው የምትናደጅውም የምትደሰችውም፡፡ ከአባቴ ይህንን ተምሬያለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የፊልም ስራ አትራፊ ነው አትራፊ አይደለም?
ገነት፡- አትራፊም ነው፡፡ አትራፊም አይደለም፡፡ አገሩን እንደሚወድ ፕሮፌሽናል ባለሙያ ካሰብነው ፊልም የአገር ገጽታን፣ ባህልን፣ ቋንቋና አጠቃላይ የአኗኗር ስርዓትን አሳማኝና አስደማሚ በሆነ መንገድ ደግሞም በቦታና በጊዜ በማይገደብ ደረጃ ለትውልዶች ሁሉ የሚሸጋገር እሴት እንዲኖረው ተደርጎ መሰራት አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ ለገበያ ሲቀርብ የአትራፊነቱ ጥያቄ የሚወድቀው ለፕሮሞሽን እንደሚከፈለው ዋጋ ወይም እንደሚሰጠው ጊዜ ይለያይ ይሆናል፡፡ ፕሮሞሽን ላይ የበረታ ፕሮዲውሰር ያተርፋል እንጂ አይከስርም፡፡

ቁም ነገር፡- ባላደርገው ኖሮ ይቆጨኝ ነበር፤ የምትይው ነገር ምንድን ነው?
ገነት፡- ባልወልድ ኖሮ በደንብ ይቆጨኝ ነበር፡፡ በእርግጥ ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ለእኔ ደግሞ የልቤን መሻት ሰጥቶኛል፡፡ ዩኒቨርስቲ ባልገባ ኖሮ በጊዜ ነበር የምወልደው፤ የሚገርምሽ ልጆቼ አድገው ለእናት አባታቸው ሲያስቡ፣ ሲጨነቁና እኛን ለማስደሰት ጥረት ሲያደርጉ ሳይ ደጋግሜ “ባልወልዳችሁ ነበር የሚቆጨኝ” ብዬ የልቤን እውነት በቀልድ እያዋዛው እነግራቸዋለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ሐውልትሽ ላይ እንዲጻፍ የምትፈልጊው ነገር ምንድን ነው?
ገነት፡- እንዴ! ሐውልትሽ ስትሉኝ እኮ ሞቴን እያስታወሳችሁኝ ነው፤ ምናለ ትንሽ ብትታገሱኝ?
ቁም ነገር፡- ለማለት የፈለግኩት አልገባሽም ?
ገነት፡- አ….አ… ተይው ገብቶኛል፡፡ ለቀልድ ያህል ነው /ሳቅ…../፡፡ ምን ተብሎ ቢጻፍ እ. . ./እንደማሰብ/ “ለልጆቿ ኖራ፤ ለልጆቿ የሞተች ምርጥ እናት!” ቢባልልኝ አይከፋኝም፡ ፡ ምክንያቱም አሁን ላይ የምኖረው ህይወት በተለይ በእነሱ ፍላጎትና ትዕዛዝ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የውስጤን እውነት የሚገልጽልኝ ይመስለኛል፡፡
Mogachoch

ቁም ነገር፡- በአሁኑ ጊዜ የጋብቻውን ያህል ፍቺው በዝቷል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ በአንቺ አመለካከት ምን ይመስልሻል?
ገነት፡- በአደባባይና በጓዳ ውስጥ ያለው ማንነታችን እንደ ሳንቲም ግልባጭ
መለያየቱ ብልሽስ ? በፍቅረኝነት ዘመን ብዙ ነገር ግልጽ አይሆንም፤ ፍቅር ፍቅር እንጂ ገበና ለገበና ተገላልጦ መተዋወቅ አይታሰብም፡፡ ፍቅር ደግሞ በአደባባይ ይጣፍጣል፡፡ ያንን ይበልጥ ለማጠናከር በመጓጓት ለመኖር ይወሰናል፤ መኖርም ይጀመራል፡ ፡ ያኔ ታዲያ እርቃን ማንነታችን፣ ድብቅ ባህሪያችን ቀስ በቀስ ሲወጣ አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ በመሰረቱ ሁለት በተለያዩ ማህበረሰብ ውስጥ ያደጉ ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ሲገናኙ መጋጨታቸው አይገርምም ፡፡ የትዳር ምስጢር ያለው እዚህ ጋር ነው፡፡ ፍጹምነት ከጓደኛችን መጠበቃችን ነው ለፍቺ የሚያበቃን እንጂ የትዳር ሚስጢሩ ረቂቅ ነው፡፡ ትዳርን እርስ በእርስ በግልጽነት ላይ ከገነባነው የትዳርን ምስጢር ለሶስተኛ ሰው አሳልፈን ካልሰጠን፣ ቤታችንን ትተን የሌላ ባለትዳሮች አድናቂ ካልሆንንና ሁሌም ማደስ ከቻልን ፍቺ የት ያገኘናል?

ቁም ነገር፡- በህይወትሽ ደግሞ እንዳይመጣ የምትፈልጊው ቀን አለ?
ገነት፡- የመጀመሪያ ልጄን ስወልድ ስቃይ ብቻ ሳይሆን ወደ ሞት አምርቼ ዳግም ነፍስ የዘራሁበት ጊዜ ስለነበር ደግሞ አይምጣብኝ፡ ፡ ደግሞ ቢመጣብኝ ደስ የሚለኝ ቀን ደግሞ፤ በስቃይ የወለድኳት ቆንጅዬዋን ልጄን፤ ከህመምና ስቃይ ጋር ግብ ግብ ፈጥሬ ቀና ብዬ አይቼ ሳም አድርጌ “ስታምር!” ያልኩበትን የእርካታ ጊዜ አቤት ደስታዬ !

ቁም ነገር፡- ሁለገብ አርቲስት መሆን ጥቅሙ ምንድነው? ጉዳቱስ ?
ገነት፡- ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ ሁለገብነት የተለያዩ አማራጭ የስራ መስኮች የመፍጠር አቅምን ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ ወደ እኔ ብትመጪ በድርሰቱ ባይሳካልኝ ዝግጅት አለልኝ፡፡ በዝግጅት ውጤታማ ባልሆን፤ ትወናው ይጠብቀኛል፡ ፡ ትወናው ይቅርብኝ ብል ደግሞ ጋዜጠኝነቱ የኔ ነው፡፡ ታዲያ ምን ጉዳት ይኖረዋል ትያለሽ? ከጥቅሙ በቀር ጉዳትስ የለውም፡፡

ቁም ነገር፡- አንድ ሰው ስንት ጊዜ ያፈቅራል? አንቺስ ስንት ጊዜ ፍቅር ያዘሽ?
ገነት፡- ነፍሱ እስከፈቀደችለት ድረስ ቢያፈቅር ምን አለበት? አመንዝራነት እንለዋለን እንጂ ፍቅርን አንገድበውም፡፡ ይህ እኮ የነፍስ ምስጢር ነው፡፡ ካልኩሌሽን የለውም፡፡ ወደ እኔ ከመጣሽ ከልጆቼ አባት ጋር አንድ ሶስት ጊዜ አላፈቀርኩም ብለሽ ነው ፡፡ ፍቅር ስቃዩ ጣፋጭ ነው፤ የኔው ፍቅር ደግሞ ሂደትም ውጤትም አለው፡፡

ቁም ነገር፡- ህይወትሽን የምትመሪበት የራስሽ የሆነ ፍልስፍና አለ?
ገነት፡- የኔ ፍልስፍና በዋናነት ‹‹ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ነው›› የሚለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፤እሹ ታገኛላችሁ›› ነው፡ ፡ በእያንዳንዱ ቀን ውሎዬና አዳሬ ህይወትን በነዚህ ፍልስፍናዎች መነፅር ውስጥ ማየት ችያለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡፡

The post “የምኖረው ለልጆቼ ነው” – አርቲስት ገነት ንጋቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ነጠላ ዜማ ሊለቀቅ ነው

$
0
0

Untitled-1
(ዘ-ሐበሻ) የላፎንቴኑ ብርሃኑ ተዘራ (ያምቡሌ) ከጃኪ ጎሲ ጋር የሰራው ነጠላ ዜማ ለድል በዓል እንደሚለቀቅ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

የአደዋ ድል በዓልን ተከትሎ የሚለቀቀው ይሄው ነጠላ ዜማ በሕዝብ ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል:: ብርሃኑ ተዘራ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሲሆን ይህን ነጠላ ዜማ ለመስራት ረዥም ጊዜ እንደፈጀበትም ታውቋል::

በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ይኸው አዲስ ነጠላ ዜማ ስለሃገር ፍቅር የሚገልጽ እንደሆነም ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቋል:: በቅርቡ የአሜሪካ “ሰላ” ኮንሰርቱን አጠናቆ ወደ አውሮፓ ያቀናው ጃኪ ጎሲ በዚሁ የብርሃኑ ተዘራ አዲስ ነጠላ ዜማ ላይ የተሳተፈ ሲሆን ስራው የተዋጣ እንደሆነም ያደመጡ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል:: ሙዚቃውን ያቀናበረውም ሄኖክ ነጋሽ መሆኑን ምንጮቻችን አስታውቀውናል::

ይህ ዘፈን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሚለቀቅ ሲሆን ዘፈኑ እንደደረሰን በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እናስደምጣችኋለን:: ይጠብቁት::

The post ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ነጠላ ዜማ ሊለቀቅ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

አርቲስት ሽመልስ አበራ ለአንድ ቀን አይኑን ያጣበት ሰኔ 30 ፊልም ዛሬ ተመረቀ

$
0
0

sene 30
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው አርቲስት ሽመልስ አበራ ጆሮ ለአንድ ቀን ዓይኑን አጥቶበት የነበረው ሰኔ 30 ፊልም ዛሬ በአዲስ አበባና በአዳማ የግል ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ ተከፈተ::

አርቲስት ሽመልስ አበራ ማየት የተሳነው ሆኖ በሚሰራበት በዚህ ፊልም ላይ; የፊልም ቀረጻው ሲደረግ ዓይኑ ላይ ለቀረፃ ሲባል በገባለት ኮንታክት ሌንስ ምክንያት የዓይኖቹ ብሌኖች ተጫጭረው ለክፍተኛ አደጋ ተዳርጎ እንደነበርና ለአንድ ቀንም ቢሆን የዓይን ብርሃኑን አጥቶ እንደነበር ዘ-ሐበሻ ኖቬምበር 23 ቀን 2014 መዘገቧ አይዘነጋም::

ሽመልስ የተፈተነበት ይኸው ‹‹ሰኔ 30›› የተሰኘው ፊልም የካቲት 15 ቀን በአዲስ አበባና በአዳማ የግል ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ ለሕዝብ መታየት የጀመረ ሲሆን በተጨማሪም የካቲት 23 ቀን በአዶት ሲኒማና ቴአትር ቤት እንደሚመረቅ ለዘ-ሐበሻ ከአዲስ አበባ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

