Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic Âť Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live
↧

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጥፋት ሐዋርያ ሲሆን

$
0
0

(ከአሌክስ አብርሃም)
ዛሬ ማታ ማለትም በ 20 /07/ 2006 ዓ/ም በሰይፉ ፋንታሁን እየተዘጋጀ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው ሾው ላይ የተመለከትኩት አሳፋሪ ድርጊት ይህን እንድፅፍ አነሳስቶኛል !
የሰይፉ እንግዶች አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ፣ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስና ኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌ ነበሩ … (በዚህ አጋጣሚ ሶስቱንም እስከዚህ ጊዜ ድረስ የማከብራቸውና የማደንቃቸው አርቲስቶች መሆናቸውን እወቁልኝ ) እናም ሰይፉ ስለስራቸው ስለግል ሂወታቸው እየጠየቃቸው ውይይቱ ሞቅ ብሏል … (ወደ 33ኛው ደቂቃ አሳልፈው ያዳምጡት)

በመሃል ሰይፉ ቀለል አድርጎ አንድ ጥያቄ ለአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ አቀረበ

‹‹ በቀረፃ ላይ ላለ ፊልም የአንድ ‹ድራግ› ተጠቃሚን ወጣት ገፀ – ባህሪ ተላብሰህ ስትጫወት ድራግ ወስደህ ነበር ይባላል ..እውነት ውሸት ?
ሚሊየን ኢትዮያዊያን ወጣቶች ታዳጊወችና ህፃናት የሚያውቁት አርቲስት ግሩም ሚሊየኖች በሚመለከቱት ፕሮግራም ላይ እንዲህ ሲል መለሰ
‹‹እውነት !! ››
Girum Ermias‹‹እንዴት ነበር አጋጣሚው ምንስ ተሰማህ›› ሰይፉ ጠየቀ
‹‹ በትወና ላይ ማስመሰል ሳይሆን ሁኖ መስራት የሚባል ነገር አለ… መምህሬ አለማየሁ ሊረዳኝ ይችላል (አለማየሁ በመስማማት ራሱን ነቀነቀ ) እናም በጭስ ተከልየ (?) የሚል ፊልም እየሰራን ነው … ቀረፃው ላይ የወከልኩትን ገፀ ባህሪ ወክየ ሳይሆን ‹ ሁኘ › ለመስራት ሃሽሽ (ድራግ) ወሰድኩ ..በቃ ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ዞረብኝ …..›› ሲል ሰፊ ማብራሪያ ሰጠ …

ይህን ፀያፍ ድርጊት እንደትልቅ የጥበብ ክስተት ማውራቱ ሳያንስ ጭራሽ በሃሽሽ ደንዝዞ መናገር ሁሉ አቅቶት ቀረፃ ላይ ባጋጣሚ የተወሰደውን ምስል በመሃል አስገብተው ያሳዩት ጀመረ … ይህ አሳፋሪ ቪዲዮ ታይቶ ሲያበቃ በአዳራሹ የታደመው ሰው ሞቅ ያለ ጭብጨባ ‹በሃሽሽ ደንዝዞ› ለታየው ‹‹አርቲስት ›› ለገሰ …..ሰይፉን ጨምሮ ! አለማየሁ ታደሰና ደረጀ ሃይሌን ጨምሮ !

1ኛ . በኢትዮጲያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ኧረ በብዙ የአለማችን አገራት ጭምር) አደንዛዥ እፆችን መውሰድም ይሁን በማንኛውም መንገድ ማቀባበል ይዞ መገኘት ቁልጭ ብሎ የተቀመጠ ወንጀል እንደሆነ ሰምተናል ( በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ) ይህን ፀያፍ ድርጊት አደባባይ አውጥቶ በትወናም ይሁን በሌላ ተልካሻ ምክንያት በሚሊየን ለሚቆጠሩ ወጣቶች ማሳየት ምናይነት ሃላፊነት አለመሰማትና ስርአት አልበኝነት ነው ?
2ኛ . አንድ ትልቅ እውቅና ያለው አርቲስት በርካታ ኢትዮጲያዊያን ተመልካቾች ባሉት ሾው ላይ በሃሽሽ ደንዝዞ ሲቀባጥር የሚታይበትን ቪዲዮ ማሳየት (ያውም እንደታላቅ ክብር በጭብጨባ ታጅቦ )የብሮድካስት ባለስልጣን መስሪያቤት …የኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስተዳዳሪወች እንዲሁም የሾው ባለቤት ሰይፉ ፋንታሁንን የሚያስወቅስ (ጠያቂ ቢኖር በህግም የሚያስጠይቅ) ፀያፍ ተግባር ነው ! ምስሉን ካሳዩ በኋላ ‹‹ድራግ አይጠቅምም ጎጅ ነው ምናምን እያሉ ማውራቱም ቢሆን ከድርጊቱ በላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ምክር አይደለም ) እዚች አገር ላይ ለትውልድ የሚገደው ማነው …የሚዲያወቻችን ስርአት አልበኝነትስ ሃይ የሚባለው በምን መንገድ ይሆን ?
3ኛ. በትወና ሰበብ ስክርቢቱ ላይ ድራግ መውሰድ ስለተፃፈ ስሜቱን ለመሞከር እና ‹‹መስሎ ሳይሆን ሁኖ›› ለመስራት ይህን ማድረጉ እንደአንድ የጥበብ መንገድ ከተወሰደ ( መምህሩ አለማየሁ ታደሰም ስላረጋገጠ) ወሲብ ነክ ስክርቢቶች ላይም ወሲብ መፈፀም ሙያዊ ፈቃድ ሁኖ ሊታይ ነው ማለት ነው ?

በዚህ አይነት አገራችን ላይ ከስር እንደአሸን የሚፈላው ፊልም ሰሪ ወጣት ሁሉ ‹‹መስሎ ሳይሆን ሁኖ›› ለመስራት በሚል ሰበብ ‹‹ወደ ፊልም ኢንዳስትሪ›› ሳይሆን ‹‹ወደብልግና ኢንዳስትሪ›› እንዲጎርፍ አንጋፋወቹ መንገድ እየከፈቱለት መሆኑን መታዘብ ይቻላል (አውቀውም ይሁን ሳያውቁ )
በአጠቃላይ ይህን ፀያፍ ድርጊት ለፈፀመው ግለሰብ …ምስሉን እንደደህና ነገር በጭብጨባ አሳጅቦ ላቀረበው የዝግጅቱ ባለቤት እንዲሁም ለህዝብ እንዲደርስ ላደረገው የቴሌቪዥን ጣቢያ ድርጊቱ ከእናተ የማይጠበቅ እጅግ የወረደና በ ሱስ አፋፍ ላይ የቆመውን በርካታ ወጣት ወደሱስ አዘቅት የሚገፋ ድርጊት መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም እላለሁ !

ከፍ ያለ አደራ የተጣለበት የጥበብ ሰው እንኳን በአደባባይ በጓዳውም ቢሆን ትውልድን የሚያንፅ ወደበጎ ነገር የሚመራ ድርጊት ይፈፅም ዘንድ የሙያው ድስፕሊን በራሱ ያስገድደዋል ! መንግስትም ይሁን የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ዝም ቢልም በበኩሌ ይህን የአርቲስቱን ድርጊት በፅኑ እቃወመዋለሁ ! አጥፊና ፀያፍ ድርጊት ነው ግሩም ኤርሚያስ አዝናለሁ !!

↧

ቴዲ አፍሮ በጊዮን ሆቴል ለዳግማ ትንሣኤ ለሚያቀርበው ኮንሰርት 1.2 ሚሊዮን ብር ተከፈለው

$
0
0

teddy afro
(ዘ-ሐበሻ) የዳግማ ትንሣኤን በዓል በማስመልከት በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሙዚቃ ኮንሰርቱን የሚያቀርበው ቴዲ አፍሮ 1.2 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለው የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ።

በቅርቡ ሱዳን ካርቱም 2 የተሳኩ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን አቅርቦ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ቴዲ አፍሮ የዶን አርትና ፕሮሞሽን፣ ኤቢሲ ትሬዲንግ፣ ጄ አር የሙዚቃ ፕሮዳክሽን እና ኤ ፕላስ ኤቨንትስ የተሰኙት ድርጅቶች በጋራ ባስተባበሩት የጊዮን ሆቴሉ የሙዚቃ ኮንሰርት ለቴዲ የተከፈለው ገንዘብ ድምጻዊውን ከኢትዮጵያ ድምጻውያን ብቸኛው ተከፋይ ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።

ኤፕሪል 26 ቀን 2014 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም በሚደረገው ይኸው የጊዮን ሆቴሉ የቴዲ ኮንሰርት የመግቢያ ዋጋው ስንት እንደሚሆን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ባይኖርም በጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ ግን በከተማው በሰፊው ይወራል።

ቴዲ አፍሮ “ወደ ፍቅር ጉዞ” በሚል በጊዮን ዝግጅቱን ካቀረበ በኋላ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ሌሎች ዝግጅቶችን ለማቅረብ እንደሚንቀሳቀስ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

↧
↧

ሞቴ ተሰውሮ –ከዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

$
0
0

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ


ሞቴ ተሰውሮ የሰረስረኛል፣
በያንዳንዱ ዕለት ይሽረረሽረኛል፣
ገንብቶ አሳምሮ ደግሞ ያፈርሰኛል፣
ሾሞ ከፍ አድርጎ ደግሞ ይሽረኛል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

የሰው ለሰው ድራማ 6 ሚሊዮን ብር የት ደረሰ? * በአካውንቱ ውስጥ 78 ብር ብቻ ነው የተገኘው

$
0
0

sew le sew
በርናባስ
(ለሎሚ መጽሔት እንደጻፈው)

በኢትዮጵያ ውስጥ ጥበብ በሁለት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የመጀመሪያው በአሁን ሰዓት ደራሲዎችም ሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች አዲስ ነገር ይዘው መምጣት ካለመቻላቸው ጋር በተያያዘ በህብረተሰቡ ዘንድ ቦታ እያጣ መምጣቱ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ ጥበብን ንግድ ያደረጉ አርቲስቶች መበራከት በራሳቸው አንገት ላይ ሸምቀቆ በማሰር ጥበቡን እየገደሉት ይገኛሉ፡፡ በአሁን ወቅት ምናልባትም ጥበብ ያለ ንግድ የታባቱ ያለ የጥበብ ሥራን ከተመለከትን ያለምንም ጥርጥር ‹‹ሠው ለሠው›› ድራማን በግንባር ቀደምትነት ማየት ይቻላል፡፡ ሲጀመር በርካቶች ለመመልከት የተሻሙበት ዛሬ ላይ ግን ‹‹ይህ ነገር አያልቅም እንዴ?›› ተብሎ የተለያየ ሂስ እየተሰጠበት ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ ውስጥ እንደ ሠው ለሠው የዘመኑ ማለቂያ አጥቶና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም መረን የለቀቀ ዕድል የሰጠው የለም፡፡

መቼም በየሣምንቱ እንደምንመለከተው ከሆነ የሠው ለሠው ድራማ ሃሣብ አልቆበት እዛው በዛው መዳከሩ ብቻ ሣይሆን፣ ገንዘብ የማባከንና የመዝናናትንም ነገር እየተመለከትን ነው፡፡ ከድራማው መውረድ ጐን ለጐን ካላስፈላጊ ታሪኮችም ጋር ተደማምሮ አሁን በተለይ ተዋናዮቹ እራስን የማዝናናት ጊዜ ላይ የደረሱ ይመስላል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ምናልባትም ለሌሎች ባይገባም መስፍን ጌታቸውና ሠለሞን አለሙ ግን ይህ ለምን እንደሚደረግ ልባቸው ያውቃል፡፡

የሠው ለሠው ድራማ ሲጠናቀቅ ፋይሉ ያልተዘጋ የክስ ሂደት ከመኖሩም በላይ በእነርሱ ላይ ክስ የመሠረቱት ወገኖች ሂሳብ ሊካፈሉ የሚችሉበት ሁኔታ በመኖሩ ከወዲሁ ብሩን በተለያየ ምክንያት በማባከን ‹‹የለንም›› ካሉ የከሳሾቻቸውን አንጀት የማሳረርና በዚህ መልኩ የማምለጥ አጋጣሚም እያመቻቹ ነው፡፡ አንድ በውጭ ሃገር የዳይሬክትንግ ትምህርት የተከታተለ ባለሙያ ሠው ለሠው ድራማን አብረን ስናይ፣ ‹‹ይህ ድራማ ማስታወቂያ ባይኖረው እኔ ዳይሬክት ባደርገው በአንድ ምሽት ላይ የሚታየው ከሰባት ደቂቃ አያልፍም ነበር›› ሲል አስገርሞኛል፡፡ በዚህ መልኩ በባለሙያ ሳይቀር የተገመገመው ሠው ለሠው አሁን በባንክ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ የተገኘበት ይመስላችኋል?

78 ብር /ሠባ ስምንት ብር/ ምናልባት ዓይናችሁን እያሻችሁ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ልታነቡና ልታስቡት ትችሉ ይሆናል፡፡ ብዙም ሩቅ መሄድ የሚያስፈልገው አይደለም ወይም የጽህፈት ስህተትም አይደለም፡፡ ባለፈው ሠሞን የፊልሙ ዳይሬክተር በአጋጣሚ ባገኛቸው ሚዲያዎች ላይ ሁሉ ‹‹ሠው ለሠው አትራፊ አይደለም›› እያለ ሲባዝን ነበር፡፡ ይህ የእርሱ ድርጊት ወይም አባባል ግን ምናልባትም በሂደት የሠው ለሠው አካውንት ሲታይ ይህ 78 ብር ይፋ ይሆንና ከመጋለጥና ህዝቡንም ግራ ማጋባቱ ስለማይቀር ሳልቀደም ልቅደም በሚል መልኩ የህብረተሰቡን አዕምሮ ለመለወጥ ወይም ተጠቃሚው እነርሱ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ቴሌብዥን ነው የሚለው ግንዛቤ ለማዘጋጀት ሆን ብሎ ያደረገው ነው፡፡

እንደ መረጃዎቹ ጠቋሚነት ከሆነ የሠው ለሠው ድራማ ዳይሬክተሮች ባለፉት ሦስት ዓመታት እንዲሁም ወራትም ተጨምሮበት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወስደዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ በተለያዩ ጊዜያት ድራማው ሲቀረጽ ወደ ክልሎችም የሚወጣበት አጋጣሚም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያትም የክልሉ መስተዳድር ለሠው ለሠው ዳይሬክተሮች በስፖንሰር መልክ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ ከዛም ሌላ ከዋሪት ቁሳቁሶች /ፈርኒቸርም/ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚህ መልኩ ታላቅ ገቢ ማግኘት የቻለው ድራማ እንዴት በባንክ ሂሣብ ውስጥ 78 ብር ሊገኝ ቻለ? ከተባለ ግን ከዚህ ጀርባ ከድራማው መጠናቀቅ በኋላ ካለው ክስ ጋር ተያይዞ ምንም ገንዘብ ባለማስቀረት ወይም እነርሱ ተጠቃሚ ላለማድረግ ሲባል ዳይሬክተሮቹ ገንዘቦቹን በተለያዩ ባንኮች ውስጥ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድ ድራማ ከዚህ ቀደም ከአንድ ዓመት በላይ እንዲጓዝ ዕድሉን የሰጠበት ሁኔታ አጋጥሞ አይታወቅም፡፡ የሰው ለሠው የዚህን ያህል ዓመት እንዲጓዝ የተፈቀደው በምን ምክንያት ነው? ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ኢ.ቲ.ቪ ከዚህ ቀደም በድራማዎች ላይ የተለያዩ የመጠጥ ምርቶችን በምስል ተቀርጸው ተካተው ሲመጡ በግምገማ እንዲወጡ አሊያም ምርቶቹ ሳይታዩ መቀረጽ አለባቸው የሚል ፖሊሲ ነበረው፡፡ አሁን በሰው ለሠው ድራማ ግን ሁሉም ምርቶች እንደልብ እየተቀረጹው ይገባሉ፡፡ ምናልባት በኢቲቪ በኩልም ከነመስፍንና ሠለሞን ጋር በጋራ በመሆን የሚቀጠቀም አለ፡፡ የሠው ለሠው የዳይሬክተሮች የአስናቀን መረን የለቀቀ የዘራፊ ተግባር እያሳዩን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ድራማ ታሪክ ውስጥ የድራማ ተዋናይ ለመመረጥ ‹‹በጡት ማስያዣና ፓንት ፎቶ ተነስታችሁ አምጡ›› ብለው የጠየቁት መስፍንና ሠለሞን በመሆን በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ አንዱ ለድራማ መመዘኛ ዲያሎግ በቃል የመያዝ ብቃት የመጀመሪያው መመዘኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሚፈለገው ገጸ ባህሪም የምትሆነውን ተዋንያን በርካታ ገምጋሚዎች ባሉበት ይመረጣል እንጂ ‹‹በፓንትና ጡት ማስያዣ የተነሣችሁትን ፎቶ አምጡ›› ብሎ መጠየቅ ምናልባት ‹‹ምን እየተሰራ ነው?›› ብሎ የሚያስጠይቅም ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያም ፎቶ ከተጠየቁት ሴቶች መካከል ወደፊት በስፋት የምናየው ነጥቦች ይኖራል፡፡ የሠው ለሠው ድራማ ከተጀመረ በኋላ ሁለት ዓመታት ያህል ‹‹ሎሚ ፒክቸርስ በሚል ሲሰራ የቆየው ባልታደሰ ፈቃድ ነው›› ቢባልም በኋላ ላይ ነገሮች እየከረሩና በህግ የተያዘ በመሆኑ ለውጥ ተደረገ፡፡ የሠው ለሠው የዳይሬክተሮች በተለያዩ ጊዜያት ከራሳቸው ተዋናዮች ጋር የሚጋጩበትም አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር፡፡ ከዚህም ከፍ ሲል ከተዋንያኖቹ ጋር በፍርድ ቤት ድረስ እስከመካሰስ ተዳርሰው ነበር፡፡ የክሳቸው መጠን ከመብዛቱ የተነሳ በሣምንት አንድ ቀን የግድ ችሎት ላይ ለመገኘት ተገደዋል፡፡

