Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

ግዛቸው ተ/ማርያም –የሐበሻ አምባሳደር በአሜሪካ!

$
0
0

ተወልዶ ያደገው ደብረብርሃን ከተማ ነው፤ ባህላዊ የሙዚቃ ተጨዋች ድምፃዊ ግዛቸው ተ/ማርያም ሲሆን በ91ዓ.ም ብሔራዊ ቲያትር ተቀጥሮ ለ6 አመት ሰርቷል። የሉሲ አፅም አሜሪካ መምጣቱን ተከትሎ በሒውስተን ከተማ ከ6 አመት በፊት አንድ ዝግጅት ይጠራል። ግዛቸውን ጨምሮ 22 አባላት ያሉት ቡድን ይመጣል። ዝግጅቱን ካቀረቡ በኋላ ሁሉም እዚሁ ቀሩ።

    (በፎቶው ግዛቸው የዲሲ ገዢ ከጀርባ በአድናቆት ሲመለከቱ እንዲሁም በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣና ሌሎች መድረኮች.. )

(በፎቶው ግዛቸው የዲሲ ገዢ ከጀርባ በአድናቆት ሲመለከቱ እንዲሁም በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣና ሌሎች መድረኮች.. )


በዲሲ የሚኖረው ግዛቸው ሲናገር ረጋ ባለ ትህትና ጭምር ነው። ማሲንቆ በመጫወት በይበልጥ የሚታወቀው ግዛቸው ክራርና ዋሽንት እንዲሁም ከባህላዊ ኦሮሚኛ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ወላይትኛ፣ አገው፣ ሱማሌና አፋር…ወዘተ ዘፈኖችን በአስደናቂ ሁኔታ ይጫወታል። በዚህ ወር በሳንሆዜ የተካሄደውን አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ጨምሮ በአብዛኞቹ አገራዊና ህዝባዊ መድረኮች ተገኝቷል። የሰርግ ዝግጅቶች ቋሚ መተዳደሪያውና ጥሩ ገቢ የሚያገኝባቸው ናቸው።

ለአንድ ሰርግ (መልስ ሳይጨምር) እስከ1ሺህ 8መቶ ዶላር ያስከፍላል። በተለያዩ የኮሚኒትና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች እየተገኘ የነፃ አገልግሎት ጭምር ይሰጣል። ይህም ብቻ አይደለም፤ ከታዋቂ የአሜሪካ ሙዚቀኞች ጋር በመጫወትና የዲሲ ገዢ በተገኙበት እስክስታ አስነክቷቸዋል። በ2010 ከአሜሪካና አውሮፓ በተወጣጡ ታዋቂ ሙዚቀኞች ማለትም ከነቴሪ፣ ኬን፣ ጆሽዋና ፖል ጋር ባለፈው አመት በድጋሚ አቅርቧል፤ ግዛቸው ሲናገር፥ « ኢምሮቫይዜሽን ይባላል። ሙዚቃ እየተጫወትክ በመሳሪያ ስሜትን መግለፅና እንደሰው እንዲናገር ማድረግ ነው» ይላል።

ስለዚሁ ዝግጅት ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የግዛቸውን ምስል አስደግፎ ዘግቧል። ከ5 ወር በፊት ዲሲና አዲስ አበባ እህትማማች ከተሞች (sister cities) ዝግጅት ላይ የዲሲ ገዢ ሜር ቬንሰንት ግሬ በተገኙበት በቢሮ አዳራሻቸው የኢትዮጵያ ባህላዊ ስራዎችን ያቀረበ ሲሆን ዝግጅቱ ኤ.ቢ.ሲ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አግኝቷል። ከዲሲ ገዢም አድናቆትን አትርፏል። ሌላው በየአመቱ የሚዘጋጅና ነገ ሐሙስ የሚከፈተው ፕሮግራም ይጠቀሳል። በኢትዮጵያ ሔሪቴጅ ካምፕ የሚሰናዳው አመታዊ ዝግጅት ለ4 ቀናት ይቆያል። ግዛቸው ሲናገር፥ «ከኢትዮጵያ በአሜሪካውያን የመጡ የማደጐ ታዳጊ ልጆች አገራቸውን፣ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን እንዳይረሱ ተብሎ የሚደረግ ዝግጅት ነው። 300 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ልጆች ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር ይመጣሉ።

ባህላዊ ምግብና ፀጉር አሰራር፣ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች አደራደርና ውዝዋዜ፣ ቋንቋና የተለያዩ ኢትዮጵያዊ ባህሎችን እንዲማሩ ይደረጋል። ባለፉት ጊዜያት ከአንዳንድ ታዳጊዎች የገጠመኝ ነገር ነበር። የአንዱን ብሄረሰብ ባህል (የመጡበትን) ስትጫወት የሆነ ስሜት ውስጥ ገብተው ታያቸዋለህ። ስጠይቃቸው “በቤቴ፣ በመንደሬ ..እንዲህ አይነት ሙዚቃ ሰመቼ ነበር፤ እንዲህ አይነት ቋንቋ ቤተሰቦቼ ይናገሩ ነበር” ይላሉ። አላማው ሃገርና ባህላቸው እንዳይረሱ ማድረግ ስለሆነ በዚህ እደሰታለሁ። የአገሬ ባንዲራ ያለበትን የሃገር ልብስ ለብሼ ለህፃናቱ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መናገር እጅግ ያኮራኛል!!» ይላል። ግዛቸው “እማማ ኢትዮጵያ” አያለ የለቀቀው ነጠላ ዜማ ድንቅ ነው።

የሐበሻ አምባሳደር ቢባል አያንሰውም!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

Trending Articles