ሰኔ 30 ፊልም በኃይሉ ዋሴ ሲጻፍ; በፍቅረየሱስ ድንበሩ እንደተዘጋጀም ታውቋል:: ሽመልስ አበራ፣ ሰለሞን ሙሄ፣ አዚዛ አህመድ፣ ካሌብ ደሳለኝና ሌሎችም የተወኑበት ሲሆን ፊልሙ የፍቅር ሕይወታቸውን ለመቀጠል ወይም ለመቋጨት ለመወሰን ሰኔ 30 ቀን በተቀጣጠሩ ፍቅረኛሞች መካከል የሚከሰተውን አጋጣሚ የሚያሳይ ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ከ42 ደቂቃ እንደሚወስድ ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ጠቁሟል::

The post አርቲስት ሽመልስ አበራ ለአንድ ቀን አይኑን ያጣበት ሰኔ 30 ፊልም ዛሬ ተመረቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር በሰራው ዘፈን የተነሳ ከደህንነት ሃይሎች ማስፈራሪያ እየደረሰው መሆኑ ተሰማ * ስልኩ ተጠልፏል

$
0
0
ጃኪ እና ብርሃኑ ከሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር በስቱዲዮ ውስጥ

ጃኪ እና ብርሃኑ ከሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር በስቱዲዮ ውስጥ

ጃኪ የተቀረጸው ዘፈኑን በሄኖክ ነጋሽ ኮምፒውተር ሲያደምጥ

ጃኪ የተቀረጸው ዘፈኑን በሄኖክ ነጋሽ ኮምፒውተር ሲያደምጥ

(ዘ-ሐበሻ) ብርሃኑ ተዘራ (ብሬ ላላ) ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ወቅታዊ ዘፈን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ካተረፈ በኋላ አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ስልኩ በደህንነቶች መጠለፉን እና በስር ዓቱ ሰዎችም ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰው እንደሚገኝ ለድምጻዊው ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::

በዛሬው ዕለት ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ፃፈው በሚል “ዘፈኑን ተሰርቄ ነው; ጃኪ የፖለቲካ ዘፈን አይዘፍንም” የሚል ጽሁፍ በፌስቡክ የተሰራጨ ሲሆን ይህ ጽሁፍ በአድናቂዎቹ እንጂ በጃኪ ጎሲ አለመፃፉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: የጃኪ ጎሲ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶቹ ላይ ይህ ዜና እስከተዘገበበት ጊዜ ድረስ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር ስለዘፈነው ዘፈን የሰጠው አስተያየት የለም:: ሆኖም የድምጻዊው አድናቂዎች ዘፈኑ ካለርሱ እውቅና ውጭ የተሰራ አድርገው የለጠፉት መረጃ ብዙዎችን ከማደናገሩም በላይ በተለይ ለአራት ቀናት ጃኪ ጎሲ በዋሽንግተን ዲሲ የሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር ሄዶ ከብርሃኑ ጋር ሲቀረጽ የተመለከቱ የዓይን እማኞች “ጃኪ ለምን ይዋሻል?” የሚሉ አስተያየቶችን በየሶሻል ሚዲያው እያሰራጩ ነው:: ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በፌስቡክ ገጹ ምንም ያለው ነገር ባለመኖሩ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ ይሻላል የሚሉ ወገኖች; ጃኪ በስሙ በወጣ መግለጫ የተነሳ በስሙና በቀጣይ ሥራው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ሳያደርስበት አቋሙን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል::

ጃኪ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን የደህንነት ኃይሎች ስልኩን በመጥለፍ ከማን ጋር እንደሚያወራ እንደሚከታተሉት ዘፈኑን እንዲያስተባብል ከፍተኛ ጫና እያደረጉበት መሆኑን ለድምፃዊው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል:: ጃኪ ከዚ ቀደም “ማን እንደ ሃገር” የሚል ነጠላ ዘፈን ሰርቶ የለቀቀ ሰሞን ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የድምፅአዊው የቅርብ ወዳጅ ተወዛዋዡ አብዮት መሃል ላይ ሰማያዊ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በኪሊፕ ሰርቶ ሲለቅ ጃኪም ይህን የሙዚቃ ክሊፕ ፌስቡኩ ላይ ሼር ሲያደርግ ደህንነቶች እንዴት ሕገመንግስቱ የማይፈቅደውን ባንዲራ በክሊፑ ላይ ትጠቀማለህ? በሚል ባደረሱበት ማስፈራሪያ ከፌስቡክ ገጹ ዘፈኑን ማስወጣቱን የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ወገኖች አሁንም ደህንነቶች በሚያደርሱበት ወከባ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል::

በጃኪ ስም አድናቂዎቹ የለጠፉት አደናጋሪ የፌስቡክ መልዕክት; ይህ በጃኪ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶች ላይ አልወጡም

በጃኪ ስም አድናቂዎቹ የለጠፉት አደናጋሪ የፌስቡክ መልዕክት; ይህ በጃኪ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶች ላይ አልወጡም


በዚህ ዘፈን ዙሪያ ድምፃዊው ብርሃኑ ተዘራን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም::

The post አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር በሰራው ዘፈን የተነሳ ከደህንነት ሃይሎች ማስፈራሪያ እየደረሰው መሆኑ ተሰማ * ስልኩ ተጠልፏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች”እና ”ሞጋቾች”ድራማ

$
0
0

Mogachoch
(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ከጌታቸው በቀለ

በቴሌቭዥን የሚተላለፉ መርሐ ግብሮች አነሰም በዛም በሕዝብ ላይ የሚፈጥሩት የእረጅም ጊዜ ተፅኖ ቀላል አይደለም።በተለይ በታዳጊ ወጣቶች እና ልጆች ላይ ለነገ እነርሱነታቸው የሚጭረው ስሜትም ሆነ አለማቸውን እና አካባቢያቸውን የሚመለከቱበት ዕይታ የጠበበ አልያም የሰፋ ወይንም የተንሸዋረረ የመሆን እድሉ ትልቅ ነው።እዚህ ላይ ወላጆች ለልጆቻቸው ከቴሌቭዥን መርሃ ግብር በኃላ የሚሰጡት የማስተካከያ ሃሳብ ወይንም ልጆችም ሆኑ ወጣቶች ጉዳዩን የሚያዩበትን እይታ ቀላል አይደለም።

የኢትዮጵያ ተለቭዥንን በሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጭነት ተአማኒነቱ የወረደበትን ደረጃ ለመግለፅ ህዝቡ ”የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እውነት የምናገረው ሰዓት ብቻ ነው” የሚለውን አባባል መግለፁ ብቻ በቂ ነው።ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ በመገናኛ ብዙሃንነት የቆየ የቴሌቭዥን ጣብያ በእዚህ አይነት ደረጃ የወረደ የመረጃ ምንጭ መሆኑ እንደ ኢትዮጵያዊነት በጣም ያሳዝና።ዛሬ ቢልልን ኖሮ ኢቲቪ በመላው ዓለም ባሉ ከተሞች ወኪሎች በኖሩት እና በቀጥታ የሚዘግቡ ዘጋቢዎች በኖሩት ነበር። ይህ ደግሞ ከወጭም አንፃር ብዙ አለነበረም።ምክንያቱም በመላው ዓለም እንደመበተናችን በነፃ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ማግኘት ከባድ አይደለም።ነገር ግን አለመታደል ሆኖ አምባገንነት፣ጎሰኝነት እና ሙስና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደጠረነፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ቴሌቭዝንም አንዱ ሰለባ ነው።ኢትዮጵያውያን ግን በሀገር ቤት የታፈነ ድምፃቸውን በቸልታ አላዩትም።በጥቂቶች አስተባባሪነት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በመላው ዓለም እና በሀገር ቤት ላሉ ወገኖቻችን ብቸኛው ነፃ የመገናኛ ብዙሃን ለመሆን በቅቷል።

የእዚህ አጭር ማስታወሻ አላማ ስለ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታሪክ ለማውራት አይደለም።ስለሚያቀርባቸው ሳምንታዊ ድራማዎች ግን ትንሽ ማለት ፈለኩ።የቴሌቭዥን ድራማዎቹን ምግብ እየበላሁም ሆነ መንገድ ላይ ባለኝ ክፍት ጊዜ እመለከታቸዋለሁ።ይህንን የማደርገው መዝናኛ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውን የሀገር ቤትን ማኅበራዊ፣ስነ-ልቦናዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ስለሚያንፀባርቁልኝ ነው።የድራማዎቹን የመሃል እንቡጥ መልእክት ፈልፍላችሁ ለማግኘት ስትሞክሩ (በስድስተኛው የስሜት ህዋስ ማለቴ ነው) ብዙ ጠቃሚ እና ጎጂ ጎኖቹን ለማየት አያስቸግራችሁም።
በስድስተኛው የስሜት ህዋስ የሶስቱ ድራማዎች እይታ

እዚህ ላይ በቴሌቭዥን ከሚቀርቡት ድራማዎች ውስጥ የሁለቱ ማለትም ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ላይ የማነሰው የጠለቀ ሂስ አለመሆኑን እና ያንን ለማድረግ የሙያው ክህሎት እንደሌለኝ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።ነገር ግን ድራማዎቹ በህብረተሰባችን ላይ ያላቸው አሉታዊ እና በጎ ተፅኖ ላይ ሃሳብ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
1/ ”ቤቶች” ድራማ