ባለፈው ሠሞን የኢትዮጵያ ቴሌብዥን ‹‹የሠው ለሠው ድራማ እስከ መጋቢት 30/2006 መጠናቀቅ አለበት›› በሚል ማሳሰቢያ የሰጠ ሲሆን፣ ዳይሬክተሮቹ ግን ‹‹ይህ የጊዜ ገደብ ፈጽሞ ሊጨመርልን ይገባል›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በርግጥ አሁን የድራማው ታሪክ ቢያልቅም ዳይሬክተሮቹ በግድ ታሪኩን እየለጠጡ የአንድ ሰው መጨረሻ የማታይበት እንጂ የዚህን ያህል የተለየ ነገር ታይቶበት አይደለም፡፡ ዳይሬክተሮቹን ከአስናቀ መጨረሻ ይልቅ ያጓጓውና ድራማው ባለለቀ እያሰኘ ያለው ዋናው ጉዳይ ከሠው ለሠው የሚገኘው ደለብ ያለ ጥቅም ነው፡፡ ለተዋናዮቹ አንድም ልብስ የማይገዛውና የተለየ ክፍያ የማያደርጉት የሠው ለሠው ዳይሬክተሮች ይህንን ድራማ ለማቆየት ሲሉ አሁን ደግሞ ወደ ‹‹ልማታዊ ቋንቋዎች›› ገብተዋል፡፡ ገንዘብ ይገኛል፤ ገንዘቡ ግን የት እንደሚገባ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ሠው ለሠው በክብር ተጀምሮ በውርደት ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜም ቢኖር የቀናት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ግን ከቴሌቪዥን ጀርባ የተፈፀመው የመስፍንና የሠለሞን ተግባር ይበልጥ ትኩረት የሚስብ ይሆናል፡፡ በርካቶች ያዘኑባቸውንና ያለቀሱባቸው ዳይሬክተሮች ዛሬ ላይ የደለበውን ገንዘብ ይዘው የተወሰኑትን በጥቅም ለመግዛት ቢሞክሩም፣ ይህ ነገር ያለቀለትና ምናልባትም ሠው ለሠው ከዚህ በላይ እንዳይዘልቅ የሚል ውሳኔ እስከመስጠት ተደርሷል፡፡ እናም 78 ብር አካውንቱ ላይ የተገኘውን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ያሸሹት የሠው ለሠው የዳይሬክተሮችን መጨረሻ በቅርብ የምናየው ይሆናል፡፡

↧

የጃኪ ጎሲ የሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሕግ ጥያቄዎች አሉበት፤ ይሳካ ይሆን? አላሙዲ ከጃኪ ጀርባ አለ?

$
0
0

የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ባለቤት ሸዋ ኢተና የጃኪ ጎሲን የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ ለማየት ለሚጠባበቁ ወገኖች ጥሪ አቀረበ። ከዚህ ቀደም የስራ ፈቃድ አውጥተንለት ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲመጣ ጉዳዩን ጨርሰን ኮንሰርት እስከመሰረዝ ደርሰናል፤ በዚህም ኪሳራ ደርሶብናል በሚል የሚከሰው የሸዋ ኢንተርቴይመንት በተለይም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ድምጻዊው ኮንሰርት ያቀርባል ብለው ሰዎች ገንዘባቸውን እንዳያፈሱ ጥሪውን አቅርቧል። “ጃኪ ባለን ስምምነት መሰረት [ከሌላ ሰው ጋር] (ምንም ዓይነት ኮንሰርት) መስራት አይችልም” የሚለው ሸዋ “በጃኪ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ሕዝቡ እንዳያዝን” ይላል። የሸዋ ባለቤት ከኢትዮቲብ ድረ ገጽ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ እናስቀንጭብዎ እና አወዛጋቢው ጃኪ በድጋሚ በማወቅም ይሁን በማያውቀው መንገድ ከሌሎች ጋር ስለመላተሙ የሚዘግበውን ጽሁፍ ከታች አቅርበናል። ከዚህ ቀደም ጃኪ ለዘ-ሐበሻ ‘ከምነው ሸዋ ጋር ምንም ስምምነት ኖሮኝ አያውቅም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም።

የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ያሜሪካ ዝግጅት ለ 2ኛ ጊዜ ውዝግብ አስነሳ

ይህ በጃኪ ኮንሰርት ዙሪያ ተክደናል የሚሉ ወገኖች ያሰራጩት መረጃ ነው።

ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በጥቂት ነጠላ ዜማዎቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘ ወጣት ድምፃዊ ነው። ጃኪ ጎሲ የኢትዮጵያን ባህላዊ የአዘፋፈን ስልቶች ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር የሚያዋህዱ ማራኪ ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ ፈጣን እውቅናን አጎናጽፈውታል። ይህ ወጣት ድምፃዊ በኢትዮጵያ የሙዚቃ አለም ገና ከጅምሩ የደረሰበት ደረጃ ወደፊት ብዙ ሊሰራና ከፍተኛ ዝናን ሊጨብጥ እንደሚችል አመላካች ነው።

ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ይታወቃል። ጃኪ ጎሲ በ2012 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በሰሜን አሜሪካ ሃገራት ሊያደርጋቸው የነበሩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች በዚህ ውዝግብ ምክንያት በመሰረዛቸው ብዙ አድናቂዎቹን እንዳሳዘነ ይታወሳል።

jacki gosseeበጃኪ ጎሲ ዙሪያ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ውዝግብ ብዙ ኢትዮጵያውያን አድናቂዎቹን ማስከፋቱ የሚያሳዝን ክስተት ሆኖ ሳለ፤ ዘንድሮም በዚሁ አርቲስት ዙሪያ በሌሎች የኢንተርቴንመንት ስራን በሚሰሩ ሁለት ድርጅቶች መካከል በድጋሚ የተፈጠረው የሚያስገርም ውዝግብ የበለጠ ህዝብን የሚያሳዝን፣ የድምፃዊውንም ስምና ዝናን የሚያጎድፍ፣ እንዲሁም በዙሪያው አብሮ ለመስራት ሽር ጉድ የሚሉትን ፕሮሞተሮች ስምና ስብእናን ከጥርጣሬ ውስጥ የሚከት በመሆኑ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ላሉ አካላትና ለአንባቢያን ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና ማሂ ፕሮደክሽን በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ የሚገኙ ሁለት የኢንተርቴንመንት ስራን የሚሰሩ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ የሺ ማርት ደግሞ በዚሁ በአትላንታ የሚገኝ የሃበሻ ሱቅ ነው። ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ለማዘጋጀት ከየሺ ማርት እና ከኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ጋር በመሆን በጋራ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማስፈጸምላለፉት ሁለትአመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመግባት የሚያስችለውን ፕሮሰስ ለመጨረስ ሙከራ በማድረግ ላይ ቆይቷል። ሆኖም በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን አማካኝነት እየተሞከረ የነበረው የፕሮሰስ ሂደት ሳይሳካ በመቅረቱ ምክንያት፤ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ከሌላ አካል እርዳታ አስፈልጎት ነበር።

በዚህም መሰረት ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን እዚሁ አትላንታ የሚገኘውን ማሂ ፕሮደክሽን የአርቲስት ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ እንዲያስጨርስለት በመጠየቅ፤ ስምምነት አድርጎ ነበር። ስምምነቱን ባጭሩ ለመግለጽ ያክል፤ ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ ካስጨረሰ ድምፃዊው በሰሜን አሜሪካ ከሚያደርጋቸው ኮንሰርቶች ውስጥፕሮደክሽኑ በሚመርጠው አንድ ቦታ ላይ ድምፃዊ ጃኪን ሊያሰራ፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንም ቃሉን አክብሮ ይህንኑ ሊያስፈጽም ነበር።

እንደ ማሂ ፕሮደክሽን መረጃ ከሆነ በዚህ ስምምነት መሰረት ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ አስጨርሶ ድምፃዊው ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚያስገባውን ቪዛ በእጁ እንዲገባ አድርጓል። ነገር ግን ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን የገባውን ቃል አክብሮ መፈጸም ሲገባው፤ ማሂ ፕሮደክሽን ያደረገውን ውለታ እንደማያውቅና የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ የቪዛ ጉዳይ ያለቀው በሼክ ማሃሙድ አል አሙዲን በኩል እንደሆነ በመናገር ላይ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ማሂ ፕሮደክሽን በተፈጠረው ሁኔታ ስለተበሳጨ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ይናገራል።

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

እዚህ ላይ በጣም የሚገርመው ጉዳይ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና በማሂ ፕሮደክሽን መካከል ስምምነቱ ሲደረግና የቪዛ ጉዳዩ ያለቀው በማሂ ፕሮደክሽን በኩል መሆኑን እያወቀ ችላ በማለቱ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ነው። ጥፋተኛው ማንም ሆነ ማን፤ የዚህ ፅሁፍ ዋናው አላማ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲን ጨምሮ ሶስቱም አካላት ውዝግቡ የሚያስከትለውን መዘዝ ከወዲሁ ተገንዝበው በቶሎ መፍትሄ እንዲያበጁለት በአፅንዖት ለማስገንዘብ ነው።

በመጨረሻም ፅሁፋችንን ላነበቡና ሃሳባችንን ለተጋሩ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ የምንሰናበተው ይህንን ጎጂና ደስ የማይል ውዝግብ በተመለከተ፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መልስ ጨምሮ፤ ሰፋያለ መረጃ በቅርቡ ይዘን እንደምንቀርብ ቃል በመግባት ነው::
——————————–

አንባቢያንስ ምን ትላላችሁ? ይህ ተወዳጅ ድምጻዊ እንደዚህ ያሉ ውዝግቦች ውስጥ መግባት ነበረበት ወይ? አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ካወጣው 4 ዘፈን አኳያ ይህ ሁሉ ነገር ይገባዋል ወይ? በሌሎች ወገኖች እንደሚከሰሰው አላሙዲ ጋር ስሙ መያያዙ በልጁ የወደፊት ሥራ ላይ የሚፈጥረው ነገር ይኖራል? አስተያየታችሁን ጻፉት።

↧
↧

Entertainment: ቅዳሜን ከአንጋፋው ድምጻዊ መሐመድ ወርዲ ጋር

$
0
0

Mohamed Wordi
(አፈንዲ ሙተቂ)

አቦ የምን መጨነቅ ነው? የምን መጨናነቅ! የምን መተጋተግ! ተነሱ እስቲ አንዴ ከመሐመድ ወርዲ ጋር ዓለማችንን እንቅጭ! ተነሱ እስቲ ከዚህ ጭቅጭቅና ጭንቅንቅ የበዛበት ዓለም ወደ ፍቅር ሐድራ እንሰደድ! ቅዳሜያችንን ከመሐመድ ወርዲ ጋር ቅዳሜ እናስመስል! በ“ገመር ቦባ” ድብርቱን እናባርር! በ“ቲስዓተ ዐሸር ሰና” የህይወት ምርጫንችን እናሳምር! በ“ሱድፋ” እድላችንን እንሞክር! በ“ፉአዲ ሐኒን” ውበታችንን እንለካው! በ“አነ ማ በንሳክ” ቃልኪዳናችንን እናድስ!

በየፌርማታውና በካፍቴሪያው ተደብተህ የተጎለትከው ሆይ! እስቲ ለዛሬዋ ቀን ተከተለኝ፡፡ በሓሳባችን ወደ ውቢቷ “ኻርቱም” በርረን በሐሴት አውድማ ላይ ውበት ሲመላለስ አብረን እናያለን፡፡ የምስራቅ አፍሪቃ ህዝቦች የጋራ ጌጥ የሆነው ሙሐመድ ወርዲ ቅዳሜአችንን ቅዳሜ ሊያስመስለው ተዘጋጅቷል፡፡
——–
በቅድሚያ የቱን ልጋብዝህ/ልጋብዝሽ? ከ“አነ ዐርፈክ ያ ፉአዲ” ብጀምርልህ ይከፋሃል? እንዴት ሆኖ ነው የሚከፋህ ጃል?.. እንዲያውም ዜማውን በደመ-ነፍስህ ጭምር ስለምታውቀው በቅድሚያ እርሱን ብጋብዝህ ነው ቅዳሜያችን የሚያምርልን፡፡…. ምክንያቱም ዜማውን የኛ ውድ የሆነው ጥላሁን ገሠሠ ሲያዜመው ሰምተህዋልና ነው፡፡ ጥላሁን እንዲህ ብሎ ሲዘፍን ሰምተኸው አልነበር?

አንቺ ከቶ ግድ የለሽም
ስለፍቅር አይገባሽም
ሁሉን ነገር እረስተሽው
ችላ ብለሽ ስለተውሽው
ቻልኩት ፍቅር ለብቻዬ
አዎን! እርሱን ነው የምልህ ወዳጄ! ሙሐመድ ወርዲ በዚሁ ዜማ ምን ብሎ ነበር መሰለህ?

