Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic Âť Entertainment
Viewing all 261 articles
Browse latest View live
↧

ዳና ምዕራፍ 3 ክፍል 53 ሐምሌ 27 /2006 ዓ.ም

$
0
0

ዳና ምዕራፍ 3 ክፍል 53 ሐምሌ 27 /2006 ዓ.ም

ዳና ምዕራፍ 3 ክፍል 53 ሐምሌ 27 /2006 ዓ.ም

↧

አባሮሽ # 1

↧
↧

የትዝታው ንጉሥ ‹‹ለክብር ዶክትሬት›› አይመጥንም?

$
0
0

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ቅርብ የሆነ ሠው ሁሉ ከሀገራችን ምርጥ አምስት ድምፃውያን መካከል አንዱን ጥራ ቢባል መሀሙድ አህመድን መጥራቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ ከዘመን አቻዎቹ የሙዚቃ ሠዎች ጋር የሠራቸው ስራዎች ከየትኛውም ሀውልት በላይ በአድናቂዎቹ ልቦና ተቀርፀው ምንጊዜም ከታላላቅ ድምፃውያን መካከል አንዱ መሆኑን ሲመሰክሩ ይኖራሉ፡፡ ይህ ሰው የሙዚቃ ሥራው ብቻ ሣይሆን ህይወቱም አስተማሪ ነው፡፡ በትምህርቱ ያላገኘውን ስኬት በጫማ ጠራጊነትና በሆቴል ቤት ሠራተኝነት ሞክሮ ብዙም ሳይቆይ እጣፈንታው ወደመራው የሙዚቃ ህይወት ማልዶ መጥቷል፡፡
mahmoud ahmed 2
ከታዋቂው የክቡር ዘበኛ ኦርኬስተራ ጀምሮ ከቬነስ ባንድ፤ ከዳህላክና ከአይቤክስ ባንድ ጋር የተለያዩ አልበሞችን የሠራ ሲሆን በክራር፤ በጊታርና በማንዶሊን የታጀቡ ጊዜውን የሚዋጁ ዘመን አይሽሬ ሙዚቃዎችም አሉት፡፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን በሚባለው በ1970ዎቹ የራሱን ጣዕም ይዞ ወደ ከፍታው መጓዝ የጀመረው መሀሙድ በ1980ዎቹ የራሱን ሙዚቃ ቤት በመክፈት በአሣታሚነቱ ዘርፍም የሀገራችንን ሙዚቃ ለማሳደግ የድርሻውን ተወጥቷል፡፡ መሀሙድ አህመድ ከዋሊያስ ባንድ ጋር በመሆን ሥራቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይዘው ከሄዱት ጥቂት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው፡፡ ከታዋቂው የሮሀ ባንድ ጋር የሠራቸው ድንቅ ሙዚቃዎችም ከትውልድ ትውልድ የመሸጋገር አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

እንደ ድምፃውያኖቿ መብዛት ዘመናዊ ሙዚቃዎቿን ለዓለም ማኀበረሠብ አቅርባ የዓለም ገበያ ውስጥ መግባት ላልቻለችው ኢትዮጵያም በግሉ ጥረት በአውሮፓ ሀገራትና በአሜሪካ ተዟዙሮ በሚያቀርባቸው የሙዚቃ ኮንሠርቶች የአምባሳደርነት ሚናውን የተወጣ ታላቅ ድምፃዊ ነው፡፡ ማህሙድ ድንበር ተሻግሮ የምዕራባውያንን ጆሮ መግዛት በመቻሉም እ.ኤ.አ በ2007 የቢቢሲ የሙዚቃ አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ከአራቱ ኢትዮጵያዊ ቅኝቶች መካከል ለትዝታ ዘፈኖች ያለው ፍቅር የተለየ ነው፡፡ ከሌሎች ድምፃውያን በተለየ መልኩም የትዝታ ዘፈኖች የራሱ መገለጫ እስኪሆኑ ድረስ ከዚህ ቅኝት ጋር በፍቅር መውደቁን የሚገልፀው ‹‹ትዝታን ስጫወት ፀጉሬ ይቆማል›› በማለት ነው፡፡ በሌሎች ዘፈኖቹም ቢሆን በምናብ ገጠር ድረስ ወርዶ የገበሬውን ህይወት ከማሳየት ባሻገር፤ ልብ የሚያረሠርሡ የፍቅር ዜማዎች በማቀንቀን እንዲሁም እንደዘመን ተጋሪዎቹም ትውልዱን በበጎ ስነ- ምግባር የሚመሩ ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኖችን በብዛትም፣ በጥራትም የሠጠን አንጋፋ ድምፃዊ ነው፡፡
mehamud ahemed 3

መሐሙድ በበጎ አድራጎት ስራዎቻቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት አርቲስቶች መካከልም አንዱ ነው፡፡ መጠጊያ መሸሸጊያ ላጡ አረጋውያን የሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ፤ ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናትና ለአዕምሮ ህሙማን የሚሠጣቸው እርዳታዎች በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ባተረፈው ዝና ልክ የተነገሩለት ባይሆንም የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህይወት መለወጣቸው ግን ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ ለችግራቸው ደርሶ ተስፋቸው እንዲለመልምና ከሞት አፋፍ እንዲመለሱ ካደረጋቸው በርካታ ሠዎች ባሻገር ጓደኞቹንና የጉራጌ ተወላጆችን በማስተባበር በጉራጌ ዞን አረቀጥ ከተማ ያሠራው የመጀመሪያ ሁለተኛና መሠናዶ ት/ቤት የልግስናው አንዱ ማሳያ ነው፡፡፡ መሀሙድ መድረክ ላይ ብቻ ወጥተው ስለ ‹‹ህዝብ›› ፍቅር በመናገር የተለከፉና ተግባሩ ላይ ምንም የሆኑ ድምፃውያን በበዙባት ሀገር እውነተኛ ወዳጅነቱን ለተለያዩ ሠዎች በሠጠው የአዕምሮ ሠላም፤ በችግር ከመፍረስ ባዳናቸው ቤተሠቦች እንዲሁም አቅም ሆኗቸው ትምህርታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ በረዳቸው ተማሪዎች ስም ደጋግሞ አሣይቷል፡፡

እንደ ህዝብ ይህንን ሠው በእርግጥ አክብረነዋል፡፡ ከፍቅርና አክብሮታችን የተነሣም አስገዳጅ ህግ ሣይወጣልን ‹‹ጋሼ›› ብለን ማንም የማይነጥቀውን ማዕረግ ሠጥተነዋል፡፡ ታዲያ በማህበረሠቡ የተሠጠው ግዙፍ ክብር ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ለሚሰጥ ‹‹የክብር ዶክትሬት›› ሣያበቃው እንዴት ቀረ?(ለነገሩ ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲዎቻችንስ የማህሙድ ያህል መች ታወቁ?!) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አንዱ መስፈርት ‹‹የማህበረሠቡን ችግር የሚፈታ አንዳች ቁም ነገር ማበርከትም አይደለምን? የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሌላው መስፈርት በተሠማሩበት ሙያ ደከመኝ ሠለቸኝ ሳይሉ በዓለም አደባባይ የሀገርን ስም ማስጠራት አይደለምን?›› ለመሀሙድ አህመድ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለመስጠት እንደመሠረት ደፋርና ጥሩነሽ የትራክ ውድድር አዘጋጅተን ከኬንያ ሯጮች ጋር ማወዳደር ወይም የዳይመንድ ሊግ ውድድር ተሣታፊ ሆኖ መመልከት ይኖርብን ይሆን? ይህ ሠው ዛሬ የሠባዎቹ መጀመርያ የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ ክፉውን ያርቅልንና መሀሙድ እንደ የዕድሜ አቻዎቹ ጋሽ ጥላሁን ገሠሠ፤ ምንሊክ ወስናቸውና ታምራት ሞላ ሠማያዊ ጥሪ ቢደርሰው የክብር ዶክትሬቱን በአበባ ጋር ከመቃብር አፋፍ ላይ ልናደርግለት ኖሯል? ወይስ እንደነ ሀዲስ አለማየሁ፤ ንጋቷ ከልካይ፤ ጥላሁን ገሠሠና ጋሽ ተስፋዬ አበበ (የክብር ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ አበበ) የዘገየ የክብር ዶክትሬት ልናበረክትለት ይሆን?
mehamud ahemed

ለነገሩ የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲዎቻችን የክብር ዲግሪዎች እየተተቹ ነው፡፡ ‹‹የክብር ዲግሪ እንዲህ ከሆነ እኔም አንድ ቀን ማግኘቴ አይቀርም›› የሚሉ ስላቆች በዝተዋል፡፡ በየዓመቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የሚወሰነው ውጤት በተማሪዎቹ አቅም ሳይሆን በዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪን የመቀበል ልክ እንደሆነ ሁሉ በየዓመቱ የሚሠጡት የክብር ዶክትሬቶችም በጀግኖቻችን ልክ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎቻችን በተሠጣቸው የሸላሚነት ኮታ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ እንዲህ ከሆነ በአንድ ዓመት ብቻ ሠላሣ አንድ የክብር ዶክተሮች ሊኖሩን ነው፡ ፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የቅደም ተከተሉም ጉዳይ መታሠብ አለበት፡፡ መሐሙድ አህመድ ተዘንግቶ አስቴር አወቀ ስትሸለም (የራሷ ክብር ያላት ድምፃዊ መሆኗ እንዳለ ሆኖ) ቀነኒሳ በቀለ ተቀምጦ ጥሩነሽ ዲባባ የክብር ዶክተር ተብላ ስትሸለም ጉዳዩ አጠያያቂ ሆኖ እንዳይቀር ልብ ማለት ያስፈልጋል፡ ፡ የዕድሜም ጉዳይ መታሠብ አለበት፡፡ መሐሙድ አህመድን የሚያህል የኢትዮጵያን ሙዚቃ አልማዝ ሆኖ ያደመቀ ታላቅ አርቲስት የዘነጋ የክብር ዶክትሬትም ከማስጨብጨቡ ይልቅ ከንፈር ማስመጠጡ ያመዝናል፡፡ ለነገሩ መሐሙድ ይህንን ነገሬ ብሎ የሚይዘውም አይመስልም፡፡ በተለመደ ምላሹ ‹‹ዝምታ ነው መልሴ›› ብሎ ያልፈው ይሆናል እንጂ፡፡

በነገራችን ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሚሰጠው የክብር ዶክትሬት ድግሪ ጥቆማ ከማንኛውም ግለሰብ ወይም ተቋም እንደሚቀበል ገልፆል በመሆኑም ማህሙድ በሰራው ሥራ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሊያገኝ ይገባዋል ከሚሉ ወገኖች መሀከል አንዱ ሰለሆንኩ እነሆ ጥቆማ ለዩኒቨርሲቲው እላለሁ፡፡

ምንጭ፡ በአዲስ አበባ የሚታተመው ቁምነገር መጽሔት የነሐሴ ዕትም።

↧

የቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዘፈን ከክሊፕ ጋር ሊለቀቅ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሰሜን አሜሪካ ካሊፎርኒያ፣ ኒዮርክ፣ ሲያትል፣ ሚኒሶታና ቴክሳስ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ካቀረበ በኋላ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰ ሲሆን እዛም የተመለሰው የጀመራቸውን ነጠላ ዜማዎች ለማጠናቀቅ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል።
teddy afro
እንደምንጮቻችን ገለጻ ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ የሚለቀው ነጠላ ዜማ ቪድዮ ክሊፕ የሚኖረው ሲሆን አብዛኛው ሥራም መጠናቀቁም ታውቋል። ዘፈኑም የሙዚቃው ክሊፕም አንድ ላይ እንደሚለቀቅ የጠቆሙት ምንጮቻችን ዘፈኑ እንደተለመደው እስካሁን ሌሎች ድምጻውያን ያልነኩትን ሃገራዊና አዲስ ሃሳብ ይዞ እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

ቴዲ በሰሜን አሜሪካ ኒዮርክ እና ሚኒሶታ ላይ አዳዲስ ሁለት ነጠላ ዜማዎችን መድረክ ላይ የለቀቀ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን እነዚህን ዘፈኖች በስቱዲዮ ቀርጾ ይልቀቃቸው አይልቀቃቸው ምንጮቻችን የነገሩን ነገር የለም።

ድምጻዊው አዲሱን ነጠላ ዜማ ከክሊፕ ጋር ከለቀቀ በኋላ በላስቬጋስ፣ ዋሽንግተን ዲሲ ዳላስን ጨምሮ የተለያዩ ኮንሰርቶች እንደሚኖሩት ታውቋል።

↧

ይህች ናት ጨዋታ፡ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ይርዳው ጤናው ካርታ ሲጫወቱ (ፎቶ)

$
0
0

በሶሻል ሚዲያ ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ የለቀቃት ፎቶ ናት። ከረዥም ዓመታት በፊት ከድምጻዊና ኮሜዲያን ይርዳው ጤናው ጋር ካርታ ሲጫወቱ የሚያሳይ ፎቶ ነው። ድምፃዊ ጎሳዬ በዚህ ዘመን ካሉ ብርቅና ድንቅ ድምጻውያን መካከል አንዱ ሲሆን ድምጻነትን እና ኮሚዲነትን በአንድ ላይ የተቸረው ይርዳው ጤናውም እንዲሁ በአስደናቂ ችሎታው ይታወቃል። ይርዳው በካናዳ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖር ሲሆን አዳዲስ ሥራዎቹን አድናቂዎቹ ሁሌም በጉጉት ይጠብቁታል። ይህችን ታሪካዊ ፎቶ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ያጋራነውም እነዚህ ሁለት ጥበበኞች ሥራቸው በጉጉት እየጠበቀ መሆኑን ከመግለጽ ባሻገር እንዴት እርስ በእርስ ሲገናኙ ጥሩ ጊዜ እንደሚያሳልፉ ለማሳየት ነው። የጎሳዬና የይርዳው ጤናው ካርታ ጨዋታን “ይህች ናት ጨዋታ” ብንላትስ?
Yiradw ena Gossaye