ይህ በየሳምንቱ ቅዳሜ ምሽት የሚቀርበው ድራማ በብዙዎች ዘንድ በአስቂኝነቱ የሚጠቀስ እና በርካታ ተመልካች ያለው መሆኑ ይታወቃል።አመታዊ ዝግጅቱን ሲያዘጋጅም የሚመለከቱት ተመልካቾች በርካታ መሆናቸውን ያሳያል።እንደ እኔ አስተያየት ድራማው ከማዝናናት ባለፈ ሊያስተምር የሚገባው በርካታ ነገሮች ይቀሩታል።በመጀመርያ ደረጃ ታሪኩ አንድ በግንብ በታጠረ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ ዙርያ ያጠነጥናል።ቤተሰቡን መካከለኛ ገቢ ያለው ቤተሰብ ለማለት ይከብደኛል።ምክንያቱም መካከለኛ ገቢ የሚባለው ሕብረተሰብ አሁን በራሱ ጠፍቷል።ከሃያ ሶስት አመታት በፊት አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር መሬት ተመርቶ ቤት የመስራት አቅም ነበረው።ዛሬ ቤት ለመስራት ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ውስጥ የሚመደብ ካልሆነ አይታሰብም።እናም ድራማው ውስጥ የሚተውኑት ቤተሰብ አባላት ቢያንስ ባለ ሁለት ሰራተኛ እና አንድ የጥበቃ ግለሰብ የሚተዳደሩ ናቸው እና መካከለኛ ከሚለው እናውጣቸው።እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ95% በላይ በእንደዚህ አይነት ኑሮ የሚኖር አይደለም።አዲስ አበባ ብቻ የግል መፀዳጃ የሌለው የሕዝብ ብዛት ከ70% በላይ እንደሆነ ከተገለጠ እሩቅ አይደለም።በመሆኑም ድራማው ተጨባጩን የሀገራችንን ሕዝብ ኑሮ አይወክልም።ይህ ግን ድራማውን ያስወቅሰዋል እያልኩ አይደለም።ጥቂቶችም ብዙሃኑ ግብር በሚከፍልበት ቴሌቭዥን እርስ በርስ ሲጨዋወቱ መመልከት በራሱ ድራማ ነውና።
Tilahun Gugsa
በእዚህ ድራማ ላይ ”ይቤ” ገፀ ባህሪ ይዞ የሚጫወተው ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ ለወጣቱ ምን ያስተምራል? ብዬ ስጠይቅ በገፀ ባህሩ ላይ ባብዛኛው አሁን በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ አንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ የሚኖረውን መልክ ይዞ ታገኙታላችሁ።ይቤ በድራማው ላይ ይጠጣል፣ይቅማል፣የተለያዩ የሴት ወዳጆች አሉት፣የሚናገረው የተደበላለቀ ማለትም ”ከአራዳ አነጋገር” እስከ እንግሊዝኛ የተደባለቁ፣ኢትዮጵያዊነት በሙሉ የጠፉበት ሆኖ እናገኘዋለን።በነገራችን ላይ ይቤ መሃንዲስ ነው እና የነገ ኢንጅነሮቻችን የሚቅሙ፣የሚያጨሱ ናቸው በመሆኑም መስርያቤቶች ከመሃንድሶች ጋር ሲሰበሰቡ የጫት በጀት መያዝ አለባቸው ማለት ነው።

ቤቶች ድራማ ሶስት መስተካከል ነበረባቸው የምላቸው አቀራረብ አይቼበታለሁ

የመጀመርያው በቅርቡ የታየው ነው ታሪኩ እንዲህ ነው።ሁለቱ የቤት ሰራተኞች ቡና እያፈሉ ሳሉ የቤት ጠባቂው ዘበኛ ያገኘውን ዱቄት መሰል ነገር ፍሙ ላይ ሲጨምሩት እና በቤቱ ውስጥ የነበሩት በሙሉ ሲሰክሩ ያሳያል።እንደ ድራማው አገላለፅ ለካ የጨሰው አደገኛ ዕፅ ነበር።ሙሉ ድራማው በወቅቱ ቀጥሎ ያሳየን ነገር ቢኖር አንድ እፅ የወሰደ ሰው ምን እንደሚታየው፣ለምሳሌ ድመት ዘንዶ እንደሚመስለው፣ሰዎች ትልቅ ሆነው እንደምታዩት በተግባር እያሳየ ትውልዱን አሰለጠነ።የሚገርመው ድራማው የእፅን አስከፊነት ሳይሆን አዝናኝነት ነው እስኪበቃን የነገረን።እፅ ያጨሱት በፖሊስ ሲያዙ እና ሲቀጡ ሳይሆን የአደገኛ እፅን አዝናኝነት ለታዳጊ ወጣት ሁሉ ተነገረው።ይህንን የተመለከተ ወጣት ”አንድ ቀን ልሞክረው” እንዲል አድረገው አቀረቡለት።ይህ ክፍል ከታየ ገና ወራት አልተቆተሩም።በአድዋ በዓል ላይ ሸለላችሁ ብሎ ያገደ ፖሊስ ያለው መንግስት በተለቭዝኑ የእፅ አወሳሰድ ስልጠና ሲሰጥ ማየት ያሳምማል።

ሁለተኛው፣ ቤተሰቡ ለሽርሽር ከሄደባቸው ቦታዎች አንዱ ቅዱስ ላሊበላን ያሳየናል።በቅዱስ ላሊበላ ቅፅር ውስጥ በአካል ቤተሰቡ ቆሞ የሚሰጠውን ገለፃ ያዳምጣል።በእምነት ቦታ በመሰረቱ የቀልድ ድራማ መስራት አስቸጋሪ ነው።ድራማው ላይ ግን ሃይማኖታውም ሆነ ታሪካዊ ገለፃ ሲሰጥ በመሃል የፌዝ እና የቀልድ ንግግሮች ይሰሙ ነበር።ይህ እንግዲህ በመሃል ከሚገባው የሳቅ ጋጋታ ጋር አብሮ ነው።የእምነት ቦታዎች የሚሰጣቸው ቦታ እና በአማኙ ዘንድም ሆነ በታዳጊ እና ወጣቶች ዘንድ የሚያሳድረው ተፅኖ ፈፅሞ አልተጤነም።ቅዱስ ላሊበላ ከመጎብኘቱ ባለፈ የከበረ ቀልድ የማይነገርበት ቦታ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነበር።በሌላ በኩል ግን የድራማው አላማ ሀገርህን እወቅ በሁሉም ቤተሰብ መለመድ አለበት የሚለውን ሃሳብ በማንፀባረቁ የሚደገፍ አይደለም እያልኩ አይደለም።ለእምነት ቦታዎች የማይባሉ ቀልዶች ቀላቀለበት እንጂ።

ሶስተኛው የድራማው አቀራረብ የገጠሩን የሀገራችንን ገበሬ ለከተማው ወጣት የሚስልበት የተሳሳተ አቀራረብ ነው።የቤቱ ዘበኛ ሁል ጊዜ እንቅልፍ በጣም ወዳጅ፣ምግብ የሚወድ፣ሥራ የማይወድ እና ግዴለሽ አድርጎ የሚስልበት ገፀ ባህሪ የኢትዮጵያን ገበሬ ፈፅሞ አይወክልም።የኢትዮጵያ ገበሬ እንቅልፍ የለውም ከማለዳ እስከ ምሽት ሲለፋ ውሎ ማታ የቀረውን ሥራ በመስራት የሚጠመድ፣ንቁ፣በሥራ የሚያምን፣ላመነበት የሚሞት እና ለወዳጁ ሟች ነው።ይህንን የህብረተሰብ ክፍል ነው እንግዲህ ለሕዝቡ ”ሎሽ ማለት ብቻ የሚወድ” ተብሎ የሚቀርበው።ይህ በእራሱ ከቀልድ ባለፈ ብዙ ማህበራዊ ነገሮችን የሚነካ ነው።በኮሜዲ ፊልሞች ላይ ገፀ ባህርያት የተለያዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን እያነሱ ያስተምራሉ እንጂ በኢትዮጵያ ገበሬ ላይ የሚሳለቅ አቀራረብ ይዘው እና ከገበሬው የምንማረው እንቅልፍ ብቻ የመሰለ አቀራረብ ማንንም አይጠቅምም።

እዚህ ላይ የቤቶች ድራማን አንዳንድ ግድፈቶች እና ማስተካከል የሚገባቸውን አቀራረቦች ላይ ሃሳብ ለመስጠት ፍለግሁ እንጂ በደፈናው ድራማውን ለማጣጣል እንዳልተነሳሁ ይታወቅልኝ።ድራማ ከአዝናኝነቱ ባለፈ ወጣቶችን በስነ-ምግባር፣በሀገር ፍቅር ስሜት እና በቅን ለሀገር መስራትን የሚያስተምር ካልሆነ በሳቅ ማንከትከትን ብቻ አላማዬ ብሎ ከተነሳ ስለ እፅ አወሳሰድ የሚያሰለጥነን ከሆነ አደገኛ ነው።ላሰምርበት የምፈልገው ለሕዝብ የሚቀርቡ ድራማዎች በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ አማካሪዎች ያስፈልጋቸዋል።ደራሲው ”ህዝብን ካሳቀ እና መንግስትን እስካላሳቀቀ ድረስ መንገዱ ሰላም ነው” በሚል አስተሳሰብ ብቻ አየር ላይ ማዋል የለበትም።

”ሞጋቾች” ድራማ

ከእዚህ በአንፃሩ በ”ኢቢኤስ”ቴሌቭዥን የሚቀርበው ”ሞጋቾች” የተሰኘው ድራማ ጥሩ፣አስተማሪ እና ትውልድን የሚያንፅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ሞጋቾች በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ የህክምና ዶክተሮች እንዴት ህዝባቸውን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ እና በማህበራዊ ኑሮአቸው ውስጥ የሚገጥማቸውን ተግዳሮት ያሳያል።የሞጋቾች ድራማ በፊልም አቀራረፅ እና የድምፅ ጥራቱ ብቻ ሳይሆን የመረጡት ሆስፒታል ተራው ሕዝብ የሚገለገልበትን እና እታች ያለው ሕዝብ የሚላቸውን አባባሎች፣ስሜቶችን ሁሉ የሚያንፀባርቅ አቀራረብ ይታይበታል።እዚህ ላይ ማስታወሻዬ አጭር ከመሆኑ አንፃር ባጭሩ ”ሞጋቾች”ድራማ ሶስት ነገሮችን ለአዲሱ ትውልድ እንደሚያስተምር ጠቅሼ ሃሳቤን ልግታ።

1/ ተምሮ በሀገር መስራትን እና ወገንን ማገልገልን
በድራማው ብዙ ክፍሎች ላይ የሚታዩት አቀራረቦች በዶክተር ደረጃ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ምን ያህል እታች ላለው ሕዝብ እንደሚጨነቁ እና ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ያሳያል።

2/ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ በአንድ ወቅት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆና ሳላ አንድ ምሽት በተፈጠረ የምሽት ዳንስ ይመሽባትና ከሰው ቤት ታድራለች።ሆኖም በእዚችው ምሽት ተደፍራ ልጅ ትወልዳለች።ድራማው ባብዛኛው የወለደቻትን ልጅ አባት በመፈለግ ስትደክም ያሳያል።ይህ አሁን ላሉት ወጣቶች እያንዳንዱ ምሽት የምትሰራ ስህተት እና ከዋልጌ ተማሪዎች ጋር መግጠም የሚያስከፍለው ዋጋ ለአመታት የሚተርፍ መሆኑን ያሳያል።ይህም በተለይ ሴት ወጣቶች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ይመክራል።

3/ በአንድ ወቅት ችግር ቢያጋጥምም መልሶ መነሳት እንደሚቻል ያስተምራል
የድራማው ዋና ገፀ ባህሪ ባንድ ወቅት ተደፍራ ልጅ ለመውለድ ተገደደች።ሆኖም ተመልሳ ጠንክራ በመማሯ ዛሬ ለህክምና ዶክተርነት በቃች።ይህ በራሱ የሚያስተምረው ትምህርት አለ።ወጣቶች ስህተት ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ግን ከስህተታቸው ተመልሰው እንደገና ተነስቶ ለቁም ነገር መብቃት ነው ዋናው ቁም ነገር ይለናል የድራማው መልእክት።

ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማዎች የረቀቀ የፕሮፓጋንዳ መስርያ አውድማ ወይንም የተበላሸ ትውልድ ማፍርያ ማሽን እንዳይሆኑ በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
የካቲት 26/2007 ዓም (ማርች 5/2015)

The post የቴሌቭዥን ድራማዎች በስድስተኛውም የስሜት ህዋሳችንም መቃኘቱን አንርሳ; የትኞቹ ያስተምራሉ? የትኞቹ መታረም ይፈልጋሉ? ”ቤቶች” እና ”ሞጋቾች” ድራማ appeared first on Zehabesha Amharic.

አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ?

$
0
0

serawit fikere
ኤልያስ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደጻፈው:
.
ሁሌም ምርጫ ሲደርስ ብቅ ብቅ የሚሉ (በኢቢሲ ማለቴ ነው!) ፊታቸው “የቁጣ አስተማሪ” የሚመስል አንዳንድ ግለሰቦች አላጋጠማችሁም? ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት እንዳይመስሏችሁ። (እነሱ አይቆጡም አልወጣኝም!) እነዚህኞቹን “የምርጫ ዬኔታ” ይሏቸዋል፡፡ ይሄ ስያሜ ለምን እንደተሰጣቸው አላውቅም፡፡ ምናልባት ቁጣ ቁጣ ስለሚላቸው ይሆን? የሚገርመው ደግሞ እየተቆጡ የሚያስተምሩን እንዴት ምርጫውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ—እንደምናደርገው ነው፡፡ (ሰላማዊ ምርጫ — በቁጣ?!)

እኔ የምለው ግን — አንዳንድ ግለሰቦች “የቁጣ ፈቃድ” አላቸው እንዴ? ወይስ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል? ከምሬ እኮ ነው—መቼም አንድ ግለሰብ (ለብቻው) 90 ሚሊዮን ህዝብን ለመቆጣት የግድ ፈቃድ ያስፈልገዋል፡፡ ፈቃድ ካለው ህግ አክባሪ ስለሆንን እንታገሰው ይሆናል፡፡ ያለዚያ ግን —- (ምንም!!)
በነገራችን ላይ —- የህወሓትን 40ኛ ዓመት በዓል እንዴት አያችሁት? እንግዲህ በዓሉ ለአንድ ወር ያህል በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ ባለፈው እሁድ ተጠናቋል፡፡(አንድ ወር አላነሰችም?) የሸገር 125ኛ ዓመት የተከበረው እኮ ዓመቱን ሙሉ ነው (ዓመትም ተንዛዛ!) አንድ ነገር ልንገራችሁ— የዘንድሮን ምርጫ ልዩ የሚያደርገው፣ የህወሐት 40ኛ ዓመት በተከበረ ማግስት በመዋሉ ነው፡፡ (የEBCን ዜና ቀማሁት አይደል!) አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ… የዘንድሮን የህወሐት በዓል ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው ብትባሉስ? (ከ40ኛ ዓመቱ ውጭ ማለቴ ነው!) ቀላል እኮ ናት! (ሮኬት ሳይንስ አደረጋችሁት እኮ!) ልዩ የሚያደርገዋ—የህወሐት የቀድሞ ታጋዮች (አሁንማ ባለ ስልጣን ሆነዋል!) ከአርቲስቶች ጋር የሆድ የሆዳቸውን ማውራታቸው ነው!! (መሞዳሞድ ሌላ ነው!)

ተቃዋሚዎች በዓሉን አስመልክቶ የሰነዘሩት ትችት ግን አልገባኝም፤ “ኢህአዴግ በዓሉን ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅሞበታል” ሲሉ ሰማሁ፡፡ (So what?) …ገና ለገና በግንቦት ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ በየካቲት በዓል ላይከበር ነው? (“ማን ላይ ቁጭ ብለሽ ማንን ታምያለሽ” አሉ!) ከዚህም የባሰውን ደግሞ ልንገራችሁ፡፡ “የህወሐት በዓል አድዋን አደበዘዘው” አሉና አረፉት! (በጉዴ ወጣ! ማለት አሁን ነው!)
በጣም ግርም ያለኝ ምን መሰላችሁ? ህወሐትም ሆነ በአጠቃላይ ኢህአዴግ እስከዛሬ ሲተቹበት የነበረው ዋና ጉዳይ —– ምስጢረኞች ናቸው፤ ሆዳቸው አይታወቅም እየተባሉ ነበር፡፡ እናም የህወሐት የቀድሞ ታጋዮች፣ 40ኛ ዓመቱን በማስመልከት ምድረ አርቲስትን ሰብስበው ደደቢት ድረስ ወሰዱ፡፡ ዋና ዋና የትግል ቦታዎችን አስጐበኙ። የትግሉን ገድል ተረኩ፡፡ ከ20 ዓመት በላይ ከርችመውት የቆዩትን ገበና ወለል አድርገው ከፈቱ። (ልብን ከፍቶ እንደ መስጠት እኮ ነው!) እና ይሄ ጥፋቱ ምንድነው? (የምርጫ ቅስቀሳ ያስብላል!?)
ዝም ብዬ ሳስበው ግን በህወሐት ላይ ለተሰነዘረው ትችት ተጠያቂዎቹ አንዳንድ ስሜታዊ አርቲስቶች ይመስሉኛል፡፡ ደደቢትን ከጐበኙ በኋላ አንዳንዶቹ በEBC ሲሰጡት የነበረውን አስተያየት ሰምታችኋል? አብዛኞቹ ባዩት ነገር የምር መደነቃቸውን ከገፅታቸውም ከአንደበታቸውም ተገንዝቤአለሁ። ጥቂቶቹ ግን ትወና ቢጤ ሳይሞካክሩ አልቀሩም (ተሰጥኦ ለመቼ ነው!) ግን እኮ ገና መጀመሪያውኑ ተነግሯቸው ነበር፡፡ “ለጉብኝቱ የመጣችሁት እንድትዘምሩልን አይደለም፤ ሁሉም ሰው ያሻውን ሃሳብ ሊይዝ ይችላል” በሚል፡፡ አንዳንድ አርቲስቶች ግን ማሳሰቢያው የገባቸው አልመሰለኝም (ቀላል ዘመሩ እንዴ!)
በነገራችን ላይ ከበረሃ ትግል ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲ ግቢ ወደ ቤተመንግስት ግቢ የመግባት ዕድል ያገኙት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በዚህ የህወሐት 40ኛ ዓመት በዓል ላይ “የታጋይነት ማዕረግ” ተሰጥቷቸዋል፡፡ (“ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም” አሉ!) ማዕረጉ የክብር ይሁን የምር ግን አልተነገረንም፡፡ የምር ከሆነ እኮ “ታጋይ ኃይለማርያም” ይባሉበታል ማለት ነው፡፡ የክብር ከሆነ ግን “የክብር ታጋይ” ነው የሚባሉት (የክብር ዶክትሬት እንደማለት!)
አያችሁ—የክብር ዶክትሬት የሚሰጠው ዩኒቨርስቲ ተገብቶ—-ትምህርት ተከታትሎ…ጥናትና ምርምር ሰርቶ — አይደለም፡፡ በተሰማሩበት ሙያ ለአገር ያበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ ተመዝኖ ብቻ ነው የሚሰጠው፡፡ ይሄም ተመሳሳይ ይመስለኛል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ታጋይ የተባሉት ለ17 ዓመት ጠብመንጃ አንግተው ስለታገሉ አይደለም፡፡ (እሳቸው ከብዕርና ከጠመኔ ውጭ ምንም አያውቁም!) እዚህ ጋ መረሳት የሌለበት ቁምነገር ምን መሰላችሁ? እርግጥ ነው አቶ ኃይለማርያም ከትግል ጋር አይተዋወቁም። እርግጥ ነው ጥይት አልተኮሱም፤ እርግጥ ነው ፈንጂም አላፈነዱም፡፡ ግን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን (መሬት ይቅለላቸውና!) ተክተው ሌጋሲያቸውን ለማስቀጠል ቃል የገቡት፣ ኃላፊነት የተሰጣቸውም ለእሳቸው ነው፡፡ (ታጋይ መባል አይበዛባቸውም!)
ለነገሩ በኢህአዴግኛ፤ ሥልጣንና ሹመትም እንደ ትግል ወይም መስዋእትነት ነው የሚቆጠረው፡፡ አቶ ኃይለማርያም፤ በጠ/ሚኒስትርነት የተሾሙ ሰሞን አዲሱን ስልጣናቸውን እንደ ትግል እንደሚያዩት መናገራቸው ትዝ ይለኛል፡፡ (አገር መምራትን እንደ ትግል ማሰብ አይገርምም?) ኢህአዴግ እኮ ልማት ማካሄዱንም፣ መልካም አስተዳደር ማስፈኑንም፣ የህግ የበላይነትን ማስጠበቁንም፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማጐልበቱንም፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ማስከበሩንም…ወዘተ (ከሀ-ፐ በሉት) እንደ ትግል ነው የሚቆጥረው፡፡ (የትጥቅ ትግል አልወጣኝም!)
አንዳንዴ ሳስበው ግን እውነቱን ነው እላለሁ፡፡ ከምሬ ነው…እነዚህ የተጠቀሱትን ጨምሮ…ኪራይ ሰብሳቢዎችን መጋፈጥ… ድህነትን ታሪክ ማድረግ… ፍትሃዊ የሃብት ሥርጭትን ማስፈን…(ሁሉንም እኩል ማደህየት እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን!) የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን ማጠናከር (“ማን ነበር አክትሞለታል” ያለው?!) ወዘተ… ቀላል ትግል እኮ አይደለም፡፡ እንዴ…ደርግን የሚያህል ግዙፍ ኃይል በትጥቅ ትግል ለመጣል እኮ 17 ዓመት ብቻ ነው የፈጀው (ትንሽ ናት አልወጣኝም!) ቀደም ብዬ ያነሳኋቸው የአገር ችግሮች ግን ይኸው ከ20 ዓመት በኋላም “መች ተነካና!” እያስባሉ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ካያችሁት .. የኢህአዴግ ሥልጣን እውነትም መስዋዕትነት የሚከፈልበት ትግል ነው ሊባል ይችላል፡፡ (ተቃዋሚዎች አልገባቸውም!)
ከህወሐት 40ኛ ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ የጀመርኩትን ወግ ሳልቋጭ ነው ወደ ትግል ትንተና የገባሁት፡፡ እናም የቀረችኝን ልጨርስላችሁ። አሁንም ጉዳዩ አርቲስቶችን ይመለከታል፡፡ (የህወሐትና የአርቲስቶችን ፍቅር ያዝልቅላቸው!?)
filfilu
በነገራችሁ ላይ ይኸኛውንም በEBC መስኮት ነው የታደምኩት (ከአንዴም ሦስቴ!) ምን መሰላችሁ? የህወሐትን 40ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለአርቲስቶች የተዘጋጀ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው፡፡ ቦታው አዳማ ይመስለኛል፡፡ ወይም እርግጠኛ ለመሆን በEBC መስኮት!!
የጥያቄና መልስ ውድድሩ “11በ11” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ለምን? አንደኛ፤ ህወኃት የተመሰረተበት ቀን የካቲት 11 ነው፡፡ ሁለተኛ፤ ጠያቂውን ጨምሮ በውድድሩ የተካፈሉት አርቲስቶች 11 ነበሩ፡፡ እናም 11 በ11 ተባለ፡፡ ምክንያቱ አላጠገባችሁም? (ደግሞ ለምክንያት!) የአሸናፊው ቡድን 5 አርቲስቶች በነፍስ ወከፍ 11ሺ ብር ነው የተሸለሙት፡፡ (የፓርቲ “ሞጃ” ይመቸኛል!) በእነዚህ ሁሉ በቂ ምክንያቶች የጥያቄና መልስ ውድድሩ “11 በ 11” ተብሏል፤ አለ – ውድድሩን የመራው አርቲስት ሸዋፈራሁ፡፡
shewaferaw
ጥያቄና መልሱ ተጀመረ፡፡ በነገራችሁ ላይ ጥያቄዎቹ በህወኃት ትግል ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ (በትንሹ የ30 ዓመት ታሪክ ማለት ነው) እኔ የምለው… የእነ ህወሐት ገድል በታሪክ ትምህርት ውስጥ ተካተተ እንዴ? (እነ ፍልፍሉ እሳት ሲሆኑብኝ እኮ ነው!) ይታያችሁ… የታጋዮች የበረሃ ስም… ህወሐት ደርግን ድባቅ የመታባቸው ዘመቻዎች፤ ቦታዎች፣ ዓመተ ምህረቶች ወዘተ ሲጠየቁ ነበር፡፡ መጠየቃቸው አይደለም የሚገርመው። መመለሳቸው ነው፡፡ ያውም እኮ ከአፍ እየነጠቁ ነበር የሚመልሱት፡፡ ቆይ… የአዲስ አበባ አርቲስትና ኮሜዲያን የህወሐትን ትግል እንዲህ የሸመደዱት መቼ ነው? ይሄውላችሁ… በመልሳቸው ፍጥነት የተገረምኩት እኔ ብቻ ብሆን ኖሮ ችግሩ ከእኔ ነው ብዬ ግለ-ሂስ አወርድ ነበር፡፡ ግን እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡

ራሱ የፕሮግራሙ አጋፋሪ፤ አርቲስቶቹ መልሱን እንደ እሳት ሲተፉበት ደንግጦ “አብራችሁ ታግላችኋል እንዴ?” አይል መሰላችሁ፡፡ (ደንግጦ አስደነገጠን!) እኔማ አውጥቼ አውርጄ ተውኩት እንጂ “ጥያቄና መልሱ …ተጭበርብሯል” ብዬ ለህወሐት ልጠቁም ዳድቶኝ ነበር (“ሃብታም በሰጠ …” እንዳልባል ፈርቼ ጭጭ አልኩ!)
ይልቅስ ምኑ ደስ አለኝ መሰላችሁ? ያሸነፈም የተሸነፈም መሸለሙ!! አሸናፊዎቹ (ቅሬታዬ እንዳለ ነው!) እያንዳንዳቸው 11ሺ ብር፤ በጠቅላላ 55ሺ ብር ሲሸለሙ፣ ተሸፊናዎቹ በነፍስ ወከፍ 5ሺ ብር፣ በድምሩ 25ሺ ብር አግኝተዋል፡፡ እኔ የምለው…አርቲስቶቹ ሽልማቱ ጥሟቸው የህወሓት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ? (ምርጫ መሰላቸው?!)

እኛም እንግዲህ ግልጽ ማመልከቻ ለሚመለከተው ወገን አቅርበን ወጋችንን እንቋጭ … የግንቦቱ አገራዊ ምርጫ እንደ ጥያቄና መልስ ውድድሩ እንዲሆን እንፈልጋለን፤ አሸናፊም ተሸናፊም የሚሸለምበት!! ያሸነፈ ደረቱን የማያሳብጥበት፤ የተሸነፈ አንገቱን የማይሰበርበት ምርጫ ያስፈልገናል። (“ታስፈልገኛለህ” አለች ዘፋኟ!)
እንኳን ለአዲስ አድማስ 15ኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

The post አርቲስቶቹ የህወሐት 40ኛ ዓመት ይደገም ቢሉስ? appeared first on Zehabesha Amharic.


ቴዲ አፍሮ ማዲንጎ አፈወርቅን ፍቅር አስተማረው

$
0
0

teddy afro

ስንታየሁ ከሚኒሶታ

በቅርቡ በጀርመን ሃገር የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅቶ በሕወሓት መንግስት ደጋፊነቱ የተነሳ ቦይኮት የተጠራበትና በኪሳራ የተመለሰው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በቅርቡ ስላወጣው አልበም ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ በሚተላለፍ አንድ ራድዮ በመቅረብ ስለድምፃዊው ዘፈን ጥሩ በማውራት ፍቅር አስተማረው::

ወ/ሮ አዚብ ትመራው በነበረው ሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ውስጥ ሠራተኛ የነበረው ማዲንጎ የሕወሓት መንግስት አፍቃሪ ከመሆኑ የተነሳ በተለይ ከመንግስት ጋር የማይተባበሩ አርቲስቶችን ልክ እንደ ሰራዊት ፍቅሬ “አቃጣሪ” በመሆን በመንግስት በማስጠመድ እና ሥራዎቻቸው በመንግስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ ሲያስደርግ ቆይቷል:: ድምፃዊው በሕወሓት መንግስት ደጋፊነቱ በመመጻደቅ ወያኔ የሰሜን አሜሪካውን አመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል ለሁለት በሰነጠቀበትና ተለጣፊ ባዘጋጀበት ወቅት በተለጣፊው ቡድን ውስጥ ሆኖ ዋሽንግተን ዲሲ በመምጣት ለከፍተኛ ኪሳራ ተጋልጦ ነበር::

ማዲንጎ በተለይ ቴዲ አፍሮ ታስሮ በነበረበትም ወቅት ሆነ ከተፈታ በኋላ በሰራው ጥቁር ሰው አልበም ዙሪያ ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር በመሆን የማጣጣል ተግባር ሲፈጽም የቆየ ቢሆንም ፍቅር ያሸንፋል የሚለው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ስለ ማዲንጎ አፈወርቅ አልበም አስተያየት ስጥ ሲባል ስለአልበሙ መልካም ነገር ከመናገሩም በላይ በተለይም ጎዳናው የሚለው ዘፈን መልካም እንደሆነ በራድዮ ቀርቦ በመናገር ለድምፃዊው ፍቅር ምን እንደሆነ አስተምሮታል::

ጎንደር ተወልዶ ያደገው ማዲንጎ የሕወሓት መንግስት ደጋፊ በመሆኑ የሚመጻደቅ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ ከኢሕ አዴግ በላይ ማንንም መልካም መሪ አታገኝም ሲል ገንጣዩን መንግስት የሚደግፍ አርቲስት ነው::

The post ቴዲ አፍሮ ማዲንጎ አፈወርቅን ፍቅር አስተማረው appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኢንተርኔትና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ ”ጥበቡ ወርቅዬ የቀድሞ ድምፃዊ፣ የአሁኑ ዘማሪና ሰባኪ

$
0
0

አቤንኤዘር ጀምበሩ

ጥበቡ ወርቅዬ አገልግሎት ለመታደም ወደ ቤዛ ቤተ/ክ በ06/07/07 ዓም ተገኝቼ ነበር። ምንም እንኳ ዝግጅቱ 8:00 ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ጥበቡ ቦታው የደረሰው ከዘጠኝ ሰዐት በኃላ ነበር። ጥቤ የቀድሞ አስታይለኛ አለባበሷ አና ፍሪዟ እንዳለች ነው፣ ፊቱ ላይም ላቅ ያለ የደስ ደስ ስሜት እና መመቸት ይታይበታል። ለአድምተኛው ምንም አይነት ቀረፃ ማድረግ አንደማይፈቀድ ከተላለፈ በኋላ ፣ ጥሪ ተደርጎለት ወደ መድረክ ሲወጣ የነበረው ህዝብ ቆሞ እያጨበጨበ እና እየጮኸ ሲቀበለው “አለማዊ” መድረክ ስራዎቹን ሳያስታውሱት የቀሩ አይመስለኝም።

በኋላ ላይ እራሱ እንደገለፀው “እዛ በታለንትና በድፍረት፣ እዚህ ግን በቅባት” ብሏል። ዝማሬን በሚያቀርብበት ወቅት በሙዚቃ ህይወቱ የሚታወቅበት መልካም ቃና ያለውን ድምፁን ወደ መዝሙር ቀይሮታል፣ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ያሉ መሸጋገሪያዎች ላይ የለመዳቸው የሙዚቃ መግቢያዎች ሲጐትቱት ታዝቤያለሁ። ለምሳሌ አንድ ጊዜ “ነይ ነይ” ብሎ ወዲያው “ሃሌሉያ” አድርግዋታል። የመዝሙር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ቃል ማካፈል ሲያልፍ፣ የትምህርቱን መነሻ ያደረገው ሐዋሪያት ስራ ምእራፍ 2 ላይ ስላለው የበአለ ሀምሳ ክብረ በአል ላይ ነበር። ጥበቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን መገንዘብ አያዳግትም፣ እንዲሁም ለእምነቱ ከፍተኛ ቅንአት እንዳለውም ጭምር። ይህም የሚያመለክተው ከፍተኛ ጊዜውም በመፅሐፍ ንባብ ላይ እንደሚያሳልፍ ነው። እራሱም እንደገለፀው ለሶስት አመት ተኩል በር ዘግቼ ጨለማ ቤት ጭምር በንባብና በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ አሳልፌያለሁ ብሏል ።
tibebu workiye

“አንዳንዶች ይመለሳል ይሉኛል፣ ግን ወዴት ነው የምመለሰው” ሲልም አፅእኖት ሰጥቷል። ምንም እንኳን ጥቤ ጥሩ አንዳነበበ አና መረዳት አንዳለው መገንዘብ ቢቻልም፣ በማስተማሩ ረገድ ግን የአቅም ውስንነትና ድፍረት እንደሚስተዋልበት ደፍሮ መናገር ይቻላል። በተለይ ባሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታን ፣ ከተጨባጭ ገሃዳዊ ሁኔታዎች እና ከስነ ልቦናዊ ዝግጅት ጋር አያያዙ የሚስቡ ትምህርቶችን ማዘጋጀት በአለም ሁሉ ላይ ባሉ የፕሮቴስታንት ቤተ/ኖች የሚንፀባረቅ ነገር ነው። እንዳየሁት የቃሉ መረዳት ቢኖረውም ከላይ የተጠቀሱት ክህሎቶች ጐድለውት ተመልክቻለሁ። ትምህርቱ ባብዛኛው ረድፍ ያልጠበቀ እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ነገሮችን መልሶ የመናገር፣ ወይም ትንታኔያዊ አስተምሮ ያለማቅረብ ሁኔታዎች ታዝቤያለሁ። ዘማሪው በትምህርቱ ወቅት የተለያዩ ነገሮችን አንስቷል፣ በአለማዊ ህይወቱ በተለይ በጫት ሱስ እጅጉን እስረኛ አንደነበረ ፣ቄማ ላይ እያሉ ከአርቲስቶች ጋር አብዝቶ ይጋጭ እንደነበር “አይወደኝም፣ ሌላ ሰው ባጠፋው ጭምር እኔ ነበርኩ የምሰደበው፣ ሰይጣን የሱ አንዳልሆንኩ ያውቅ ስለነበር ነው። ” ብሏል።