“አነ ዐርፋክ ያ ፉአዲ
ጠል ዐዛበክ ዋ ሱሃዲ
ዋ ሽጃያ አነ ዐዛቢ”

ነበር ያለው፡፡ ታዲያ ሙሐመድ ወርዲ የዘፈነውን ጋሽ ጥላሁን እንዲሁ በጋጠወጥነት ወደ አማርኛ የመለሰው እንዳይመስልህ! የወርዲ ቡራኬ አለበት፡፡ በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዘመን የካርቱም መንገድ ለኛ የውሃ መንገድ ነበረ፡፡ ለሱዳኖችም ከዋዲ ሃልፋ ይልቅ ሸገር ትቀርባቸው ነበር፡፡ እናም በዚህ ምልልስ መሀል የኛዎቹ አንጋፋዎች (ጥላሁን ገሠሠ፣ ምኒልክ ወስናቸው፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ዓሊ ሸቦ፣ ዓሊ ቢራ ወዘተ..) እና የሱዳኖቹ ገዲም አርቲስቶች (አሕመድ አል-ሙስጠፋ፣ ሰይድ ኸሊፋ፣ ሙሐመድ ወርዲ፣ አብዱልከሪም አል-ካብሊ፣ አብዱል ዓዚዝ አል-ሙባረክ ወዘተ…) የአንድ ቤተሰብ ልጆች ሆነው ነበር፡፡ ሱዳኖቹ ያዜሙትን የኛዎቹ ወደ አማርኛ፣ ኦሮምኛና ሶማሊኛ እየመለሱ ይጫወቱታል፡፡ የኛንም ዘፈን ሱዳኖች በቋንቋቸው እየተረጎሙ ይዘፍኑታል፡፡ አንዳንዴ ዕድል ሲገጥማቸው ሁለቱም አንዱን ዜማ በአንድ መድረክ ላይ በየቋንቋቸው ይጫወቱታል፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ነው እንግዲህ የሙሐመድ ወርዲ “አነ ዐርፈክ ያ ፉአዲ” ወደ አማርኛ የተመለሰው፡፡ አገኘኸኝ አይደል? እንዲያ ነው ነገሩ ወዳጄ! እነ ጋሽ ጥላሁን እንደ አሁኖቹ ዘፋኞች (አንዳንዶቹን ማለቴ ነው) የሱዳንና የፈረንጅ ዜማን ወደ አማርኛ እየገለበጡ “የራሴ ድርሰት ነው” ብለው ሊያሞኙን አይከጅሉም፡፡ ዋናው አርቲስት ባለበት ጭምር እየዘፈኑ ያሳዩትና “እንዴት ነው! አበላሽቼብህ ይሆን?” በማለት ምክርና እገዛ ይጠይቁታል፡፡ ሱዳናዊው አርቲስትም በሰማው ነገር ላይ የራሱን አስተያየት ይሰጣል፡፡ የኛዎቹም ከሱዳናዊያኑ አርቲስቶች የሚሰጣቸውን አስተያየት ተንተርሰው እጅግ የተሻለ ስራ ይሰሩና ህዝቡን እንካችሁ ይሉታል፡፡ ለዚያም ነበር ስራው የሚዋጣላቸውና ዘመን ተሻጋሪ የሚሆንላቸው፡፡
*****

አዎን ወዳጄ! ኑሮ አይሞላም፡፡ ላይሞላ ነገር ሁልጊዜ “ተዐብ ዘምዛሚ” መሆን አንችልም፡፡ ሁል ጊዜ መነጫነጭ ይገድለናል፡፡ “ራሃ” እና “ፌሽታ” በአቅማችን ማድረግ አለብን! በዛሬዋ ቀን ጭንቀትን ድራሽ አባቱ እናጥፋው፡፡ እናም የወርዲ ግብዣዬን ልቀጥልልህ!

በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ወዳጆች ከመሐመድ ወርዲ ዜማዎች መካከል ለ“ገመር ቦባ” እና ለ“ቲስዐተ ዐሸር ሰና” (ብዙዎች የሚያውቁት “ሰበርታ” በሚለው ስም ነው) ልዩ ፍቅር አላቸው፡፡ እኔ ግን ብዙ ልጠራልህ እችላለሁ፡፡ በተለይም “ሱድፋ”፣ “ቃሲ ቀልበክ”፣ “አልሀወል አወል”፣ “አነ ማ በንሳክ”፣ “አዚብኒ ወተፈነን”፣ “አንናስ አል-ጊያፋ”፣ “ሐረምተ አድ-ዱንያ”፣ “ያ ኑረል ዐይን”፣ “ሸተል ዘማ”፣ “አል-ሙርሳል” የመሳሰሉትን በአንደኛ ደረጃ አሰልፋቸዋለሁ፡፡ ታዲያ ከዚህ ቀጥዬ የትኛውን ልጋብዝህ?… “ሱድፋ”ን ልመርጥልህ ወድጄ ነበር፡፡ ሆኖም ቪዲዮውን ከበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ በቅርበት ያገኘሁትንና ሙሐመድ ወርዲ የዛሬ 18 ዓመት ገደማ በኛ ስታዲየም የተጫወተውን “ዐዚብኒ ወተፈነን”ን ልጨምርልህ፡፡ እግረ መንገድህን የኛ ህዝብ ወርዲን ምን ያህል እንደሚወደው ታይበታለህ፡፡

ዐዚብኒ ወዚድ ዐዘባ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ
ዜይመን ሳኒ ገልበክ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚክ፡፡
አዚብኒ ወተፈነን ፊ አልዋን ዐዛቢ
ማ ቲምሳሕ ዲሙዒ ማ ቲርሐም ሸባቢ፡፡
ኸሊኒ ፊሹጁኒ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ
ዜይ መንሳኒ ገልበክ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ፡፡
ቪዲዮውን በሚከተለው ሊንክ ላይ ተመልከተው….

በመሀሉ የዛሬዋ ቅዳሜ ምርጫችን ስላደረግነው ሙሐመድ ወርዲ ታሪከ-ህይወት ጥቂት ሐተታ ካስፈለገህ እነሆ ልበልህ ወዳጄ!

ሙሉ ስሙ ሙሐመድ ዑስማን ሳሊሕ ወርዲ ነው፡፡ እርሱ ግን “ሙሐመድ ወርዲ” ወይንም በአጭሩ በቤተሰቡ ስም “ወርዲ” ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡ የተወለደው እ.ኤ.አ. በ1932 ዋዲ ሀልፋ በተሰኘው ሰሜናዊው የሱዳን ክፍለ ሀገር፣ “ሱወርዳ” በተባለች ትንሽዬ የገጠር መንደር ውስጥ ነው፡፡ እናቱ የኑቢያ ተወላጅ ስትሆን አባቱ ዐረብ ነው፡፡ ወርዲ የሙት ልጅ ነው፡፡ ሁለቱንም ወላጆቹን በልጅነቱ ነው ያጣው፡፡ በመሆኑም በዘመዶቹ ጥበቃ ስር ሆኖ ነው ያደገው፡፡ ትምህርቱን በዋዲ ሀልፋ እና በካርቱም ተከታትሏል፡፡ የተወለደበትን ሀገር እስከ 1956 በመምህርነት ሙያ ካገለገለ በኋላ በወቅቱ ይሞካክራቸው የነበሩት ዘፈኖች በኦምዱርማን ሬድዮ ጣቢያ ተቀርጸው በመተላለፋቸው በህዝብ ልብ ውስጥ ገባ፡፡ ያገኘው የሞራል ድጋፍ ማነሳሻ ስለሆነው መምህርነቱን ትቶ የአርቲስትነቱን ጎራ ተቀላቀለ፡፡ ከዚያም ሱዳኖች ከሚያፈቅሯቸው ቁንጮ ዘፋኞቻቸው አንዱ ለመሆን በቃ፡፡

ወርዲ በህይወቱ የተረጋጋ ኑሮ አልኖረም፡፡ በሱዳን የተለዋወጡት መንግሥታት በተቃዋሚነት እየፈረጁት አንገላተውታል፡፡ በመሆኑም ለሀያ ዓመታት ያህል በካይሮና በለንደን ነው የኖረው፡፡ በ2002 ግን ወደ ሀገሩ በክብር ተመልሷል፡፡ ወርዲ በሙዚቃው ዕድገት ላደረገው አስተዋጽኦ ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሸልሟል፡፡ ከልዩ ልዩ የአውሮጳ፣ አፍሪቃና እስያ ሀገራትም ሽልማቶችን ተቀብሏል፡፡ ሱዳኖች እ.ኤ.አ. በ2000 ባደረጉት ምርጫ “አል-ገመር ቦባ” የተሰኘው ዘፈኑ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ “ነጠላ ዜማ” ተብሎ ተመርጧል፡፡ መሐመድ ወርዲ በመጨረሻዎቹ ዓመታት በደረሰበት የጤና መታወክ ሁለት ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ ሆነው ነበር፡፡ ይኸው የኩላሊት ህመም ፋታ ነስቶት በየካቲት ወር 2012 ከዚህች ዓለም አሰናብቶታል፡፡

መሐመድ ወርዲ ከብዙ በጥቂቱ እንዲያ ነበር፡፡ አሁን በርሱ ዘፈኖች “ራሓ” ማድረጋችንን እንቀጥል፡፡

—-
ታሕሳስ 6/2013

↧

የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ

$
0
0

girum ermias

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው ማራኪ መጽሔት እንደዘገበው በቅርቡ በሰይፉ ፋንታሁን የኢቢኤስ ሾው ላይ ቀርቦ በአዲስ ፊልሙ ላይ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ መስራቱን ለማህበረሰቡ ያሳየው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጠበቆች ህብረት በጋራ የወንጀል ክስ አቅርበውበታል።

ጠበቃ ማቲያስ ግርማ ለማራኪ መፅሄት እንዳስረዱት በክሱ ላይ ሰይፉ ፋንታሁንና አለማየሁ ታደሰ ደጋፊ ሀሳብ በመስጠታቸው ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል። አርቲስቱ ምንም እንኳ ለፊልም ግብዓት “መስለው ሳይሆን ሆነው” ለመስራት ያደረጉት ተግባር ቢሆንም ህብረተሰቡን ከወንጀል ለመጠበቅ ሲባል ክስ እንደተመሰረተባቸው የጠበቆች ተወካዩ አስረድተዋል።

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

“ይህንን የበለጠ ማጣራት የነበረባቸው ፖሊስና አቃቤ ህግ ቢሆኑም ፣ በግልፅ በሀገሪቱ የአየር ክልል የተላለፈውን መረጃ ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸውም ገልፀዋል። በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ስርዓት በተለይ ግሩም በክሱ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ ሰባት አመት እንዲሁም የ50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል።

በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 1996/97 አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ/ሀ መሰረት እስከ ” አደንዛዥ ዕፅን እራሱ ወይም ሌላ ሰው ሊጠቀምበት በማሰብ የገዛ፣የተጠቀመ፣ እንዲጠቀም ያደረገ፣,,,” ከ7 ዓመት እስከ 50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል። እነ ሰይፉ ደግሞ “ወንጀልን ባለማወቅ” ክስ ተመስርቶባቸዋል።

መጽሔቱ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ ለግሩም በቅርብ መጥሪያ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

↧

የገመና ድራማው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የፍርድ ቤት ማዘዣ ደረሰው (ማዘዣውን ይዘናል)

$
0
0

Daniel tegegne(ዘ-ሐበሻ) በከሳሽ የፊልም አሰሪ ወ/ሮ ቤተልሄም አበበ እና በተከሳሽ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መካከል ያለው የፍርድ ሂደት መታየቱን ቀጥሎ አርቲስቱ የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደደረሰው ለዘ-ሐበሻ እስከነ ማስረጃው የደረሰው መረጃ አመለከተ።

ከዚህ በፊት በዚሁ ክስ የተነሳ በካራማራ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የተለቀቀው አርቲስት ዳንኤል በወ/ሮ ቤተልሄም የቀረበበት አቤቱታ ለፊልም ሥራ 662 ሺህ 120 ብር ከተቀበለ በኋላ ፊልሙን ሳይሰራ ቀርቷል በሚል “የማጭበርበር” ክስ እንደሆነ ተገልጿል።

ከሳሽ ወ/ሮ ቤተልሄም አበበ የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም ጽፋ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበችው ባለ 5 ገጽ የክስ ማመልከቻ፣ 2 ገጽ የማስረጃ ዝርዝር፣ 2 ገጽ ልዩ ልዩ ማስረጃዎች በድምሩ 9 ገጽ ክሱን የሚያስረዱ ወረቀቶች ከፍርድ ቤት ማዘዣ ጋር ለአርቲስት ዳንኤል የደረሰው ሲሆን አርቲስቱም መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም በጠበቃው በኩል መረከቡን በፊርማ አረጋግጧል።

በዚህም መሠረት ዳንኤል ለቀረበበት ክስ ሚያዝያ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በሬጅስራር ጽህፈት ቤት በኩል ማስረጃውን እንዲያቀርብና እንዲሁም ግንቦት 12 ቀን 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጉዳዩ በችሎት እንዲታይ ፍርድ ቤቱ አዟል።
Daniel Tegegne

ዘ-ሐበሻ ይህን ጉዳይ ተከታትላ ትዘግባለች።

↧

በሰው ለሰው ድራማ ላይ ዶ/ር ሆኖ የሚተውነው አርቲስት ድራማው በግል ሕይወቱ ላይ ጉዳት እንዳስከተለበት ገለጸ

$
0
0

afro times (1)_Page_08(አፍሮ ታይምስ) ዘወትር ረቡዕ ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የ “ሰው ለሰው” ድራማ ላይ የዶክተሩን ገፀ-ባህሪ የሚጫወተው አርቲስት ልዑል ግርማ ከድራማው ጋር በተያያዘ ችግር እንደገጠመው ገለፀ።
አርቲስቱ ሰሞኑን ለአፍሮ ታይምስ እንደተናገረው በድራማው ውስጥ ዋናው ገፀ-ባህሪ (መስፍን) በደረሰበት ከባድ የመኪና ግጭት አደጋ አካሉ የማይንቀሳቀስ ከመሆኑም በላይ በውጭ አገር ታክሞ የመዳን ተስፋው የተመናመነ መሆኑ በድራማው እየታየ ሲሆን፣ ዶክተሩ “ተስፋ የለውም” ብሎ መናገሩ የችግሩ መነሻ ነው።

“ሜክሲኮ የሚገኘው ኬኬ ህንፃ ላይ ለግል ጉዳይ በተገኘሁበት ወቅት ሁለት ወጣቶች ከላይኛው ደረጃ ላይ ሆነው ‘ሌባ ዶክተር’ በማለት ጉዳት አድርሰውብኛል፤ የምኖርበት አካባቢ ሰዎችም ‘አንተ ከመቼ ወዲህ ነው ዶክተር የሆንከው?’ በሚል ‘አጭበርባሪ’ እና ‘ሌባ’ እያሉ ሰድበውኛል፤ ዘመዶቼም ለእናቴ ‘ክፉ ልጅ ከመውለድ ቢቀር ይሻል ነበር’ እያሉ መውጫ መግቢያ አሳጥተውናል” ያለው አርቲስት ልዑል ግርማ፣ “ሰዎች ገፀ-ባህሪን እና እውነተኛ ማንነትን ነጣጥለው ባለማየታቸው ለችግር ተዳርጌያለሁ” ሲል ተናግሯል።

“የድራማው ፅሁፍ ሲሰጠኝ ቀድሞውኑ እንዲህ አይነት ነገር ሊከሰት እንደሚችል ገምቼ ደራሲዎቹን አነጋግሬ ነበር” ያለው አርቲስት ልዑል፣ ይሁንና ከህክምና አማካሪያቸው ጋር ተነጋግረው የፃፉት በመሆኑ ምንም “የሚመጣ ነገር አይኖርም” በሚል አሳምነውት ስራውን እንደቀጠለ ይገልፃል። በድራማው
ላይ ለአቶ መስፍን የመዳን ተስፋ እንደሌለው መንገሩ ከአቶ አስናቀ ጋር ተሻርኮ ያደረገው የመሰላቸው የድራማው ተከታታዮች ብዙ መሆናቸውንና በዚህም በእውነተኛ ኑሮው ላይ ተፅዕኖ መፈጠሩንና ለችግር መጋለጡን የሚገለፀው አርቲስቱ “መጠየቅ ካለባቸው እንኳን ተጠያቂዎቹ ደራሲዎቹ እንጂ እኔ ልሆን
አይገባም፤ የሰራሁትም እምቢ ማለት ህዝብን መናቅ ይሆንብኛል በሚል ነው።

ደግሞም ገፀ-ባህሪው እና እውነተኛ ማንነቴ የማይገናኙ በመሆናቸው ሰዎች በእኔ ላይ ያሳደሩትን የጥላቻ መንፈስ ሊያነሱልኝ ይገባል” በማለት ለአፍሮ ታይምስ ቃሉን ሰጥቷል።

↧
↧

የጃኪ ጎሲ አዲሱ ነጠላ ዜማ “ፊያሜታ”ን ያድምጡ [Video]

$
0
0

ጎሳዬ ቀለሙ “ጃኪ ጎሲ” በአማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋ የሠራው አዲሱ ፊያሜታ ነጠላ ዜማ ያድምጡ። ዜማው ገና ከመለቀቁ በሶሻል ሚድያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ዘፈኑ ቀይባህርን ዞሮ ይመለሳል ልቤ እያለ ያቀነቅናል፤ ተስፋ እንደማይቆርጥና እንደተከፋ እንደሚኖር በዘፈኑ ይናገራል።

Jacky gosee

↧

ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ከተሾመ አሰግድ ለሰረቀው ዘፈን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? ወይስ ማን አለብኝነት ያልፈዋል?