↧
↧

ድምጻዊት እናና ዱባለ አረፈች

$
0
0


“እርጎዬዎች” በመባል በሚታወቁትና በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ገናና ከነበሩት 5 እህትማማች ድምጻውያን መካከል አንዷ የነበረችው ድምጻዊት እናና ዱባለ ከዚህ ዓለም በሕይወት መለየቷ ተዘገበ። በ1971 ከእናቷ ወ/ሮ እርጎዬ ጸጋውና ከአባቷ ዱባለ ታርፋለህ በጎንደር አዘዞ እንደተወለደች የሕይወት ታሪኳ የሚያስረዳው ድምጻዊት እናና “ጭር ሲል አልወድም” በሚለው ዘፈኗ ትታወቃለች።
ድምጻዊት እናና ዱባለ አረፈች
አራት ኪሎ ወደ ካሳንቺስ መውረጃ አካባቢ እርጎዬዎች በሚለው አዝማሪ ቤት ከቤተሰቦቿ ጋር በመሆን ስታገልግል እንደቆየች የሚነገርላት ድምጻዊት እናና በ8 ዓመቷ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ሙዚቃ እንዳሰደዳት የሕይወት ታሪኳ ይናገራል።

የሙዚቃ አልበም በ1982 ዓ.ም “አምስቱ እርጎዬዎች” በሚል ከቤተሰቦቿ ጋር በማውጣት ወደ ሙዚቃው ሕይወት ጠልቃ የገባቸው እናና ከእህቶቿ ጋር ሶስት፣ ለብቻዋ ሁለት ሙሉ ካሴት ያሳተመች ሲሆን ከድምጻዊ አበበ ፈቃደ ጋር በሁለት የሙዚቃ ስብስቦች በቅብብሎሽ ያቀረበቻቸው ዜማዎቿ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ እንደሆኑላት የሙዚቃ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ ይገልጻሉ።

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች እንደሚሉት እናና ዱባለ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለማውጣት በዝግጅት ላይ የነበረች ቢሆንም በድንገተኛ ህመም አዲስ አበባ ቤተዛታ ሆስፒታል ገብታ ህክምና ስትረዳ የቆየች ቢሆንም ይህችን አለም ተሰናብታለች።

በድምጻዊቷ እረፍት የተነሳ ዘ-ሐበሻ የተሰማትን ሐዘን እየገለጸች ለቤተሰቦቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን ትመኛለች።

↧

4 ድምፃውያን ለአዲሱ ዓመት የሙዚቃ አልበሞቻቸውን ይለቃሉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አዲስ አመትን በማስመልከት 4 ዝነኛ ድምፃውያን የሙዚቃ አልበሞቻቸውን እንደሚለቁ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። እንደመረጃው ከሆነ ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት ለአንድ ድምጻዊ ሶሻል ሚድያ፣ ብሉ ቱዝ፣ ፍላሽ ድራይቭ እያሉ ሲዲ አውጥቶ ሸጦ ለማትረፍ የማይታሰብ ቢሆንም ይህንን ተቋቁመው ድምጽውያኑ ሥራዎቻቸውን ይለቃሉ።
Ephrem Tamiru
ለረዥም አመታት የሙዚቃ አልበሞችን ሳይሰራ የዘለቀው ኤፍሬም ታምሩ የድሮ ዘፈኖቹን በድጋሚ በኮሌክሽን መልክ ሰርቶ ያጠናቀቀ ሲሆን በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የኤፍሬምን አልበም የሚያሳትመው ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ሲሆን ኤልክትራ ከወራት በፊት የወጣውን የአስቴር አወቀ ሲዲ ሳያሳትም ቀርቶ በራሷ መንገድ እንዳወጣችው ይታወሳል። እንደ ምንጮች ገለጻ የአስቴር የመጨረሻው አልበሟ በጣም የተሰማላት ቢሆንም በሽያጭ በኩል ግን አይደለም። አብዛኛው ሰው በሶሻል ሚድያ፣ በኮፒና ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመከፋፈል ድምጻዊቷን አክስሯታል።

ከኤፍሬም በተጨማሪ በናሆም ሪከርስ በኩል አልበሙን የሚለቀው ታምራት ደስታ ሲሆን፤ በአብ ኢንተርቴይመንት በኩል ደግሞ አብነት አጎናፍር አዳዲስ ሥራዎቹን ይዞ ይቀርባል። በሌላ በኩልም በሰላም ሪከርድስ አማካኝነት ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ ኢን ዘ ሐውስ) አዲሱን የሙዚቃ አልበሙን በአዲስ አመት ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቴዲ አፍሮ “ሰባ ደረጃ” የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ በቅርብ ቀን እንደሚለቅ ለቴዲ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

↧

አዲሱ የቴዲ አፍሮ “በ70 ደረጃ”ነጠላ ዜማ ሙሉ የዘፈን ግጥም

$
0
0

በሰባ ደረጃ

ከመኮንን ድልድይ ከእንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንቺን ብዬ ሳይከብደኝ እርምጃዉ
በሰባ ደረጃዉ

አዝማች፡
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያዉ ዶሮ እንዳይል በከንቱ እረ አንቺን ወዶ ..(ዶሮ ማነቂያ፣ ዕሪ በከንቱ)
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሞያለሁ ከበርሽ ማዶ

ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ
ማታ ማታ

አምጣት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለዉ
ማነዉ ብላችሁ ማነዉ ማነዉ?

ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ

ዘበናይ ዘበናይ….

ሲመሽ ወደ ማታ ሁሉ ዘግቶ በሩን
ታም ታራም ሳረገዉ ብቅ በይ ክራሩን

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ፀጉራን ተተኩሳዉ እንደ አርምዴ ሜሪ
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ.

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምጵ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላወስ አቃተኝ
ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተካሽ በመዉ ዛሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ

አዝማች

በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
እንደ አውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሀይ ሳይነጋብኝ ሌት

ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ

ማታ ማታ
ማታ ማታ

ሞልቶ በአራዳ የአርመን ዳቦ
ሳሳ አካላቴ ሰዉ ተርቦ
አቅፎ ገላዉን አልጠገብ ያለዉ
ማነዉ ብላችሁ ማነዉ ማነዉ?

ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሳን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ

ዘበናይ ዘበናይ….

አይወጣም ደረጃ ቢፈጥን ሴሼንቶ
እንደኔ ካሌደ በፍቅር ተገፍቶ

ታም-ታራራም-ታራራም…..

መድፈሪያሽ ወርቅ ነዉ ብርም አይገዛሽ
ልብ የሌለዉ ሀብል ግድም አይሰጥሽ

ታም-ታራራም-ታራራም…..

ከአንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማርትሬዛ
ወደወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉስ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰዓት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምርሽ ታዪበት

ዘበናይ ዘበናይ….

ግጥምና ዜማ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድ እና ቤዝ ጊታር፡ ዳግማዊ ዓሊ
ናሙና ዝግጅት፡ አብርሃም ዘዉዴ
ክራር፡ ታመነ መኮንን
ድምጵ ቀረጳ፡ ክብረት ዘ/ኪዮስ
ፕሮዲዩስድ፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
አዲሱ የቴዲ አፍሮ “በ70 ደረጃ” ነጠላ ዜማ ሙሉ የዘፈን ግጥም

↧

የቴዲ አፍሮ በሰባ ደረጃ ነጠላ ዜማና የበእውቀቱ ስዩም ዕይታ

$
0
0

ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ ›› በሰባ ደረጃ የተባለ(ች) ነጠላ ዘፈን ለቆልናል፡፡

‹‹በሰባ ደረጃ››ን እኔ ስሰማው እልም ያለ የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ፍቅርን ልዩ በሆነ ቦታና ልዩ በሆነ ሥፍራ የሚያሳይ ዘፈን፡፡ በአማርኛ ዘፈን ባህል ውስጥ ቦታን ማስጎብኘት የተለመደ ነው፡፡ ‹‹የሐረር ልጅ ነች ወጣቷ/ጀጎል ነው ቤቷ››አይነት ዘፈን ሞልቶናል፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዘፋኝ፣ ያስጎብኝነት ሚናም ደርቦ ሲጫወት ኖሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተፈቃሪዋ ሴት ሁሌም ከታሪካዊ ቦታ አጠገብ ለመወለድ ትገደዳለች፡፡
ቴዲ በዚህ ዜማው ባልተሄደበት መንገድ ሄዷል፡፡ ሲጀምር፣እዚህ ግባ የማይባል ፣ለዓይን የማይሞላ ቦታ መረጠ፡፡ብዙ ጊዜ፣ታሪካዊ ቦታ ሲባል፣አክሱም ላሊበላ፣ፋሲል ሶፍኡመር ጀጎል እንላለን፡፡ ካሜራው በኒህ ቅርሶች ላይ አፍጥጦ ኖሯል፡፡ ታሪክ አክሱም ላይ ጀምሮ ጀጎል ላይ የተጠናቀቀ ይመስል፡፡

ብዙዎቻችን በሸገር ላይ አድልኦ ስንፈጽም ኖረናል፡፡ አዲስ አበባ ለአቅመ ቅርስ የምትበቃ ከተማ አትመስለንም፡፡ሸገር ታሪክ ሲሠራባትና ሲሠራላት እንደኖረች አናውቅም፡፡ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፡፡ ቴዲ ይህንን እይታ ቀየረው፡፡

ሁለተኛ፣

ከላይ የጠቀስኳቸው ቅርሶች የጌቶች መታሰቢያ ናቸው፡፡ የምድራዊና ሰማያዊ መሪዎችን የሚወክሉ ናቸው፡፡የስም የለሹን፣የተርታውን ሰው ኑሮ የሚያሳዩ ቅርሶች ግን ደምቀው አልወጡም፡፡አይተን እንዳላየን፣ቸል ብለናቸው ቆይተናል፡፡ቴዲ ግን ማንም ሲወጣበትና ሲወርደበት ለኖረው አንድ መንገድ ዘፈነለት፡፡መዝፈን ቢሉህ ዝም ብሎ መዝፈን ብቻ አይደለም፤ አንድ ውብ የሆነ የፍቅር ታሪክ ተረከበት፡፡ነጠላ ዜማው ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሰባ ደረጃን በድሮ ዓይናችን አናየውም፡፡አሪፍ ጥበብ ዓይን ገላጭ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

የቴዲ አፍሮ በሰባ ደረጃ ነጠላ ዜማና የበእውቀቱ ስዩም ዕይታሦስተኛው ነጥብ፣

ዘፋኞች ልዩ ቦታን ሲያሳዩ ኖረዋል፡፡ቴዲ ደግሞ አንድን ልዩ ዘመን ለማሳየት ሞክሯል፡፡የቴዲን ዘፈን ስሰማ፣ በካሳሁን ግርማሞ ዘመን የኖረ አንድ ሮሚዎ ይታየኛል፡፡ሸዋ ዳቦ ሳይቋቋም፣ከአርመን ሱቅ ፉርኖ በሚሸመትበት ዘመን፣ምኒባስ ሳይገባ ፣ሰዎች ሴቼንቶ የሚሳፈሩበት ዘመን፣ከጄኔራሎች በላይ ሴቼንቶ ነጂዎች ስመጥር የነበሩበት ዘመን፣ሴቶች የጥላቸውን ቁመት አይተው ሰአት ከመገመት ወጥተው፣ክንዳቸው ላይ ሰአት ማሰር የጀመሩበት ዘመን – በዚያ ዘመን የኖረ አፍቃሪ ይታየኛል፡፡አንድን ልዩ ዘመን በሲኒማና በልቦለድ ማሳየት የተለመድ ነው፡፡ በጣም አጭር ቆይታ ባለው ዘፈን ውስጥ ዘመንን ለማሳየት በመሞከር ግን ቴዲ ፋና -ወጊ ይመስለኛል፡፡

ዜመኛ ስላልሆንሁ ስለቴዲ ዜማ ምንም ማለት አልችልም፡፡ያም ሆኖ ፣ግጥሙ የተዋጣለት እንደሆነ መመስከር እችላለሁ፡፡አንድ ቦታ ላይ‹‹አንደ አርሚዴ ሜሪ››የሚል ሐረግ ሰምቻለሁ፡፡ ዜመኛው፣ሜሪ አርምዴን ፣አርምዴ መሪ ብሎ መጥራት የገጣሚነት ነጻነቱ ይፈቅድለታል፡፡ገጣሚ እንደ ህጻን ልጅ፣እንደ እብድና እንደ ቅዱሳን ከቋንቋ ሕግ በላይ ነው፡፡እንደ ጋዜጠኛ፣በሰዋስው ህግ አይታሠርም፡፡እንዲያውም ሳይራቀቁ መግጠም ፣ፈሳሽ ውስጥ ሳይገቡ መስጠም አይታሰብም፡፡

በነገራችን ላይ በድሮ ዘመን በኢትዮጵያ የአባት ስም ከልጅ ስም ቀድሞ ይጻፍ ነበር፡፡ቴዲን ትውፊትም ያግዘዋል ለማለት ፈልጌ ነው፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ፣በሚቀጥለው ጽሁፌ እናወጋለን፣

እስከዛ ድረስ ያንን ክራር ወዲህ በል! ታንታራራም ታራራም ታራራም!