አርቲስቱ ድሮ በመቃብር አካባቢ እንኳን ሲያልፍ እጅጉን ይሸበር እንደነበርና አሁን ግን በራሱ አገላለፅ “በኮንፊደንስ ነው” ሲል ተደምጧል። ለሱ ከአለም ለመውጣት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደነበርና ብዙ የሚይዙ ነገሮች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። “የሙዚቃ ዝና፣ ሙዚቃቤት፣ ቁጥሩ የበዛ የሙዚቃ መሳሪያና ሌሎችም ነበሩ” ብሏል። ወደ ጌታ ከመጣ በኋላ መንፈሳዊ ክንውኖቹን ሲናገር፣ 1900 በላይ ሰዎችን ወደ ጌታ አንደመለሰ (የመገናኛ ብዙሃን የተጠቀሙትን ሳይጨምር) ፣ ትልልቅ አርቲስቶችን ሰብስቦ አንደመሰከረ፣ ወደ ጌታ አንደመለሰ እንዲሁም ብዙዎች በመንገድ ላይ እንደሆኑ ገልፅዋል። ሌላው አሁን አሁን በአንዳንድ ድህረ ገፆች ላይም እንደሚታየው ተአምራዊ አገልግሎቱ ነው።

ከንግግሩ መረዳት የሚቻለው እነዚህ እነዚህ አገልግሎቶች ሁሉም ቤት እንዲገቡ ይፈልጋል ፣ በቃሉም “ካሁን በኃላ ኢንተርኔትንና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ” ብሏል። በቅዳሜው አገልግሎት በስራ ማጣት የተፀለየላት ወጣት ፣ ስራ ማጣቷ መንፈሳዊ ተግዳሮት እንደነበር እና በፀሎት ወቅት ጮሆ ሲወጣ በዛው ቅፅበት አቤቷ ስልክ ተደውሎ ለስራ መጠራትዋን እሱ ሲናገር አሷ እጇን በማውለብለብ በእሁዱ ፕሮግራም አረጋግጣለች። እንዲሁም እሱ ፀሎት ያደረገላቸው ሰዎች በእንቅልፍ ወደ መንግሥት ሰማያት ደርሰው እንደተመለሱ ጠቅሷል፣ በስልክ ልውውጥ አጋነንትን እንዳስወጣም ጭምር። ትላልቅ አርቲስቶች ላይ ያለ መሪ መንፈስ ሲመታ መንጋው ይበተናል የሚለው አርቲስቱ፣አሁን ላይ ብዙ አርቲስቶች አንደሚደውሉለት እርሱም አንደሚፀልይላቸው መስክሯል። ሌላው የገረመኝ ነገር በትልልቅ ዘፋኞች ስም የተሰየሙ አርኩሳን መናፍስቶች መኖራቸውን መግለፁ ነው፣ ምድራዊ ህግ ስለማይፈቅድ እንጂ ቢጠራቸው እየጮሁ ወደ አርሱ እንደሚመጡ ገልፅዋል። ድምፃውያኑ አንደ ኮካ በስማቸው የተሰየሙ መናፍስት መኖራቸው አያስገረመኝ፣ ይህችን አረፍተ ነገር በሚናገርበት አፍታ ሁለት አርቲስቶች ወደ አእምሮዬ መጡ።ታደለ አና ሰማኸኝ። በእነዚህ ሙዚቀኞች የተሰየሙ መናፍስት ይኑሩ አይኑሩ ባላውቅም፣ ኖረው ቢጠራቸው ብዬ አሰብኩት። የታደለ “አጋቡዮ” እያለ የሰሜ “አላበድኩም ፣ ጤነኛ ነኝ፣ ያዥኝ” እያሉ ወደ ፊት ሲሮጡ በምናቤ ታየኝ።

ጥቤ ጌታ ይባርክህ። ቸር!

The post “ኢንተርኔትና ሚድያውን አጨናንቀዋለሁ ” ጥበቡ ወርቅዬ የቀድሞ ድምፃዊ፣ የአሁኑ ዘማሪና ሰባኪ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ተሰናበተች

$
0
0

Meron Getenet

ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋር በውዝግብ ውስጥ ሆኖ የሰነበተው ዳና ድራማ አንዴ ሲቆም አንዴ ሲጀመር እዚህ ደርሷል:: ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድራማውን እናንተ የማትጨርሱት ከሆነ እኔ እጨርሰዋለሁ በሚል እስከማገድም ደርሶ ነበር:: ሆኖም ግን ድራማው ከተወሰኑ ሳምንታት መቋረጥ በኋላ እንደገና የተጀመረ ሲሆን ሊጠናቀቅም ከ7 ክፍል የማይበልጥ እድሜ እንደቀረው ይነገራል::

የድራማው አዘጋጆች በዳና ድራማ ላይ ወሳኝ ገጸባህርይ የነበራትን አርቲስት ሜሮን ጌትነትን ያሰናበቱ ሲሆን እርሷን ተክታ ወጣቷ አርቲስት ዕጸሕይወት አበበ የህሊናን ቦታ እንደምትጫወት የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ በተዘጋጀ የግጥም መድረክ ላይ ባቀረበችው ግጥም በስርዓቱ ባለስልጣናት ጥርስ እንደተነከሰባት ሲገለጽ የነበረችው አርቲስት ሜሮን ጌትነት በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ እንደምትገኝ ዘ-ሐበሻ ያላት መረጃ ያመለክታል::

ሜሮን አሜሪካ የመጣችው ቀለበት ያሰረችለት ሰው ጋር አብራ ለመኖር ነው የሚሉ የቅርብ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ቢገልጹም ከአርቲስቷ በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም::

የዳና ድራማዋ ሕሊና ካለ ሜሮን በ ዕጸህይወት እንዴት ይተወን ይሆን? – በቀጣይ ሳምንት የምናየው ይሆናል::
Estehiwot abebe

The post ሜሮን ጌትነት ከዳና ድራማ ተሰናበተች appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ ገንዘብ ለሚወዱና ለገንዘብ ለሚሞቱ አዲስ ግጥም ጻፈ

$
0
0

teddy afro
*** ለፍቅር በቀር*** (የቴዲ አፍሮ አዲስ ግጥም)

አትቁጠሩ ገንዘብ ንዋይ አትደርድሩ
በፍቅር በቀር ከንጉሱ ስለማታድሩ
ያላቹት አይገባውም ቋንቋው ይለያል
ፍቅር ብቻ ዘምሩለት ያኔ ይሰማቹሃል
መግባቢያው ነውና ፍቅር ያደገበት
ለህሊናው ሊኖር ኪሱን የጠላበት
ፍቅር ብቻ በሉት ካለበት ይመጣል
ከነፍስ ከስጋው ፍቅር ተዋህዷል
ግድ አይሰጠውም ገንዘብ ቢደረደር
ልቡ አይደነግጥም ለፍቅር በቀር
ሃብቴ ብሎ ይዟታል ቀሪ ንብረቴም
በፍቅር በቀር መንገስ አይፈልግም
አባት ነው አባትነት አይቼበታለው
ቸር ነው ያለውን ሲሰጥ አይቻለው
ፍቅር ነው ፍቅርን ሲዘምር ሰምቻለው
ይህ ብላቴና በመዋደድ ነው የሚያምነው
ከነፍስ ከስጋው ፍቅር ተዋህዷል
ፍቅር ብቻ በሉት ካለበት ይመጣልX2

The post ቴዲ አፍሮ ገንዘብ ለሚወዱና ለገንዘብ ለሚሞቱ አዲስ ግጥም ጻፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሚካዔል በላይነህ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን” ትንሳዔ ሰንደቅ ነውን?

$
0
0

(ዳኝነት መኮንን እና ማስረሻ ማሞ)

በኢትዮጵያ የሙዚቃ አድናቂዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ካተረፉት የልብ አድርሶች አንዱ ድምጻዊ ሚካዔል በላይነህ ነው። “ሕይወትን ከምንጯ ጠጣሁ ተመልሼ” እያለ ሲዘፍን በእርሱ ሙዚቃ ሌሎች ሕይወትን ከምንጯ ደግመው እንዲጠጡ ያደርጋል ቢባልም የተሳሳተ ሚዛን አይመስለንም።
michael belayneh

የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊዎች በሚካዔል ዘፈን ጉዳይ ከበርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ጋራ ሲወያዩ የሚነሳው አንድ ዋነኛ ነጥብ አቀንቃኙ የ60ዎቹ ወርቃማ የሙዚቃ ዘመን ትንሳዔ ዐይተኛ ትዕምርት (exceptional symbol) መኾኑ ነው። ከዚህ ተነስተን በ7 ኪሎ መጽሔት የመጀመርያ ዕትም ላይ ይህ ርእሰ ጉዳይ ቢዳሰስ ተገቢ ይኾናል ብለን ሁለት ኹነኛ ጭብጦችን አንስተናል።

1ኛ) ሚካዔል የፈረንጅ ዘፈን የግጥም ሐሳቦችን ወደ አማርኛ በመተርጎም ወደ ሙዚቃው ዓለም ጎራ ብሎ፤ ጥልቅ የኾነውን የኢትዮጵያውያንን ኑሮና ሕይወት ወደሚበረብረው ሙዚቃ እንዴት ሊሻገር ቻለ? የሚለው ቀዳሚው ጭብጥ ሲኾን የዚህ ፊቸር ጸሐፊዎች በሚካኤል የሙዚቃ ዕድገት ላይ ሐሳብ የሚሰጡ ደርዘን የሙዚቃ ባለሞያዎች አነጋግረዋል።

