የኡዛዛ አሌይና ዘፋኞች ሔለን በርሔና ናዳ አል ቃላ –ሊያዩት የሚገባ (Video)
የኡዛዛ አሌይና ዘፋኞች ሰሞኑን ተገናኝተዋል:: ታዋቂዋ የሱዳን ድምጻዊት ናዳ አል ቃላ ከኢትዮጵያዊቷ ሄለን በርሄ ጋር በተገናኙበት ወቅት እርስ በራሳቸው ያላቸውን አድናቆትና ፍቅር የተገለለጹት በሚከተለው መልኩ ነበር:: ሁለቱም ይህን ተወዳጅ ዘፈን በአንድ ላይ ዘፍነውታል:: ይመልከቱት:: The post የኡዛዛ አሌይና...
View Article‹‹የጥላሁን ገሠሠ ሚስትነት ከሕግ የበላይ አያደርግም.. ወ/ሮ ሮማንን በሕግ እፋረዳታለሁ!›
በቅርቡ በዘከርያ መሀመድ ተጽፎ ለንባብ የበቃውን ‹ጥላሁን ገሠሠ የህይወቱ ታሪክና ሚስጥር› የሚለውን መጽሐፍ ተከትሎ የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ‹ከመጽሐፉ መታተም ጀርባ ሌላ ታሪክ አለ› በሚል በቁምነገር መጽሔት ቅጽ 14 ቁጥር 203 አስተያየቷን ሰጥታ ነበር፡፡ በቃለምልልሱ ላይ ስማቸው ከተጠቀሱ ሰዎች...
View Articleየማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ተከበረ * አላሙዲ 5 ሚሊዮን ብር ሸለሙት
(ዘ-ሐበሻ) የትዝታው ሙዚቃ ንጉሥ የሚል የክብር ስያሜን ከኢትዮጵያውያን የተጎናጸፈው ዝነኛው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመኑ ተከበረ:: ማምሻውን በሸራተን አዲስ በተከናወነው በዚሁ የማህሙድ አህመድ የሙዚቃ ዘመን 50ኛ ዓመት ልደት ላይ ድምፃዊውን የሚዘክሩ የተለያዩ ፕሮግራሞች...
View Articleየአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል)
(ዘ-ሐበሻ) ሼህ መሃመድ አላሙዲ ከአርቲስት ማህደር አሰፋ ጋር ግንኙነት ጀምረዋል የሚለው ወሬ ሲወራ ከቆየ ሰንበትበት ብሏል:: በተለይም ማህደር ለትዳር ከምታስበው ጓደኛዋ ጋር ከተለያየች በኋላ ብዙ ጊዜ ከሼኩ ጋር ታይታለች:: በትናንትናው ዕለት ደግሞ ይህን የሁለቱ ግንኙነት በአደባባይ ታይቷል:: የአርቲስት ማህሙድ...
View Articleጎሳዬ ቀለሙን ምን ነካው ?
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ እዚህ ሀገር ድንገት ተነስተው አየር ምድሩን ሁሉ መሙላት የሚፈልጉ አሉ ። ቢችሉ እሰየው ። ግን ክፋቱ ደግሞ ሀገሪቱ ለዚህ አትመችም ። በወጡበትየሚጨብጡ የሚረግጡትን አጥተው በወጡበት ፍጥነት ሲወርዱ አይተናል ። ድምፃዊ ጎሳዬ ቀለሙም ከእነዚህ አንዱ እንዳይሆን እሰጋለሁ ። በግሌ እንደነ አብርሀም...
View Articleየጆሲ ኢን ዘሓውስ ምክር ለጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) – Video
ከሊሊ ሞገስ ጃኪ ጎሲ ከለቀቃቸው በጣት የሚቆጠሩ ዘፈኖች ውስጥ በጣት የሚቆጠሩትን ከሌሎች ዘፋኞች ካለፈቃድ ወይም ደግሞ አትውሰድ እየተባለ በጉልበት ወስዶ በመስራት ስሙ ይጠራል:: የተሾመ አሰግድ “የኔ አካል”, የኤርትራዊው ፍጹም ዮሐንስ ‘ፊያሜታ’ (ከዩቲዩብ እስከመታገድ ደርሶ ነበር)… እንዲሁም አሁን የአብርሃም...
View Articleቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ –ኮርኩማ አፍሪካ
የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ አፍሮ አዲሱን ነጠላ ዜማ ለሕዝብ ለቀቀ:: ቴዲ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሐሙስ ጁላይ 2 ያለው ሲሆን አዲሱ ነጠላ ዜማው ከወዲሁ የሶሻል ሚዲያውን አጥለቅልቆታል:: በስጋት ቀፎን ተይዞ እስራት አዋቂው ሸሽቶ ረሃብ ነግሶ ርዛት በምድሯ ሊቆይ ማንስ ይደፍራል ታንኳ ላይ ወጥቶ ወንዝ...