$
0
0


ይታየው ከሚኒያፖሊስ

ከዓመት በፊት በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 38  ነዋሪነቱ ሚኒሶታ የሆነው ስመ ጥሩው ድምጻዊ ተሾመ አሠግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቆ ነበር። ካለፈቃዱ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) የተባለው ድምጻዊ የተሾመን “የኔ አካል” ወስዶ መሥራቱን አምርሮ መቃወሙንም አንብበን ነበር። “አንድ ዘፋኝ የአንዱን ወስዶ ለሕዝብ ሲያቀርብ ባለቤቱን ማስፈቀድ ይኖርበታል” ያለው ተሾመ “ጎሲ ከ20 ዓመት በፊት የተጫወትኩትን፦ “የኔ አካል የኔው ነሽ፤ ምን አወርስሻለሁ፤ አንጀቴና ልቤን ያው ትቼልሻለሁ”” ዘፈኔን ካለፈቃድ በክሊፕ ጭምር ማውጣቱ ክፉኛ በድሎኛል” ካለ በኋላ “ድምጻዊው ጎሳዬ ቀለሙ የኔን ብቻ ሳይሆን ዘፈኑን የደረሱልኝን ገጣሚው ይልማ ገብረአብን እና የዜማ ደራሲውን አበበ መለሰን ሁሉ ተዳፍሯል። ይህንን ዘፈን በፈረንጆች በ1987 ዓ.ም አካባቢ ከነራሄል ዮሐንስ ጋር በጋራ ባወጣሁት አልበም ውስጥ ሳካትተው ግጥሙን እና ዜማውን የሰጡኝ እነርሱ ናቸው። በሙዚቃ ክሊፑ ላይ የነዚህ ስም አልተጠቀሰም። ይልቁንም የሌላ ሰው ስም በመጻፍ የኛን ሥራ የራሱ በማስመሰል አቅርቦ ሥራዬን ዘርፏል” ሲል ቅሬታውን አሰምቶ እንደነበር አንበበናል።
jacki gossee
“ወደ ሕግ ጋር መሄዴ የማይቀር ነው። ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሼ እሞግተዋለሁ” ያለው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “የኔ አካል” የተሰኘውን ሥራዬን ካለፈቃዴ ተነጥቂያለሁና ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ፤ በጠራራ ጸሐይ ነው የተዘረፍኩት።” በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰረቁ ዘፈኖች ሲወጡ ከኦርጂናሉ ዘፋኝ በይሁንታ መገኘቱን እና አለመገኘቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲል ጥሪውን አቅርቦ ነበር። “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሞ (ጃኪ ጎሲ) የተሾመ አሰግድን ዘፈን መሥራቱን አምኖ በቪድዮ ክሊፑ ላይ ምስጋና አቅርቧል” በሚል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ለተሾመ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ተሾመም “ይሄ ገሎ ማዳን ነው። ነጮጭ ሲናገሩ መጀመሪያ አቁስለውና ከዛ ለቁስሉ ማበሻ ጨርቅ ስጠው ይላሉ። ጎሳዬም ያደረገው ያ ነው። ዘፈኑን ካለፈቃዴ ወስዶ፤ ክሊፑም ከመልዕክቱ ጋር የማይገናኝ አድርጎ ሰርቶ በመጨረሻ ተሾመ አሰግድን አመሰግናለሁ ብሎ ቢጽፍ ምን ዋጋ አለው? ከገደለኝ በኋላ ማርኩህ ቢለኝ ምን ዋጋ አለው?” በማለት አምርሮ ሲናገር መስማታችን ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመስከረም ወር 1945 ተወልዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል። የመጨረሻ ካሴቱን ካወጣ 17 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በሗላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል መልሷል። 

ተሾመ ጎሳዬ ሰረቀኝ ባለው ዘፈን ዙሪያ ይህን ቢናገርም ጆሲ ሾ ላይ የቀረበው ጃኪ ጎሲ በማን አለብኝነት እንደውም ተሾመ ስለዚህ ዘፈን አያገባውም ሲል መናገሩ ይታወሳል። ጎሳዬ ቀለሙ ይህን ያለው ለደራሲው እንደገና ስለከፈልኩት ተሾመ ይህ ዘፈን የኔ ነው ብሎ መከራከር አይችልም ሲል በቲቪ መድረክ መናገሩ ይታወሳል። ይህን ያለው ሃገር ቤት ሆኖ ነበር። ዛሬ ተሾመ አሰግድ በሚኖርበት ሰሜን አሜሪካ ጎሳዬ ቀለሙ መጥቷል። ተሾመ ፈቃድ ይፈልጋል። ሆኖም ግን ጃኪ በማን አለብኝነት “ድምጻዊው የለፋበትን ሥራ አያገባውም” ሲል ተናግሯል። ጃኪ እነ ምነው ሸዋ ላይ እንዳሳየው በግትርነቱ ይቀጥል ይሆን ወይስ ተሾመ እንዳለው ወደ ሕግ በመሄድ ጃኪን በስርቆት ይከሰው ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል።

↧

አንቀላፍቶ የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያነቃቃው የብዙአየሁ ደምሴ “ሳላይሽ”አልበም

$
0
0

Bizuayehu Dimesse – Bewalashebet [New Single]በተስፋሁን ብርሃኑ

አሁን አሁን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ እጅግ እየቀዘቀዘና እድገቱ እምብዛም የማይታይበት እየሆነ የመጣ እንደሆነ በርካታ ነባር ድምፃውያን፣የግጥምና ዜማ ደራሲዎችና የሙዚቃ አፍቃሪያን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

ምክንያታቸው ደግሞ የሁሉም ማለት ይቻላል ሙዚቃ ሳትጠራቸው ወቅቱና ገንዘቡን ብቻ ያገኙ በርካታ ወጣቶች ወደሙዚቃው በመግባታቸውና ለግጥሙና ዜማው እምብዛም የማይጨነቁ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው መታየት የሚፈልጉ በብዛት መምጣታቸው የሙዚቃውን እድገት ቁልቁል ያስኬደው ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጡት ምክንያት የኮፒ ራይት ጥሰት ሲሆን ነባርና የብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያን ቀልብን ገዝተው የዘለቁ ድምፃውያን ካሴቶቻቸውን ቶሎ ቶሎ ባለማውጣታቸውና አንዳንዶቹም ከነአካቴው ከሙዚቃው በመራቃቸው የሙዚቃ እድገቱን አስተጓጉሎታል ይላሉ፡፡

አዳዲስና ወጣት ድምፃውያን በብዛት እየመጡ ነው፡፡ አብዛኞቹ ታዲያ የነባር ድምፃውያንን ሙዚቃ ዳግሞ በመጫወት ድምፃቸውን እያሟሹ ዘፋኞች ለመሆን በቅተዋል፡፡ ምን ያህልም እንደተሳካላቸው ፍርዱን ለሙዚቃው አፍቃሪ እንተዋለን፡፡

ከነዚህ የነባር ድምፃውያን ሙዚቃዎች ተጫውተው ከተሳካላቸው ድምፃውያን መካከል አንዱ ብዙአየሁ ደምሴ አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም ምክንያቱም ከአራት ዓመታት በፊት የታዋቂውን ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰን ዘፈኖች ሙሉ ካሴት በመስራት የሙዚቃ አፍቃሪያንን አስደምሟልና ነው፡፡ በዚህ አልበሙ አብዛኛው የሙዚቃ አፍቃሪ ከሙሉቀን ያልተናነሰ ብቃት እንዳለው መስክረው ለታል፡፡ ምንም እንኳ “አስፈቅጃለሁ” “አላስፈቀደኝም” በሚል ያለመግባባት በሁለቱ ድምፃውያን መካከል ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በኋላም በሰይፉ ፋንታሁን አማካኝነት ሊታረቁ ንደቻሉ ሰምተናል፡፡ በዚህ ካሴቱ በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን አድናቆትን ችረውታል፡፡ ትንሽ ዝምድና ከድምፃዊው ጋር ያለው ቴዲ አፍሮ ሳይቀር ምስክርነቱን የሰጠበት አጋጣሚ ነበር፡፡

ከሁለት ወራት በፊት ዜማ አማን በተባለ ከበርካታ ድምፃውያን ጋር በአማኑኤል ይልማ የተዘጋጀው ካሴት ላይ ባወጣቸው ሁለት ዘፈኖች በርካታ አድናቆትን ተችሮት ነበር፡፡ ከአንድ ወር በፊት የራሱን ሁለተኛ ካሴት “ሳላይሽ” በሚል መጠሪያ በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት ከሚኖርበት ካናዳ አድናቂዎቹ አበርክቷል፡፡ በዚህም የራሱን የአዘፋፈን ስልት እንዲሁም ከአንድ የሙሉቀን መለሰ ዘፈን በስተቀር ሁሉም አዲስ ግጥምና ዜማ በማቅረቡ እጅግ ተወዶለታል፡፡ ካሴቱም በወጣ በአጭር ቀናት በብዙ ሺህ ኮፒዎች እንደተሸጡለት ተነግሯል፡፡

አሁንም በበርካታ መዝናኛ ስፍራዎችና በተለያዩ ቦታዎች የዚህን ድምፃዊ ሙዚቃዎች መደመጥን ቀጥለውበታል፡፡ በዚህም እጅግ እንደተሳካለት መመስከር ይቻላል፡፡ ብዙአየሁ ደምሴ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ከአንድ ዓመት በላይ በካናዳ እየኖረ ይገኛል፡፡ ከመላው ዓለም የኮንሰርት ጥሪ እየቀረበለት ያለው ወጣቱ ድምፃዊ ምናልባትም ከፋሲካ በኋላ ጥሪውን ተቀብሎ ኮንሰርቶችን ሊያቀርብ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ የነባር ድምፃዊያንን ሙዚቃ በመጫወት በርካታ ድምፃውያን የራሳቸውን ችሎታ ሳያሳዩ ተውጠው የቀሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ነገር ግን ብዙዓየሁ ደምሴ በመጀመሪያ አልበሙ ተጠቅሞበት የነበረውን ሙሉቀን መለሰን በመተው በራሱ የአዘፋፈን ስታይል ጥሩ ካሴት ለአድማጩ አበርክቷል፡፡ ይህም ወጣቱን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ በዚህ በያዝነው 2ዐዐ6 ዓ.ም ከሸዋንዳኝ ኃይሉ ካሴት በኋላ የአድማጭን ቀልብ ገዝቶ እስከ አሁን የቆየውና በእጅጉ እየተደመጠ ያለው “ሳላይሽ” የብዙዓየሁ ደምሴ ካሴት ነው በዚህም አንቀላፍቶ የነበረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ መነቃቃትን
ፈጥሮለታል ለማለት ይቻላል፡፡ ብራቮ ብዙዓየሁ!!

ዘ-ሐበሻ በኪነጥበብ ዙሪያ የሚሰጡ አስተያየቶችን ለማስተናገድ ሁሌም ዝግጁናትና ይሳተፉ።

↧

“ሆድ ይፍጀው”እንዳለ ያረፈው የሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ካለፈ 5 ዓመት ሞላው

$
0
0


ከቅድስት አባተ

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ድረገጽና ሚኒሶታ ውስጥ በሚታተመው መዲና ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነበር። የጥላሁንን 5ኛ ዓመት ሕልፈት ለማስታወስ እንደገና አቅርበነዋል።

ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ዘመኑ ከልጅነት እስከ እውቀት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ሆኖ በህዝብ አንቀልባ ላይ ያደገ ነው፡፡ ምክንያቱም ገና በ12 እና 13 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስለተቀጠረ እንደ ወላጅ ሆኖ ያሳደገው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ግን ህዝቡ እንደ ወላጅነቱ ስለ ጥላሁን ገሠሠ ሁኔታ በተለይም እጅግ የከፋ አደጋ ሲደርስበት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ዘመናት እንደ ዋዛ እየከነፉ ነው፡፡

ተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድረስ ማለትም በሶስት ስርዓቶች ውስጥ ልዩ ልዩ አደጋዎች ቢደርሱበትም በየትኛውም ዘመን ግን ይፋ የሆነ መረጃ ለህዝቡ አልተሰጠም፡፡ ከህግ አንፃርም የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎች ፍትህ አላገኙም፡፡ ህግና ስርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ የዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አደጋዎች እንዴት እንቆቅልሽ ይሆናሉ? ብለው የሚጠይቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች አድናቂዎቹም አሉ፡፡

ለምሳሌ በዘመነ አፄ ኃይለስላሴ ስርዓት ወቅት የጥላሁን ገሠሠ ወላጅ እናት በሰው እጅ በሽጉጥ ተገድለዋል፡፡ ይህን ወንጀለኛ ለማግኘት ጥላሁን ገሠሠ ብዙ ዋተተ፡፡ የናቱ ገዳይ ይገኝበታል ተብሎ የሚታሰብበት ስፍራ ሁሉ አሰሰ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ጥላሁንም የህይወት ታሪኩን በሚገልፀው መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፡-

‹‹እናቴ የተቀበረችው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ነው፡፡ በእውነቱ የእናቴ በሰው እጅ መገደል እንደ እብድ አደረገኝ፡፡ የእናቴን ገዳይ ለማግኘት ሶስት አራት ዓመታትን ወስዶብኛል፡፡ እዚህ ቦታ (እዚህ ሰፈር) ታየ ሲባል እዚያ ሄጄ ሳደፍጥ፣ ከዚህ ተነስቶ ሄዷል ስባል ወደተባለበት ቦታ በመሄድ ስንከራተት ጠላቴን በጭራሽ ላገኘው አልቻልኩም›› (ገጽ 75)

ጥላሁን ገሠሠ የናቱን ገዳይ በመፈለግ ብዙ መከራ ደርሶበታል፡፡ ለፖሊሶቹ እንዲያፈላልጉት ገንዘቡን አውጥቷል፡፡ ገዳዩን በመፈለግ ሲባዝን በትዳሩ ውስጥ ክፍተት በመፈጠሩ የመጀመሪያ ባለቤቱ የሆነችዋንና በጣም ከሚወዳት ከወ/ሮ አስራት አለሙ ጋር የነበረው ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ የናቱን ገዳይ ይዞ ህግ ፊት የሚያቀርብለት አካል አጥቶ ጥላሁን ገሠሠ እንደ ተቆጨ አልፏል፡፡

የሚገርመው ነገር የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መኖሩን አንዳንድ ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ በ1980ዎቹ ውስጥ ይታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች እንደገለፁት ከሆነ ደግሞ፤ የጥላሁን ገሠሠን እናት ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረ ሰው በንጉሱ ዘመን ተይዞ መታሰሩን ይገልፁና ደርግ ድንገት ወደ ስልጣን ሲመጣ ለእስረኞች ሙሉ ምህረት ሲያደርግ ይህም ተጠርጣሪ ከእስር ቤት መውጣቱን ፅፈዋል፡፡

ይህ ተጠርጣሪ በእርጅና ውስጥ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ መኖሩም ይነገራል፡፡ ግን በወቅቱ አስፈላጊውን ምርመራ ባለመደረጉ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ዓመታት አለፉ፡፡
ከዚህ በኋላ ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ ላይ ከመጡት አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሰው የ1985 ዓ.ም አንገቱን በስለት ቆርጦ ለመግደል የተደረገው እጅግ ዘግናኝ ክስተት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ታሪክ ውስጥ እንቆቅልሽ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ተሸፋፍኖ የኖረ አደጋ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠን ማነው አንገቱ ላይ በስለት የቆረጠው?

እንቆቅልሹ ይሄ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ራሱ መናገር አልፈለገም፡፡ ‹ሆድ ይፍጀው› ብሎት ለምን?

አንዳንድ ሰዎች በዚህ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ጥላሁን ገሠሠ በህይወት እያለ አንገቱ ላይ በስለት ስለደረሰበት አደጋ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ቢወጣ ደስ አይለውም፤ በዚህም ሳቢያ በጭንቀት እና በብሽቀት ይጎዳል፤ ስለዚህ ጉዳዩ ሆድ ይፍጀው ተብሎ ቢታለፍ ይቀላል፡፡ ምክንያቱም ጥላሁን እንዲገለፅበት ካልፈለገ ብንተባበረውስ የሚሉ አሉ፡፡
ይህን ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ በቅንነት ካየነው ከጥሩ መንፈስ የመነጨ ስለሆነ ልንቀበለው እንችላለን፡፡ ግን እኮ የተፈፀመው ወንጀል ነፍስ የማጥፋት ሙከራ ነው፡፡ በየትኛው የህግ አግባብ እንዲህ አይነት ሙከራ ወንጀል ነው! ስለዚህ ይሄ ጉዳይ እስከ መቼ ነው ምስጢር ሆኖ የሚኖረው? የፖሊስ ሃይል ባለበት ሀገር እንዲህ አይነት ፍጥጥ ግጥጥ ያለ ድርጊት ላለፉት 19 ዓመታት በምን ምክንያት ነው ምስጢር ሆኖ የኖረው?

