Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Entertainment
Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የአሜሪካ አቀባበል አጨራረሱም እንደ አቀባበሉ ቢሆን

$
0
0

[ቴዲ ድንቅ – አትላንታ]
እንደአጀማመሩ ያስጨርስልን
ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች፣ በተለይ በአሜሪካ ኮንስርት ለማቅረብ ሲመጡ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመሩ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቶች አሉ። አንዳንዱ እንደ አገር መሪ በሊሞ፣ ሌላው በሄሊኮፕተር፣ … ሌላው በፈረስ .. ሌላው ደግሞ እንዳቅሚቲ በ እቅፍ አበባ ተቀብሎ ፣ በራሱ መኪና ሆቴል ያደርሳል። አንዳንዱ የአሜሪካ ፖሊሶችን አነጋግሮ ወይም ተስማምቶ በሞተር ሳይክል የሚያሳጅብም አለ። ኦባማ ነው ወይስ ሌላ እስክንል ድረስ በአምስትና ስድስት ሊሞዎች መቀበልና ማጀብም አለ። አንዱ ከበፊቱ ለመብለጥ በሚደረግ ጥረት ፣ ወደፊትም ሌላ ዓይነት አቀባበል ልናይ እንችላለን

ጃኪ ጎሲን በሂሊኮፕተር

ጃኪ ጎሲን በሂሊኮፕተር

ጥሩ ነው። አርቲስትን ማክበር፣ ለአገራችን ባለሙያዎች ክብር መስጠት ደስ ይላል። እኛም አርቲስቶቻችን ሲከበሩና ደስ ሲላቸው ስናይ ደስ ይለናል እንጂ አይከፋንም። ደስታችን ዘለቄታዊ እንዲሆን ታዲያ …….

….ደስታችን ዘለቄታ ያለው እንዲሆን ታዲያ ..፣ ከዚያም በኋላ ያለው፣ እስከመጨረሻው ድረስም የሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት ፣ እንደ አጀማመሩ እንዲሆን፣ እንዲጨነቁለት፣ እንዲፎካከሩለት እንፈልጋለን።

ቴዎድሮስ ታደሰን በሊሞ

ቴዎድሮስ ታደሰን በሊሞ

ሰው ተስቦ እንዲመጣ ፣ ከአቀባበሉ ጀምሮ ለማሳመር ጥረት እንደሚደረግ ሁሉ፣የመጣው ሰውም ተደስቶ እንዲሄድ አብሮ ጥረት ይደረግ። ለአቀባበሉ ዕቅድና ግብ፣ ስብሰባና ውሳኔ እንደተደረገ ሁሉ፣ ለዝግጅቱ ማማር፣ ለኮንስርቱ የተዋጣለት መሆን፣ የመጣው ሰው እንዲደሰት፣ አርቲስቱ የሚጠበቅበትን ያህል በሚገባ እንዲጫወት፣ በሰአት ተጀምሮ ፣ በስአት እንዲያልቅ፣ የመጣው ሰው በጋጠወጦች እንዳይረበሽ አብሮ ዕቅድና ግብ፣ ስብስባና ውሳኔ ሊኖር ያስፈልጋል።

 

ጸጋዬ እሸቱን በሊሞ

ጸጋዬ እሸቱን በሊሞ

አርቲስቱ እና ፕሮሞተሮቹም መጨረሻ ላይ ከመጨቃጨቅ ፣ ቀድመው ዝርዝሩን ተወያይተው እንዳማረባቸው፣ እንደአቀባበሉ በሊሞና ሞተር ብስክሌት ባይሆንም፣ ቢያንስ ተቃቅፈው በሰላም ለመያየት ያብቃቸው። ፕሮሞተሮችም፣ ብዙ ጊዜ እንደሚታየው፣ ሲጀመር አብረው ሰርተውና አጀማመሩን አሳምረው፣ ካለቀ በኋላ በገንዘብም ይሁን፣ “ያንተ ጥፋት ነው፣ ያንቺ ጥፋት ነው” ተባብለው ከመጣላትም ይሰውራቸው። ለስኬት አብሮነት እንዳለ ሁሉ፣ ባይሳካምም፣ አለመሳካቱ የሁሉም እኩል ሃላፊነት ሊሆን ይገባል።

ተመስገንን በሰረገላ

ተመስገንን በሰረገላ

እናም ኮንሰርቶቻችን አቀባበል ላይ አሁን አሁን እንደሚታየው ያማረ አጨራረስም እንዲኖራቸው እንመኛለን።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 261

Trending Articles