↧
↧

የሚካኤል በላይነህ እና የብዟየሁ ደምሴ ድንቅ የሚኒሶታ ሙዚቃ ኮንሰርት (ቪድዮዎች)

$
0
0

ኦገስት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ሚካኤል በላይነህ እና ብዟየሁ ደምሴ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት አቅርበዋል። በርካታ ሕዝብ በታደመበት በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ሁለቱም ድምጻውያን ድንቅ የተባለ ሥራዎቻቸውን ከማቅረባቸውም በላይ ድምጻቸው ልክ ሲዲን እንደማድመጥ መሆኑ ታዳሚውን አስገርሟል። ከሙዚቃው ኮንሰርት በሌላ ቦታ የምትገኙ እንድትካፈሉ ዘ-ሐበሻ 4 ዘፈኖችን እንዲህ ታካፍላችኋለች። መልካም መዝናኛ።





የሚካኤል በላይነህ እና የብዟየሁ ደምሴ የሚኒሶታ ሙዚቃ ኮንሰርት (ቪድዮዎች)

↧

አበባዮሽ… (ግጥም)

$
0
0

abebayehoshአበባዮሽ የለም (2X)
መብራቱ አለ? የለም…በየሰፈሩ የለም፥
ውሀውስ አለ? የለም…በየሰፈሩ የለም፥
ኔትዎርኩስ አለ?…በየሰፈሩ፥
መንገዱስ አለ? …በየሰፈሩ፥
ታክሲውስ አለ?… በየሰፈሩ፥
ዋይ ዋይ
ድንቄም ሙዳይ፥ ከብለል በይ (2X)
የራበው አለ? የለም …በየመንደሩ የለም
የከፋው አለ? የለም …በየመንደሩ የለም፥
ለሙት ዓመቱ፥… ችግኝ ትከሉ፣
ዲሽ የሌላቸው…ሰዎች ተጉላሉ፤
ጧት ማታ አዩ፥… ችግኝ ሲተክሉ፥
አበባ ይበቅላል…በየገጠሩ
ውጭም ተልኳል…ተሳክቶ ምርቱ
ዋናው ዶላር ነው….ስንዴ የት አባቱ።
ዋይ ዋይ
የእህል ሙዳይ ከብለል በይ (2X)
አ ብለን መጣን አ ብለን (እያዛጋን)
ሚበላ አለ ብለን።
ኡ ብለን መጣን ኡ ብለን (እየጮህን)
ቀባሪ አለ ብለን።
የእድርተኞች ቤት የለም ካቡ ለካቡ የለም
እንኳን ውሻቸው…. ሞቶአል እባቡ።
ዋይ ዋይ
የእንባ ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)
በሉ ልጆቼ የለም ብሉ በተራ፤ የለም
ቤት ያፈራውን….ደረቅ እንጀራ፤
ተደራጅቼ፣… ወጥ እስክሰራ።
እንኳን ወጥና፣…. የለኝም ኩሽና፣
ስዞር አድራለሁ፣… ቁራሽ ስጠና።
ዋይ ዋይ
የእንጀራ ሙዳይ ከብለል በይ። (2X)
የደመወዝ ለታ የለም የአስቤዛው የለም
ቫቱን አስልቼ፣…. ደላድዬው፣
የ20/80ው፣…. ጎኔን አለው።
ከጎኔ ጎኔ፣…. ኪሴን ኪሴን፤
ወዳጄን ጥሯት፣…. ውሽማዬን፣
እርሷም ከሌለች፣….ኮማሪቷን፣
እንፈፅማለን፣… ራዕይውን፣
እናሳካለን፣… ሌጋሲውን፣
ከዚያም አበሉን… ተሰብስበን።
ዋይ ዋይ
የእጦት ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)
መጣልኝ ብለሽ፣….ብትሞነጭሪ፣
ብትራቀቂ፣….ነሽ አሸባሪ።
ከእጮኛ ጋር …ቡና ብትጠጪ፣
በዚያው እደሪ፣ ቤት እንዳትመጪ
ዋይ ዋይ
የክስ መዝገብ ገለጥ በይ። (2X)
ቅዳሜ መጥቶ …ልዘይረው፣
ጋዜጣ ብሻ፣… የት ላግኘው?
ፉክክር ገባ፥… ሰልፍ ብጠራ፥
ፈቃዴን ነጥቆ፥… እርሱ አሰማራ፥
በሰልፉ ዋዜማ፥… ተንኳኩቶ በሩ፥
ሄጄ ማነው ስል፥… ሰልፍ እንዳትቀሩ፥
ዋይ ዋይ
የጉድ ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)
ከብረው ይቆዩ ከብረው
በዓመት አንድ ልጅ ሰድደው፣
በቀን ሶስት ጊዜ በልተው፣
ልጅ ትምህርት ቤት ልከው፣
ከሙሰኛ ጅብ ተርፈው፣
ከበሮት ውሃ ቀድተው፣
መብራት ሳይሰጉ አብርተው፣
ለታክሲ ግፊያ ትተው፣
ቀንቶት 40/60ው፣
ጋዜጣ ሸጠው፣ ገዝተው፣
መሳቀቁንም ትተው፣
ሃሳቦትንም ገልፀው፣
የታሰሩቦት ተፈተው፣
የወደዱትን መርጠው፣
ቻናል ቀያይረው አይተው፣
በሃቅ ነግደው አትርፈው፣
ግብሩን በልኩ ከፍለው፣
ከብረው ይቆዩ ከብረው።
ከብረው ይቆዩ በደግ (2X)
የወለዱት ልጅ ይደግ።
ከብረው ይቆዩ በፏፏ (2X)
የወለዱት ልጅ ይፏፏ።
ይሸታል ጠጅ ጠጅ (2X)
የኢትቪዮጵያ ደጅ።
የሸታል ሽሮ ሽሮ (2X)
የማምዬ ጓሮ።
/ዮሐንስ ሞላ/

↧

አዲስ ሙዚቃ ከ65%: ጦርነት ኪሳራ፤ አብዮት ቁማር ነው! (Video)

$
0
0


ጦርነት ኪሳራ አብዮት ቁማር ነው
ለኛ ሚበጀው የእርቅ መንገድ ነው።
አዲስ ሙዚቃ ከ65%: ጦርነት ኪሳራ ፡ አብዮት ቁማር ነው! (Video)

↧

ብርሃኑ ተዘራና አብዱ ኪያር ካልጋሪን በፍቅር አደመቋት

$
0
0

ከሔርሜላ አበበ

በምዕራብ ካናዳ ኑሯቸውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በካልጋሪ ከተማ ያደርጉት የእግር ኳስ ፈስቲቫል እሁድ ኦገስት 31 ምሽት ተጠናቀቀ:: በዚሁ ውድድር ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲሆን ኤድመንተን ቫንኮቨር ዊኒፔግና ካልጋሪ ከባድ ፉክክር አሳይተው በቫንኮቨር አሸናፊነት ውድድሩ ተጠናቋል::

abdu kiar
የመዝጊያውም ምሽት ዝንኛ በሆኑት ውድ አርቲስቶቻችን ብርሃኑ ተዘራ እና አብዱ ኪያር ካልጋሪ ውስጥ ታይቶ በማያቅ መልኩ እጅግ ብዙ ህዝብ በተገኘበት ልዩ በሆነ በሃገርና በወገን ፍቅር የሞላ ድግስ ተጠናቋል::

የሃገርና የወገን ፍቅር የሚለውን አባባል የመረጥኩበት ምክንያት እጅግ ብዙ ኤርትራዊያኖች ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር በያንዳንዱ ቡድን ዉስጥ አብረው የተሰለፉ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው:: ካናዳ በተለይ ምዕራብ ካናዳ ኳስ ሜዳ ላይ የታየው ሌላ የፍቅር መንፈስ ነጮች ኢትዮጵያ የሚል ማሊያ ለብሰው በኳስ የወንድማማችነትን ፍቅር ለጉድ ስላሳዩንም ነው::

የምሽቱን መድረክ አብዱ ኪያር ገብቶ ከፈተው ከዛም ብርሃኑ ቀጠለው:: ሁለቱ ምርጥ አርቲስቶች ለዲጄውም ጊዜ ሳይሰጡት ለሶስት ሰአታት ያህል እያፈራረቁ ድንቅ ስራዎቻቸውን በተከታታይ እያቀረቡ ትንሹን ትልቁን ሴቱን ወንዱን ኢትዮጵያዊውን ኤርትራዊውን ፍጹም ፍቅር ወደ ሆነ መንፈስ ወስዱት:: ጥበብ እንደዚህ ለህዝብ ሲቀርብ እና ጥበበኛው በስሜት እያንዳንዷን ደቂቃ ነፍስ ሲዘራባት ማየት እጅግ ያስደስታል:: የአገሪቱ ህግ ሆኖ ከሌሊቱ ስምንት ተኩል ሙዚቃው እንዲቆም ተደርጎ እንጂ እነሱም እኛም ከባድና ጥልቅ የፍቅር ድባብ ውስጥ ነበርን::
ዛሬ ጥበብን በጥቅምና በሆድ ለመቀየር በሚሞከርበት ዘመን ፣ የጥበብ ሰው ጥበቡን ትቶ ካድሬ መሆን በሚፈልግበት በዚህ ዘመን ፣ ስለአገር መዝፈን በጣም በከበደበት ዘመን ፣ ብርሃኑ ተዘራን እና አብዱ ኪያርን ስለፍቅር ስለ አገር እና ስለ አንድነት ሲዘፍኑ ማግኝት በጣም ደስ ይላል በተለይ በስደት ሲሆኑ ደግሞ እጥፍ ድርብ ደስ ይላል::
tezera birhanu
በናቴም አንድ ነኝ ባባቴም አንድ ነኝ
ከኢትዮጵያ ሃገሬ የለም የሚለየኝ
በናቴም ሃበሻ ባባቴም ሃበሻ
አንድ ናት ኢትዮጵያ እስከመጨረሻ
እያለ ብርሃኑ ተዘራ ሲዘፍን አዳራሹ እንዴት በጩኸት ይናጋ እንደነበር መመስከር ግድ ይላል:: ብርሃኑ ተዘራ ፈጣሪ ጥበቡን ከ እድሜ ጋር ይስጥልን እንላለን::
አቤት ብታያቸው አቤት ብታያቸው
እህልና ውሃ ማርና ወተታቸው
አርቴፊሻል ሆኗል እንዳለ ኑሯቸው
ዘመናዊው ባርነት ስላስገደዳቸው
ዜግነት ቀየሩ ካዱኝ አትበያቸው
በወረቀት የሰው በደም ያንቺ ናቸው
እያለ አብዱ ኪያር ሲዘፍን የነበረው ሺህ የሚጠጋ ህዝብ እንዴት አብሮት በፍቅር መንፈስ ይዘል እንደነበር ባይኔ ሳይ ልቤም እየተላወሰ ነበር:: አብዱ ኪያር የምታምነው ጌታ እድሜውን ከጥበብ ጋር አብዝቶ ይስጥልን ብለናል:: እውነትም እኔ እራሴ በወረቀት የሰው(የካናዳ) በደም የኢትዮጵያ እኮ ነኝ::

ከራሳቸው ዘፈን ውጭ ጉራግኛ ትግርኛ ኦሮምኛ ብቻ ምን ቀረ ሁለቱ ምርጥና ድንቅ አርቲስቶች እያንዳንዷን ዘፈን ሲሰሩ ኦሪጅናል ሲዲው የሚጫወት እስኪመስል ድረስ ኩልል እያለ በጥበብ ስራዎቻቸው እጅግ በጣም ያስደስቱ ነበር:: እያንዳንዱ ሰው ፊት ላይ የደስታና የፍቅር መንፈስ ሲነበብም ነበር በተለይ ቫንኮቨሮች ዋንጫውን ስለወሰዱት ደስታቸው ላቅ ያለ ነበር::

የምዕራብ ካናዳ እግር ኳስ መዝጊያ ምሽትን በሚያስደስት ሁኔታ አሳልፈናል ኮሚቴዎችም እጅግ ድንቅ ምርጫ አርጋችኋል አዳራሹ ሙዚቃው ስነስርአቱ እጅግ ደስ ያሰኝ ነበር በርቱልን:: ከብዙ ከተማ የመጣውን ስፖርተኛና የስፖርት ቤተሰብ ካልጋሪ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ እጅግ ባማረ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበትና ፍቅር በሞላበት መልኩ በአስደሳች መስተንግዶ ተንከባክባችሁናል እናመሰግናለን::

↧
↧

Art: የድፍረት ፊልም ድፍረት –አበራሽ በቀለ ስንት ጊዜ ትደፈር?

$
0
0

በድንበሩ ስዩም

ልክ የዛሬ ሣምንት ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ ብሔራዊ ቴአትር ቤት አካባቢ በከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ስር ዋለ። በቁጥጥር ስር የዋለበት ምክንያት “ድፍረት” የተሰኘ ፊልም ስለሚመረቅ በዚህም ምረቃ ላይ ባለሥልጣናት፣ አምባሳደሮችና ታላላቅ ሰዎች ለመታደም ወደ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ስለተጓዙ ነው። እነዚህ ሁሉ ትልልቅ ስብዕናዎች ወትሮም ባልተለመደ ሁኔታ ለድፍረት ፊልም እንዲህ ከያሉበት ነቅለው መምጣታቸው ራሱ አነጋጋሪ ነገር ነበር። ምክንያቱም ፊልም ስለሚወዱ ነው ወይስ በሌላ ምክንያት እያልኩ ሳሰላስል ነበር። ብቻ ቴአትር ቤቱ ከተለመደው ሁኔታ ለየት ባለ መልኩ በእጅጉ ደምቋል። ቀይ ምንጣፍ ተዘርግቷል። ቆነጃጅት ሞዴልስቶች እንግዶችን ሲቀበሉ ቆዩ። አዳራሹ ሞላ። ታዳሚዎች ቦታቸውን ያዙ። ያ በጉጉት የሚጠበቀው ድፍረት ፊልም ሊጀመር ሆነ።
Art1470
ይህን ድፍረት የተሰኘውን ፊልም ፕሮዲዩስ እንዳደረገችው የሚነገርላት በአለማችን ላይ እጅግ ዝነኛ ከሆኑት የፊልም ተዋናይቶች መካከል በግንባር ቀደምነቷ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ ነች። አንጀሊና የድፍረት ፊልም ኤግዝኪቲቭ ፕሮዲውሰር ወይም አንጡረ ገንዘቧን አውጥታ ያሰራች ነች ተብሎ ሲነገር ቆይቷል። ስለዚህ ፊልሙ በባለቤትነት የአንጀሊና ጆሊ ነው ተብሎ ይታሰባል። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ደግሞ ኢትዮጵያዊው ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ነው።