2ኛ) የሚካዔል የቅርብ ጊዜ የሙዚቃ ሥራዎች የብዙሃን ብልሃት (collective wisdom) ውጤት ናቸው። አንዳንድ ባለሞያዎች የሙዚቃውን ሙጡቅነትም ከዚህ የመነጨ እንደኾነ ይገምታሉ። ታዲያ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን የባተው የብዙሃን ብልሃት በግለኛ መክሊቶች (individual talents) ላይ የበላይነት በመቀዳጀቱ ይኾን?” ከ1950ዎቹ መጀመርያ እስከ 1960ዎቹ መጨረሻ ባለው ጊዜ የኪነ ጥበብ ዛር ከጠርሙሱ የወጣበት ዘመን ነበር ብለው ለመናገር የሚደፍሩ ብዙ የሙዚቃ ባለሞያዎች እና የኢትዮጵያ ሙዚቃ አጥኚዎች አሉ። እነዚህ ባለሞያዎች በዚህ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን” እየጎመራ የመጣው የብዙሃን ብልሃት የአንድን ድምጻዊ ሥራ ውብ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽዖ ሳያበረክት አይቀርም ብለው ያትታሉ። ሐሳቡ እንዲህ ነው፤ በዚያ ዘመን ገጣሚው አምጦ የወለደውን፣ ዜመኛው በምናቡ ያረገዘውን፣ ሙዚቀኛው በመሣርያው ምናብን ከግጥም ጋራ እየፈተለ . . . እያባዘተ . . . የሙዚቃ ልቃቂት ሰርቶ፤ ሁሉም በጋራ የሸመኑትን ለአድማጩ የነፍስ ፍሰሐ ያቀብላሉ። እነዚህ ባለሞያዎች ይህን አቋማቸውን ለማስደገፍ በሶሻል ሳይንስ እና ኔትዎርክ ቲዮሪ የሕዝብ ብልሃት (wisdom of crowds) ላይ የተደረጉ ምርምሮችን ማጣቀሻ ያደርጋሉ።

ይኹንና እነዚህ ባለሞያዎች ወርቃማ በሚሉት ዘመን የተነሱ እንደ እነ ምንሊክ ወስናቸው፣ ጌታቸው ካሳ፣ ግርማ በየነ፣ ሰይፉ ዮሐንስ እና ወዘተ . . . የግለኛ መክሊት ባለቤቶች ነበሩ። እነዚህ ምሳሌዎች የብዙሃን ብልሃትን መላ ምት ፉርሽ የሚያደርጉ ናቸውን? በፊቸራችን በጊዜው የነበሩ የበርካታ ታዋቂ አቀንቃኞችን ሥራዎች በመመርመር ብዙሃኑ የትኛውን እንደሚከተሉ ለማየት ሞክረናል። ያገኘነው ውጤት የባለሟያዎቹን ሐሳብ የሚያረጋግጥ ነው።

ከዚያ በሁዋላ የቡድን የፈጠራ ሥራ ውጤት የኾኑት ሙዚቃዎች ብዙ አቀበት እና ቁልቁለት እያስተናገዱ እስከ 1990ዎቹ ዘልቀዋል። በዚህ ላይ-ታች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ የግለኛ መክሊት ባለቤቶች ታይተዋል፥ ንዋይ ደበበ ለ1970ዎቹ አጋማሽ እና ለ1980ዎቹ ዐይነተኛ ትዕምርት ተደርጎ ቢወሰድ የተገባ ነው። ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ አንድ ሰው ራሱ ገጣሚ፣ ራሱ ዜመኛ፣ ራሱ አቀናባሪ መኾን ሥጦታ ብቻ ሳይኾን ፋሽን ኾነ። በዚህ ወቅት ላይ ይሠሩ የነበሩት አብዛኛዎቹ ሥራዎች የፋሽኑ ተከታዮች ኾኑ። ከእነዚህ በግል መክሊተኞች መካከል አንዳንዶቹ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላይ አሻራቸውን ጥለው ያለፉ ናቸው።

ከእነዚህ መካከል እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እና ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን) ይገኙበታል። እጅጋየኹ ሽባባው ነፍሷ የሚወደውን ሥራ ሠራች። አብዛኛዎቹ ዘፈኖቿ በሰው ልጅ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥኑ፣ ታሪክን መሠረት ያደረጉ፣ ብሔርተኝነትን የሚያጸኑ እና ሰው መኾንን የሚያስታውሱ ናቸው። የቴዎድሮስ ካሳሁን ሥራዎች ደግሞ ማንነትን የሚያጠይቁ፣ ፍቅርን የሚሰብኩ፣ ፖለቲካን የሚጓጉጡ እና ብሔርተኝነትን የሚያንጹ ናቸው።

የሙዚቃ ባለሞያዎቹ እነዚህ ጥቂት ዘፋኞች የሂደቱ አዎንታዊነት መገለጫዎች ሳይኾኑ ከተራው ጎራ የማይመደቡ (outliers) እንደኾኑ ይናገራሉ። በግለኛ መክሊቶች ዘመን የተፈጠሩ አብዛኞቹ ሙዚቃዎች በጥራት ቀድሞ ከነበረው በጋራ ሲታዩ ያነሱ ናቸው። የሚካዔል ሙዚቃዎች ይህን የግለኛ መክሊት መጋረጃ ሸነቆረ፤ ይሸረክተው ይኾን?

ማሳረጊያ

እውን ሚካዔል በላይነህ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን” ትንሳዔ ትዕምርት ነውን? ሚካዔል ወደ ሙዚቃው ዓለም ሲመጣ “አንተ ጎዳና – አንተ መንገድ”ን ይዞ ተከሰተ። መንገድ እያናገረ መጣ። መንገድን እንደ አንድ ገጸ ባሕርይ ጥያቄ እየጠየቀው አዜመ። ይህ ዐይነቱ አመጣጥ ብዙም የተለመደ አይደለም። የመጀመርያው አልበሙ አብዛኞቹ ዘፈኖች ሐሳባቸው ከእንግሊዝኛ የተወሰዱና ወደ አማርኛ የተተረጎሙ ናቸው። “ይህ ተጽዕኖ ምናልባት በየክለቡ በሚዘፍንበት ጊዜ ድምጹን የፈታው በእንግሊዝኛ ዘፈኖች ስለኾነ ይኾናል” ብለው የሚሄሱ ባለሙያዎች አሉ። “ሙዚቃው እንደ ወንዝ የሚፈስ፣ የተረጋጋና ስክነት የተሞላበት ነው” የሚሉ ማሞካሻዎች የሚቀርቡለት ሚካዔል፥ በወቅቱ አስቀድሞ ለቆት በነበረው ነጠላ ዜማ ራሱን አስተዋውቆ ስለነበር ወደ አድማጮች ለመድረስ ብዙም አልተቸገረም ቢባል ስህተት አይኾንም።
michael

የሚካዔል ሁለተኛ ሥራ “መለያ ቀለሜ” የሚል አልበም ነው። ይህ ሥራው “ሙዚቃ ማለት ቺክቺካ ነው” ወይም “ለክለብ አስረሽ ምቺው ድለቃ የሚኾን ነው” ብለው ከሚያስቡና ከሚያምኑ አድማጮች ጋራ የማይሰናሰል ነው የሚሉት ሃያሲዎች፤ “የሚካዔል “መለያ ቀለሜ” ጸጥታ የረበበበት፣ ተመስጦ የሚያሻው፣ ጊዜ፥ ቦታ፥ እና ተመክሮ ተውበው የተቀመሩበት ምጡቅ ነገር ግን ዩኒቨርሳል ሥራዎች አካትቷል” በማለት “መለያ ቀለሜ”ን ውዳሴ ያዘምኑለታል። በዚህ መወድስ የማይስማማ አንድ ሃያሲም “ለአንዳንድ አድማጮች ነፍስ የሚያሳርፍ የሚባል ዐይነት ነው እንጂ፥ “መለያ ቀለሜ” ዩኒቨርሳል አይደለም” ሲል ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል። በ“መለያ ቀለሜ” አልበሙ ሚካዔል “ጥልቅ የኾኑ ሐሳቦችን ያዘሉ፣ ማንነትን የሚበረብሩ፣ ግጥም ብቻ ሳይኾን የተዋጣለት ሰዓሊ የቀመራቸው ሥዕሎችም እንድሚቀባ ተሰድረዋል” የሚሉ ማሞካሻዎችም በበዙ ሃያሲዎች ተችሮታል። የግርማ ይፍራሸዋ ፒያኖ ከሚካዔል ድምጽ ጋራ ተሰናስሎ በጸጥታ ሲደመጥ (እጅግ ተጋነነ ካልተባለ) የደከሙ የደም ስሮችን ያነቃቃል . . . በእያንዳንዱ የሰውነት ክፍል ውስጥ እንደ ወንዝ ይፈሳል። የዚህ ሙዚቃ ምሥጢር ሌላ አይደለም። እውን የሚካዔልን “መለያ ቀለሜ” የብዙሃን ብልሃት ዳግም መወለድ ነው ልንል እንችል ይኾን? ሚካዔል ድምጹን ይዞ መጣ፤ እነ ጌትነት እንየው አምጠው የወለዱትን ምጡቅ ድርሰት ሰጡት፣ ግርማ ይፍራሸዋ ከፒያኖው ውስጥ አዕዋፍን የሚያስንቅ የሙዚቃ ሕብር ፈጠረ።

ከዚያስ? ሚካዔል ወደየት እየተጓዘ ነው? ከ“መለያ ቀለሜ” በኋላ ይዞት የመጣው ሣልሳዊ አልበሙ “ናፍቆት እና ፍቅር” የብዙኃን ብልሐት (collective wisdom) ልቆ ታይቶበት ይኾን? ይህ ቅምሻ ነው፤ ለዚህ እና ለሌሎች ጥያቄዎች መልስ ሙሉውን ጽሑፍ በ7 ኪሎ መጽሔት ላይ ይጠብቁ!

Source: 7 ኪሎ መጽሔት

The post ሚካዔል በላይነህ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን” ትንሳዔ ሰንደቅ ነውን? appeared first on Zehabesha Amharic.

የኮሜዲያን ዳንኤል ቁንጮ ቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቆው ኮሜዲያን ዳኒ ቁንጮ በ37 ዓመቱ ማረፉን ዘ-ሐበሻ ትናንት መዘገቧና የቀብር ስነ ስር ዓቱም ዛሬ እንደሚፈጸም መዘገባችን አይዘነጋም::
daniel kuncho
ዳንኤል ቁንጮ ከእናቱ ወ/ሮ አስራት ሰቤ እና ከአባቱ ወልዴ ኪሮ በ1970ዓ.ም አዲስ አበባ 4ኪሎ – ፊት በር ተወለደ፡፡ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በዳግማዊ ምኒሊክ ተማረ፡፡ ትያትር በተለያዩ ክበባት ተምሯል – ሰዓሊም ነበር፡፡

ዳ ኤል ቁንጮ – በተለያዩ ክለቦች በዲጄነት ሲያገለግል ከነዚህም ውስጥ ፒያዛ – በአካልፀ ሆቴል እና 22 ማዞሪያ – ሰገን ሆቴል ይጠቀሳሉ፡፡ ኮሜዲያን ዳኒ ቁንጮ በርካታ የኮሜዲ ሥራዎቹን አበርክቷል፡፡

እናቱ ወ/ሮ አስራት ሰቤ ልጃቸው በታመመበት ወቅት ወደ ሚዲያ ቀርበው ‹‹እባካቹ ልጄን አትርፉልኝ?›› ሲሉ ተማጽነው ነበር፡፡ ሐሙስ ዕለት ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ለህክምና ገባ፡፡ ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2007ዓ.ም በአደረበት ህመም በ37 ዓመቱ ያረፈው ዳን ኤል ቀብሩ – ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በሳሊተ ምህረት ቤተ-ክርሲቲያን (ጉርድ ሾላ) ወዳጅ ዘመዶቹና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ተፈጽሟል::

The post የኮሜዲያን ዳንኤል ቁንጮ ቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ appeared first on Zehabesha Amharic.