ይህ በጥላሁን ገሠሠ አንገት ላይ የደረሰው አደጋ ይፋ ባለመሆኑ ጉዳዩ ለብዙ ሃሜታዎች ክፍት ሆኖ ኖረ፡፡ ለምሳሌ አደጋውን የፈፀመው ራሱ ጥላሁን ገሠሠ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች መረጃዎች ደግሞ አንድ ሰው በራሱ ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሊፈፅም ፈጽሞ አይችልም በማለት ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ የጥላሁን ገሠሠን የህይወት ታሪክ የሚያወሳው መጽሐፍ ‹መሰናዘሪያ› ጋዜጣን ጠቅሶ በተለይም አደጋው እንደደረሰ ጥላሁንን ሲያክሙት ከነበሩት ባለሙያዎች መካከል ዶ/ር ባዘዘው ባይለየኝ የተናገሩትን በሚከተለው መልኩ አቅርቧል፡፡
‹‹ጥላሁንን ከምሽቱ 12፡30 ላይ ሰዎች በአንቡላንስ ሆስፒታላችን ድረስ ይዘውት መጡ፡፡ በጆሮው አካባቢ ደም ይፈሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም በአየር ቧንቧው ማለትም ማንቁርቱ ላይ ተቆርጦ ደም ይፈሰው ስለነበር ባደረግንለት የመጀመሪያ እርዳታ ደሙን አቆምን፡፡ በጎን በኩል በስለቱ የደረሰው ጉዳት ጉበቱን አግኝቶታል፡፡ ግራ እጁ ላይ ያለው የደም ስር ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረና በጠቅላላውም ሁለት ሰዓት የፈጀ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለታል፡፡ በመተንፈሻ አካሉ በደሰበት ጉዳት ምክንያት ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጊዜያዊ የመተንፈሻ መሳሪያ ተደርጎለት የሚተነፍሰው በዚያው ነበር፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው መተንፈስ አይችልም፡፡ አንድ ሰው ራሱን አንድ ቦታ ላይ ሊወጋ ይችላል፡፡ ሶስት ቦታ ላይ ራሱን አቆሰለ ማለት ይከብዳል፡፡ ድፍረቱም አቅሙም አይኖረውም›› (ገጽ 105) በማለት ሀኪሙ ገልፀዋል፡፡
የህክምና ባለሙያው የሰጡት አስተያየትም አሳማኝ መንፈስ አለው፡፡ ስለዚህ አደጋውን ያደረሰው ሌላ አካል ነው ብለን እንድንጠረጥር ያደርገናል፡፡

ጥላሁን ገሠሠ አደጋው በደረሰበት ወቅት የታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች ስለ ሁኔታው ያቀረቧቸውን መጣጥፎች በሙሉ መልሼ አይቻቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ እጃቸው ላይ ትክክለኛው መረጃ ስለሌለ ከመላ ምትና ከተጠየቅ (Logic) በስተቀር የተደራጀ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ዛሬ በህይወት የሌለው ታዋቂው የመድረክ አስተዋዋቂውና የጥላሁን ገሠሠ ጓደኛ የነበረው ስዩም ባሩዳ ተጠይቆ ሲመልስ፣ ‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ ጥላሁን ገሠሠ በቢላዋ አንገቱን ሊቆርጥ ቀርቶ፣ ጥፍሩን እንኳን በምላጭ ለመቁረጥ የሚፈራ ነው›› በማለት ገልፆታል፡፡ በወቅቱ የተጠየቁት የጥላሁን ገሠሠ ጓደኞች ሲናገሩ፣ ጥላሁን በራሱ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ጠቁመዋል፡፡ ታዲያ ማን ነው አደጋ ያደረሰበት?

tilahun
ዛሬ ጥላሁን በህይወት የለም፡፡ አንገቱ ላይ የደረሰበት አደጋ ‹‹በሆድ ይፍጀው›› ሰበብ ለዘመናት ምስጢር ሆኖ መኖር ያለበት አይመስለኝም፡፡ በወቅቱ ፖሊስ የተደራጀ ምርመራ ማድረጉ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ያ የምርመራ ውጤት ለፍርድ ቤት ይቅረብ ወይስ አይቅረብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ጉዳዩንም በሐገሪቱ ውስጥ የተከሰተ አንድ ትልቅ ወንጀል አድርጎ የመመልከት አዝማሚያም አልተስተዋለም፡፡ ስለዚህ እኛ እንደ ጥላሁን ገሠሠ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› ብለን ማለፍ ያለብን አይመስለኝም፡፡ እውነታውን ካላወቅን ሆዳችንን ይቆርጠናል፡፡ ከቶስ የማይክል ጃክሰንን አሟሟት በተመለከተ የነበረውን የፍርድ ቤት ሂደት ያየ፣ ጥላሁን ገሠሠን ሲያስታውስ ምን እንደሚል አላውቅም፡፡ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው አልታወቀ፡፡ ጥላሁን ገሠሠን አንገቱን በስለት የቆረጠው አልታወቀ፡፡ ምንድን ነው ጉዱ?
ሌላው አሰገራሚውና አሳዛኙ ጉዳይ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ነው፡፡ ያንን የሚያክል የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ እንደ ዋዛ ሞተ ሲባል በእጅጉ ያስደነግጣል፣ ይቆጫል፣ ያሳስባል፡፡

ሃሳብ አንድ
ድንገት ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሐገሩ ኢትዮጵያ የመጣው ጥላሁን ገሠሠ ማታ በቤቱ ውስጥ ታመመ፡፡ ባለቤቱ እና ቤተሰባቸው በድንጋጤ ይዘውት ወደ አንድ የግል ሆስፒታል ሄዱ፡፡ እዚያም እንደደረሱ የኢትዮጵያው የሙዚቃ ንጉስ ተገቢውን ህክምና አለማግኘቱን ባለቤቱ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ በጥላሁን ገሠሠ የህይወት ታሪክ ውስጥ የሚከተለው ተጽፏል፡፡

‹‹ሰው ታሞብናል! እባካችሁ ዶክተር ጥሩልን›› አለቻቸው፣ እጅግ በተጣደፈ ሁኔታ፡፡ ድምፅ ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ‹‹መጀመሪያ ካርድ አውጡና ነርሷ ትየው›› አለ በተረጋጋ ስሜት፡፡
‹‹እባካችሁ ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ በጣም አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል›› አለች ቶሎ እንዲረዱላት እተንሰፈሰፈች፡፡ ደንገጥ ብሎ ከልቡ የሚሰማት አጣች፡፡

‹‹ወ/ሮ ሮማን መላ ቅጡ ጠፍቶባት አይኖቿ ከወዲያ ወዲህ ሲዋትቱ ከወደ ጥግ በኩል የቆመ አንድ ዊልቸር አይታ ሄደች፡፡ እየገፋች ስታመጣው ያዩዋት ጥበቃ አብረው ወደ መኪናው አጋፏት››
‹‹ጥላሁንን ከመኪናው አውርደው ተሽከርካሪው ወንበር ላይ አስቀመጡት፡፡ ጥላሁንም ቁርጥ ቁርጥ ባለ ትንፋሽ፤ ‹‹እባክህ ዶክተርዬ ተንፍሼ ልሙት፣ የምተነፍስበት ነገር አድርግልኝ›› በማለት የመማፀኛ ቃል ወርወር ያደርጋል፡፡ ሐኪሙ በዝግታ መጥቶ አጠገባቸው ቆም አለና ጥላሁን የተቀመጠበትን ዊልቸር ከወ/ሮ ሮማን በመውሰድ እዚያው በዚያው በክሊኒኩ ኮሪደር ላይ ወደ ፊትና ወደኋላ እየገፋ በዝምታ ተመለከተው፡፡

‹‹ወ/ሮ ሮማን ስለ ህመሙ ስትነግረው በቀዘቀዘ ደንታቢስ ስሜት ያያታል፡፡ ያ ጎልቶ የሚታይ ድንጋጤዋ ስሜት፣ ፊት ለፊቱ ያለው የህመምተኛው ቅዝታ ቅንጣት ያህል ርህራሄ ያሳደረበት በማይመስል ስሜት፡፡
‹‹ስንት አይነት ልበ ደንዳና በየቦታው አለ!›› አለች ወ/ሮ ሮማን በውስጧ፡፡ ስለ ህክምና ስነ-ምግባር በአደባባይ የተገባው የሄፓክራተስ የቃል ኪዳን መሀላ እንደ ጤዛ ተኗል፡፡
‹‹ኧረ ባካችሁ አንድ ነገር አድርጉለት!! ምነው ዝም አላችሁ?›› አለች፡፡ ‹‹ኧረ እባካችሁ እርዱልኝ?›› አለችው፣ አጠገቧ የቆመውን ሐኪም፡፡

‹‹ዶክተርዬ መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ ሲማፀን ሌላ ሐኪም ደርሶ ‹‹አስም አለበት እንዴ?›› አለ፡፡ ኋለኛውም እንደ ፊተኛው ሐኪም ርህራሄ ባጣ ስሜት፡፡ ከራሱ ከጥላሁን ይልቅ ስለ እሱ ልዩ ልዩ የህመም አይነቶችና ባሕሪይ በይበልጥ የምታውቀው ባለቤቱ ነች ማለት ይቻላል፡፡ ‹‹ባለሙያ ነኝ ማለት ባልችልም ስለ በሽታው በየጊዜው ከዶክተሮች ጋር የምነጋገረው እኔ በመሆኔ ብዙ ልምዶችና መረጃዎች አሉኝ›› ትላለች ወ/ሮ ሮማን፣ የአያሌ ዓመታት ግንዛቤዋን እያነፃፀረች፡፡
‹‹አስም ሳይሆን የልብ ህመም አለበት›› አለች ወ/ሮ ሮማን ፈጠን ብላ፡፡

‹‹እንግዲያው ጎተራ አካባቢ የልብ ህክምና የሚሰጥበት ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ስላለ ወደዚያ ይዘሽው ሂጂ›› ብለዋት መልሷን ሳይጠብቁ ትተዋቸው ወደ ጉዳያቸው ተመለሱ፡፡ (ከገፅ 116-170 በከፊል የተወሰደ)
ይህ ከላይ የተፃፈው ታሪክ እውነት ከሆነ ለጥላሁን ገሠሠ ሞት አንዱ ምክንያት ሊሆን ነው፡፡ ሆስፒታል ደርሶ ህክምና አላገኘም፡፡ በስርዓት ተቀበለውም የህክምና ባለሙያ የለም ማለት ነው፡፡ እናም ይሄን የሚያክል ስህተትን በምንድን ነው የምናርመው? ስለ ጉዳዩስ የቤተዛታ ሆስፒታል አስተዳደር ምነው ዝም ይላል? መልስ የለውም? የሀኪሞች ማህበርስ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ አጀንዳ አይነጋገርም? ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርስ? የህክምና ህጉስ የሄፓክራተስን የቃል ኪዳን መሐላ አላከበሩም ተብለው በሚተቹ ሀኪሞችና ተቋማት ላይ ምን ይላል? ይሄ የማይክል ጃክሰንን የአሟሟት ምስጢር የፈተሸ ችሎት የተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የጥላሁንን ገሠሠን ህልፈት ክፉኛ አስታወሰኝ፡፡

ሐሳብ ሁለት
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤትና ቤተሰቦች፣ የልብ ህክምና የሚሰጥበትን ሆስፒታል ቢፈልጉ ያጡታል፡፡ ከዚያም ጎተራ አካባቢ ወዳለው ሰናይ ክሊኒክ ይደርሳሉ፡፡ እዚያም እንደ አንድ የህክምና ተቋም ተገቢውን እርዳታ እንዳላገኙ ተገልጿል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጅን እያለ የፈለገውን ኦክስጅን ሳያገን ማለፉን በፅሑፍ ተገልጿል፡፡ እንደ ባለቤቱ ገለፃ በሁለተኛውም ሐኪም ቤት ውስጥ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ጥላሁን ገሠሠ አላገኘም፡፡ የባለቤቱ የወ/ሮ ሮማን በዙ በተደጋጋሚ ሐኪም ቤቶቹን እና የህክምና ባለሙያዎቹን እየጠቀሱ የሰሯቸውን ስህተቶች ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተገቢው ማጣሪያ ሳይደረግ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ብቻ ይነገራል፡፡

አሁን ‹‹ሆድ ይፍጀው›› የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሐኪሞቹም ሆኑ የህክምና ተቋማቱ ሆድ ይፍጀው ብለው ተቀምጠው ከሆነ እኔ ሆዴን ቆርጦኛል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጂን አጥቶ ከሞተ እና ዝም ከተባለ ጥፋተኛው ራሱ ጥላሁን ነው ማለት ነው? ጊዜው የሆድ ይፍጀው አይመስለኝም፡፡
በአጠቃላይ ጥላሁን ገሠሠ የእናቱን ገዳይ አላወቀም፡፡ ህግም የናቱን ገዳይ አግኝቶ ተገቢውን ውሳኔ አልሰጠለትም፡፡ ከዚህ ሌላም አንገቱ ላይ በስለት የደረሰበት አደጋ እስከ ዛሬ ድረስ ምስጢር ሆኖ ኖሯል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ‹‹ዶክተርዬ! መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ እጅግ በአሳዛኝ ተማፅኖ፣ እርዳታ ሳይደረግለት እንዳለፈ ይነገራል፡፡ በዚህም ጉዳይ ተጠያቂው ማን እንደሆነ የሚነገር ጉዳይ የለም፡፡ ሁሉም ነገር ዝም ነው፡፡ ውስብስብ የሆነው የማይክልጃክሰን አሟሟት ግን በግልፅ ችሎት ፍትህ አግኝቷል፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎችና ሞቱ ግን እንቆቅልሽ ሆኖ ይኖራል፡፡ እንቆቅልሹስ ሳይፈታ ለትውልድ እናስተላልፍ?S

ይህ ጽሁፍ በሚኒሶታ እየታተመ በሚወጣው መዲና ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነው።

↧
↧

የቢዚ ሲግናል፣ የጃሉድና የናቲ ማን የአዲስ አበባው ኮንሰርት ተዘረዘ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ ተጫዋች ቢዚ ሲግናልን አጅበው ኢትዮጵያዊያኑ ጃሉድ እና ናቲ ማን ይሳተፉበታል የተባለው የአዲስ አበባው ኮንሰርት ተሠረዘ። የፊታችን ቅዳሜ ቴዲ አፍሮ በግዮን ሆቴል ለዳግማዊ ትንሣኤ በዓል በሚያቀርበው ኮንሰርት ቀን በተመሳሳይ በሚሊኒየም አዳራሽ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የነዚሁ ታዋቂ አርቲስቶች ኮንሰርት መሰረዝ የከተማው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል።

የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ ቢዚ ሲንግናል

የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ ቢዚ ሲንግናል


የአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ቢዚ ሲግናልን ጨምሮ በርከት ያሉ የሬጌ ሙዚቃ ተጫዋቾጮች በተለይም ጸረ ግብረሰዶማዊ አቋም ስላላቸው በአብዛኛው በግል አውሮፕላኖች እንደሚጓዙ ጠቅሰው ወደ አዲስ አበባም በግል አውሮፕላን ለመሄድ አስበው አውሮፕላን አለመገኘቱን ጠቅሰው ለኮንሰርቱ መሠረዝም ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ገልጸዋል።
jalud
የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ጌይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፈቃድ ሰጥቶ እያለ በኋላም ሰልፉ እንዲቀር ከተደረገ በኋላ የጸረ ጌይ አቋም ያለው ድምጻዊ ቢዚ ሲግናል ኮንሰርት መሰረዙ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።