ስለዚህ የአንጀሊና ጆሊ ስም እና ዝና በአለም ላይ የናኘ በመሆኑ ድፍረት የተሰኘ ፊልም ፕሮዲዩስ አደረገች እየተባለ በመነገሩም የፊልሙ ስምም እንደዚያው ገነነ። የተለያዩ ሁለት አለማቀፍ ሽልማቶችንም አገኘ ተባለ። በየድረ-ገፁ ሰፊ ሽፋን ተሰጠው።
የዚህ ፊልም ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ ጉዳይ በመሆኑ አያሌ ኢትዮጵያዊያንም ሊመለከቱት ወደዱ፤ ናፈቁ። ለዚህም ነው ፊልሙ በሀገሩ ኢትዮጵያ ለመታየት ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት። በዚህ ቀን አንጀሊና ጆሊ እና ባለቤቷ ብራድ ፒት ይመጣሉ ተብሎ ወሬ የተናፈሰ ቢሆንም በመጨረሻም ሁለቱም ከያኒዎች አልመጡም። ለዚህ ደግሞ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር በሰጠው መልስ ኢቦላን ፈርተው ነው ያልመጡት ብሏል።

ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር ቤት ይህን ፊልም ለመመረቅ ከ1200 ታዳሚያን በላይ ቁጭ ብለዋል። የፊልሙ ባለቤት አንጀሊና ጆሊ ከምትኖርበት ከዩናይትድ ስቴትስ በስካይፒ ለብሔራዊ ቴአትር ቤት ታዳሚያን በድምጿ መልዕክት እያስተላለፈች ነው። ይህን ያልተነገረለት የኢትዮጵያ ታሪክ እዩት እያለች ተረከች። መልካሙንም ተመኘችልን። በመጨረሻም ያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ድፍረት ፊልም ተጀመረ። ትንሽ እንደተጓዘ ድንገት ፊልሙ ቆመና ጨልመው የነበሩት የአዳራሹ መብራቶች በሩ። ያልተለመደ ሁኔታ ስለነበር ሁሉም ድንግጥ አለ። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ዘረሰናይ ወደ መድረኩ መጣ። ምን ሊናገር ነው ተብሎ ሲጠበቅ አንድ ያልተለመደ ጉዳይ ተናገረ። “ፖሊሶች መጥተው ፊልሙ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታግዷል ብለዋል። ስለዚህ እዚህ ላይ ማቋረጥ እንገደዳለን። ነገሮች ሲስተካከሉ በሌላ ጊዜ እንገናኛለን” ብሎ ይቅርታ ጠይቆ ታዳሚውን አሰናበተ።

ብዙ የተወራለት፤ በየቦታው በሽልማት መንበሻበሹ የተነገረለት ድፍረት ፊልም የከፍታ ጣሪያ ላይ ከወጣ በኋላ ድንገት ሽምድምድ አለ። ለመሆኑ ፊልሙ ለምን ታገደ? ከድፍረት ፊልም በስተጀርባ ምን ችግር አለ? የሚሉትን ነጥቦች ለማየት እሞክራለሁ።

ድፍረት የተሰኘው ይኸው (የአንጀሊና ጆሊ) ፊልም የታሪኩ መሠረት እና የጀርባ አጥንት ወይም የታሪኩ እስትንፋስ የሆነው የዛሬ 18 ዓመት እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተ አንድ አስገራሚ ታሪክ ነው። ታሪኩ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው። ድፍረት ፊልምም የዚህን እውነተኛ ታሪክ ሁኔታ ነው ወደ ፊቸር ፊልምነት ቀይሮት የሰራው። ታሪኩ እንዲህ ነው።

የዛሬ 18 ዓመት አንዲት አበራሽ በቀለ የምትባል የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት አርሲ ውስጥ ቀርሳ በምትባል ከተማ ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖር ነበር። አንድ ቀን ወደ ትምህርት ቤት ደብተሯን ይዛ ስትሔድ ድንገት በፈረሰኞች ትከበባለች። ከዚያም በፈረሳቸው ላይ አፈናጠዋት ይዘዋት ይነጉዳሉ። ሰዋራ ቦታ ወደሚገኝ ቤት ያስገቧትና ከፈረሰኞች መካከል አንደኛው የ14 ዓመቷን አበራሽን ይደፍራታል፤ ክብረ-ንፅህናዋን ይወስዳል። አበራሽም በማታውቀው ሰው እንደተጠለፈች ትገነዘባለች። ይህ ሰው በተደጋጋሚ የወሲብ ጥቃት ይፈፅምባታል። አበራሽ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ በዚያች ቤት ትቆያለች። በመጨረሻም ከዕለታት በአንዱ ቀን ታግታ ከምትደፈርበት ቤት ታመልጣለች። ስታመልጥ ደግሞ በቤት ውስጥ ያገኘችውን ጠመንጃ ይዛ ነበር። ታዲያ ባመለጠችበት ሰዓት ጠላፊዎቿ ነቁ። እንደገና ሊይዟት ወደ አበራሽ በቀለ ዘንድ መሮጥ ጀመሩ። እሷም እንዳይዟት ለማምለጥ እግሬ አውጭኝ እያለች ትበራለች። እነሱም እንደሚታደን አውሬ ያዛት እያሉ ይከተላሉ። በመጨረሻም ድጋሚ ሊይዟት፤ ሊጠልፏት ተቃረቡ። አበራሽ በቀለ ስንት ጊዜ ትጠለፍ? ስንት ጊዜ ትደፈር? ስንት ጊዜ ካለ ፍላጎቷ፣ ካለ ፈቃዷ ትጠቃ? አበራሽ ከዚህ ጉድ የሚያላቅቃት አንድ አማራጭ በእጇ አለ። ጠመንጃ! ቆም አለች። በእጇ ላይ ያለውን ጠመንጃ ሊይዛት ወደተቃረበው ሰው ላይ ተኮሰች። ሊይዛት የነበረው ሰው ወደቀ። ሕይወቱም አለፈች። ያ ሰው የጠለፋት፣ ያለፍላጎቷ የደፈራት፣ ክብረ-ንፅህናዋን የገሰሰው ሰው ነበር። አበራሽ በቀለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።

ከዚያም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ይህን ጉዳይ ሰማ። ማህበሩ ለአበራሽ በቀለ ጥብቅና ቆመ። ከብዙ ጊዜ ክርክር በኋላ አበራሽ ነፃ ወጣች። ነፃ የወጣችበት ምክንያት ራሷን ለመከላከል በወሰደችው እርምጃ ነበር።

ይህ ከላይ የሰፈረው ታሪክ እውነተኛው የአበራሽ በቀለ ታሪክ ነው። ወደ ዝርዝሩ ስንገባ አበራሽ በቀለ ብዙ መከራ የደረሰባት የ14 ዓመት ጉብል ነበረች። ከምትኖርበት ቀርሳ እስከ ዛሬ ድረስ በስደት ነው ተሸሽጋ ያለችው። አበራሽ አሳዛኟ የዚህ ማህበረሰብ አካል ነች። የመደፈርን እጣ ፈንታ ተሸክሜ አልኖርም ብላ ለህሊናዋ ነፃነትና አርነት የቆመች የሴቶች ተምሳሌት ነች።

የዚህችን ልጅ ሙሉ ታሪክ የዛሬ 15 ዓመት አለማቀፉ ቴሌቭዥን ጣቢያ BBC የ50 ደቂቃ ግሩም የሆነ ዶክመንተሪ ፊልም ሰርቶ ለአለም አሰራጨው። አበራሽ ከ15 ዓመታት በፊት ከገጠሯ ቀርሳ ተነስታ የአለም ህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሆነች የጥቃትና የነፃነት አርአያ ሆነች። የBBCቴሌቭዥንም በሰራው School Girl Killer በተሰኘው ዶክመንተሪ ፊልም ምክንያት ለአበራሽ በቀለ ድጋፍና እርዳታ ያደርግላት እንደነበር ባለታሪኳ ራሷ ሰሞኑን በሬዲዮ ፋና አዲስ ጣዕም ተብሎ በሚጠራው የሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ከ18 ዓመታት በኋላ መግለጫ ሰጥታለች።
አሁን ደግሞ ወደ መነሻችን እና ዋና ርዕሰ ጉዳያችን ወደሆነው ድፍረት ፊልም እንምጣ። ድፍረት የተሰኘው ፊልም ታሪኩ የተፃፈውና ዳይሬክት የተደረገው በዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ነው። “በዚህ ፊልም ውስጥ ያለው ታሪክ ሙሉ በሙሉ የኔ ነው። የኔን ታሪክ ሳያስፈቅደኝ ፊልም ሰርቶበት ማሳየት አይችልም። እኔ በታሪኩ ምክንያት ላለፉት 18 ዓመታት ተሸሽጌ ነው የምኖረው። በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነኝ። እንደገና ካለኔ እውቅና ታሪኬ ፊልም ሆኖ ሲወጣ የተረሳው ነገር ደግሞ መነጋገሪያ ሆነ። እኔን በበቀል የሚፈልጉኝ የሟች ቤተሰቦች አሉ። ይሔ ፊልም ደግሞ ደህንነቴም እንደገና አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርገኛል” የሚል ሃሳብ ያለው ንግግር በአዲስ ጣዕም የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ስትናገር ተደምጣለች።

በዚህ ምክንያትም ፍርድ ቤት ከሰሰች። ፍርድ ቤቱም ፊልሙ ለህዝብ እንዳይታይ፣ እንዳይመረቅ የእግድ ትዕዛዝ ሰጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ከብሔራዊ ቴአትር ቤት የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ ድፍረት ፊልም እንዲቆም የተነገረው። እናም ድፍረት ቆመ። ታገደ።
የድፍረት ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ለአዲስ ጣዕም አዘጋጅ በሰጠው መግለጫ ይህ ታሪክ የአበራሽ ብቻ አይደለም። የብዙ የኢትዮጵያ ሴቶች ታሪክ ነው። በወቅቱ በልዩ ልዩ ሚዲያዎች ስለቀረበ የሕዝብ ታሪክ ነው። ይህን ታሪክ ወስጄ እንደፈለኩ ልፅፍበት ላስተምርበት መብት አለኝ የሚል ሃሳብ ሰንዝሯል።

ባለታሪኳ አበራሽ በቀለ ደግሞ ይህን አባባል ትሞግታለች። ይህ ታሪክ የሕዝብ ታሪክ አይደለም። የኔ ታሪክ ነው። በ14 ዓመቷ የተጠለፈች። በ14 ዓመቷ የተደፈረች፤ በ14 ዓመቷ ጠመንጃ ይዛ ከጠላፊዋ ቤት ያመለጠች፤ በ14 ዓመቷ ጠላፊዋ ደግሞ ሊደፍራት፣ ሊጠልፋት ሲል እምቢኝ ብላ ጠመንጃ ተኩሳ የደፈራትን የገደለች ሌላ ባለታሪክ ካለች ትምጣ። የዚህ ታሪክ ባለቤት እኔ ነኝ፤ ብላለች አበራሽ በቀለ።
ጉዳዩ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከፍቷል። ዘረሰናይ እንደሚለው ከሆነ የአበራሽን ታሪክ ማንም ሰው እንደልቡ በነፃነት ካለ እሷ ፈቃድ ፅፎ ሊጠቀምበት፣ ፊልም ሰርቶ ሊያገኝበት፣ ሊሸለም ሊሞገስበት ይችላል ወይ? የአበራሽ ታሪክ ራሱ ያልተፃፈ ድንቅ ስክሪብት ነው። እሷ ሳትፈቅድ ይህን የሕይወት ስክሪብቷን መውሰድ ይቻላል ወይ?

በድፍረት ፊልም ዙሪያ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮች አሉ። ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ከአበራሽ ሌላም ክስ መጥቶበታል። ከሳሹ ደግሞ አቶ ፍቅሬ አሸናፊ የተባሉ ሰው ናቸው። ሰውየው የሕግ ባለሙያዋ የወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ወንድም ናቸው። እርሳቸው ደግሞ የስክሪብቱ መነሻ ሃሳብ የኔ ነው የሚል ክስ ይዘው ፊልሙ እንዲታገድ ከአበራሽ በቀለ ጋር ሆነው ዘረሰናይን ከሰዋል።

ድፍረት ሌላም አነጋጋሪ ነገሮች አሉት። በፊልሙ ውስጥ በዋናነት ታሪኩ የተሰራው ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ አበራሽ በቀለን (የፊልም ስሟ ሂሩት) እሷን ከእስር ለማስፈታት የሚጥሩትን፣ የሚዳክሩትን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ነው። በድፍረት ፊልም ውስጥ ወ/ሮ መአዛ፣ የአበራሽ በቀለ (የሂሩት) ጠበቃ ሆነው ነው የሚታዩት። ፊልሙ መአዛ አሸናፊን በአበራሽ ሕይወት ውስጥ አግንኖ ሲያወጣ የሚያሳይ ነው። እውነታው ግን ይሄ አይደለም። የዛሬ 18 ዓመት የአበራሽ ጠበቃ ሌላ ሴት ናቸው። ዛሬ በህይወት የሉም። ወ/ሮ መአዛ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር እንጂ የአበራሽ ጠበቃ እንዳልሆኑ ይነገራል። ድፍረት ፊልም ላይ ግን ጠበቃ ሆነው ቀርበዋል።

ድፍረት ፊልም ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደወጣበት ዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ይገልጻል። የፊልሙ ፕሮዲዩሰር አንጀሊና ጆሊ ነች እየተባለ ሲነገር ቆይቷል። አሁን አሁን ደግሞ ዘረሰናይ ሲናገር አንጀሊና ለፊልሙ ምንም ሳንቲም አላወጣችም። ፊልሙን ስለወደደችው ስሟን እንድንጠቀምበት ጠየቅናት፤ ፈቀደችልን። ስለዚህ በስሟ ለመጠቀም እንደ ኤግዝከቲቭ ፕሮዲዩሰር አድርገን ተጠቀምንበት ሲል ከፊልሙ ምርቃት አንድ ቀን በፊት ዘረሰናይ እንደተናገረ የአዲስ ጣዕም የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ገልጸዋል። እውነት አንጀሊና ጆሊ ብሯን ሳታወጣ፣ በባዶ ሜዳ ነው ሕዝብ የምታሳስተው? ብለን እንድንጠይቅም ያደርጋል። ይህን ዘረሰናይ የሚናገረውን ነገር እንዴት መቀበል ይቻላል? በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት ያለባት ራሷ አንጀሊና ጆሊ ነች። ፊልሙን እሷ ፕሮዲዩስ እንዳደረገችው በየአደባባዩ ሲነገር ቆይቶ አሁን ደግሞ ሸራፋ ሳንቲም አላወጣችበትም እየተባለ ነው። ይህ የአመቱ ሌላው አስገራሚ ታሪክ ነው። እውነት ከሆነ ደግሞ አንጀሊና ጆሊ አጭበርባሪ እና ዋሾ ሴት መሆኗ ነው።