“የስለት ልጅ ነኝ”–አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾው ጋር)

$
0
0

በቅርቡ ወገኔ የሚለውን ተወዳጅ ነጠላ ዜማ የለቀቀው አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ በየነ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ስለ ሙዚቃ ሕይወቱና ስለራሱ ሕይወት ተናገረ:: ብርሃኑ “የስለት ልጅ ነኝ” ብሏል:: ቃለምልልሱን ይከታተሉት::

“የስለት ልጅ ነኝ” – አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾው ጋር)

The post “የስለት ልጅ ነኝ” – አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾው ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.


” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ

$
0
0

-ነቢዩ ሲራክ

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !
angelina jolie
የዛሬዋን አጠር ያለች የማለዳ ወጌን እንድሞነጫጭር ምክንያት የሆነኝ ትናንት መጋቢት 20 ቀን 2007 የልጆች ምርጫ Nickelodeon’s 28th Annual Kids’ Choice የተሰኘውን አመታዊ የሽልማት ስነ ስርአት አዋርድ በማሸነፍ ተሸላሚ የሆነችው የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ሽልማት አይደለም። ሰብዕናዋ ፈቅዶ የዘራችው አጎምርቶ ለደስታዋ ድርብ ደስታ መሆኑን በማየቴ እንጅ …ቅዱስ መጽሐፉ ” የዘራቸውን ታጭዳላችሁ! ” እንዳለው ከመከራው ኑሮ አቅፋ ደግፋ ያሳደገቻቸው ልጆቿ በአሳዳጊ እናታቸው አንጀሊና ጆሊ ማሸነፍ እየፈነደቁ ሲያቅፉና ሲስሟት የተሰማኝ የደስታ ስሜት ለመግለጽ ያህል ነበር ብዕሩን መጨበጤ …

የተጨበጨበላት ድንቋ የፊልም ተዋናኝ ፣ ደራሲና በጎ አድራጊዋ አንጀሊና ጆሊ ሽልማቷን ስትቀበል ባሰማችው ንግግር ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” ነበር ያለችው … አዎ ልዪነተ መልካም ነገር ነው ! አንጀሊና እንዳለችው ልዩነት መልካም ነገር ነው ፣ ልዩነት ጌጥ መሆኑን አምኖ በሚያስማማው ነገር ተስማምቶ መኖር ይቻላል ።
angelina_jolie_zhara
አንጀሊና እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2005 ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በጉዲፈቻ ወስዳ ያሳደገቻት ዘሐራ ተለውጣለች ። እነሆ አሳዳጊ እናቷ ስትሸለም ከእቅፍ ወርዳ ከጎኗ ተቀምጣ ደስታዋን የምትጋራ የጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት አድምቃታለች ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” እኔም እላለሁ በፍቅር እንድትዋጅ ፍቅርን ስጥ … ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ”

ደስ ሲል: )

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም

The post ” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኮሜዲያን አለባቸው ተካ አልባሳትና የግል ቁሳቁስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ተሰጠ

$
0
0

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቶክ ሾው አዘጋጅና አቅራቢ የነበረው የኮሜዲያን አለባቸው ተካ የግል የመድረክ አልባሳትና የግል ቁሳቁሶች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ሙዚየም ተበረከተ፡፡
alebachew teka
ለሙዚየሙ የተሰጡት የአለባቸው ተካ የግል ቁሳቁሶች መሃከል የመድረክ ልብሶቹ፤ፎቶግራፎች፤ዋንጫዎች፤መፅሔቶችና የአለባቸውን ተካን ስራና የግል ሕይወት የተካተተበት ዶክመንተሪ ፊልም እንደሚገኝበት የአለባቸው ባለቤት ወ/ሮ ሳባ ሀይሌ ለቁም ነገር መፅሔት ተናግራለች፡፡
አለባቸውን ከዚህ ዓለም የተለየበትን 10 ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የግል መጠቀሚያ ንብረቶቹን ጠብቃ በማቆየት ለሙዚየሙ ያስረከበችው በተለያየ ጊዜ ስለ አለባቸው ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚፈልጉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስለ ስራውና ማንነቱ በተደራጀ መልኩ መረጃዎች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ በማሰብ እንደሆነ አስድታለች፡፡

አለባቸው በህይወት በነበረበት ጊዜ የሰራቸውን ስራዎች ከግምት በማስገባት ከታላላቅ ኢትዮጵያውያን ባለታሪኮ ጎን ሆኖ ሥራው ለትውልድ እንዲተላለፍ ዪኒቨርቲው በመፍቀዱ ከፍ ያለ ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡

የዛሬ አስር ዓመት ለስራ ወደ ጅማ ከተማ ሲያመራ በደረሰበት የመኪና አደጋ ሕይወቱን ያጣው አለባቸው ተካ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይቀርብ በነበረው ፕሮግራሙ አማካይነት የተረሱ ቀደምት የጥበብ ሰዎችን ከማስታወሱም በላይ የተቸገሩ ወገኖቹን እንዲረዱ በማድረግ ‹የድሃ አባት› የሚል የክብር ስም ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ የአለባቸውን ተካን ስራና ህይወት ከሚያሳየው ዶክመንተሪ ፊልም በተጨማሪ የአለቤ ማስታወሻ የተሰኘ ልዩ ፕሮግራም በቅርቡ ለማቅረብ እየተሰራእንደሆነ ወ/ሮ ሳባ አስታውቃለች፡፡

Source: ቁም ነገር መፅሔት 14ኛ ዓመት ቅፅ 14 ቁጥር 200 ልዩ ዕትም\

The post የኮሜዲያን አለባቸው ተካ አልባሳትና የግል ቁሳቁስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ተሰጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ”–ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር)

$
0
0

ተወዳጁ ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ ሾው ጋር ያደረገው ሁለተኛ ክፍል ቃለምልልስ ተለቋል:: በቃለምልልሱም አዳዲስ ነገሮችን ተናግሯል:: “በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምሳተፈው በአስተዳደጌ የተነሳ ነው” ይለናል:: ያድምጡት::

“ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ” – ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር)

The post “ሰዎች በውስጥ ባለህ ነገር ሳይሆን በውጭ አለባበስህ ነው የሚለኩህ” – ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾ ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.

አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል)

$
0
0

መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:-

መልካም አመት በዓል – አብዱ ኪያር

ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን
ቤት ለሌሉት ለራቁት በአካል
በያሉበት መልካም አመት በዓል

አንቺ የኢትዮጵያ እናት ይለፍልሽ
ከአመት እስከ አመት ይሙላ ጓዳሽ
አንተ የኢትዮጵያ አባት እሺ ይበልህ
ከሰው እንዳታይ እንዳይጎድልህ

ጀግናዋ እህቴ የናቷ ልጅ
ከብረሽ ቆይልን ውለጅ ክበጅ
ወንድሜ አንበሳው ያባቱ ልጅ
ክፉ አያሳይህ ደጋጉን እንጂ

ከአገር ርቀው ለተሰደዱት
በህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉት
በህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉት
ያድርግላቸው እንደሚመኙት

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ካለም ሚለየን ከማንም ዜጋ
የሚያሳምመን ልክ እንደ አለንጋ
ልብ ውስጥ ታትሞ የማይዘነጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካ
እኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካ
ኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

የወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ
ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙ
የቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ
አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ
የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ABDU_KIAR

The post አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ ለቀቀ (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

“በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም”–ቴዲ አፍሮ

$
0
0

teddy afro
ከቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የተላከ መልዕክት

ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ እና የሌላ ሀገር ተወላጅነት ባላቸዉ ንፁሀን ዜጉች ላይ በተፈፀመዉ አሰቃቄ የግድያ ወንጀል አዝነን ሳናበቃ ፦ በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን እጅግ አሳዛኝ ፤ አረመኔያዊ ተግባር ሳይና ስሰማ የተሰማኝን ሐዘን ለመግለፅ ቃላትም ሆነ ቋንቋ ያጥረኛል።

እንኳን የኔ በሚሉት የራስ ወገን ይቅርና ክቡር በሆነዉ የትኛዉም የሰዉ ልጅ ፍጡር ላይ እንዲህ አይነቱ ፍፁም ርሕራሔ የሌለዉ ኢሰብአዊ ተግባር ሲፈፀም ማየትም ሆነ መስማት የሚፈጥረዉን ጥልቅና መሪር የሀዘን ስሜት ለመረዳት ወገን ሆኖ መገኘት ብቻ ሳይሆን ሰዉ ሆኖ መፈጠር ይበቃል።

እንደ ሰዉ ሰዉ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም።
ከመቼዉም ጊዜ በበለጠም እኛ ኢትዮጵያዊያን ማንኛዉም አይነት ልዮነት ሳይወስነን በግፍ ለተጠቁት ወጉኖቻችን በአንድነት ቆመን ወገናዊነታችንን የምናሳይበት ወቅት አሁን ነዉ።

የኛ አለመግባባትና አንድ አለመሆን እንዴህ ላለ መጠቃት አሳልፎ ሲሰጠን ዛሬ አዲስ ባይሆንም መደጋገሙ እና ተጠናክሮ መቀጠሉ ግን እዚህጋ ይበቃል ልንል ይገባል።

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን መንካት የእሳት ዘንግ መጨበጥ እንደሆነ የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነትን ጨምሮ በዘመናት የቀደመ ታሪክ የታየና ወደፊትም የሚቀጥል የመሆኑ ሐቅ ከአለት የፀና ነዉ። ይህም ቃል ኪዳን በልኡል እግዚአብሔር የታተመ የማይቀየር ቃል ነዉ።

ላስተዋለዉ የምስራቹ ደጅ ላይ ሲደረስ ይህ የጣሩ ድምጽ ጅማሬ ስለሆነ የኢትዮጵያ ብርሀን ዓለምን ሊሞላ የተጣሏትም፤ ያዋረዷትም ፈፅመዉ ሊከደኑ እጅግ ጊዜዉ ቀርቧልና አይዟቹሁ ፅኑ ። ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ አንድነታችን ሊጠናከር የሚገባበትም ጊዜ አሁን ነዉ።

በመጨረሻም በግፍ የተገደሉትን ንፁሀን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዛአብሔር በቀኝ መንግስቱ እንዲያሳርፍ እየተማፀንኩ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላዉ ኢትዮጵያን ወገኖች መፅናናትን እመኛለዉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

The post “በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም” – ቴዲ አፍሮ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 261 articles
Browse latest View live