በሚሊኒየም አዳራሽ ለዳግማዊ ትንሳኤ የፊታችን እሁድ ይደረጋል ተብሎ የነበረው ኮንሰርት ከተሰረዘ በሁላ የተሰጠው ምክንያት ለዘፋኙና ባንዱ ማመላለሻ የአውሮፕላን ማጣት ይሁን እንጂ ከበስተጀርባው የጸረ ጌይ ጉዳይና ሌሎችም ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት በጊዮን ሆቴል ለሚያደርገው ኮንሰርት በትናንትናው ዕለት የመድረክ ግንባታ ሥራ መጀምሩን ለማወቅ ችለናል።

↧

የጃኪ ጎሲ የሕግ አማካሪ ተናገሩ፡ “ሸዋ ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮን፣ ሔኖክ አበበንና ጆኒ ራጋን ከሷል”፤ በሸዋ ላይ የ$400,000 ካሳ ክስ አቅርበናል

$
0
0

የጃኪ ጎሲ የሕግ አማካሪ ተናገሩ፡ “ሸዋ ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮን፣ ሔኖክ አበበንና ጆኒ ራጋን ከሷል”፤ በሸዋ ላይ የ$450,000  ካሳ ክስ አቅርበናል
(ዘ-ሐበሻ) ከደቂቃዎች በኋላ የጃኪ ጎሲ የዋሽንግተን ዲሲ ኮንሰርት ከመጀምሩ አስቀድሞ ከዘ-ሐበሻ ጋር ቃል የተመላለሱት የጃኪ ጎሲ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ አስፋው የፍርድ ሂደቱ የጃኪ የሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ከመደረጋቸው በፊት ቢጠናቀቅ እንኳ የሌሎች ከተማዎችን ኮንሰርቶች ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደለሌለና በተሳካ ሁኔታ እንደሚደረጉ አስታወቁ። የሕግ አማካሪው “ለጃኪ ክስ መከላከያዎችን ስናሰባስብ ከዚህ ቀደም ሸዋ ኢንተርቴይመንት በቴዲ አፍሮ፣ በሄኖክ አበበና በጆኒ ራጋ ላይ ክስ መመስረቱን ማስረጃውን አግኝተናል” ካሉ በኋላ በተለይም ሄኖክ አበበና ጆኒ ራጋ በዋሽንግተን ዲሲ በሸዋ የተነሳ የደረሰባቸውን ሸዋ የጃኪን ኮንሰርትም ለማሰናከል 11ኛው ሰዓት ላይ ክስ መመስረቱን በማስታከክ አብራርተዋል።

ሸዋ ኢንተርቴይመንት በፍርድ ቤት የጃኪን ስም በመጥፎ ነገር እንዳያነሳ ተነግሮት እያለ በዘ-ሐበሻ ላይ ወጥቶ የተናገረው በሕግ ሊያስጠይቅ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ መንግስቱ የጃኪ ኮንሰርትን ለማሰናከል ባደረገው ጥፋት እስከ 400 ሺህ ዶላር በሚጠጋ የካሳ ክፍያ በሕግ ጠይቀነው ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዟል ብለዋል። ሸዋ ኢንተርቴይመንትም በተመሳሳይ የ$500 ሺህ ዶላር የካሳ ክፍያ ክስ መመስረቱን ለዘ-ሐበሻ መግለጹ ይታወሳል። አቶ መንግስቱ በጃኪ ጎሲና ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽንን ወክለው ለዘ-ሐበሻ የሰጡትን ቃለምልልስ ይከታተሉት።

↧

ጃኪ ጎሲ ተሾመ አሰግድን ይቅርታ ጠየቀ

$
0
0

jacky teshome
በApril 24, 2012 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዕትም ላይ ዝነኛው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ካለፈቃዴ “የኔ አካል” የሚለውን ተወዳጅ ዘፈኔን ወስዶ ተጫውቷል በተቃውሞ ነበር። ከጊዜ በኋላ ድምጻዊ ጃኪ ጎሲ በጆሲ ሾው ላይ በመቅረብ “ከዚህ በኋላ ተሾመ ይህን ዘፈን የኔ ነው ብሎ መጠየቅ አይችልም፤ ለዜማና ግጥም ደራሲዎቹ ከፍዬበታለሁ” ሲል ተናግሮ እንደነበርም ይታወሳል።

ጃኪ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሲመጣ ይታየው የተባሉ ጸሐፊ “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ከተሾመ አሰግድ ለወሰደው ዘፈን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? ወይስ ማን አለብኝነት ያልፈዋል?” ሲሉ ተሾመ ከዚህ ቀደም የሰጠውን ቃለምልልስ በመጥቀስ አስተያየት ጽፈው ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ኮከብነት እየተጓዘ የሚገኘው ጃኪ ይህን አስተያየት በብልህነት የተመለከተው ይመስላል። በዚህም መሠረት ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው የመጀመሪያው የሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቱ ላይ ሰው ባልጠበቀው ሁኔታ ዝነኛውን ድምጻዊ ወደ መድረክ በማምጣት አብሮት “የኔአካል” የሚለውን ተወዳጅ ዘፈን ካቀነቀኑ በኋላ ድምጻዊ ጃኪም ካለፍቃዱው ወስዶ በመስራቱ ይቅርታ ጠይቋል። ጨምሮም ዘፈኑን የሰራው ከመውደዱ የተነሳ እንደሆነ ገልጿል። አርቲስት ተሾመ አሰግድም “እዚህ ሃገር ሰንመጣ መንገዱን ያሳየን ሰው አልነበረም። ጥረታችን የቀድሞ ሙዚቃኞቻችን ውለታ እንዲህ በቀላል እንዳይረሳ ሙዚቃዎቹን ስትጫወቱ በፈቃድ ጥያቄ ጠይቃችሁ ተጫወቱ። [የኔ አካል] ከኔ በበለጠ ጃኪ ተጫውቶታል። አብልጦ ነው የተጫወተው፤ ሞቅ አድርጉለት” ብሎ አርቲስቱም ይቅርታውን ተቀብሏል። ጃኪም የሕዝብ ድምጽን ማድመጡ፤ ከምንም በላይ ይህን ስመጥር አርቲስት በመድረክ ጋብዞ እንዲታወስ በማድረጉ ዘ-ሐበሻ አድናቆቷን በዚህ አጋጣሚ እየገለጸች፤ አንባቢዎች በዘ-ሐበሻ የተጀመረው የጃኪና የተሾመ ጉዳይ መቋጨቱን በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን። መልካም የሥራ ዘመን ለሁለቱም።
የይቅርታውን ስነስርዓት ቪዲዮ ይመልከቱ

የግርጌ ማስታወሻ ጥቂት ስለስመጥሩ አርቲስት ተሾመ አሰግድ፦
በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመስከረም ወር 1945 ተወልዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል። የመጨረሻ ካሴቱን ካወጣ 17 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በሗላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል መልሷል።

↧

ቴዲ አፍሮ፣ ጃኪ ጎሲ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ሚካኤል በላይነህ በኢትዮጵያውያኑ እግር ኳስ ጨዋታ ሳንሆዜ ላይ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ

$
0
0

teddy afro vs jacky gosee
(ዘ-ሐበሻ) በሳንሆሴና ሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤርያ ለ31ኛ ጊዜ በሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የሚገኙ ድምጻውያን ከወዲሁ ታወቁ።

ላለፉት 31 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን በሰሜን አሜሪካ ሲያገናኝ የቆየው ይኸው የስፖርት ፌስቲቫል ከጁን 29 እስከ ጁላይ 5 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ሆቴሎችም ከወዲሁ እየሞሉ እንደሚገኙ ከስፖርት ፌዴሬሽኑ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዘንድሮው ኳስ ጨዋታ ወቅት የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሚደረጉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቴዲ አፍሮ፣ ጃኪ ጎሲ፣ ሸዋንዳኝ ሃይሉና ሚካኤል በላይነህ የሚያቀርቧቸው ኮንሰርቶች ከወዲሁ የሕዝብን ቀልብ ስበዋል።

ሐሙስ ጁላይ 3 ቀን 2013 ቴዲ አፍሮ፣ አርብ ጁላይ 4 ቀን 2014 ጃኪ ጎሲ፣ ቅዳሜ ጁላይ 5 ሚካኤል በላይነህ እና ሸዋንዳኝ ኃይሉ የሙዚቃ ኮንሰርታቸውን በሳንሆዜ ያቀርባሉ።

↧
↧

ሄኖክ የሺጥላ – (አምቦ ተነሽ አትነሺ)

$
0
0

Wallaggaa2014_3
አምቦ

በደምሽ የተገነባ
በሕልምሽ ላይ የታለመ
ከቅባት ከ ማር ከቡናሽ
ያተርፍሽው ይሄን ሆነ ።
ምነው አምቦ የላቀች የገብረ ምድህን ሀገር
ምነው አንቺ የጸጋዬ የአዴ አርገጡ ሰፈር
አምቦ የቀዊሳ አድባር
አንቺ የ ቦራ ጨፌ
ምነው ምድርሽ በደም እና በንባ ጎርፍ ረጠበ
ምነው የልጆችሽ ደም የሰሜን እግር አጠበ።

አንቦ አንቺም አልፎልሽ ብሎልሽ ደምሽ ፈሰሰ
ይሄው ደስ ይበልሽ ዛሬ የተመኘሽው ደረሰ።

ህጣናቶችሽ ተደፍተው
እናት አንጀቱዋን አስራ
ዋይታ እንደ እልልታ ባገሩ ፣ በየመንደሩ ተጠራ
ጩኸት ፈለገሽ ሆነ ፣ አንድ መሆን ይኸው ተፈራ።
የሃዘን ድንኩዋን እንደ ንግሥ ቤቀየሽ ላይ ተሰየመ
ወጣትነትሽ አረጀ፣ ክብርሽ ተገሶ ፈረሽ
ሳምራዊነትሽ ቀለመ።
አምቦ የእትብቴ አፈር
ወተቱን ከቦራዬ ግት
ማር አልያም ደሞ አጉዋት
ግትሽን ግቼ እንደ ጊደር
ከሳር ፣ ካዛባ ፣ ከፍጉ
ከከብቶች ትንፋሽ ጋ ሳድር
በህጻን ከንፈሬ አቅፌ
በህጻን ልቤ አፍቅሬሽ
በህጻን ልቤ ኑሬሽ
ጉልበቴን ያጠነከርሽው
ዛሬ
በደም ሆነ እናትነትሽ
ያን ደግነት ረሳሽው።

አምቦ ወና አትሁኝ ቀና በይ
ጉልበትሽን አሳያቸው
ዛሬም አርበኞች በምድርሽ
ላንድነት ይሰየሙልሽ
ዛሬም ጸጋዬን ውለጂ ፣ አንድነት ጉልበት ይሁንሽ።
አምቦ ተነሽ አትነሺ
ድሮም ትልቅነት እንጂ ማነስ አያምርብሽም
አምቦ ለቅሶዬን አድምጭ
አምቦ እጅሽን ለባንዳ ለሰሜን ተኩላ አትስጪ።
አምቦ የጎጃም በሩዋ
አምቦ የኩሽ ምድሩዋ
አንቦ የቀዊሳ ሀገር
አንቦ የሃብተግዮርጊስ የድናግዴ ምድረ ምውጫ
አምቦ እሉ አባ ቦራ የነ ዋቆ ፈረስ መጠጫ
የኔ አያና ጦር ሰፈር
አምቦ ምድረ ኢትዮጵያ
ይብቃሽ ብቻሽን ማልቀሱ
ይብቃሽ ብቻሽን ደም መርጨት ፣ ይብቃሽ ጥቁር ደም ማፍሰሱ።
አምቦ ልጆችሽን ጥሪ
አምቦ አንድ ላይ ጩሂ
አምቦ ደምሽ ይመልስ
አምቦ የዋቃ ዝናር የጠፋው ክብሩ ይመለስ
ባክሽ ተባብረሽ ጩሂ።