ይህ የሰሞኑ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነው ድፍረት ፊልም ገና ተመዘው ያላላቁለት ጉዳዮች አሉ። አበራሽ በቀለ እና ፍቅሩ አሸናፊ የክሳቸው መጨረሻ ምን ይሆን? ድፍረት ፊልም ስንት ብር ወጣበት? ስንት ብርስ አገኘ? አንጀሊና ጆሊ እና ድፍረት ፊልም እውነተኛ ግንኙነታቸውን ማነው የሚያስረዳን? አበራሽን ሳያስፈቅዳት ታሪኳን የደፈረው ማን ነው? እነ አበራሽ በቀለ መክሰስ ያለባቸው አንጀሊና ጆሊን ነው ወይስ ዘረሰናይን? የፊልሙ ባለቤት ማን ነው? በነዚህና በሌሎች አስገራሚ ጉዳዮች ላይ ሳምንት እመለስበታለሁ።

↧

የማለዳ ወግ …በዓሉ በጆሲ ደምቆ ተሸኘ ! * ዝክረ አለባቸው ተካ እና የጆሲ ድንቅ ስራ …

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

* ዝክረ አለባቸው ተካ እና የጆሲ ድንቅ ስራ …
* የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን …
ጆሲ በ2007 ዓም አዲስ አመት ልዩ ዝግጅቱ ታዋቂው ድንቅ ኮሜዲያን አለባቸው ተካን በተገቢ መንገስ አዘከረው ። አርቲስት አለባቸው ተካ ድንቅ ኮሜዲና የመጀመሪያ ቶክ ሾው አቅራቢ ነበር ። አለቤ በተለይም በኢቲቪ የቶክ ሺው ዝግጅቱ በርካታ አርአያነት ያለው ስራዎችን የሰራ ታላቅ ወንድም ነበር ። አርቲስት አለባቸው ተካ ሰርግ ሰርጎ ከአቅመ ደካማ ድሃ ወገኑን በማብላት በማጠጣት ደስታ አለኝታነቱን አሳይቶ ፣ አርአያነት ያለው ስራ ሰርቶ ያሳየን ብቻኛ አርቲስትም ነበር። ለራሱ ሳይኖር ለሌሎች ኢትዮጵያን ለሚወዱ በተለይም ለድሆችና ለከፋቸው የቆመ ወንድም ነበር ። በድንገተኛ አደጋ አለፈ ፣ አዘንን ! እሱ ካለፈ በኋላ ግን እሱን የሚያስታውስም ሆነ የእሱን ቤተሰቦች የሚደግፋቸው አልነበረም ።

ጆሲ ግን አለቤን አልረሳውም ። በወዳጆቹ አማካኝነት ቀን ዘንበል ያለባትን የአለባቸው ተካ ቤተሰቦች አገኘ። በመጀመሪያ ያገኛት ታናሽ አህቱን አህት የሻሸወርቅን ነበር ። ጆሲ ፕሮግራሙን ሲጀምር በተረካው እንደሰማነውና እንዳየነው የአለቤ እህት የሽዋወርቅ በአነ ድምጻዊ ግርማ ተፈራ ድጋፍ በአንድ መዝናኛ ቡና ማፍላት ስራ ወደ ጀመረችበት ቦታ ሄዶ ተዋወቃት !
alebachew teka

alebachew teka 2
ይህ እየተከታተልኩ ፣ አሁን የአዕምሮ በሽተኛ የሆነው ሌላው ከልታማ ታዋቂ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ታወሰኝ ! ልመንህ አሜሪካ በስደት ሲኖር አዕምሮው ተነክቶ ፣ ሀገር ቤት ከገባ አመታት መቆጠራቸውን ሰምቻለሁና የዚያ ዘመኑ ፈርጥ ጥርስ የማስከድነው ፣ ዛሬ ከንፈር የሚመጠጥለት ኮሜዲያን ልመንህ ታወሰኝ ! ልመንህ አሁንም አዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች እየተንከራተተ ይሆን? … ሰብሳቢ ደራሽ አጥቶ እንደነበር ባውቅም ዛሬ ሰብሳቤ ደጋፊ አግኝቶ እንደሁ አላውቅም … በልመንህ ህይወት የጀመርኩት በተመሳሳይ ሁኔታ የሚነወከራተቱ ደራሽ ደጋፊ ያጡ ቀን የዘነበለባቸው ጋዜጠኛ ሰሎሞንን ጋዜጠኛ ዳሪዮስ ሞዲን ፣የጥበብና የስፖርት ሰዎች አሰብኳቸው ! ሁሉም ለዚህች ሃገርና ህዝብ የድርሻቸውን ሲወጡ አጨብጭበንላቸው ፣ ሲደካክሙና ቀን ሲዘነብልባቸው የረሳናቸው ግፉአን ናቸው!

… እንዲህ የተረሱ ወገኖችን ከያሉበት እያስታወሱ ድጋፍ ትብብር እንድናደርግ ትልቁን ስራ አየሰራች ያለችው የኢቢኤስ “አርአያ ሰብ ” ዝግጅት መሪ ጋዜጠኛ ህሊና አዘዘ ብዙ የተረሱና በአዲሱ ትውልድ የማይታወቁ የሃገር ባለውለታዎች የማስተዋቀቋን ድንቅ ስራ አስታወስኩ ። ጋዜጠኛ ህሊና እንዲህ ህይወትና የቀደሙ የተደበቁ ማንነቶችን እያሳየች ማስተማሯን በቀጠለችበት አጋጣሚ የጆሲ ኤንድ ሃውስ አስደማሚ ዝግጅት ቀጥሏል! በዛሬው ዝክረ አለባቸው ተካ ዝግጅት ቀልቤን ከነጎደበት መለሰው …አናም ቀልቤን ከሄደበት መልሸ ወደ የጆሲ ልዩ የዓውዳመት ልዩ ዝግጅት አቀናሁ … !
ጆሲ ባማረው መኖሪያ ቤቱ ባቀረበው ዝግጅት ከእህት የሻበወርቅ ተካ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ስለአለባቸው የልጅነት ህይወት አስተሳደግ ፣ ለወገኖቹና ለቤተሰቦቹ ሲደግም እስከተቀጠፈበት ድረስ የራሱ መኖሪያ ቤት አለመስራቱን ሃብት አለማካበቱን ፣ በሚወደው መኪና መንዳት አደጋ በመጨረሻው በድንገት ማለፉን መራራ መርዶ ፣ በህልፈቱ መርዶ ይደግፍ ይረዳው የነበረ ወንድሙ በድንጋጤ መሞቱን ድርብ ሃዘን ፣ ከዚያም የቤተሰቡ ደጋፊ አልባ መሆን ፣ የሚረዳቸው የወንድሙ ልጆች ትምህርት ሳይቀር ማቆማቸውን ፣ የአንዱን ወጣት የታክሲ ደላላ መሆን ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰቸው ያንዷ ጉብል በድህነት የተደቆሱ ቤተሰቦችን ለመደገፍ አረብ ሃገር ለመሄድ አስባ መንገዱ በመዘጋቱ ትምህርቷን በችግር ተከባ መቀጠሏን ፣ የአለባቸው የወዳጅ የስራ ባልደረቦች የተባሉትን ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ደጋፍ አለማድረጋቸውን ፣ እንደ ወ/ሮ አሚና ያሉት ጎረቤቶች ለየሽወርቅ ያደረጉት ድጋፍ ሁሉንም ልባችን በሃዘን እየተሰበረው አሳዛኝ ያልሰማነውን ታሪክ ከእህቱ ጋር በአቤቱ ከአለቤ ወንድም ባለቤት ጋር ቁርቁስ ካለው ቤት ደጃፍ የሆነውን ሰማን !

አጠር ላድርገው …ጆሲ ከሃዘን ትካዜው ያወጣነወ ዘንድ እንደዋዛ ወደ ሙዚቃው ዝግጅት ልውሰዳችሁ ብሎ በአስገራሚና ባልተጠበቀ አቀራረብ ለአለቤ እህት አለ የተባለ የኮስሞቲክ ሱቅ ቁልፍ አስረከባት ! ስጦታው ጎረፈ …ያዘነ የተከዘ ልባችን ትፍስህት አገኘች …እኒያን የጨለመባቸው የአለቤን ወንድም እናት ሳናስበው አመጣና እሳቸውንም በሚያስደንቅ ስጦታ አንበሻበሻቸው! በችጋር የተጠበሱ ፣ ያዘኑ ፣ የተከዙ ፣ ተስፋ የጨለመባቸውና የተጨነቁት የአለባቸው ቤተቦች ብቻ ሳይሆን እኛም የጆሲ ታዳሚዎች በጆሲ በጎ ምግባር የምንይዝ የምንጨብጠው አጣን !
jossy gebre
ጆሴ ሌላም እንግዳ ነበረው … ሌሎች ያደገችው ሃገር ግፉአን ! አበባና ሮቤል ድሃ አደግነታቸው ሳያንስ ኤች አይ ቪ ተጠቂዎች ናቸው ፣ የደሃ የጀርባ አጥንቱን ያሳየን የጆሲ የክበር እንግዶች ሆኑ ! ልዩ የድጋፍ ገጸ በረከት ተበረከተላቸው። ዝርዝሩን ለወተወው … ትምህርት ያቆመችው አበባ ትምህርት እንድትቀጥል ስጦታ ተበረከላት ፣ ለሮቤልም እንዲሁ : ) ጆሲ ከሜሪ ጆር ፣ ከዳሸን ፣ ከመድሃኒአለም ሞል እና ከቀሩት በጎ አድራጊዎች ጋር በመተባበር ጆሲ ድጋፉን በማቀናጀት በስጦታና በተቆራጭ ሁሉንም ተገፊወች አንበሸበሿቸው: ) ልዩ የአውደ አመት ስጦታ: )
ጆሲ ስለተደረገው ነገር ሁሉ አመሰገነ ! የድጋፍ ትብብር ሲጠይቅ አሻፈረኝ ስላሉት ሲናገር አንረዳም አንሰጥም ማለታቸውን ባይኮንነውም “ለካስ ለመስጠትም መሰጠት አለበት!” ሲል የተናገረው ታላቅ መልዕክት ንፉጎች ልብ ብለን ልንሰማው የሚገባ ቀዳሚ ቁምነገር ነበር ! ከገባን …
ዝግጅቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃረበ …ክብር እንግዶቹ የአውደ አመቱን ኬክ ቆረሱ ፣ አልቅሰው ታሪካቸውን ነግረው ልባችን ሰብረው ያሳዘኑን የአለቤ ቤተሰቦ በአሉን በደስታ እየጨፈሩ ብሩሁን መጭ ጊዜ ይቀበሉ ቀን ከፈጣሪ በታች ብልሁ ጆሱ የአንበሳውን ድርሻ ያዘ ፣ ዝግጅቱ ተከወነ ! …
እንዲህም አልኩ ..ጆሲ ጧሪ የሌላቸውን በሚደግፈው መቅዶንያን ባቋቋመው ወጣት እና በመሰሎቹ እጹበ ድንቅ ምግባር ስንደመም ለከረምነው ባሳየህን ፋና ወጊ በጎ ምግባር ኮርተናል : ) በጥቁቷ እንኳ ለበጎ ምግባር ሳይሰለፉ “ሃብታችን ህዝብ ነው! ” እያሉ በሚያደነቁሩን በሃገሬ ጥበብ ባለሙያዎች የታመምን ብዙዎች ባንተ በወጣቱ ድምጻዊና የተዋጣልህ ቶክ ሾው አዘጋጅ እውነተኛ የህዝብ ሃብትነትም ኮራን! ይብላኝ ለሆዳሞች … በእጅጉ እንኮራን እወቀው አልሃለሁ !

እንዲህም ሆነ …ዝግጅትህ እየተላለፈ እያለ በርካታ መልዕክቶች ደረሱኝ …በምኖርበት አረብ ሃገር ሳውዲና በቀረው አለም የሚገኙ ወዳጆቸ በሰራህው ድንቅ ሰብአዊ ስራ ተማርከው እርዳታና ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸውልኛል! በጎ ሃሳብ ነው አልኳቸው ! ዳሩ ግን ያንተን አላማ ለመደገፍ እሰክንደራጅና እስኪሳካ ቢያንስ የተሳካልን በአረቡ አለም ያለን ወገኖች በአጠገባችን ከአፍንጫችን ስር የሚንከራተቱ የተቸገሩትን የኮንትራት ሰራተኞች በመደገፉ ሰብዕናችን እናሳይ ማለት ወደድኩ! ብቻ በአመት በአሉ ልዩ ዝግጅት ጆሲ ባንተ ደምቀናል !
በአሉ በአንተ በጆሶ ኤንድ ሾው ልዩ ዝግጅት ደምቆ ተሸኘ !

የልጅ አዋቂው ጆሲ እናመሰግንሃለን !
መልካም በዓል!