View Articleለመሆኑ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ማን ነዉ? የሕይወት ታሪኮቹና የፍቅር ሕይወቱ ምን ይመስል ይሆን?
ለመሆኑ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ማን ነዉ? የሕይወት ታሪኮቹና የፍቅር ሕይወቱ ምን ይመስል ይሆን? Zehabesha.com
View Articleበሕወሓት $5 ሺህ ዶላር የተደለለው ድምፃዊ ደረጀ ደገፋው በዲሲ ከፍተኛ መገለል እየደረሰበት ነው
ቢሆነኝ ከዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት መንግስት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ላይ አንጃ በመፍጠር በስርዓቱ ደጋፊ በሼህ መሀመድ አላሙዲ ሌላ ፌዴሬሽን አቋቁመው በኢትዮጵያውያን ቦይኮት መደረጋቸው ይታወሳል:: ከአንድ ዓመት በፊት የወያኔ መንግስት በሚኒሶታ...
View Articleየሰው መጽሐፍ ታሪክን በፊልም ካለፈቃድ ወስዶ ሰርቷል በሚል በ10 ሚሊዮን ብር የተከሰሰው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለሐምሌ...
በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ “ሦሥት መዓዘን” ፊልም እና በደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ “ፍቅር ሲበቀል” የተሠኘ ረጅም ልብወለድ መፅሐፍ መካከል የነበረው የ10 ሚሊዮን ብር የፍትሐብሔር ክስ ክርክር ለፍርድ ማስፈፀሚያ የሚሆን ብር ማስያዣ ማቅረብ ይችላል የሚል ሀሣብ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ባቀረበው ተቃውሞ መሠረት...
View Articleአብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ –መልካም አመት በዓል (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል)
መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል:: ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:- መልካም አመት በዓል –...
View Articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ በቴዲ አፍሮ ምክንያት 200 ሺህ ዶላር ከሰረ * ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
· ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር (ክንፉ አሰፋ፣ ፍራንክፈርት) ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት...
View Articleብዙአየሁ ደምሴ በፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያኑን ሲያዝናና አመሸ (Video)
የኢትዮ-አውሮፓ የ እግር ኳስ እና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮ በፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ስነስርዓት ተደርጓል:: በዚህ በዓል ላይ ከታዩት ደማቅ ፕሮግራሞች መካከል ደግሞ የድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ የሙዚቃ ኮንሰርት ነው:: ደማቅ ሆኖ ባለፈው በዚህ ኮንሰርት ላይ የነበረውን የብዙአየሁ እንቅስቃሴ ለማየት እዚህ ይጫኑ::
View Article“ዘፈኑን እየተውኩ ወደ ዝማሬው ዓለም እየገባሁ ነው”–ድምፃዊት(ዘማሪት) ዘሪቱ ጌታሁን [ቃለ-ምልልስ]
ዘሪቱ ከበደ ዘፈን አቁማለች ወይንስ አላቆመችም የሚሉ አናጋጋሪ ጉዳዮች በርካታ ጊዜያት ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ከእርሷ አንደበት ይህ ነው የሚባል ቁርጥ ያለ ምላሽ ሳይሰጥበት በመቆየቱ በበርካቶች ዘንድ አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዘሪቱ በየወሩ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለገበያ በሚበቃው ሪቪል...
View Articleአርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት አዲሱን “መማር”ነጠላ ዜማ አቀነቀነ (ቭዲዮን ይመልከቱት)
(ዘ-ሐበሻ) በኮምፒውተር ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ባችለሩን የተቀበለው አርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት በርከት ያሉ ተመራቂዎች በተገኙበት አዲሱን መማር የተሰኝውን ነጠላ ዜማ አቀንቅኗል:: ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እንኳን ደስ ያለህ እያልን ይህን ታሪካዊ ቭዲዮ ጋብዘናችኋል::
View Articleመንግስት በሕዝብ የተመረጠው ቴዲ አፍሮን በስነጥበብ ዘርፍ ለመሸለም ፍላጎት እንደሌለው በይፋ አሳየ
(ዘ-ሐበሻ) በየዓመቱ የሚካሄደና ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚከናወነው ‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት› በየዘርፉ የተመረጡ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎችን መንግስት ልክ እንደምርጫው አጭበርብሮ ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች አስቀመጠ:: ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በተሰጠው...
View Articleቃልኪዳን አለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን “እውነት ማለት”ግጥም እንዲህ ያነበዋል (Video)
የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተማሪ የሆነው ወጣት ቃልኪዳን ዓለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን ተወዳጅ ግጥም እንደሚከተለው አንብቦታል:: ይመልከቱት::
View Article“ቴዲ አፍሮ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል”– (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)
የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ስጋቱን በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ነበር የገለጸው:: ተካፈሉት:: ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ...
View Article