ሄኖክ የሺጥላ

↧

“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ

$
0
0

ጥያቄ፡- እኔ የማውቀው ሪቼ መወለድህን ነው፤ አንተ ግን ሰዎች ሲጠይቁህ የጨርቆስ ልጅ ነኝ ነው የምትለው፡፡ በትክክል የተወለድከው የት ነው?
መኮንን፡- የሪቼ አጥቢያው ጨርቆስ አይደል…? ሰፈሩ ጨርቆስ ነው፤ ልዩ ስሙ ሪቼ ቢባልም ያው ጨርቆስ ነው፡፡ እኔ በጨርቆስ ሲጠራ ነው ደስ የሚለኝ፡፡
1527014_587389751333753_1530774389_n
ጥያቄ፡- ሰፈሬ፣ የተወለድኩበት ጨርቆስ ነው ብለህ የምትናገርበትና ይህን በመናገርህ የምትደሰትበት የተለየ ምክንያት አለህ?
መኮንን፡- የወለድኩበት፣ ክርስትና የተነሳሁበት፣ አሁንም የምኖርበት ነው፡፡ አካባቢውን ውስጣ ውስጡን ሁሉ የቤቴን ያህል አውቀዋለሁ፡፡ ጨርቆስ ውስጥ ብዙ አብሮ አደግ ወንድሞችና እህቶች አሉኝ፡፡ ስለዚህ እኔ የጨርቆስ ልጅ ነኝ፡፡ እዚያ ያለው ህይወቱ፣ አኗኗራችን፣ ጨዋታው፣ ደስታው በሙሉ ከውስጤ ጋር ተዋህዷል፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም የጨርቆስ ልጅ መሆኔን በኩራት እንድናገር ያደርገኛል፡፡
ጥያቄ፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ቀልዶች ይነገራሉ፤ አንዳንዶችም ጨርቆስ አካባቢ ከሌላው የከተማችን አካባቢ የተለየ አድርገው ሲያወሱት እንሰማለን፣ አንተንስ እንዲህ አይነት ነገሮች ገጥመውህ አያውቁም?
መኮንን፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ነገሮች ሲባሉ እሰማለሁ፡፡ እንዳልከው ቀልዶችም ይቀለዳሉ፡፡ ነገር ግን የህይወት ትክክለኛው ገፅታ ያለው እኛ ጋር ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጨርቆስ ከድህነት ጋር ተያይዞ ሲወሳ ልንሰማ እንችላለን፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ በከተማችን ከጨርቆስ በበለጠ ድህነት የተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ብዙ ናቸው፡፡ …በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ ውስጥ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ በኋላ ነው እየሰፋ የሚሄደው፡፡ ጨርቆስ ብዙ ቀልደኞችን፣ ብዙ ፀሐፊዎችን ያፈራ የህይወትን አስኳል በኑሮህ የምትረዳበት ምርጥ አካባቢ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ጨርቆስ ተወልደው ለትልልቅ ቁም ነገሮች የበቁና መልካም ስም ያገኙ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ አንተ እነማንን መጥቀስ ትችላለህ?
መኮንን፡- እነ ተመስገን መላኩ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ዘነበ ወላ፣ ኢሳያስ ግዛው (ኢሳግ ስቱዲዮ)… ብዙ ናቸው፡፡ በተለያየ ሙያ ውስጥ የተሰማሩ ከአውሮፕላን አብራሪነት ጀምሮ የጨርቆስ ልጆች ያልገቡበት የሙያ መስክ የለም፡፡ ዶክተሩ፣ መምህሩ፣ መካኒኩ፣ ኢንጂነሩ… በጥቅሉ የጨርቆስ ልጅ የሌለው ‹‹የለም›› የሚለው ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ጥያቄ፡- እንግዲህ የተወለድከው አዲስ አበባ ያውም ጨርቆስ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ የንግግር ዘዬህ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ይወሰዳል፤ ይህ ከምን የመጣ ነው?
መኮንን፡- እኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ በምንወዳቸው ነገሮች ተፅዕኖ ስር መውደቃችን የተለመደ ነው፡፡ እኔ እጅግ አድርጌ ባላገር እወዳለሁ፡፡ እኛም ቤት ሆነ ጎረቤት ሰዎች ለጥየቃ ከባላገር ከመጡ አብሬያቸው ማውራት ደስ ይለኛል፡፡ ከሽማግሌዎችም ጋር መወያየት ደስታን ይሰጠኛል፡፡ ሄድ መጣ ከሚልባቸው ሰዎችም ጋር መጫወት ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአነጋገራቸው ልዩ ትኩረቱ እሰጣለሁ፡፡ የባላገሩ እና የሽማግሌዎቹ አነጋገር በእነዚያ ጊዜያት ውስጤ ገብቶ የቀረ ይመስለኛል፡፡ አሁንም ድረስ ባላገርና ሽማግሌ ሳገኝ ከእነርሱ ጋር ማውራት ያስደስተኛል፡፡ በተለይም እኛ በተለምዶ ‹‹ቢጩ›› ከምንላቸው ጋር መጫወት ደስ ይለኛል፡፡
ጥያቄ፡- በብዙ የኮሜዲ እና ሌሎች ገፀ ባህሪያቶችህ ሽማግሌ መስለህ ነው የምትሰራው፣ እኔ እንደውም ከሽማግሌ ውጪ የሰራኸውን ገፀባህርይ አላስታውስም፡፡ ይህ ነገር አስበኸው የሆነ ነው ወይስ በአጋጣሚ?
መኮንን፡- ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ከሽማግሌዎችና ከባላገር ሰዎች ጋር የማደርጋቸው ውይይቶች በእኔ አነጋገር ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በመደበኛው ህይወት ይንፀባረቃል፡፡ ከጓደኞቼ ጋር በምጫወትበት ወቅት አነጋገሩ ሳላስበው ይወጣል፣ ልማድ ሆኖብኛል፡፡ ምናልባት ይሄ ነገር በድራማ፣ ቴአትር እና ፊልም አዘጋጆች ዘንድ መኮንን የሽማግሌን ገፀ ባህሪ ጥሩ አድርጎ ይጫወትልኛል የሚል እሳቤ እንዲኖር አድርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን ሌሎችን ገፀ ባህሪያትም ጥሩ አድርጌ እጫወታለሁ የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡
ጥያቄ፡- እንደ ወጣት ወይም እንደ ጎልማሳ ደረቱን ነፋ ያደረገ ቆፍጣና ሰው ገፀ ባህሪን ተጫውተህ ታውቃለህ?
መኮንን፡- ከሽምግልና ውጪ እንደ ወጣት ሆኜ የሰራሁት ነበር፣ ነገር ግን ብዙም አልታይም፡፡ ከቴዲ ስቱዲዮ ጋር ነበር የሰራሁት፡፡ እሱ ቢታይ ኖሮ መኮንን ሁሉንም ሆኖ መስራት እንደሚችል ይታወቅልኝ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የሚያሰራኝ ካገኘሁ እሰራለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ በሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብቻ ተወስኜ እንድቀር ያደረገኝ የዳይሬክተሮች ምደባ ነው፡፡ እነርሱ ይህን ገፀ ባህሪ እርሱ አሳምሮ ይጫወተዋል ብለው ካመኑ መስራት ነው ያለብኝ፡፡ ለዚህ ነው ሌላውን መስራት የማልችል እስኪመስል ድረስ በሽማግሌው ወጣ ያለ ገፀ ባህሪ እንድሞክር ዕድል የሰጠኝ የለም፡፡ ሌላውንም ገፀ ባህሪ መስራት እንደምችል ገብቷቸው ዕድል የሰጡኝ ሳምሶን ወርቁ እና ዳንኤል ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡
ጥያቄ፡- በቲቪም፣ በመድረክም፣ በፊልምም ጋቢ እና ካፖርት ለብሰህ የምትታይ ከመሆኑ አንፃር ሰዎች በመንገድ ሲያገኙህ ምን ይሉሃል?
መኮንን፡- ብዙ ሰዎች ጋቢ ለብሼ ወይም ካፖርት ደርቤ የሚያገኙኝ ስለሚመስላቸው ሸንቀጥ ብዬ ሲያገኙኝ ይደነግጣሉ፡፡ ለካ ሽማግሌ አይደለህም ብለው የሚገረሙ አሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ‹‹እርስዎ›› እያሉ የሚያወሩኝ ሞልተዋል፡፡ በዕድሜ ከእኔ በላይ የሆኑት እንደውም ወልደው ሊያደርሱኝ የሚችሉት ሳይቀሩ ‹‹እርስዎ›› እያሉ ያወሩኛል፡፡
ጥያቄ፡- የእውነት ግን… አንተ እንዲህ ሲሆን ምን ይሰማሃል?
መኮንን፡- ስለ እውነት ለመናገር ደስታ ነው የሚሰማኝ፡፡ ምን ያክል ውስጣቸው እንደገባሁ የማረጋገጥበት አጋጣሚ ስለሆነ ሁሌም ደስተኛ ነው የምሆነው፡፡
ጥያቄ፡- ለአንድ አርቲስት የችሎታው መለኪያ ሆኖ የሚቀርበው የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ወክሎ መጫወት መቻሉ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ከሽማግሌው ወጣ ብሎ ሌሎችንም የመሞካከር ዕቅዶች የሉህም?
መኮንን፡- በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህ አሁን በህዝቡ ዘንድ የምታውቅበት የሽማግሌ ምስል ይቀየራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ የሽማግሌ ገፀ ባህሪ ደጋግመው ስላዩኝ እንደ አርቲስት ሳይሆን የሆነ ቦታ እንደሚያውቋቸው ሽማግሌ ነው የሚያስቡኝ፡፡ ለዚህም ነው ሽማግሌዎቹ ሳይቀሩ ‹‹አንቱ›› እያሉ የሚያወሩኝ፡፡ ስለዚህ ይህን ነገር ለመቀየር አንዳንድ ስራዎች እየሰራሁ ነው፡፡ በቅርቡ ለእይታ የሚበቁ ቀየር ያሉ ገፀ ባህሪያትን እየሰራሁ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ከዚያ በኋላ የሽማግሌው ይቀራል ማለት ነው?
መኮንን፡- አይቀርም፣ እንደውም በሌላ መልኩ ተጠናክሮ ነው የሚቀጥለው፡፡ በተለይ ከስር ያሉ ህፃናትን በጥሩ ስነ ምግባር የመቅረፅ ሚና ያላቸው ሽማግሌ ሆነው ይመጣሉ፡፡ በዚህ ላይ የራሴን ፕሮጀክት ቀርጬ እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ ልጆች ሀገራቸውንና ባህላቸውን እዲወዱ፣ ራሳቸውን ከመኪና አደጋ እንዲጠብቁ፣ ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸውና በትምህርታቸው እንዲተጉ የሚያበረቱ ገፀ ባህሪ ሆነው ይመጣሉ፡፡
ጥያቄ፡- የኪነ ጥበብ ህይወትህ መነሻው ከየት ነው?
መኮንን፡- እኔ ሁሉ በፈጣሪ ሆነ ነው የምለው፡፡ ባይሆንማ የእኔ ሀሳብ ሌላ ነበር፡፡ ትንሽ በቀለሙም፣ ትንሽ በኳሱም ገፋ ብዬ ነበር፡፡ ህይወትን የማሸንፈው፣ እንጀራ የምቆርሰው ከሁለቱ በአንዱ ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና ወደዚህ መጣሁ፡፡ በትምህርቴ ትንሽ ደህና ነበርኩ፣ ኮሌጅም ገብቼ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬያለሁ፡፡ በእግርኳሱም እስከ ምድር ጦር ቢ ቡድን ድረስ ደርሼ ነበር፣ አባቴ ነው ያስተወኝ፡፡ መብራት ኃይል ገብቼ ኤሌክትሪክ ስሰራ ቆየሁና ምኑንም ሳላውቀው በቀጥታ ወደ ኪነ ጥበቡ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬ ተዋናይ ሆኛለሁ፡፡ ለነገሩ በተፈጥሮዬ አንድ ነገር ላይ ብቻ መቆየት ደስ አይለኝም፡፡ ኤሌክትሪኩ ሰልቸት ብሎኝ ስለነበር ኪነ ጥበብ ጥሩ የለውጥ ቤት ሆኖኛል፡፡ እዚያውም ማርኮ አስቀርቶኛል፡፡ አሁን ሲሸንጠኝ የቤቴን የመብራት ገመድ በጥሼ ከመቀጠል ውጪ ኤሌክትሪኩን እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ፡፡ ኳሱም ተረት ተረት ሆኗል፡፡
ጥያቄ፡- የኪነት ህይወትህ መነሻ ጊዜ መቼ ነው?
መኮንን፡- ጊዜው 1989 ነው፡፡ የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ ተመስገን መላኩ ከእኔ ቀድሞ ጀምሮ ስለነበር በየተገናኘንበት አጋጣሚ ሁሉ ‹‹አንተ እኮ አርቲስት ብትሆን ያዋጣሀል›› እያለ ይወተውተኝ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ተውኔት የመፃፍ ዝንባሌው ነበረኝ፣ እተውናለሁ ብዬ ግን አስቤ አላውቅም፡፡ በወቅቱ የቴአትር አፃፃፍ ዘዴን ማወቅ እፈልግ ስለነበር መምህራን ማህበር አዳራሽ የፀጋዬ ገ/መድህን ‹‹ሀሁ በስድስት ወር›› ሲሰራ እዚያ ወሰደኝ፡፡ እዚያው ኤሌክትሪክ መስራት ስለምችል አንዳንድ የመድረክ መብራቶችን መስራት ጀመርኩ፡፡ አርቲስት ሳምሶን ወርቁ እዚያ ሲያገኘኝ ‹‹አንተ መስራት ትችላለህ›› አለና በማዘጋጃ ቤት በሚታየው ‹‹የሲኦል ነፍሳት›› ቴአትር እንድሳተፍ አደረገኝ፡፡ በዚሁ ተጀመረ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ነው፡፡
ጥያቄ፡- ትራጄዲ ገፀ ባህሪያት ይመቹሃል?
መኮንን፡- ደስ ይለኛል፡፡ ሰውን ከማሳቅና ከማስለቀስ የቱ ይሻላል ብለህ እንዳትጠይቀኝ እንጂ ትራጄዲም ሌላውም ለእኔ አንድ ነው፡፡
ጥያቄ፡- አትጠይቀኝ ብትለኝም እጠይቅሃለሁ… ከኮሜዲ እና ከትራጄዲ የቱን ነው ይበልጥ የምትወደው?
መኮንን፡- እንደ ሰው ከጠየቅከኝ ምናልባት ኮሜዲው ሊበልጥብኝ ይችላል፡፡ እንደ አርቲስት ከጠየቅከኝ ግን ሁለቱም ለእኔ ልዩነት የላቸውም፡፡ ስሰራ ሁለቱንም በፍቅር ነው የምሰራው፡፡ እንደውም ትራጄዲ የበለጠ ጥንቃቄ እና ተመስጥኦን ስለሚፈልግና ትንሽ ከበድ ስለሚል ደስ ይለኛል፡፡ ሰዎች ከባድ ነገርን መወጣት ይበልጥ ደስታን ይሰጠን የለ? በነገራችን ላይ በጣም ብዙ ሰዎች ያለቀሱበት ‹‹አያትየው›› የሚል ፊልም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በየመንገዱ በስክሪን ይታይ የነበረ ነው፡፡ እዚያ ላይ እኔ የምጫወታቸው ሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብዙ ሰዎችን ያስለቅሱ ነበር፡፡ እናቴ ራሷ እስክትረሳኝና በኋላም ‹‹አፈር አባቱ ይብላ ይሄ ሟርተኛ›› እስክትል ድረስ የተጫወትኩት ነው፡፡ በአብላጫው የተጫወትኩት ኮሜዲን ስለሆነ ሰዎች በኮሜዲያንነት ነው የሚያውቁኝ፡፡
ጥያቄ፡- ኮሜዲያን ነኝ ብለህ ታስባለህ?
መኮንን፡- በጭራሽ አላስብም፡፡
ጥያቄ፡- ለምን?
መኮንን፡- ኮሜዲ ገፀ ባህሪያትን እጫወታለሁ እንጂ ኮሜዲያን ነኝ ብዬ አላስብም፡፡
ጥያቄ፡- የኮሜዲያን ማህበር አባል አይደለህም?
መኮንን፡- ነኝ፡፡
ጥያቄ፡- ታዲያ ኮሜዲያን የተሰባሰቡበት ማህበር ውስጥ ምን ዶለህ?
መኮንን፡- ኧረ ነገር አብርድ… ኮሜዲያን ነህ ብለው ጠሩኝ፣ ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የተባለ ድርጅት የኮሜዲ ትርዒት ለማሳየት ጋብዞን ሂልተንና ሸራተን ሰርተናል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ‹‹በማህበር ብትደራጁ መልካም ነው›› የሚል ሀሳብ ሲያመጣ ጓደኞቼ የማህበሩ መስራች ስብሰባ ላይ ጠሩኝ፡፡ ማህበር ለማንኛውም ነገር ጥሩ ነው፡፡ ከዕቁቡም ከዕድርም ጀምሮ ያለው የጋራ ነገር ጥሩ ስለሆነ ኮሜዲያን ነኝ ብዬ ባላስብም አባል መሆኔ ክፋት የለውም በሚል ነው አባል የሆንኩት፡፡
ጥያቄ፡- ብዙ ጓደኞችህ ‹‹መኮንን ላዕከ›› በሚለው ስም አይጠሩህም፡፡ ብዙዎቹ ‹‹አባዬ›› ነው የሚሉህ፡፡ ይህ ነገር ከክበበው ገዳ ጋር የ‹‹ሸምሱን›› ቪሲዲ ከሰራችሁ በኋላ የተፈጠረ ነው?
መኮንን፡- በየቦታው የተለያየ ስም ነው ያለኝ፡፡ እንዳልከው እሱ ሸምሱን ሆኖ እኔ ሽማግሌውን ሆኜ በሰራነው ቪሲዲ ‹‹አባዬ›› እያለ ነው የሚጠራኝ፡፡ አጠራሩ ቀለል ያለ እና አዝናኝ ስለሆነ አፍ ላይ ቶሎ ይቀራል፡፡ ጓደኞቼ አጠራሩ ስለተመቻቸው ያው ‹‹አባዬ›› ይሉኛል፡፡ እኔን ብዙ ሰው በመኮንን የሚያውቀኝ አይመስለኝም፡፡ ድፍን የፒያሳ ሰው ‹‹አባዬ›› ነው የሚለኝ፡፡ ወደ ተረት ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ስትወርድ ‹‹አከቤ›› ሲሉኝ ትሰማለህ፡፡ በጉራጊኛ አጎቴ ማለት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ቡድን የመምራት ብቃትህን ብዙ ጓደኞችህ ያነሱታል፡፡ ያለህበትን ቡድን አንድ መንፈስ፣ አንድ ልብ የማድረግ ችሎታህ ከየት የመጣ ነው?
መኮንን፡- የአንድ ሰው መገለጫው እና የሰብዕናው መጠንሰሻ ቤተሰብ ነው፡፡ ያደግኩበት አካባቢ ማህበረሰብ ለዚህ ነገር ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እኔ ተወልጄ ያደግኩበት ጊቢ አስራ አራት ቤተሰብ ያለበት ነው፡፡ ለአስራ አራቱ ቤት አንድ ኩሽና (ማዕድ ቤት)፣ አንድ ሽንት ቤት፣ አንድ ቧንቧ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ጠብ የለበትም፡፡ ሁሉም በስምምነትና በመደማመጥ ነው ተከባብሮ የሚኖረው፡፡ በፍቅር የሆነ ነገር ሁሉ ያምራል፣ ምንም አያስቸግርም፡፡ የእኛ ሰው ደግሞ የሚያነሳሳውና የሚመራው ይፈልጋል እንጂ ሁሌም ለመተባበር ዝግጁ ነው፡፡ በል እንዲህ አድርግ የሚለው አስተባባሪ ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ ንፁህ ልብ ይዞ የሚገኝ ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይከብደውም፡፡ ይህን ከተወለድኩበት አካባቢ ተምሬዋለሁ፡፡ የሁሉ ነገር ቁልፍ ንፁህ ልብ ነው፡፡ ንፁህ ሆነህ ስትቀርበው ንፁህ ሆኖ የማይቀበልህ ማንም የለም፡፡ ቁልፉ ነገር ይሄ ነው፡፡ እንደውም አንድ ምሳሌ ልንገርህ አንዴ አንበሳ፣ ነብርና ዝሆን ከሰው ጋር ሆነው ሰርከስ እየሰሩ በቴሌቪዥን አየሁ፡፡ እንዴት ነው ሊግባቡና ሊዋደዱ የቻሉት ብዬ ሌሊቱን ቁጭ ብዬ አደርኩ፡፡ መልሱን ያገኘሁት ሊነጋጋ ሲል ነው፡፡
ጥያቄ፡- መልሱ ምንድነው?
መኮንን፡- ሰውዬው ነው መጀመሪያ ጫካ የሄደው፡፡ በቃ ራሱን ሰጣቸው፣ ንፁህ ልቡን ይዞ በደመነፍሱ ነው የሄደው፡፡ ልቡ አብጦበት አልሄደም፣ የሚበላውን ሰጣቸውና በሉ፡፡ ከዚያ ደጋግሞ እንደዚያ አደረገ፡፡ ንፁህ ልብ እንዳለው ስላወቁ ወደዱት፡፡ ሲቀር ናፈቁት፡፡ ቆይቶ ሲሄድ ገና ከሩቅ አይተውት ወደ እርሱ መጡ፣ ከዚያ ‹‹ኑ ወደ ከተማ እንሂድና ሰርተን እንብላ›› አላቸው፡፡ በደመ ነፍስ ተግባብተው ያን ትርዒት አሳዩን፡፡ ንፁህ ስትሆን እንኳን ሰው አውሬም ይቀርብሃል፤ ይወድሃል፡፡
ጥያቄ፡- ሰዎችን በስራዎችህ ታስደስታለህ፣ አንተንስ ምን ያስደስትሃል?
መኮንን፡- ከጓደኞቼ ጋር ቁጭ ብለን ውይይት ስናደርግ የተለየ ደስታ አለኝ፡፡ ከዚህ ውጭ ማንበብ በጣም እወዳለሁ፡፡ ካላነበብኩ እንቅልፍ አይመጣልኝም፡፡ ጊዜው ያለፈበት ጋዜጣም ቢሆን የማንበብ ልማድ አለኝ፡፡
ጥያቄ፡- ቦሌ አካባቢ ታይተህ አታውቅም፤ ለምንድነው?
መኮንን፡- እኔንጃ… ምክንያቱን ባላውቀውም አይመቸኝም፡፡ ፒያሳ ደስ ይለኛል፣ ጨርቆስ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ቦሌ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ… አይመቸኝም፡፡ ወደዚያ የምሄድበት ጉዳይ እንዲኖረኝም አልፈልግም፡፡ ምናልባት ንፅፅሩን ማሰብ ስለማልፈልግ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የፈሩት ይደርሳል እንዲሉ ቦሌ አሁን ጨርቆስ ሆኗል፡፡ መሀል ቦሌ ጨርቆስ ክፍለ ከተማ እየተባለ መጠራት ጀምሯል፡፡ የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል ማለት እንግዲህ ይሄ ነው፡፡
ጥያቄ፡- በርገር ትወዳለህ? ይመችሃል?
መኮንን፡- በልቼው አውቃለሁ፡፡ እንደ በርገር ነው፤ እንደ ቤታችን በር በጣም ገር ነው፡፡ ሸጋ፣ ገራገር ነው፡፡
ጥያቄ፡- ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብለህ ተመኝተህ አታውቅም?
መኮንን፡- ይሄን ጥያቄ ትናንት ማታም የሆነ ሰው ጠይቆኝ ነበር፡፡ እኔ ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብዬ ተምኝቼም አስቤውም አላውቅም፡፡ ይልቅ እስከዛሬ አብረሃቸው ከሰራኸው ማን ተመችቶሃል ካልከኝ ፋንቱ ማንዶዬ ነው፡፡ ልጅ ሆኜ በጩጬነቴ እንዴት ተሻምተን እናየው እንደነበር አሁንም ይታወሰኛል፡፡ ‹‹የት ሄደሽ ነበር›› ሲል ሰው ሁሉ እንዴት ደስ እንደሚለው አስታውሳለሁ፡፡ ከፋንቱ ጋር መስራቴ ልዩ ደስታን ፈጥሮብኛል፡፡ ከመስራቴም ባሻገር ያሳየኝ ባህሪ ቀለል አድርጌ በጥሩ ሁኔታ እንድሰራ አድርጎኛል፡፡ ተተኪን እንዴት ማፍራት እንዳለብን በተግባር አስተምሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ጀማሪን ማስጠጋት ዝናቸውን የሚቀንስባቸው የሚመስላቸው አሉ፡፡ ሌሎች ያላሳዩንን ፊት ፋንቱ አሳይቶኛል፡፡ ያቺ አጋጣሚ ለእኔ ልዩ ትርጉም አላት፡፡ አሁን ባለኝ ህይወትም የፋንቱን አርአያነት ተከትዬ ነው እየተገበርኩ ያለሁት፡፡
ጥያቄ፡- በመጨረሻ ምን የምትለው ነገር አለህ?
መኮንን፡- የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ ስለዚህ የምናደርገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር የሚወደድ እንዲሆን በቅን ልቦና እና በንፁህ ልብ ይሁን እላለሁ፡፡ እግዚአብሔር የወደደው ነገር ከሆነ ሁሉም አልጋ በአልጋ ነው፡፡
ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ቅን እንሁን እላለሁ፡፡ ሁለተኛ ጥበብና ጠቢባንን ያላከበረ ህዝብና መንግስት አይከበርም አይከብርም ለማለት እወዳለሁ፡፡ ባለሙያው ለሙያው ሲታገል መንግስትም ሙያውን ለማስከበር ቢጥር ለሀገር የሚጠቅም ውጤት ይገኛል፡፡
ከዚህ በተረፈ ለእኔ እዚህ መድረስ እገዛ ላደረጉትና ልረሳቸው ለማይቻለኝ ለአቶ አበበ አያሌው፣ ለመስፈን ከበደ፣ ለሳምሶን ወርቁ፣ ለክበበው ገዳ፣ ለእንዳልክ እሱባለው፣ ለያሬድ አስራት፣ ለሰላማዊት አለማየሁ፣ ለእሸቱ ታዬ፣ ለእህቴ አማከለች ላዕከ፣ ለጌታቸው ላዕከ፣ ለአለማየሁ ላዕከ እኛን እዚህ ለማድረስ ብዙ መስዋዕትነት ለከፈሉት እናትና አባቴ እንዲሁም እስከዛሬ አብረውኝ ለሰሩት እና ለጨርቆስ ነዋሪዎች በሙሉ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እናንተም ታሪክ አለህና ‹‹መድረኩን እንካ ተናገር›› ስላላችሁኝ ከልብ አመሰግናችኋለሁ፡፡