↧

ላልተወለድከው ልጄ (በበዕውቀቱ ሥዩም)

$
0
0

ሚስቱ አረገዘችበት ፡ ደነገጠ – እንድታስወርደው ጠየቃት አሻፈረኝ አለች፡፡ በጣም ተቆጣ ! ቁጣው ሲውል ሲያድር ቁዘማ ሆነ ፡፡ ቁዘማው ላልተወለደው ልጁ ደብዳቤ እንዲፅፍ አነሳሳው ፡፡
ሁለት ደብዳቤዎችን እንዲፅፍ አነሳሳው ፡፡ ሁለት ደብዳቤዎችን ፃፈ፡፡ የደብዳቤዎቹ ሙሉ ቃል ይሄ ነው፡፡
አንደኛው ደብዳቤ፡-

lije
ልጄ የወገቤ ክፋይ፡-ከኔ ወገብ ከተለያየንበት እንዲሁም ከእናትህ ማህፀን ከተገናኘህበት ሰዓት ጀምሮ እንደምን አለህልኝ እኔ ትወለዳለህ ከሚለው ሀሳብና ሰቀቀን በስተቀር ደህና ነኝ ልጄ ፡፡
ይሄን ደብዳቤ የፃፍኩልህ የፊደልንና የቋንቋን ጣጣ ከማህፀን እንድትጀምረው ለማስገደድ አይደለም ፡፡
ይልቁንስ ለውሳኔ እንዳትቸኩል ከመምጣትህ በፊት ግራ ቀኙን እንድትመረምር ነው፡፡ አሁን ጨቅላ አይደለህም የ3 ወር ጎረምሳ ነህ ! አውራ ጣትህን መጥባት ጀምረሃል፡፡
ጊዜህን እንደጥንቱ በራስ በመቆም ብቻ እንደማታሳልፈው አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ 6 ወሮች አሉህ ፡፡ በእኚህ ቀሪ ጊዜያት እንድትፋፋባቸው ሳይሆን እንድታስብባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሁሉም ነገር አስብ ፡፡
ከመቸኮልህ በፊት አስብ ፡፡ እኔ 40 ዓመት ሞልቶኛል፡፡ ግን በዕውቀትና በጥበብ ካንተ እንደማልበልጥ አውቃለሁ፡፡ ‹‹ ማወቅ ማለት ከውጭ ያለውን መማር ማለት አይደለም፣ ከመወለዳችን በፊት ያለውን ማስታወስ ነው ›› ብሏል ሰውዬው ፡፡
ይህንን ብሂል ያመንኩ ቀን ስቅስቅ ብዬ ነው አለቀስኩ፣ ለካ አባቴ ቄስ ትምህርት ቤት ያስገባኝ ፤ አንደኛ – ሁለተኛ -ሦስተኛ ደረጃ ትምህርት ያስተማረኝ ፤ ባለ ድግሪ ፤ በለ ማዕረግ ያሰኘኝ አልባሌ ቦታ ከምውል ብሎ ኖሯል ፡፡ ስለዚህ ‹‹ የምወለደው ለማወቅ ስለምፈልግ ነው ›› አትበል! ፡፡ እኔ ካንተ አላውቅም ፤ ካንተ አልበልጥም፤ ምናልባት የምበልጥህ በንዴትና በሽበት ብቻ ይሆናል፡፡
ልጄ ወዳጄ የወገቤ ክፋይ እንዳትወለድ የማሳሳብህ ስለምጠላህ አይደለም ! ‹‹እወድሃለው›› – ‹‹እወልድሃለው›› አላልኩም ‹‹እወድሃለው›› ፡፡ ግን የወደድነውን በባዶ ቤት አንጋብዝም ፤ እናትህ ‹‹ ሁላችንም እዚህ ምድር ስንመጣ ዕርቃናችንን ነው ›› ትላለች ፡፡ ብወዳትም አላመንኳትም ፡፡
ጥቂቶች ለብሰው እንደሚወለዱ አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ከካናዳ የመጣች ጓደኛዬ ስትነግረኝ ካናዶች አንድ ልጅ ሲወልዱ ብዙ ሺህ ብር ከመንግስት ይሰጣቸዋል፡፡ የስካንዲቪያን ሠዎች አርግዘው በታዩ ጊዜ አስተዳደሮቹ ለመጪው ልጅ የሚሆን ቁሳቁስ ፣ ቤት ያሰናዱላቸዋል፡፡
የፈረንጅ ልጆች ስንቅ ሳይዙ ወደዚህች ምድር አይመጡም ! ለፈረንጅ አባቶች ልጅ ክፍት የስራ ቦታ ማለት ነው ፡፡ ሲሳይ ነው ፡፡ ስለዚህ አንድ ካናዳዊት ብታስወርድ እህል የሞላው ጎተራ አቃጠለች ማለት ነው፡፡ እኔ አሁን ውጭ ሀገር ኖሬ አላውቅም ፣ ግን የሰማሁትን ይዤ ብዙ አስባለሁ፡፡
የፈረንጅ ሽማግሎች ጡረታ ሲወጡ በመውለድ የሚጠመዱ ይመስለኛል፡፡ በዕድሜዬ መግፋት ያጣሁትን ደመወዝ በሚስቴ ሆድ መግፋት እመልሰዋለሁ የሚሉ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ የተነሳ እናትህ ‹‹እናትህ ሁላችንም የመጣነው ዕርቃናችንን ነው›› ስትል የባልነቴን ጭንቅላቴን ባወዛውዝላትም አላምናትም፡፡
ከላይ እንዳስነበብኩህ የፈረንጅ ልጆች ለብሰው ይወለዳሉ ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ለወላጆቻቸው ካፖርትና ቀሚስ ይዘው ወደዚህች ዓለም ይመጣሉ ፡፡ የሀበሻ አባት ግን ሚስቱ ስታረግዝ የድሮ ሱሪውን ማሳጠር ይጀምራል፡፡ አለበለዚያ ልጁ ሲወለድ ምን ይለብሳል ? ልጄ ወዳጄ የወገቤ ክፋይ ፡- ይሄ ሁሉ የሆነው በእኔ ጥፋት አይደለም ፤ ጥፋቱ ሁሉ የእናትህ ነው፡፡ እመነኝ ፡፡
የመጀመሪያ ስህተቷ ሴት መሆኗ ነው፡፡ ግዴለም ትሁን ፤ – ለምን ተቆነጃጀች ? – ግዴለም ትቆንጅ ፤ ለምን በደጄ አለፈች ? – ግዴለም ትለፍ፤ ለምን ሠላምታዬን መለሰች ? – ግዴለም ትመልስ፤ ለምን እኔን አመነች ? – ግዴለም ትመን፤ ለምን እሺ ብላ ተሳመች ? – ግዴለም ትሳም፤ ለምን…… ? – ግዴለም አንዴ ሆኗል ! ፡፡ ልወቅሳት አልፈልግም ምክኒያቱም እወዳታለሁ፡፡
እንዲያውም ጥፋተኛው እኔ ሳልሆን አልቀርም ፡፡ የመጀመሪያው ስህተቴ ወንድ መሆኔ ነው ፤ ወንድ ባልሆን ኖሮ ከድንበር አትሻገራትም ነበር ፡፡ ክኒኑን እንደ ቁርስ ምሳዬ ሳላሰልስ እወስደው ነበር ፡፡ የክኒንና የወንድ ዝምድና ግን አይገርምም ? ወንዶች ክኒንን ይሰሩታል – ሴቶች ይውጡታል፡፡ የለም! ስህተቱ የእኔም የእናትህም አይደለም ! ያንተ ነው፡፡ መጀመሪያ ማሰብ ነበረብህ << Think twice before you born once ok! >>
እኔና አናትህ መደሰት መብታችን ነው ለመደሰት ቀን መቁጠር የለብንም ! አንተ መወለድ መብትህ ነው ግን መብትህን ለመጠቀም ጊዜና ቦታ መምረጥ አለብህ ፡፡ አሁን ምን አጣደፈህ? ተው እንጂ ልጄ ጥድፊያ በዘራችን የለም ! ምናልባት ‹‹ዕድገት እየታየ ነው›› የሚል ወሬ ከሰማህ አትመነው ፡፡ ከእናት ሆድ በስተቀር እዚህ ሀገር ያደገ ነገር የለም፡፡
ልጄ በርግጥ ካንተ ጋር እደራደራለሁ፡፡ ካልተወለድክ በጣም ብዙ ነገር ላደርግልህ ቃል እገባለሁ ፡፡ ካልተወለድክ ጥሩ አባት እሆንሃለው፡፡ አስብበት!፡፡ የማነበው መፅሀፍ ላክልኝ ባልከው መሰረት የአቤ ጉበኛን ‹‹ አልወለድም›› ን ልኬልሃለው ፡፡ መልስህን በቶሎ እጠባበቃለሁ፡፡
*****
ሁለተኛ ደብዳቤ :
እምቢ አልክ ! መልዕክትህን አንብቤ ደሜ ፈላ! ግትር ነህ ! ቂል ነህ ! ‹‹ የወፎችን ድምፅ መስማት ስለምፈልግ በቅርቡ እወለዳለሁ›› ብለሃል ፡፡ አትጃጃል፡፡
የሞባይልና መኪና እንጂ የወፍ ድምፅ እዚህ አዲስ አበባ ከየት አምጥተህ ነው የምትሰማው ? ፍላጎትህ ይህ ከሆነ አማዞን መሀል ተፈጠር፡፡ በአጠቃላይ መልዕክትህ ሁሉ ግትርነትህን የሚያሳይ ነው ! ፡፡ እናትህ ልዝብ ጨዋ ናት፡፡ ቤተሰቦቿም ለስላሶች ናቸው፡፡
እኔም ትሁትና ተግባቢ ነኝ ታዲያ ይሄ ግትርነት ከየት መጣ ? በሁለታችንም ደም ውስጥ ግትርነት ከሌለ አንተ ከየት ወረስከው ? መቼም ልጄ ነህ ብዬ ለማመን መልክህን የግድ ማየት የለብኝም፡፡ ጠባይህም ከእኔ የተገኘ መሆኑን ማወቅ አለብኝ ፡፡ ባህሪህ የእኔ አይደለም ፡፡ የእናትህም አይደለም፡፡ ስለዚህ የእኔ ልጅ አይደለህም ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የምነጋገረው ካንተ ጋር አይደለም ፤ ከእናትህ ጋር ነው ፤ ከእርሷ ጋር ሁሉን እንጨርሳለን፡፡
*****
© በዕውቀቱ ሥዩም

↧

ቴዲ አፍሮ ከ9 ዓመት በፊት ሆላንድ መድረክ ላይ የተጫወተው ዘፈን እንደአዲስ መለቀቁን “ሕጋዊነትን ያልተከተለ ስርጭት”አለው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በሶሻል ሚዲያዎች ከፍተኛ አድማጭን ያገኘውን “ቀስተዳመና” የተሰኘውን ነጠላ ዜማ በማሰመልከት ቴዲ አፍሮ በፌስቡክ ከገጹ በሰጠው ቃል “ሕጋዊነትን ያልተከተለ ስርጭት” ሲል አወገዘው።
Teddy Afro Teddy Afro rocks ESFNA Closing Night 2013 (video)
አርቲስቱ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “ቀደም ሲል (ሰባ ደረጃ) በሚል ርዕስ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በኦፊሻል ድረ ገጱ ላይ አዲስ ሙዚቃ መልቀቁ ይታወቃል። ነገር ግን የዚህን ስራ መዉጣት ተከትሎ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ከአርቲስቱ እዉቅና ዉጪ በሶሻል ሚዲያዉ ላይ የተሰራጨ ሕጋዊነት የሌለውና ከዘጠኝ አመት በፊት አርቲስቱ በሆላንድ አገር መድረክ ላይ የተጫወተዉን ጥራቱን ወይም ደረጃዉን ያልጠበቀ ሙዚቃ ባልታወቁ ወገኖች እንዲሰራጭ ተደርጓል። ይህ እንዲሆን ያደረጉት ወገኞች ምክንያትም ሆነ ምንጭ ለጊዜዉ ባይታወቅም፡ ጉዳዩ ከአርቲስቱ የኮፒራይት መብት አንጻር ሲታይ ሕጋዊነትን ያልተከተለ በመሆኑ እዉቅና የሌለዉ ስርጭት መሆኑን ለአርቲስቱ አድናቂዎችና ወዳጆች በሙሉ ለመግለጽ እንወዳለን።”

↧
↧

ነዋይ ደበበ በስዊድን ተቃውሞ እንደሚጠብቀው ተገለጸ

$
0
0

በስቶኮልም ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አና ተውልደ ኢትዮጵያውያን በጋራ “ልማታዊ አርቲሰት” ንዋይ ደበበ ኮንስርት ሊያቀርብ አይደለም ሊያስበው እንደማይገባ አሰታወቁ።
neway debebe
የኢትዮጵያውያን ስቃይ ላይ ጭቆና ላይ ከወያኔው ጋር በመሆን ጮቤ ዳንኪራ የሚረግጠው ንዋይ ደበበ ወደ ስቶክሆልም ሴፕቴምበር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለመዝፈን ስለሚመጣ ውርደቱን ማከናነብ ደግሞ ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይጠበቃል ያሉት በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከዓባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ! ከዓባይ በፊት በግፍ የታሰሩት ይፈቱ! ከዓባይ በፊት ሰብዓዊነት ይቅደም! የህዝብ መብት ይከበር! … ድምፃችን ይሰማ! መሪዎቻችን ይፈቱ! ንጹኀንን መግደልና ማሰር ይቁም! መንግሥት ከኃይማኖት ላይ እጁን ያንሳ እንድሁም የዞን ዘጠኝ እና የእስረኛ ጋዜጠኞች ስቃይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰቆቃ የጋዜጠኞች ስደት የፖለቲክ መሪዎች እና አጠቃላይ የዜጎች ግድያ ቁስሉ የኛ የዲያስፕራውያንም ስለሆነ ቦይኮቱን በመቅላቀል ንዋይ ደበበን በመጣበት አሳፍረን መመለስ አለብን።” ብለዋል።

“አዲስ ዓመት የአምባገነንነት ዘመን ውጣ የነፃነት ዘመን ግባ ብለን ካለው የተሻለ ነገር የምንፈጥርበት እንዲሆንልን በመመኘት ካለፉት ብዙ አዲስ አመቶች የሚለይበትን እና በሕይወታችን ትርጉም ያለው ለውጥ የምናመጣበት እንዲሆን የህሊና ጥንካሬያችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል::” ያሉት ኢትዮጵያውያኑ የነዋይን ዝግጅት ቦይኮት ለማድረግ የተለያዩ ወረቀቶችን እየበተኑ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በዲያስፖራ ከገዳዩና አሳሪው መንግስት ጎን ቆመው የሚወጉትን አርቲስቶች ቦይኮት ማድረግ ከጀመረ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳ ሃመልማል አባተ እንዲሁም በቅርቡ ሸዋፈራው ደሳለኝ ዝግጅቶቻቸው ቦይኮት ተደረገው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው አይዘነጋም።

↧

የአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ 10 ሚሊዮን ብር ታገደ

$
0
0

(አዲስ አድማስ) ሙያው ቴዎድሮስ ተሾመና በደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ መካከል በተመሰረተው የመብት ይገባኛል ፍትሃብሄር ክርክር፣ ፍ/ቤት በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ላይ የ10 ሚሊዮን ብር እግድ ከትናንት በስቲያ አስተላለፈ፡፡ ከሳሽ ደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ፤ ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም ለፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፤ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለእይታ ያበቃው “ሦስት ማዕዘን” የተሰኘ ፊልም ጻሪክ በ2000 ዓ.ም ካሳተሙት “ፍቅር ሲበቀል” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሃፍ የተወሰደ ነው የሚል አቤቱታ አሰምተዋል፡፡
tewedros teshome
“ሦስት ማዕዘን” የተሰኘው ፊልም መፅሃፋቸው ታትሞ ከወጣ ከ5 ዓመት በኋላ ለዕይታ እንደበቃ በክሳቸው የጠቆሙት ከሳሽ፤ አርቲስት ቴዎድሮስ ያለደራሲው ፈቃድ የቦታና ገፀ-ባህርያት ስሞችን በመቀያየር ብቻ የመፅሀፉን መሰረታዊ ጭብጥና የታሪክ ፍሰት በፊልሙ ውስጥ መጠቀሙን አመልክተዋል፡፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ፊልሙን በተደጋጋሚ ለተመልካች በማሳየት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በክስ ማመልከቻው ላይ የጠቆሙት ደራሲው፤ ተከሳሽ በፈፀሙት ተግባር ከፍተኛ የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸውና ፊልሙ የመፅሃፉ ቀጣይ ህትመት ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ በመጠቆም የ10 ሚሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል፡፡

ከሳሽ የመፅሃፉን ጭብጥ፣ መቼትና የተለያዩ ታሪኮች ከ“ሶስት መአዘን” ፊልም ታሪክ ጋር በማመሳከር ለፍ/ቤቱ በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው መስከረም 6 በዋለው ችሎት፤ የክስ ማመልከቻው ለተከሳሽ ደርሶ መልስ እንዲሰጥበትና የከሳሽ ምስክሮች እንዲቀርቡ ለጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ጳጉሜ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፉት ማመልከቻ የ10 ሚሊዮን ብር ክስ ማቅረባቸውንና ቢፈረድላቸው ፍርዱን የሚያስፈፅሙበት ንብረት እንደማያገኙ በመጥቀስ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች ካላቸው ገንዘብ ላይ 10 ሚሊዮን ብር እንዲታገድላቸው ማመልከታቸውን ያስታወሰው ፍ/ቤቱ፤ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በዘመን ባንክ ከሚገኘው የሂሳብ ደብተራቸው 10 ሚሊዮን ብር እስከ ቀጣዩ ቀጠሮ ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ፊልሙን በተደጋጋሚ ለተመልካች በማሳየት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በክስ ማመልከቻው ላይ የጠቆሙት ደራሲው፤ ተከሳሽ በፈፀሙት ተግባር ከፍተኛ የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸውና ፊልሙ የመፅሃፉ ቀጣይ ህትመት ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ በመጠቆም የ10 ሚሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል፡፡

ከሳሽ የመፅሃፉን ጭብጥ፣ መቼትና የተለያዩ ታሪኮች ከ“ሶስት መአዘን” ፊልም ታሪክ ጋር በማመሳከር ለፍ/ቤቱ በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው መስከረም 6 በዋለው ችሎት፤ የክስ ማመልከቻው ለተከሳሽ ደርሶ መልስ እንዲሰጥበትና የከሳሽ ምስክሮች እንዲቀርቡ ለጥቅምት 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ጳጉሜ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፉት ማመልከቻ የ10 ሚሊዮን ብር ክስ ማቅረባቸውንና ቢፈረድላቸው ፍርዱን የሚያስፈፅሙበት ንብረት እንደማያገኙ በመጥቀስ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች ካላቸው ገንዘብ ላይ 10 ሚሊዮን ብር እንዲታገድላቸው ማመልከታቸውን ያስታወሰው ፍ/ቤቱ፤ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በዘመን ባንክ ከሚገኘው የሂሳብ ደብተራቸው 10 ሚሊዮን ብር እስከ ቀጣዩ ቀጠሮ ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