↧

ይድረስ ለ‹‹ሰው ለሰው ድራማ›› ደራስያንና ፕሮዲውሰሮች

$
0
0

sew le sew
ይድረስ…

መቼም ለአርቲስት ‹‹አድናቂህ ነኝ›› ከሚለው ቃል በላይ የልቡን የሚያደርስለት ሌላ ቃል አይኖርምና ከመቶ ሃያ ክፍሎች በላይ ለተሻገረው ድራማችሁ ያለንን ልባዊ አድናቆት በማስቀደም እንጀምራለን፡፡ እንኳን በርካታ ተመልካቾች የወደዱትን ረጅም ድራማ መፃፍ ቀርቶ አንዲት ገፅ ደብዳቤ አሣክቶ መፃፍም ራሱን የቻለ ጥበብ ይጠይቃል፡፡ ድራማችሁ ይህን ያህል ርቀት ሲጓዝ ጠንካራዎቹን እያደነቅን፤ ደካማዎቹን ተዋንያን ደግሞ በልባችን እየተቸን ዕድሜ ሠጥቶን እዚህ ደርሠናል፡፡ ታዲያ ከሠሞኑ ገብታችሁበታል የተባለው ውዝግብ እኛም በልባችን ይዘነው የተቀመጥነውን ቅሬታ እናወጣ ዘንድ ምክንያት ሆነን፡፡

ሰው ለሰዎች ሆይ!

ድራማችሁን የሚያስተላልፈው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የሰው ለሰው ባለቤት ስፓርክስ የፊልም አምራች አልተግባቡም የተባለው እውነት ይሆን? የንትርካችሁ መነሻ ደግሞ ድራማውን ቶሎ ጨርሱት የሚል ነው አሉ፡፡ እናንተም’ኮ አበዛችሁት፤ ቅዳሴ እንኳን ረዘመ ብሎ የሚያጉረመርም ህዝብ ባለበት ሀገር ድራማን ማንዛዛት ምን የሚሉት እርፍና ነው? ከሶስት ሺህ ዘመን ታሪካችን በቀር በዚህች ሀገር ምን ረጅም ነገር አለ? ዕድሜያችን አጭር፣ ደስታችን አጭር፣ የእግር ኳስ ስኬታችን አጭር…… ታዲያ ምን ታይቷችሁ ነው የድራማውን ዕድሜ የማቱሳላ ለማድረግ የቆረጣችሁት? ኢቴቪም’ኮ እውነቱን ነው የቴሌቪዥን ጣቢያና ስፖንሰር ተገኘ ብላችሁ ታሪኩ ቀድሞ ያለቀ ነገር እንደመስቲካ ስታላምጡ ሌላ ዓመት መጨመር ነበረበት? ቀድሞም ያደነቅናችሁ እኮ ለድራማው ጥሩነት እንጂ ለተንዘላዘለ እድሜው አልነበረም፡፡ ‹‹ታዲያ ታሪኩን ሰብሰብ አድርጋችሁ ጨርሱት›› የሚል ደብዳቤ እስኪረደርሳችሁ ድረስ ተመልካች ተገኘ ብሎ ድራማን ማንዛዛት ምን ይጠቅማል? ደግሞ ይህ ተመልካች ቤቱ ድረስ የመጣለትን ድራማ ማየቱ ሥራችሁን ለመውደዱ እንዴት ዋስትና ይሆናል? እንኳን ድራማ የኢቴቪ ዜናና ዶክመንተሪዎችንም ልባችን እያዘነ እንኳ እንመለከት የለ? ታዲያ የታየ ሁሉ ይወደዳል እንዴ?
Sew Le Sew Part 124 HD (new)
ሠሞኑን የድራማችሁን መንዛዛት አስመልክቶ በአንድ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ የተለጠፈ ፅሑፍ ተመልክተን ነበር፡፡ ምነው ድራማውን አንዛዙት፡፡ ይህንንም ቶሎ እንዲጨርሱልን ለቻይናውያን አሳልፈን እንስጣቸው እንዴ? ለዚህም ቻይናውያን ይምጡልን? የሚል ሃሳብ የያዘ ፅሁፍ ነበር፡፡ እንግዲህ ስንት የኑሮ ጥያቄዎች አናታችን ላይ የሚጨፍሩብን አንሶ ከጥበቡ ይልቅ ቢዝነሱ የበዛ የሚመስል አንድ ድራማ ለምን ተንዛዛ ብለን መቼም ሰልፍ አንወጣም፡፡ እናንተ ግን ምነው የአየር ሠዓቱን የስልጣን ወንበር ይመስል ሙጭጭ አላችሁበት?

ሰው ለሰዎች ሆይ!

ድራማችሁ የተበላ እቁብ ሆኗል እየተባለ ነው፡፡ ህዝቡ ታሪኩን ቀድሞ ጨርሶታል፡፡ ከሐዋሳ እስከ ዱባይ የተንሸራሸራችሁባቸው የተለያዩ መቸቶችም ሆን ተብሎ ስፖንሰር ለማብዛትና ቢዝነሳችሁን ለማሳደግ እንጂ የግድ ሆነው የተደረጉ አይመስለንም፡፡ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ተዋናዮችን እየለዋወጣችሁ የምታሣዩን ድራማ ይሁን እግር ኳስ እጅግ ግራ አጋብታችሁን ነበር፡፡ ተቀያሪ ተዋናዮቹን እንደምንም እየለመድን ስንመጣ ደግሞ በፕሮዲውሰሮች መካከል አለመግባባት ተፈጠረ ተባለ፡፡ ‹‹ደራስያኑ ሥነ-ምግባራቸው ብልሹ ነው፤ ከእነርሡ የማይጠበቅ ነገር ሊያደርጉ ሞክረዋል›› የሚል አይነት ክስ ከአንዷ የቀድሞ የድራማው ተዋናይ ተነገረ፡፡ በዚህም አዘንን፡፡

ሰው ለሰዎች ሆይ!

የእናንተ ጉዳይ በዚያ ብቻ ሳያበቃ ከሰሞኑ ደግሞ ድራማችሁን እንድትጨርሱት ብቻ ሳይሆን እንዴት መጨረስ እንዳለባችሁም ትዕዛዝ ተሰጥቷችኋል አሉ፡፡ ምናልባት ድራማን በትዕዛዝ ለመጨረስ በዓለም የመጀመርያዎቹ ደራስያን በመሆን በጊነስ የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሳትመዘገቡ አትቀሩም፡፡ እናንተስ ‹‹ታሪኩን ሰብስበን መጨረስ አልቻልንም›› ማለታችሁ አሳፋሪ አይደል? ሰው እንዴት የበተነውን ታሪክ መሰብሰብ ያቅተዋል? ለነገሩ አስናቀን የሚያህል ትልቅ ገፀ ባህሪ ፈጥራችሁ ከከፍታው ለማውረድ ሳትቸገሩ የቀራችሁ አይመስለንም፡፡ ቀድሞስ ሳይቸግራችሁ ራሳችሁ ላይ ማን አንግሡት አላችሁ? ወይ ለምን መላው ከጠፋችሁ የአስናቀን ነገር እንደ ዩክሬኗ ክሬሚያ ‹‹በህዝበ ውሳኔ›› አትዳኙትም?

ሰው ለሰዎች ሆይ!

Sew Le Sew – Part 125 HD (New)መቼም አስናቀ-መር የሆነ ድራማችሁ መቋጫው እንደ ምፅዓት ዘመን ከሚርቅ የህዝቡን ውሳኔ ሰምታችሁ አስናቀን ወይ በቁጥጥር ስር ታውሉት አልያም የአሸናፊነት ቁልፉን ሰጥታችሁን፡፡ ታሪኩን ታጠናቅቁልን ይሆናል፡፡ የረዘመ ነገር ሁሉ መች ይወደዳል? ፍቅር እስከመቃብር የተወደደው’ኮ በስነ-ፅሑፋዊ ውበቱና ከዘመኑ ቀድሞ የተገኘ በመሆኑ እንጂ እንዲሁ በመዘርዘሙ ብቻ አልነበረም፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እድሜው ላይ ብቻ ሳይሆን ውበቱ ላይ ተጨንቃችሁ ለድራማችሁ የደራሲነት መላ ስጡት፡፡

ሰው ለሰዎች ሆይ!

በእርግጥ እናውቃለን የድርሠት ፍዳ እልህ አስጨራሽ ነው፡፡ ያንን ሁሉ ባለሙያ በአግባቡ እየመሩ ተወዳጅ የሆነ የቴሌቪዥን ድራማ ማቅረብ ትልቅ የሙያ ክህሎትና ሀላፊነት ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም ግን በየጊዜው የምትገቡበት እሠጥ አገባ ለስማችሁ ጥሩ አይደለም፡፡ እኛም በድራማችሁ ላይ ባሳያችሁን ብቃት እንጂ በፍርድ ቤት ባደረጋችሁት የመካሠስ ታሪክ ልናስታውሳችሁ አንሻም፡፡ የድራማውን ግማሽ ሰዓት የሚወስድ የስፖንሰር ሽፋን እንዳላችሁ እየታወቀ በባንካችሁ የተቀመጠው ገንዘብ ሠባ ዘጠኝ ብር ብቻ እንደነበር መስማታችን ደግሞ ሌላው አነጋጋሪ ነገር ነው፡፡ መቼም ድራማውን ለፅድቅ እንደማትሠሩት እናንተም፤ እኛም አሳምረን እናውቃለን፡፡ ዱባይ ድረስ እየሄዳችሁ የምትሠሩት ድራማ ያስገኘላችሁ ትርፍ ‹‹የህዝብ ፍቅር›› ብቻ ከሆነ ይኸው የህዝቡን ፍቅር አግኝታችኋልና ድራማችሁን መላ በሉት፡፡ እባካችሁ!

ምንጭ፡ ይህ ጽሁፍ የተገኘው ከቁም ነገር መፅሔት 13ኛ ዓመት ቅፅ 13 ቁጥር 177 ይድረስ… ዓምድ ነው፡፡

↧
Viewing all 261 articles
Browse latest View live