↧

‹‹የእናቶች ምርቃት ለእኔ ህይወት ሆኖኛል›› -Jossy in the house

$
0
0

በራሱ የሙዚቃ ስልት በመጫወት ተወዳጅነት ለማትረፍ የቻለ ድምፃዊ ነው፡፡ እስከዛሬም በተለያዩ አገራት እየዞረ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አድናቂዎቹን በማዝናናት ላይ ይገኛል፡፡ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ጆሲ ኢን ዚ ሃውስ›› (Jossy in the house) የሚል የራሱን ቶክ ሾው የኢቢኤስ የቲቪ ጣቢያ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ የፕሮግራሙ ይዘት የብዙ የኢቢኤስ ተመልካቾችን አይን ሊስብ የበቃ ባለሙያ ለመሆን ችሏል፡፡
በተለይ በዚህ ዓመት በትንሣኤ በዓል ላይ አቅርቦት በነበረው ፕሮግራሙ ላይ የቀድሞዋን ተወዳጅ ድምፃዊ ማንአልሞሽ ዲቦ ልጆች ገጥሟቸው በነበረው የህይወት ፈተና ዙሪያ በሰራው ዘጋቢ ፊልም ምክንያት ልቡ ያልተሰበረ የፕሮግራ ተከታታይ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡
ዛሬ መተሳሰብና መረዳዳት እንደሰማይ በራቀበት ዘመን ዮሴፍ (ጆሲ) በፕሮግራሙ ላይ እንዲህ የተረሱና የወገን ድጋፍ የሚያሻቸው ወገኖችን ከህዝቡ ጋር በማገናኘት ህይወታቸው እንዲለወጥ ያደረገው አስተዋፅኦ የተከታተሉ ተመልካቾች እደግ፣ ተመንደግ፣ ተባረክ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ ከድምፃዊና የቶክ ሾው አዘጋ ዮሴፍ ገብሬ ጋር ያደረግነው ቆይታ እነሆ፡-
jossy gebre
ጥያቄ፡- አዲሱ አልበምህ ከምን ደረሰ?
ዮሴፍ፡- አልበሙ ከሞላ ጎደል አልቋል፡፡ ለፋሲካ ይደርሳል የሚል ሃሳብ ነበረን፡፡ አንዳንድ የስፖንሰር ሺፕና ሌሎች ጉዳዮች ነበሩን፡፡ እነዚያን ጉዳዮች ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ነበር የጨረስነው፤ ከዚያ በኋላ ያሉት ነገሮች ለማስተካከል እየሞከርን ነው ያለነው፡፡ የጆሴ ሾው ምዕራፍ 3 ልጀምር ስለሆነና ትንሽ ለየት ባለ መልክ ይዘን ለመውጣት ስለፈለግን ትንሽን ድካሞች ነበሩበት፡፡ ያንን አስተካክለን አልበሙ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለ1 ወር ከ15 ቀን ውስጥ ለአድማጭ ወደ መልቀቁ እንሄዳለን፡፡
ጥያቄ፡- አልበሙን ዜማ፣ ግጥምና ቅንብር ከእነማን ጋር ነበር የሰራኸው?
ዮሴፍ፡- በርካታ ሰዎች አሉበት፡፡ ይልማ ገ/አብ፣ ጌትሽ ማሞ፣ መለሰ ጌታሁንና ሙያው ላይ ይሰራሉ የሚባሉ የተለያዩ ሰዎች ጋር ነው የሰራሁት፡፡ ዜማውና በቅንብርም ሁሉም ጋር ነው የተሰራው ማለት ይቻላል፡፡
ጥያቄ፡- በዚህ አልበም ላይ የበፊቱን ስታይል ይዘህ ነው የመጣኸው ወይስ የተለየ?
ዮሴፍ፡- የበፊቱ እስታይል 6 ወይም 7 ዓመት በፊት ነው ይዤ የወጣሁት፡፡ ያኔ ደግሞ ወታት ነበርኩ፣ አሁን ወደ መብሰሉ ስለሆንኩ በዚያው ልክ በሰል ያሉ ዜማዎች ናቸው፡፡ ለበፊቱ አድናቂዎችም የሚሆኑና እንዲሁም አገራዊ ፋይዳ ያላቸው መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ፣ ሀገርኛ ባህልን የሚያስተዋውቁ ሆነው የዕድሜዬን ያህል አልበሙም አድጎ ይወጣል፡፡
ጥያቄ፡- የአልበሙ ርዕስ ታውቋል?
ዮሴፍ፡- የተመረጡ ርዕሶች አሉት፡፡ ግን ሊወጣ ሲል ነው አንዱ ርዕስ የሚመረጠው፡፡
ጥያቄ፡- አልበሙን የገዛው ወይም የሚያከፋፍለው ማነው?
ዮሴፍ፡- ያንን ለጊዜው ምስጢር ላድርገውና ስፖንሰርሽፕ ከአንድ ካምፓኒ ጋር ጨርሰናል፡፡ ከዚ ባለፈ ግን የማከፋፈል ስራው እንዴት እንደሚሆን እያሰብንበት ስለሆነ ለጊዜው ይፋ አልሆነም፡፡
ጥያቄ፡- በአንተ እይታ አሁን እንደሚታወቀው የሙዚቃው ኢንዱስትሪ የገጠሙት ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?
ዮሴፍ፡- ምክንያቶቹ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሁልጊዜ እንደሚባለው የኮፒራይት ያለመከበር ችግር ዋነኛው ነው፡፡ ነገር ግን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀዛቀዘ የሚያመላክቱ እንደ ብዙአየሁ አይነት ስራዎች አሉ፡፡ የብዙአየሁ አልበም በደንብ ተሰምቶ ነበር፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን ተሰርተው መቅረብ የሚችሉ አልበሞች አሉና ከእነኛ አንዱ የመሆን ዕድል አልመህ ያለውን ስራ በደንብ አጠንክረህ ሰርተህ ማቅረብ እንጂ ከሙያው ጨርሶ መራቅ አያስፈልግም፡፡ ምናልባት ከሚሰሙ ስራዎች መካከል አንዱ ትሆናለህ፡፡ አለበለዚያም ሪስኩን ወስደህ የሚመጣውን መቀበል ነው፡፡
ሌላው ግን ሁሉ ነገር ጨምሯል፣ ዛሬ አንድ ማኪያቶ አንዳንድ ቦታ 13 ብር ገብቷል፡፡ ከጓደኛህ ጋር ሆነህ ሁለት ማኪያቶ ከጠጣህ 26 ብር ነው፡፡ የእኛን ሲዲ በ25 ብር ለመግዛት እንደ ከባድ ይቆጠራል፡፡ አብዛኛው ሰው ለሙያው የሚሰጠው ቦታ ከደብል ማኪያቶ በታች ሆኗል፡፡ ለሙያው ክብር ብንሰጥ መልካም ነው፡፡ ድሮ እኛ ልጅ እያለን አዲስ ዘፈን ሲወጣ በየሙዚቃ ቤቱ ደጃፍ እንሰባሰብ ነበር፡፡ ሌላው ችግር ብዙ በመፅሔትና ጋዜጦች ላይ አላግባብ የአርቲስቱ ይሰጥ የነበረው ያልሆኑ ስም ማጥፋቶች ይወጡ ነበር፡፡
ወደ መፍትሄው ስንሄድ ያንን ገፅታ ለመቀየር አርቲስቱ ዝም ብሎ ከመዝፈን ባለፈ በማህበራዊ ስራዎች ውስጥ ራሱን ማሳተፍ አለበት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔም የጀመርኩት ነገር አለ፡፡ እኔ ብቻም ሳልሆን የሙያ ባልደረቦቼም በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈው ያ ገፅታ ከተቀየረ በኋላ ህዝቡ ውስጥ የእኔነት ስሜት ፈጥሮ ገበያውን የመመለስ ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡
ጥያቄ፡- አንተስ ለአዲሱ አልበም ከአድማጮችህ ምን ትጠብቃለህ?
ዮሴፍ፡- መልካም ነገሮችን እጠብቃለሁ፤ ጥሩ ነገሮች ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጥሩ ነገር ሰርቻለሁ፡፡ በተለያዩ ባለሙያዎች አሰምቼ በጣም ቀና የሆነ ምላሽ ነው ያገኘሁት፡፡ አድማጩ ሰምቶት ደግሞ የሚሰጠውን ምላሽ አብረን እናየዋለን፡፡
ጥያቄ፡- ‹‹ጆሊ ቶክ ሾው››ን እንዴት ጀመርከው?
ዮሴፍ፡- ት/ቤት ውስጥ እያለሁ ሚኒ ሚዲያ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡ ከ9-12ተኛ ክፍል ስማር በጣም ታታሪ ጋዜጠኛ ስለነበርኩ ይመስለናል የሚኒ ሚዲያው ኃላፊ ጭምር ነበርኩኝ፡፡ 10ኛ ክፍል ላይ የህዝብ ግንኙነትና የተማሪዎች ተወካይ ተብዬ ከ3 መምህራን ጋር የሹመት ደብዳቤ ደርሶኛል፡፡
ጥያቄ፡- የት ነበር የምትማረው?
ዮሴፍ፡- ናዝሬት አዳማ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ነበር የምማረው፡፡ እዚያ ነበር የጋዜጠንነት ህይወት የጀመርኩት፡፡ በየእረፍቱ እየገባሁ አምስቱን ቀናት ሙዚቃ ማሰማት፣ ስነ ፅሑፍ ማቅረብና ፕሮግራም መምራት የመሳሰሉትን እሰራ ነበር፡፡
መርካቶ ከወንድሜ ጋር ቢዝነስ እየሰራሁ ኢትዮ-ኒውስ፣ ዘ ፕሬስ፣ አዲስ አድማስ ላይ ከ60 በላይ አርቲክሎችን ጽፌያለሁ፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኝነት ከዚያ ጀምሮ ያደገ ሙያ ነው፡፡
ወደ ቶክሾው ስንመጣ ለምሳሌ ክዊን ላቲቫ ዘፋኝ ናት፡፡ የራሷ ቶክሾውም አላት፡፡ ሌሎችም እንደዚያው፡፡ እኔም የራሴ ቢኖረኝ ብዬ አልም ነበር፡፡ ኢቢኤስ ቲቪ ሲመጣ ፕሮግራሞች ይፈልግ ነበርር፡ ከባለቤቶቹ ጋር ተገናኝተን ለመጀመር አሰብኩኝ፡፡ በወቅቱ አልበሙ ትንሽ ያዝ ስላደረገና ልጀምር አልቻልኩም ነበር፡፡ ከቆይታዎች በኋላ ጀመርኩኝ፡፡
ጥያቄ፡- የፕሮግራሙ ፎርማት ምንድነው?
ዮሴፍ፡- ሲጀመር የታዋቂ ሰዎች የህይወት ሂደት ምን ይመስላል፣ አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ታዋቂ አይሆንም፡፡ እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እዚያ እውቅና ላይ የደረሱበት መንገድ እንዴት ነው? የሄዱበት መንገድ ለሌሎች መማሪያ መሆን በሚቻልበት መልኩ ማቅረብ ነው፡፡
ስለ አርቲስቶቹ የነበረን ገፅታ ጥሩ ስለነበር አርቲስት ከተጠቀምንበት በጣም ብዙ ነገር የማድረግ አቅም አለው፡፡ ብዙ ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የአርቲስቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያልታዩ ማንነቶችን እያሳዩ ያለውን መንፈስ ሊቀየር የሚችል መንፈስ ይዞ ነበር የተነሳው፡፡ ያንንም ስናደርግ የታመሙት፣ የተጎዱ፣ የተረሱትን፣ የትኛቸው ያሉት ብለን የመጠየቅ መንፈስ ይዘን መጣን፡፡ ከዚያም የበዓለት ዘመድ ጥየቃ የሚል ፕሮግራ ጀመርን፡፡ እያልን አሁን ያሉት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ፕሮግራ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ከቋንቋ አጠቃቀም ጀምሮ፣ ከአቀማመጥ፣ በእያንዳንዱ ነገር ከልጅ እስከ አዋቂ የሚከተለው የቤተሰብ ፕሮግራም እንደሆነ ነው እየሰራን ያለነው፡፡
ጥያቄ፡- ምን ያህል ፕሮግራሞች ሰራችሁ?
ዮሴፍ፡- እስካሁን ዓመቱን ሙሉ ስንሰራ ነበር፡፡ ሶስት ልዩ የበዓል ፕሮግራሞች ሰርተናል፡፡ ለአዲስ ዓመት፣ ለገና እና ለፋሲካ፣ ከእነሱ ሌላ በእርግጠኝነት ከ3-4 ፕሮግራሞች ካልሆነ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ነበር ስናቀርብ የነበረው፡፡ ስኬታማ ያደረገንም ፕሮግራም ያለመድገማችን ነው፡፡ ዓመቱን ሙሉ አዲስ ነገር እያሳየን ነው እዚህ የደረስነው፡፡
ጥያቄ፡- ሰዎችን መርዳት እና ማገዝ የፕሮራሙ አካል እንዴት ልታደርገው ቻልክ?
ዮሴፍ፡- ሰዎችን የማገዝና የመርዳት ነገር አሪፍ ፕሮግራም አዘጋጅ ስለሆንክ ወይም እውቀት ስላለህ ስለዚህ ብቻ ሳይሆን ልብ ይፈልጋል፡፡ አንተ ትንሽ በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ ያንን ትሰራለህ፣ ለምሳሌ 5 ብር ኖሮህ 1 ብር በመስጠት የምትደሰት ከሆንክ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ትሰራለህ፡፡ እንደዚህ አይነት ልብ ከሌለህ የፈለገው ጎበዝ ጋዜጠኛ ብትሆን አትሰራውም፡፡ ይሄ የልብ ነገር ነው፡፡
ጥያቄ፡- የማንአልሞሽ ቤተሰቦች ህይወትን በፕሮግራም ላይ ለማቅረብ ምን አነሳሳህ?
ዮሴፍ፡- የእኔ ታላላቆች ወይም በዘመዶቼና ቤተሰቦቼ በተለይ በዳግማይ ትንሣኤ ወቅት ‹‹አክፋይ›› በሚባለው ስነ ስርዓት ውስኪ እና በግ ይዘው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ የክብር መገለጫ ነውና ያንን ሃሳብ ይዤ ነው ወደዚህ ያመጣሁት፡፡
ፕሮግራሙ ላይ በዓል ከተለመደው ፕሮግራም ውጭ የተለየ ነገር መሰራት አለበት አልኩኝ፡፡ ትዝ የሚልህ ከሆነ ለ2006 አዲስ ዓመት እነ ማንአልሞሽ ቤተሰቦች ቤት ሄጄ ነበር፡፡ በሁኔታው እኔ ብቻ ሳልሆን ተመልካቾችም በጣም ነበር ያዘኑት፡፡ ከዚያ በኋላ የአባባ ተስፋዬም የአርቲስት ዘሪቱ (እንቁጣጣሽ) ጉዳይም ነበር፡፡ ስለዚህ የማንአልሞሽ ልጆች ጥሩ ኑሮ የሚኖሩ፣ አሪፍ ት/ቤት ይማሩ የነበሩ፣ የአንዲት ታዋቂ ዘፋኝ ልጆች ነበሩ፡፡ አሁን ያሉበት ህይወታቸው ሲታይ በጣም ያሳዝናል፡፡ ቤታቸው በጣም ሩቅ ነው፣ በተለይ የማንአልሞሽ ዲቢ ሁለተኛ ልጅ ምስጢረ የተናገረችው ንግግር በጣም ልብ ይሰብር ነበር፡፡ እንደማንኛውም ሰው እኔም ልብ ተነክቶ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የምችለውን ነገር ሁሉ አድርጌ ህይወታቸው የሚስተካከልበት ነገር ልፈልግ በማለት ተነሳሁ፡፡
ጥያቄ፡- ልጆቹ የት ነበሩ አሁን የት ደረሱ?
ዮሴፍ፡- የሚኖሩበት አካባቢ በጣም ሩቅ ነበር፡፡ የት/ቤት እና የመኖሪያ ቤት ችግር ነበረባቸው፡፡ አንደኛዋ ልጅ የጤና ችግር ነበረባት፡፡ ወንድየው ት/ቤት ቢገባም የመማሪያ ቁሳቁስ ችግር ነበረበት፡፡ ከዚህ አንፃር በቂ ነው ባይባልም ዛሬ ሩቅ ከሚባል ሰፈር ወጥተው እዘህ ግሎባል ሆቴል አካባቢ ከዋናው አስፋልት 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኝ ንፁህ ቤት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ቤቱ አንዳንድ ነገሮች ቢቀሩትም እየተስተካከለ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎችም እያገዙን ነው፡፡ አሁን ህይወታቸውን ከሞላ ጎደል በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ እነሱም ህይወታችን እንደ አዲስ ጀመረ ብለው ነው ደስታቸውን የገለፁት፡፡
ጥያቄ፡- ፕሮግራሙ ከተላለፈ በኋላ ምን ምላሽ አገኘህ?
ዮሴፍ፡- ከፕሮግራሙ በኋላ ያለው ነገር ማመን ያቅትሃል፡፡ ፕሮግራ የተላለፈ ቀን ባህሬን ዝግጅት ነበረኝ፡፡ ሰው ሾውን ካየ በኋላ ነው ማታ ወደ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለመከታተል የመጣው፡፡ የነበረው ምላሽ በታም የሚገርም ነበር፡፡ በነጋታው ሰኞ ፌስ ቡክ ስከፍት ከነበረው የፌስ ቡክ ፋን ከነበረው 94 ሺ ገደማ በአንድ ቀን ልዩነት ወደ 106 ሺ ከዚያም በተከታታይ ቀናት ከ120 ሺ በላይ ሆነ፡፡
እዚህም ስመጣ በየመንገዱ የሚያልፈኝ ሰው አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ይክበር ነው ያልኩት፡፡ ይሄ ብርታት ሆኖኝ እኔ ላይ የነበሩ ፕሮግራሞች የበለጠ እንድገፋበት ጉልበት ሆነኝ፣ የእናቶች ምርቃት ለእኔ ህይወት ሆኖኛል፣ ምርቃት በጣም ነው የምወደው፣ ያደኩበት ቤተሰብ እንደዚ ስላሳደገኝ ምርቃት በጣም ነው የምወደው፡፡ ከገንዘብ በላይ ምርቃት ደስ ይለኛል፡፡
አንዳንድ ሰዎች በቃል መግለፅ የማይችሉት ፍቅር አሳይተውኛል፡፡ የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፍቅሩን በፍቅር ይመልስልኝ ነው የምለው፡፤ መልካም ነገር ስሰራ ለራሴ ብዬ ነው ያደረግኩት፡፡ እንደ ፕሮግራምም ስታየው ጥሩ ነገር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን እንደዚህ ህይወትህ ግልብጥ ብሎ እስኪቄር ድረስ ይሆናል ብዬ በፍፁም አልጠበቅኩም ነበር፡፡ ይህን ክብር መልሼ ለእግዚአብሔር ነው የምሰጠው፡፡
ጥያቄ፡- ከዚህ በኋላ እኛም አግዘንህ እንርዳ ያሉ በጎ አድራጊዎች የሰጡ ካሉ?
ዮሴፍ፡- በቂ ነው ባይባልም የመጡ ሰዎች አሉ፡፡ የመጡትን እናመሰግናለን፡፡ አሁንም እጄ ላይ ያሉ ጥቂትም ቢሆኑ መታገዝ የሚገባቸው ሰዎች በእነዚህ ፕሮግራሞች ለመርዳት እንሞክራለን፡፡ እኔም አቅሜ በሚችለው ሁሉ ከማገኘው ነገር ላይ ለማገዝ እሞክራለሁ፡፡
ጥያቄ፡- የወደፊት እቅድህስ ምንድን ነው?
ዮሴፍ፡- ምዕራፍ 3 ባይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተለያየ መልኩ የማህበረሰቡ ችግሮችን የሚቀርፉ ምክሮች ወይም ትምህርቶች፣ ምሳሌ መሆን የሚችሉ ፋይዳዎችን የፕሮግራማችን አካል ለማድረግና የበለጠ የፕሮግራሙን ይዘት አሳድጎ የማህበረሰቡ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ነገሮች እንዲሆኑ አቅደናል፡፡
እስካሁን የሠራናቸውን ፕሮግራሞች በተመለከተ ተመልካች አስተያየት እንዲሰጡን እናደርጋለን፡፡ የምዕራፍ 3 ፕሮራሞች በአዲስ አቀራረብ፣ በጥራት ሰርተን ለእይታ እናበቃለን፡፡
ጥያቄ፡- የማን አልሞሽ ልጆች የወደፊት ህይወት የት ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል?
ዮሴፍ፡- ልጆቹ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በትምህርታቸው ታታሪ ናቸው፡፡ አንደኛው ልጅ የትምህርት መሳሪያ ያስፈልጉት ነበር፡፡ ላፕቶፕ በስጦታ አግኝተንለታል፡፡ ከዚያ ውጭ ደግሞ በትምህርቱ ሂደት ውስጥ የሚያስፈልጉት ነገሮች እንደ ወንድም አግዘዋለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ምስጢረም ትምህርቷን እስክትጨርስ የስኮላርሺፕ እድል አግኝታለች፡፡ ፍቅርተም (የማንአልሞሽ ወንድም ልጅ) ጤናዋ ተስተካክሎ ወደ ትምህርቷ የምትመለስበት ሁኔታ ተመቻችቶላታል፡፡ ቲጂም (የማንአልሞሽ እህት) ያቋረጠችው የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ትቀጥላለች፡፡ መሰረታዊው ነገር እራሳቸውን ችለው ጥረው ነገ ለሰው የሚተርፉበት ህይወት ላይ ያቆምናቸው ይመስለኛል፡፡ ቀሪው ነገር የራሳቸው ጥረት ይሆናል ማለት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ስኬታማ ነህ?
ዮሴፍ፡- እንደ ጀማሪ ጥሩ ነው፡፡ ግን የስኬት መጨረሻ ይሄ አይደለም፡፡ ገና ብዙ ይቀረኛል፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር እንደምደርስ እምነት አለኝ፡፡
ጥያቄ፡- ደስተኛ ነህ?
ዮሴፍ፡- የምፈልገውን ነገር ስለምሰራ፣ የምፈልገውን ስላደርግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በህይወት ውስጥ ስትመላለስ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ እኔ የምሰራው የህዝብ ስራ ነው፡፡ ከማህበረሰቡ የምታገኘው ምላሽ ደግሞ ጥሩ እየሆነ ሲመጣ ከዚህ በላይ ደስተኛነት የለም፡፡ ከራስህም አልፈህ በሰዎች ህይወት ውስጥ ምክንያት መሆንህ በራሱ ከማንም በላይ ደስተኛ ያደርግሃል፡፡
ጥያቄ፡- የምትጨምረው ነገር ካለ?
ዮሴፍ፡- በመጀመሪያ አክብራችሁ ስለጋበዛችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ በአዲስ አልበም፣ በአዲስ የቲቪ ሾው ሲዝን ጥሩ ነገሮችን ይዘን ራሳችንን አሻሽለን የምናርመውን አርመን፣ የምናዳብረውን አዳብረን ለማህበረሰቡ ይጠቅማል በምንለውና ባደገ የስራ አካሄድ ወደ ህዝቡ እንመጣለን የሚል እምነት አለኝ፡፡

↧
Viewing all 261 articles
Browse latest View live